ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
СтатистикаThe best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13:00
- Постов за неделю
- 64
- Всего постов
- 106
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 529
- 1/48двое суток
- 5 190
- 1/72трое суток
- 5 597
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
የቼልሲው የመስመር አጥቂ ፔድሮ ኔቶ የሳዑዲውን አልሂላል ለመቀላቀል መስማማቱ እየተዘገበ ነዉ። ቼልሲ ተጨዋቹን ለመሸጥ ክፍት መሆኑ ሲዘገብ ወደ 60 ሚሊዮን ዩሮ ከተጫዋቾቹ ዝዉዉር ይፈልጋል ተብሏል። ኔቶም ከአልሂላል ጋር በግል ጉዳዮች ከስምምነት ደርሷል ተብሏል። ኔቶ በዚህ ክረምት ስሙ ከማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጋር ሲያያዝ ነበር። #ዳጉ_ጆርናል
ለመኪናዎ በተመጣጣኝ ዋጋ ያሎትን ይዘው ይምጡ ፣ ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይራለን 👉 ማይክ ባትሪና ጎማ መሸጫ 🤳 913701702/975293297
видео или голосовое, без подписи
👉 ክርስቲያን ሮሜሮ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ 👉 ስፔንስ ወደ ኢንተር ሚላን መዘዋወራቸው ይፋ ሁኗል #ዳጉ_ጆርናል
የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ የሚያካሂደው የቦምብ ድብደባ ቀጥሏል። የሊባኖስ ብሔራዊ የዜና ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፣ የእስራኤል ኃይሎች በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ በርካታ መንደሮች እና ከተሞች ላይ የቦምብ ድብደባ እና የውድመት ዘመቻቸውን ቀጥለዋል። የእስራኤል ኃይሎች በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ በማሻ አል-ማንሱሪ አካባቢ ከፍተኛ ፍንዳታ ማድረሳቸውን NNA ዘግቧል። በተጨማሪም በማጅዳል ዙን ፣ አል-ማንሱሪ እና በአቅራቢያው በሚገኙ ሸለቆዎች የማሽን ጠመንጃ ተኩስ እንደነበር ተዘግቧል። የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች እና ድሮኖች አሁንም በአየር ላይ በረራቸውን እንደቀጠሉ ዘገባው አክሎ ገልጿል። ፍንዳታዎቹ የእስራኤል ታንኮች በቢንት ጅቤል ወረዳ ወደምትገኘው ሃዳታ ካደረጉት እንቅስቃሴ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የተከሰቱ መሆናቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል ። በሚኪያስ ጸሀዬ #ዳጉ_ጆርናል
በጃፓን በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ምክኒያት የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአውሮፕላን ማረፊያ መውጣት አልቻሉም ። በምስራቅ ጃፓን በጣለው “ታይቶ በማይታወቅ” ከባድ ዝናብ ምክኒያት ቢያንስ የአራት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ 7 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቶኪዮ ናሪታ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመንግስት ህንፃዎች ውስጥ ተጠልለው እንዲያድሩ አስገድዷል ። ሐሙስ ምሽት ከቶኪዮ በስተምስራቅ በምትገኘው ቺባ ግዛት ላይ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ የመሬት መንሸራተት ስጋት እና የኤሌክትሪክ መቆራረጥንም አስከትሏል። በቺባ እና በሌሎች አካባቢዎች ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ የተላለፈ ሲሆን 45 ሺህ ያህል ቤቶች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል። በዛሬው እለት ዝናቡ ቢቀንስም ባለስልጣናት ግን በአካባቢው ስላለው የጎርፍ አደጋ እያስጠነቀቁ ነው። በሚኪያስ ጸሀዬ #ዳጉ_ጆርናል
