HUHCSF ✞
СтатистикаHaramaya University, Harar Health Campus Christian Students Fellowship Worship Center: @ Me'erab Harar MKC Meet Leaders: @DestaMekonnen
- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 116
- 1/48двое суток
- 132
- 1/72трое суток
- 143
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📣 3 ሳምንት ቀረው .... ✨መዝሙረ ዳዊት 133:1 ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። 🖐ሰላም ቅዱሳን ከዚህ በፊት እንደተናገርነው የሃረማያ ሃረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ክርስትያን ተማሪዎች ሕብረት አባል የሆንን እና ሆነን ያለፍን በአንድነት በጸሎት : በዝማሬ : ቃሉን በመስማት በጌታ ፊት የምንሆንበት ፤ እርስ በእርስ የምንጨዋወትበት ፤ ስለ ቀጣይ እርምጃዎች በአንድነት የምንመክርበት የምናመልክበት ፕሮግራም እለተ ቅዳሜ ነሃሴ 23 በአዲስ አበባ ተዘጋጅቷል ። ስለዚህ እስከ ፕሮግራሙ ቀን ድረስ እየጸለይን ፣ እንዲሁም ወዳጆቻችን እየጋበዝን፣ በዚህ ፕሮግራም ላይ የምንችል ሁላችንም እንደንገኝ ጥሪ እናቀርባለን ።
ሰላም የጌታ ውዶች! 👋🤗 "ከማማረር ወደ መዘመር" በሚል ርዕስ በፌሎሺፓችን የተዘጋጀው የትንቢተ ዕንባቆም ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በዚህ ሳምንት ቅዳሜ፣ ነሐሴ 2 ይቀጥላል። 📖 የዕለቱ ርዕስ፦ "የእግዚአብሔር መልስ፣ የነቢዩ ዝምታ" "ጻድቅ ግን በእምነቱ ይኖራል።" (ዕንባቆም 2፥4) ከእግዚአብሔር ቃል በመማር አብረን እንባረክ። 📚 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን፣ ማስታወሻችሁን እና ክፍት ልባችሁን ይዛችሁ በሰዓቱ ተገኙ። 📢 ይህን የተባረከ ጊዜ ለሌሎችም በማካፈል ወዳጆቻችንን እንጋብዝ፤ ከላይ ያለውን ፖስተር በProfile እና Story ላይ በማጋራት ፕሮግራሙን እናስተዋውቅ። 🙏 እንጠብቃችኋለን! ጌታ ይባርካችሁ።
ሰላም የጌታ ውዶች 👋🤗 “ከማማረር ወደ መዘመር” በሚል ርዕስ በFellowshipኣችን የተዘጋጀዉ የትንቢተ ዕንባቆም ተከታታይ ትምህርት በዚ ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 25 ይቀጥላል። በባለፈዉ የነበረዉ introduction ስለነበር በዚ ሳምንት ክፍል አንድን አብረን እንማራለን። 📌 የዕለቱ ርዕስ፦ “የነብዩ መልስ ያጣላቸዉ ጥያቄዋች እና የእግዚአብሔር ዝምታ” • በዚህ የተባረከ ትምህርት ጊዜ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። •ከእግዚአብሔር ቃል በመማር አብረን እንባረክ። 📖 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን እና ማስታወሻችሁን ይዛችሁ በጊዜ አንደትገኙ ይሁን። • እንዲሁም ይህን የተባረከ ጊዜ ለሌሎችም በማካፈል ወዳጆቻችንን እንጋብዝ። ከላይ ያለዉን Poster በProfile እና Story ላይ በማድረግ ፕሮግራሙን እናስተዋውቅ። ተባረኩ 🙏
