Ismaiil Nuru
Статистикаዘመንን እናሰልማለን እንጅ ኢስላምን አናዘምንም! ሀሳብ/አስተያየት፦ @Ismaiilnuru_Bot
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 172
- 1/48двое суток
- 197
- 1/72трое суток
- 212
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ፍትህ ሃይማኖቱ ምንድን ነው? ────────── • ────────── ሰዎች «ፍትህ እምነት የለውም» ይላሉ። እንዴት ማስረዳት እንደሚችሉ እነርሱ ራሳቸው የሚያውቁ አይመስለኝም። ፍትህ እምነት አለው። ለዚህ ነው ዓለም በሙሉ ፍትህ ላይ መግባባት ያልቻለው። እኛ ሙስሊሞች ፍትህ የምንለው አላህ ፍትህ ያለውን ብቻ ነው።ሌላውም በሃይማኖቱ እንዲሁ ፍትህ የሚለው እምነቱ ፍትህ ያለውን ነገር ብቻ ነው ። ለምሳሌ :- አንድ ሙስሊም የሰረቀ ሰው እጁ መቆ ረጡ ፍትህ ነው ብሎ ያምናል።ክርስቲያኑ ደግሞ ይህን ጭ ካኔ ይለዋል ። ዝሙት የፈፀመ መገ ረፉን ሙስሊሙ ፍትህ ይለዋል። የ «ሰብአዊነት» ሃይማኖት ተከታይ ደግሞ ይህን የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው ብሎ ያምናል! አንድ ሙስሊም ሶዶ• ማዊና ሌዝ•ቢን ከከፍታ ላይ ፈጥ-ፍጦ መግ~ደልን ፍትህ ነው ብሎ ያምናል ። የሊብራሊዝም ሃይማኖት ተከታይ ደግሞ ከጅምሩ ሶዶ-ማ-ዊነትን ወንጀል ነው ብሎ አያምንም ! አንድ ሙስሊም ሴትን ልጅ የደ•ፈረ•ን መግ ደል ትክክለኛ ፍትህ ነው ብሎ ያምናል ። በአንፃሩ ክርስቲያኑ ወይም በህግ የሚያምነው ሰው እድሜ ልክ ወይም 20አመት ምናምን መታሰርን ፍትህ ይለዋል። ታድያ ሰዎችን በሙሉ የሚያግባባው ፍትህ የቱ ነው ? እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ በጣም ከሚደንቁኝ ነገሮች አንዱ የ 6/7 ሃይማኖት ተከታዮች ሆነው በአንድ ላይ የሆነ ወን ጀል ላይ ፍትህ ለእገሌ የሚሉት ነገር ነው። የ 7ቱም እምነት ተከታዮች ግን ፍትህ ምንድን ነው ቢባሉ የሚሰጡት ምላሽ 7 አይነት ነው ! ለምን ከተባለ ፍትህ ሃይማኖት ስላለው ! ይህ ጥያቄ ደግሞ ለሙስሊሞች ነው:- የሆነ የበ ደል አጀንዳ በመጣ ቁጥር ከሌሎች ጋር በመሆን «ፍትህ ለእገሌ» የምትሉት በየትኛው ፍትህ ሳይድ ሆናችሁ ነው ? ከአላህ ህግ ውጭ ፍትህ የሚያሰፍን አለ ብላችሁ ታምናላችሁ ? እንደዚያ ብላችሁ ካላመናችሁ ደግሞ በቁርአን የሚፈርድ መንግስት በሌለበት ሁኔታ ፍትህ ለእገሌ ማለቱ ምን ጥቅም አለው? በፍትህ ትርጉምና እሳቤ ላይ ካልተግባባሃው ሰው ጋር ፍትህ ማለት ስሜት ይሰጣል? «የማይማንን ፍርድ ይፈልጋሉን? ፍርድን ከአላህ የበለጠ አሳማሪ ማነው?፤ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች» (አልማኢዳህ 50) ከአላህ ሸሪዐ ውጭ ፍትህን የሚሻ ሰው የአላህን ፍትሀዊነት እንዳላረጋገጠስ ማስረጃው ይኖራችሁ ይሆን ? ፍትህ ደግሞ አንድ ናት ። ሁለት ፍትህ የለም። ፍትህም ሃይማኖት አለው ! ቴሌግራም፡- t.me/ismaiilnuru
без подписи
без подписи
ዝሙትን የሚከለክል ህግ ግን የላቸውም ! አላህ በእዝነቱ ይዞን እንጅ ከሰማይ እሳት 🔥 ቢዘንብ ሲያንሰን ነውኮ ...