ብስኩት ልግዛልሽ ብሎ በማታለል የ5 ዓመት ህፃን ልጅን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ። በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ዛላ ፍሬ ቀበሌ ደነቤ ፋማ ቀጠና ልዩ ስፍራ ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው፡፡ ተከሳሽ በሀሩ ሽርሞሎ የተባለ ሲሆን የ5 ዓመት ህፃን ልጅ የሆነችውን ግለሰብ በግምት ከቀኑ 11:00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ዛላ ፍሬ ቀበሌ ደነቤ ፋማ ቀጠና ልዩ ስፍራው ደነቤ ተብሎ በሚጠራበት ስፍራ ብስኩት እገዛልሻለሁ ብሎ በማታለል የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኑርዬ ከድር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠረበት የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀም ወንጀል የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ ያስተላልፋል፡፡ ተከሳሽ ወንጀሉን አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ የተከራከረ ሲሆን ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ ከሰማ በኃላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የቀረበበትን የወንጀል ክስና ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ ጥፋተኛ ተብሏል ። በዚህም የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉን ኮማንደር ኑርዬ ከድር ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ነገ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡- ✅ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 👉አርሴማ ቤተክርስቲያን ፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጀሞ ሚካኤል፣ አፍሪካ ህንጻ፣ ዱላ ማርያም፣ ጎፋ ካንምፕ፣ ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን እና አካባቢው ፣ 👉መለኛው ግሮሰሪ ፣ ጣፎ ገብርኤል፣ ገመናይ ማርያም፣ ሜታ ቢራ ፋብሪካ፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ መብራት፣ ቆሬ አደባባይ፣ አሚጎ ኮንዶሚንየም በከፊል ፣ ፋና ት/ቤት እና አካባቢው ፣ ✅ከጠዋቱ 3፡00-10፡30 👉ጣፎ የታችኛው ኮንዶሚየም፣ አባዶ በከፊል፣ ለብርሃን ዳቦ ቤት፣ አቃቂ ኬላ፣ ገላን ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ወሰርቢ፣ አፍሪካ ሕብረት፣ መቻሬ ኮንዶሚኒየም፣ ልደታ ፀበል፣ ሜክሲኮ በከፊል፣ትንባሆ ሞኖፖል፣ ሳር ቤት ቴሌ እና አካባቢው፣ ✅ከረፋዱ 4፡00-9፡30 👉ዊንጌት ት/ቤት፣ ድሬ ቆዳ ፣ ጊዮን በረኪና ፣ መከላከያ መኖሪያ ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ሚኒሊየም ሰፈር ፣ ሸጎሌ ጨፌ ሰፈር ፣ ጉለሌ እጽዋት ማዕከል፣ ኪዳነ ምህርት፣ ሸጎሌ መንደር 7 እና አካባቢው፣ 👉 ዊንጌት ጤና ጣቢያ፣ አበራ ሆቴል፣ እምነበረድ፣ አጠና ተራ፣ ኢትዮ ጠቢብ ፣ ደጉ ሆቴል፣ ሰፈረ ሰላም እና አካባቢው ፣ 👉ለቡ፣ ቻድ ኢንባሲ፣ 72 መንደር በሙሉ፣ ተክለ ሀይማኖት ቤተክርስቲያን ፣ ሁጃድ ቻይና ድርጅት (ካምፕ)፣ ጀሞ 3፣ ጀሞ ፌደራል ሆስፒታል፣ ጊኒር፣ ሁጃድ ፋብሪካ እና አካባቢው ፣ 👉ቤላ ሰብስቴሽን ጀርባ ያሉ ቤቶች ፣ ቤላ አቦ ቤተክርስቲያን ፣ ፈረንሳይ ጉራራ ቤተክርስቲያን እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡ ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ማሊ በ20 ዓመት እስራት የተቀጣውን ፈረንሳዊ ባለስልጣን በምህረት ለቀቀች። የማሊ ፕሬዚዳንት አስሚ ጎይታ በ20 ዓመት እስራት የተቀጣውን አንድ የፈረንሳይ ዜጋ በምህረት ፈትተዋል። ባለፈው ዓመት የወታደራዊው መንግስት በሀገሪቱ የፈረንሳይ ኤምባሲ ባልደረባ የሆኑትን ያን