ሰላም የጌታ ውዶች 👋🤗 “ከማማረር ወደ መዘመር” በሚል ርዕስ በFellowshipኣችን የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት በዚ ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 11 ይጀምራል። 📌 የዕለቱ ርዕስ፦ “የነብዩ ጥያቄ የእግዚአብሔር ዝምታ” • በዚህ የተባረከ ትምህርት ጊዜ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። •ከእግዚአብሔር ቃል በመማር አብረን እንባረክ። 📖 መጽሐፍ ቅዱሳችሁን እና ማስታወሻችሁን ይዛችሁ በጊዜ አንደትገኙ ይሁን። • እንዲሁም ይህን የተባረከ ጊዜ ለሌሎችም በማካፈል ወዳጆቻችንን እንጋብዝ። ከላይ ያለዉን Poster በProfile እና Story ላይ በማድረግ ፕሮግራሙን እናስተዋውቅ። ተባረኩ 🙏
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን! 🕊️ የ2014 ዓ.ም. ተመራቂዎች ለኅብረታችን ያበረከቱትን ልዩ ስጦታ ላበስራችሁ እወዳለሁ🎁; እሱም ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ የሚታየው አኮስቲክ (ቦክስ) ጊታር ነው🎸. እግዚአብሔር ይባርካችሁ🙏, በሄዳችሁበት ሁሉ ይምራችሁ, ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ይሁን✨. የምንወዳችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን, አብረን ላሳለፍነው ድንቅ ጊዜ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን 📖 መዝሙር 65፥4📖 “አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ 2:24 (NASV) 🎧 | Listen 👂 & Blessed 🙌🥰 👉Join&Share @SERVANTJOHN
#ስለእኛ✝️ He himself bore our sins in his own body on the tree, so that we, being dead to sins, should live for righteousness. By his wounds you were healed. 1 Peter 2:24 Blessed🙌🥰 Share&Join 👉 @SERVANTJOHN
የ21 ቀን የፆም ጸሎት ጥሪ 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን! የፊታችንን ሦስት ሳምንታት (21 ቀናት) በፌሎሺፓችን የታወጀ የፆም እና የጸሎት ጊዜ እንደሚኖረን ስንነግራችሁ በደስታ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የምንቆይበት መሪ ርዕሳችን፦ "እግዚአብሔርን መፈለግ" የሚል ስሆን። ይህን በሶስቱ ሳምንታት ከፋፍለን ፀሎታችንን የሚንቀጥል ይሆናል። 📌 የመጀመሪያ ሳምንት፦ እግዚአብሔርን መፈለግ በመመለስ 🙇♂️ 📌 ሁለተኛ ሳምንት፦ እግዚአብሔርን መፈለግ በቅድስና 🕊️ 📌 ሦስተኛ ሳምንት፦ እግዚአብሔርን መፈለግ በመታመን ❤ 📌 የዚህ ሳምንት ጸሎት ነገ ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀምር ስሆን፣ ቅዳሜና እሁድን በግል ካሳለፍን በኋላ፣ ከሰኞ ጀምሮ በጋራ እንጸልያለን። 🤝 የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 🙌
ሰላም የጌታ ቤተሰቦች፤ ባለፈው ሳምንት በገለጽነው መሠረት፣ የ2014 ባች ተመራቂ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የምንሸኝበት ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል። 🎓✨ በመሆኑም ሁላችሁም በተባለው ሰዓት ከቀኑ 11:00 ጀምሮ እንድትገኙ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን። 🕒 ጌታ በኅብረታችን መካከል ይገኝ! ነገ እንገናኝ! 🙏✨ 📖 መዝሙር 65፥4📖 “አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
ሰላም ወዳጆች ከዚህ በታች የሚገኘው የፌሎው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ነው ። አስራታችሁንና ስጦታችሁን እንድታስገቡበት ይሁን ። ተባረኩ🙌 1000634424109 Eshetu and eden
ሰላም የተወደዳችሁ በትናንቱ ማስታወቂያ እንደሰማችሁት የፀጋ ስጦታዎች እና አጠቃቀማቸው በሚል ርዕስ እየተማርነው ያለ የትምህረት ክፍለ ጊዜ የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል። የዚያ ቀን መርሃ ግብር የጥያቄ እና መልስ ክፍልን ያካትታል ስለዚህ ጥያቄያችሁን እስከ ማክሰኞ ምሽት 2፡00 ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ። ጥያቄ ለመላክ: 0904790081 0960479442 ተባረኩ🙏 📖 መዝሙር 65፥4📖 “አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
ሰላም ወዳጆች እንዴት ናችሁ በባለፈዉ ጊዜ ሲነገር እንደነበረው ለባቢሌ ቃለህይወት ቤተ ክርስቲያን የቦታ ማስጠበቂያ 5,000,000 ብር እንደተጠየቁና እኛም እንድናግዛቸው ጌታ በረዳን አቅም በዚህ የባንክ አካውንት እንድንጠቀም በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን🙏 (የአንድ ኩፖን ዋጋ 100 ብር፡ከዚያ በላይ መግዛት እንችላለን) 1000017533178(Ethiopian kale heywet church Harar)
✋ሰላም እንዴት ናችሁ በግቢ ያላችሁ የፌሎ አባላት። እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ የጠበቀን እግዚአብሔር ይባረክ። 👉 በነገውም እለት ከጠዋቱ 12:30-2:00 ድረስ የሚቆይ ስለ አዲሱ አመት እግዚአብሔረን የምናመሰግንበት ፕሮግራም ስለተዘጋጀ መጥታችሁ እንድትካፈሉ ስንል በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን። ተባረኩ።
“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።” — ፊልጵስዩስ 4፥6 ሰላም ሰላም በግቢም ሆነ ቤት ያላችሁ የህብረታችን አባላት የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ ። 👉 ጌታ ቢፈቅድና ቢንኖር ከጳጉሜ 1(ቅዳሜ)-5(ዕሮብ) ባሉት ቀናት ፦ ስለ 2017 ጌታን የምናመሰግንበት ፣ - ቀጣዩንም ዓመት ለጌታ አሳልፈን የሚንሰጥበት የጾምና የጸሎት ጊዜ ተዘጋጅቷል። 👉 ስለሆነም ግቢ ውስጥ ያለን ሁላችንም በእነዚህ ቀናት ውስጥ በተለመደው የማለዳ ፀሎት ጊዜ (12፡30-1፡30) Church በመገኘት በህብረት ፀሎት እናደርጋለን፤ ነገር ግን የጾም ጸሎት ፕሮግራሙ የሚቆየው እስከ ስድስት ሰዓት ስለሆነ የምንችል ሁላችንም በግላችን ስጋችንን ለእግዚ/ር እያስገዛን በእግዚ/ር ፊት በፀሎት እንድንሆን በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።
ሰላም ወደ ግቢ የተመለሳችሁ የfellowship አባላት 👉 የማለዳ ፀሎት ፕሮግራም ነገ(ዕሮብ) ጠዋት ይጀምራል። ስለዚህም ነገ ጠዋት 12:30-1:30 ድረስ የፀሎት ጊዜ ስለሚኖረን የምንችል ሁላችን በሰአት እንድንገኝ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።👈
✋ሰላም ወደ ጊቢ የተመለሳችሁ የህብረታችን አባላት በአንድነት የሚኖረን የህብረት የአምልኮ ጊዜ ቀጣይ ቅዳሜ ማለትም በ 17 ጅማሮውን እንደሚያደርግ ለማሳወቅ ነው ተባረኩ🙏 📖 መዝሙር 65፥4📖 “አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”