ቬዚሊየርን በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ውስጥ አለመረጋጋት ለመፍጠር በሴራ ተሳትፈዋል ሲል ከሰዋቸው ነበር። የማሊ ወታደራዊ መንግስት መሪ በሀገሪቱ ኤምባሲ ውስጥ ይሰሩ ለነበሩ እና የስለላ ስራ አከናውነዋል ተብለው በ20 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸው ለነበሩት የፈረንሳይ የስለላ ወኪል ሐሙስ ዕለት የፕሬዚዳንታዊ ምህረት አድርገውላቸዋል። የስለላ ወኪሉ ከአንድ ዓመት በፊት በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት፣ ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ግንኙነት ባቋረጠው ወታደራዊ መንግስት የሚመራቸው የማሊ ባለስልጣናት፣ ያን ቬዚሊየር በሀገሪቱ ላይ ሴራ በመጠንሰስ ከሰዋቸው ነበር። የማሊ መንግስት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ ምህረቱ በችሎት ወቅት በተሰጠው ፍርድ የተረጋገጡትን እውነታዎች ዋጋ የሚያሳጣ አይደለም ብሏል። አክሎም ግለሰቡ ወዲያውኑ ከሀገሪቱ ግዛት እንዲወጡ ይደረጋል ብሏል። በ2020 እና በ2021 በተካሄዱት ተከታታይ መፈንቅለ መንግስት በወታደራዊ ኃይል በምትመራው በዚህች የምዕራብ አፍሪካ ሀገር እና በቀድሞ ገዢዋ ፈረንሳይ መካከል ያለውን ግንኙነት ያበላሸው ይኸው ፍርድ የተሰጠው በሰኔ ወር ላይ ነበር። በጄኔራል አስሚ ጎይታ አመራር ስር ሀገሪቱ ከምዕራባውያን በተለይም ከፈረንሳይ ፊቷን በማዞር ከሩሲያ ጋር የቀረበ ግንኙነት መመስረትን መርጣለች። መግለጫው አክሎ እንደገለጸው የምህረት እርምጃው የጎይታን፣ ለሰላም እና ለውይይት ያለቸውን ቁርጠኝነት፣ እንዲሁም ባህላችንን የሚገልጹትን የቀደሙትን የይቅርታ፣ የእንግዳ ተቀባይነት እና የቸርነት እሴቶች የሚያሳይ ነው። ፈረንሳዊው የስለላ ወኪል በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ዓመት እ.ኤ.አ ነሐሴ 13 ቀን ወታደራዊ መንግስቱን ለመጣል መፈንቅለ መንግስት ሊያካሂዱ ነበር ከተባሉ በርካታ የማሊ ወታደራዊ መኮንኖች ጋር አብረው ነበር። ፈረንሳይ በበኩሏ በባለስልጣኑ ላይ የቀረበው ክስ መሰረት የሌለው ነው ስትል ትሞግታለች። ሰላማዊ ነጋሲ #ዳጉ_ጆርናል
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በሀረር ከተማ በመኖሪያ ግቢ ውስጥ ሀሺሽ በማብቀል ለሽያጭ ያዘጋጀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በሐረሪ ክልል ሐረር ከተማ ሸንኮር ወረዳ ቀበሌ 08 በመኖሪያ ግቢ ውስጥ ሀሺሽ በማብቀል ለሽያጭ ለማዘጋጀት የተሰማራ ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። ተጠርጣሪው በመኖሪያ ግቢው ውስጥ ሀሺሽን በመዝራትና ለሽያጭ የሚያዘጋጅ መሆኑን የሚያመላክት መረጃ በማህበረሰቡ ጥቆማ ለፖሊስ መድረሱን ተከትሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሸንኮር ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የኮሚቲ ኦፊሰር የሆኑት ዋ/ሳጅን መሐመድ ሱፊያን ገልፀዋል ። በህግ የተከለከሉ አደንዛዥ እፅ እንዳይመረቱ፣ እንዳይሰራጩና በተለይም በህብረተሰቡ መካከል እንዳይሸጡ የፖሊስ አካላት የሚያደርጉት ቁጥጥር ቀጣይነት እንዳለው ታውቋል። በዚህ ረገድ የማህበረሰቡ ጥቆማ የወንጀል መከላከልና የህግ ማስከበር ስራን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳለው በመጠቆም፣ ህብረተሰቡ በአካባቢው የሚመለከታቸውን አጠራጣሪ የአደንዛዥ እፅ ምርትና ሽያጭ እንቅስቃሴዎች ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል። የተያዘው ተጠርጣሪ በህግ አግባብ በሚመለከተው አካል ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን፣ ከምርመራው በኋላ በሚገኘው ማስረጃ መሰረት ቀጣይ የህግ ሂደት እንደሚከናወን ተገልጿል። #ዳጉ_ጆርናል
በደብረ ብርሃን ከተማ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 162 ሴቶች ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ ሆነዋል ተባለ። የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተጠናቀቀዉ የ2018 በጀት ዓመት በአንድ ማዕከል አገልግሎት ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸዉ 162 ሴቶች አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል ። የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ሙሉጌታ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ከ162 ቱ መካከል 88 የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህፃናት መሆናቸዉን አቶ ጥላሁን አክለዋል ። የተቀሩት 74ቱ ከ18 ዓመት የዕድሜ ክልል በላይ ያሉ ሴቶች መሆናቸዉ ተገልጿል ። ሆስፒታሉ በሚሰጠዉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች የህክምና ፣የስነ ልቦና እና የፍትህ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ ተጠቁሟል ። ሆስፒታሉ ይህን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ2017 ዓመት ጀምሮ በተደራጀ መልኩ እየሰጠ ሲሆን መጉላላትን በእጅጉ መቀነሱ ተጠቁሟል ። ሴቶችን እንዲህ ካሉ ጥቃቶች ለመከላከል ሁሉም የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል የተባለ ሲሆን ወላጆች የልጆቻቸዉን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከታተል ይገባቸዋል ተብሏል ። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
ዶናልድ ትራምፕ ከውጭ በሚገቡ ድሮኖች ላይ እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ ቀረጥ ጣሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከውጭ በሚገቡ ድሮኖች እና መለዋወጫዎቻቸው ላይ እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ቀረጥ ጥለዋል። ይህም የተደረገው የብሔራዊ ደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል እና አሜሪካ በውጪ አቅራቢዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል። እርምጃው በ21 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተናገሩት፣ ሀገሪቱ በውጭ የድሮን ምንጮች ላይ ከመጠን በላይ ጥገኛ ናት በማለት አስተዳደራቸው ከቁልፍ አጋሮች የሚመጡትን ጨምሮ በድሮኖች እና በመለዋወጫዎቻቸው ላይ ቀረጥ እንደሚጥል አስታውቀዋል። ትራምፕ በፈረሙት አዋጅ መሰረት፣ ለብሔራዊ ደህንነት ዓላማዎች የተወሰነ መጠን ወይም ልዩ አቅም ላላቸው ድሮኖች የ100 በመቶ የዋጋ ተመን ቀረጥ እንደሚጣል በነጩ ቤተመንግስት ይፋ አድርገዋል ። በተጨማሪም በትናንሽ ድሮኖች ላይ 25 በመቶ ቀረጥ እንደሚጣል ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ከአውሮፓ ህብረት፣ ጃፓን፣ ሊችተንስታይን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ስዊዘርላንድ እና ታይዋን ለሚመጡ ድሮኖች እና መለዋወጫዎች 15 በመቶ ቀረጥ የሚጣል ሲሆን፣ ከብሪታንያ ለሚመጡ ድሮኖች ደግሞ 10 በመቶ ቀረጥ እንደሚጣል ነጩ ቤተመንግስት አክሎ ገልጿል። ሰላማዊ ነጋሲ #ዳጉ_ጆርናል
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በአዲስ አበባ ጉብኝት አደረጉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ:: የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ መጽሀፍ፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል:: በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብትና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል:: አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። #ዳጉ_ጆርናል