ሰላም ሰላም የተወደዳችሁ ፤ እንደምን አላችሁ ቤተሰብ ፤ ጥሩ የ እረፍት ጊዜ እያሳለፋችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን!☺️ እንደሚታወቀው የህብረታችንን 20 ኛ አመት በሃረር በደማቁ ግንቦት ወር ላይ አክብረናል። ጌታም በጣም የተወደደ ጊዜ እንደሰጠን እናስታውሳለን ። ወንድሞች በህብረት ሲቀመጡ በረከት እና ህይወት ከላይ መታዘዙ የምናውቀው ብሎም በተግባር ያየነው ሃቅ መሆኑን ያየንበት አንዱ ትውስታ ሆኖ አልፉል። አሁን ደግሞ 📆 ሐምሌ 26 (ቅዳሜ @3:00Lt) በድጋሚ አዲስ አበባ ለመገናኝት በዚህ ፌሎ ያለፉ ወንድም እና እህቶችን ለመተዋወቅ ብሎም ጸጋን ለመካፈል ተቀጣጥረናል። ለዚህም ራሳችሁን እያዘጋጃችሁ እንደሆነ ከብዙዎቻችሁ ሰምተናል። በ እለቱ ከ ፌሎ ፋሚሊዎቻችሁ ብሎም በ ቲም አብራችሁ ካገለገላችሁት ወንድምና እህት የመገናኝት ብሎም የማውራት ሰፊ እድል ይኖራል ። ስለዚህ ይህን እድል ለመጠቀም እየተደዋወላችሁ አብራችሁ እንድትመጡ ስንል በጌታ ፍቅር እናሳስባለን ። ለሜድስን ተማሪዎች ምናልባት ግቢ የመመለሻ ቀን ነሐሴ 1 እንደሆነ በጥቂቱ እየተሰማ ስለሆነ officially እስኪነገር ለጊዜው ከጉዟችሁ ጋር አብራችሁ ብትዘጋጁበት መልካም ነው:: ቦታው:- አዋሬ ሙሉወንጌል ቤ/ክ, ካዛንቺስ, እንደራሴ ለበረከት ሁኑ!🤗 (የክብረ በአሉ አስተባባሪዎች)
https://maps.app.goo.gl/V4CW3qjAGCsz6ZwK7?g_st=atm
ሰላም ሰላም የተወደዳችሁ፤ እንደምን አላችሁ ፤ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ!😇 ሁላችሁም እንደምታስታውሱት ግንቦት 10 (እሁድ) ሃረር ላይ በነበረን የ 20 ኛ አመት ክብረ በአል እለት ቃል በገባነው መሰረት፤ እነሆ አዲስ አበባ ላይ ዳግም ለመሰብሰብ ቀን ቀጥረናል። እንኳን ደስ አላችሁ! 🤩 የህብረቱ ዋና መሪዎች እና የክብረ በአሉ አስተባባሪዎች ባደረጉት ውሳኔ በዚህ ህብረት ያለፉ ብሎም አሁን ያሉት አብረው ስለ ቀጣይ እርምጃዎች በአንድነት እንዲመክሩ እና ጌታን እንዲያከብሩ አዲስ አበባ መገናኘቱ ግድ ሆኗል ። ለዚህም ከቦታ መረጣና ፈቃድን መጠየቅ ጀምሮ በሚያስፈልገው ሁሉ ዝግጀታችንን እያገባደድን ሲሆን ፤ የምንጠብቀው የሁላችሁንም መገኝት ብቻ ነው። ቀኑ እና ቦታው እንደሚከተለው ይሆናል;- 📆 ቀኑ --> ጌታ ቢፈቅድ እና ብንኖር ሐምሌ 26 ( ቅዳሜ ከ 3 ሰአት ጀምሮ ) ይሆናል። 💒 ቦታው ->> አዋሬ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ( አጋጣሚ በሚመስል ግን በ እግዚአብሔር ፈቃድ ይህን ቦታ ያገኝንበት ሂደት ሁላችሁም በአካል ስትገኙ የምናወራችሁ ይሆናል። ለፍንጭ ያክል ግን የ ሃረማያ EVASU የመጀመሪያው Staff የነበረ ወንድም በዚህች አጥቢያ መጋቢ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፤ በ እለቱም እርሱ የሚለን ነገር ይኖራል፤ ፓ/ር ዜናነህ ።) 📌 የቦታው መገኛ ለማወቅ 👇 የ Google Map መመልከት ይችላሉ፤ በ እለቱም ከተለያየ አካባቢ የምትመጡትን እናንተን ለመቀበል የተሰናዱ ወገኖች ይኖራሉ። ስልካቸውን ቀኑ ሲቃረብ የምናሳውቅ ይሆናል ። እስከዚያው ፕሮግራማችሁን በማስተካከል እየጸለያችሁ እንድትጠበቁ ይሁን። በቸር ያገናኝን!!🙌
ሰላም ለእናንተ ይሁን የተወደዳችሁ የህብረታችንን ተመራቂ ተማሪዎች የምንሸኝበት የሽኝት መርሀ ግብር ከፊታችን #ቅዳሜ በ23-09-2017 #ከሰዓት 8:00 በመሆኑ መደበኛ የቅዳሜ የህብረት ጊዜ የሰዓት ለውጥ ማድረጉን ለማሳወቅ እንወዳለን። በእነዚህ የትምህርት ዓመታት ያየነውን እግዚአብሄርን ስለተመራቂ ወንድም ና እህቶች በምስጋና የምንጠራበት የህብረት ጊዜ ይሆናል። 📖 መዝሙር 65፥4📖 “አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።”