«መጤው እስልምና እንጅ እኛ አይደለንም!» «እናንት ሙስሊሞች መጤ ናችሁ» ለሚሉ ክርስቲያኖች በመልስነት የሚሰጥ ንግግር ከሆነ ሰነበተ።መጤነት የሚለው ፅንሰ ሀሳብ መነሻው ድንበር ነው ። የቦታ ባለቤት አለመሆንን የሚገልፅ መሆኑ ነው ።ይህ የመሬትና የቦታ ክለላ የመጣው የሰው ልጆች በምናባቸው ባሰመሩት ወሰን እንጅ አላህ ማስረጃ ያወረደበት ክፍፍል ሆኖ አይደለም። መጤ መባል የሚያሸማቅቅህ ከሆነ አንተ በሰው ሰራሽ ድንበር ታምናለህ ማለት ነው ።አላህ ምድርን ሰፊ አድርጎ የፈጠራት በየትኛውም አቅጣጫዋ ተንቀሳቅሰህ እንድታመልከው ነበር።በክቡር ቃሉ እንዳለው :- يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ أَرْضِي وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ «እናንተ ያመናችሁ ወይ! ምድሬ ስፊ ነችና እኔንም ብቻ አምልኩ» (አል ዐንከቡት 56) እዚህ ምድር ላይ አላህ ድንበር አስቀምጦ ይህ የእገሌ ያ የእገሌ ነው ብሎ ያከፋፈለው መሬት የለም ፤ ነገር ግን ሰዎች ራሳቸው ድንበር አበጁና ለነዚሁ ድንበሮች ራሳቸውን ባሪያ አደረጉ። አላህ የሰጣቸውን የመንቀሳቀስ ነፃነት በራሳቸው ወይም በጠላ ቶቻቸው እጅ ገደቡ። ከዚያም አልፎ የኔ ያንተ የሚል ምናባዊ ወሰን አስቀምጠው እርስ በርስ ይተላለቃሉ። «የሀገራችን» ኩፋ••ሮች መጤ ሲሉ እንዳልሆነ ለማሳመን የሚጥር ሰው በድንበር ያምናል ማለት ነው።ይህም ድንበር ኢትዮጲያዊነት መሆኑ ነው።በተቃራኒው መጤነት ወንጀል መሆኑን እያፀደቀላቸው መሆኑን ግን አይረዳም። በዚህ እሳቤ መሰረት ረሱል ﷺ ወደ መዲና «መጤ» ሆነው ነው የገቡት።ነገር ግን መዲና ላይ «በጥገኝነት» ከመኖር አልፈው «በሰው ሀገር ላይ» ኢስላማዊ መንግስት መሰረቱ። ቋሚ ነዋሪ ሆነው እዚያው ሞተው ተቀበሩ። ዛሬ ላይ ረሱል ﷺ ሲነሱ በማንም ሰው አእምሮ ቀድሞ የሚመጣው መዲና እንጅ መካ እስከማይሆን ድረስ! ረሱል ﷺ ከዚህም አልፈው የተሰደዱበት ሀገር ሰዎችን ይዘው የትውልድ ሀገራቸው «ዜጎች » ላይ ጦርነት ከፍተው ድል አድርገው ገብተዋል። በዘመኑ እስቤ ይህ «ባንዳነት» ይባላል! «እኛ ሳንሆን መጤው እስልምና ነው» ብለው ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ረሱልም ﷺእምነታቸውም መዲና ላይ መጤ ናቸው ማለት ነው ! ስለዚህ መጤነት ነውር ከሆነ ዲነል ኢስላም ለመዲና ሰዎች ነውር ነበር። ወይም ረሱል ﷺ ሰው ሀገር ላይ መጤና እምነታቸውም መጤ ነበር ማለት ነው ! የመዲና ሰዎች መጤ ስለሆናችሁ ሀገራችንን ልቀቁ ወይም መብታችሁን አናከብርም ቢሉ በነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ ትክክል ነው ማለት ነው ! ከጅምሩ የአደም ልጆች ሁሉ የተፈጠሩበትን ዲን «መጤው እሱ ነው » ማለት በራሱ የዲናዊ እውቀት ሸፋፋነት እንጅ ሌላ አይደለም ! አላህ ምድርና ሰማያትን የፈጠረበትን እምነት መጤ ማለት በራሱ የዐቂዳ ፈሳድ እንጅ ሌላ አይደለም! ኢስላም በድንበርና በድንበር ላይ በተመሰረቱ ማንነቶች ሁሉ አያምንም ። ያ ባይሆን •ሙዐዊያ ከመካ ሻም ሄዶ አስተዳዳሪ አይሆንም ነበር! •ዐሊይ ኩፋ ላይ •ዐምር ኢብኑል ዐስ ግብፅ ላይ •አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ ዒራቅ ላይ •አቡ ሁረይራ በህረይን ላይ •አቡ ዑበይዳህ ፍልስጤም ላይ •አመውያ ኸሊፋዎች ቱርክና ስፔን ድረስ ሄደው አያስተዳድሩም ነበር። አይ መጤ እንዳንባል አርፈን መካችን ላይ እንኑር ብለው ይቀመጡ ነበር። እሽ ሰሃቦች ይህን ያደረጉት በዚህ ዘመን ቢሆን «ሰው ሀገር ሄደው እምነታቸውን ማስፋፋታቸው » አግባብ አይደለም ልንል ነው ? ወይስ መጤ ስለሆኑ ሀገራት ወደ ቦታቸው ይመልሷቸው ልንል? እኛ ኢትዮጲያውን ነን «ብለን» ለማሳመን የምንጥረው የሀገር ባለቤትነታችን እንዲታመንልን ነው አ ? ስለዚህ ሰሃቦች ከመካ ተነስተው ኢራቃዊ ፣ ሻማዊ ወይም ግብፃዊ ሳይሆኑ ሰው ሀገር ላይ መኖራቸው ጥፋት ነበር ማለት ነው ? ኢትዮጲያዊ ነን «ስንላቸው » የማይቀበሉን ከሆነ የሰው ልጆች ሁሉ የተፈጠሩበትን እምነት መጤው እሱ ነው እንድንል የፈቀደልንስ ማን ነው ? ኢማሙ አህመድ (ግራኝ) በኢስላማው ወንድማማችነት ትስስር ድንበር ተሻግሮ ሄዶ በቱርኮች ትብብር የሀገሩን አፄዎች መፋለሙስ ባንዳነት ነበር? ኢማሙ አህመድስ መጤ ነበር? ኢስላም ለምድር ሁሉ የወረደ ዲን ነው። እስልምናን በድንበርና በሐገርተኝነት ጠባብ አስተሳሰብ ጠርንፈን ከመረዳት እንውጣ ! ቴሌግራም :- t.me/ismaiilnuru
без подписи
እንተባበረው! ዱዐችን የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነው። የማንኛችን ዱዐ መቅቡል እንደሚሆን አይታወቅም! ተባበሩት ያ አህባብ !
ይህ ውብ ዲን አንተ ጋር የደረሰው 313 ጀግኖች በድር ላይ በመፅናታቸው ነው !! ቴሌግራም :- t.me/ismaiilnuru
без подписи
без подписи
без подписи
አቡ ጁሐይፋ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል :- «ዐሊይን ረዲየላሁ ዐንሁ ጠየቅኩት ፥ እናንተ የረሱል ቤተሰቦች በአላህ መፅሀፍ (ቁርአን) ውስጥ ካለው ወሕይ ውጭ (ረሱል ለናንተ ብቻ የሰጧችሁ) መፅሃፍ አላችሁ ? አልኩት። እሱም ፡- «ፍሬን በፈለቀቀና ሰውን በፈጠረው ጌታ እምላለሁ ! አላህ ለአንድ ሰው የሚሰጠው የቁርአን ግንዛቤና በዚህች ወረቀት ውስጥ ከተፃፈ ነገር ውጭ (ረሱል ለኛ ብቻ የሰጡን መፅሃፍ የለም) አላውቅም ።» አለኝ። እኔም ፡- «በዚች ወረቀት ውስጥ ያለው ምንድን ነው ?» በማለት ጠየቅኩት ። እሱም « ስለ ደም ካሳ ፣ ስለ (ሙስሊም) እስረኛን ማስፈታት እና አንድ ሙስሊም ካፊርን ቢገድል እንዳይገደል (የሚል ድንጋጌ ) ነው የሰፈረበት በማለት መለሰልኝ። (ቡኻሪይ 3047) በኢስላም የገደለ የሚገ•ደለው ሟች ሙስሊም ከሆነ ነው።ሟች ካ •ፊር ከሆነና ገ •ዳይ ሙስሊም ከሆነ~ በስህተት ከሆነ ግማሽ የሙስሊም ደም ካሳ ፣ሆን ብሎ ከሆነ ደግሞ ሙሉ የሙስሊም ደም ካሳ ይሰጠዋል እንጅ ሙስሊሙ ገ• ዳይ አይገ°ደልም ። ካፊሩ ዚሚይ (ግብር እየከፈለ የሚኖር)፣ ወይም ሙዓሂድ (የሰላም ውል የተፈራረመ) አለያም ሙስተእመን (በዋስትና የገባ) ቢሆን እንኳን ሙስሊሙ ለሱ ተብሎ አይገ°• ደልም። ምክንያቱም ረሱል (لَا يُقْتَلَ مُسْلِمٌ بِكَافِرٍ) ስላሉ፤ ሙስሊም በካ• ፊ ር አይገደ--ልም። ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፈው «አንድ ሙስሊም ዚሚይን ሆን ብሎ ገ°ደለ።ክሱም ወደ ኡስማን መጣ። ዑስማንም አልገደሉትም፤ ይልቁንም የደም ካሳውን አጠነከሩበት፤ ልክ እንደ ሙስሊም ደም ካሳ ። » (ዳረ ቁጥኒይ 3289) ኢብኑ ሐዝም እንዲህ አሉ ፡-«ይህ ትክክለኝነቱ የጠነከረ ነው ፤ ከዚህ ውጭ ከሰሃቦች የተገኘ የለም፤ ከዑመር የዘገብነው ሲቀር፥ እሱ (ዑመር ) ረዲየላሁ ዐንሁ በዚህ መሰል ጉዳይ ላይ ገዳ። ዩን ሙስሊም ወደ መገ። ደያ ቦታ እንዲወሰድ አዘዙና ከዚያም አብረው መልእክት ላኩ ፤ አትግ•ደሉት ነገር ግን የደም ካሳውን አስከፍሉት » (ኢርዋኡል ገሊል 7/312) [ኢብኑ ሀጀር (አት ተልኺስ 4/16) ላይ እንዳሰፈሩት] ኢማሙ አህመድ ሙዓሂድን ስለገ•ደለ ሙስሊም ብይን ተጠየቁ። እሳቸውም :- «ቂሳስ (ነፍስ በነፍስ መገደል) ይነሳለታል።የደም ካሳ ግን ይጨመርበታል። የገደ•ለው በስህተት ከሆነ ግን የሙዓሂድ የደም ካሳ ይከፍላል ።እሱም ግማሽ የሙስሊም ደም ካሳ ነው ። (መሳኢሉል ኢማሚ አህመድ ወብኑ ራህዊየህ 7/3498) ስለሆነም እስልምና በእኩልነት አያምንም። በእኩልነት ቢያምን ነፍስን በሃይማኖት ለይቶ ብይን አያስቀምጥም ነበር። የእኩልነት ፍልስፍና ፡- እኩልነት ከወረቀት ባለፈ በተጨባጩ አለም ህልውና የሌለው እውነታ ነው።ማንም አካል የርሱ አመለካከትና እምነት የተሻለ መሆኑን ያምናል።ከርሱ ውጭ ያሉ እምነትና አመለካከቶች ደግሞ ትክክል እንዳልሆኑ ያምናል ።ስለሆነም ለአመለካከቱ የበላይነት ይሰራል እንጅ ሀሰት ነው የሚለውን አመለካከት ከርሱ ጋር እኩል እንዲሆን አይሰራም። ምክንያቱም ስህተት ነው ብሎ ስለሚያምን! ስህተት ነው የሚለውን አመለካከት ከርሱ ሐቅ ጋር እኩል መብትና ደረጃ እንዲኖረው ሊቀበል ሎጅካል አይደለም። ለምሳሌ ካፒታሊስቶችና ሶሻሊስቶች ስንት ሚሊዮን ህዝብ የፈጁት በእምነታቸው የበላይነት እንጅ በእኩልነት ስለማያምኑ ነው። ስለሆነም አንዱ አንዱ ጋር ለመጠ ፋፋት እንጅ እኩልነት ለሚሉት ወረቀት ላይ ያለ ፍልስፍና አይሰሩም።አንተ ዳቦን ዳቦ ነው ብለህ ስታምን ሌላው ዳቦ ማለት ድንጋይ ነው ብሎ እያመነ እኩል ነን ካልክ ለምን ከጅምሩ ዳቦ ድንጋይ ነው ብለህ አታምንም ? ምክንያቱም ሁለቱም እኩል ነዋ! ሙስሊሙ ያልገባው እውነታ አላህ በ «ላኢላሃኢለላህ » ከሁሉ እምነቶችና አመለካከቶች የበላይ ያደረገው መሆኑን ነው ! ስለሆነም አላህ ከሌሎች ጣኦት አምላኪዎችና ካ• ፊሮች ጋር በምድሩም ይሁን በሰማዩ ላይ እኩል መብትና ግዴታ አልሰጠውም! ደሙንና ገንዘቡንም ከሌሎች ደምና ገንዘብ የበላይ አድርጎታል። እነሱም ቢሆኑ ይህን እውነታ ጠንቅቀው ያውቃሉ። እኛን ከነርሱ ጋር እኩል መብት የላቸውም ብለው ስለሚያምኑ ደማችንን ርካሽ ደም ይደርጋሉ። በእኩልነት የሚያምኑ ከሆነ የሁ-ዳና ነሷ-ራዎች ለምን ይገድ--ሉናል ? ኢስራ--ኢል በጋ-ዛ አሜሪካ በዒራቅ፣ አፍጋን፣ ሱማሊያ፣ ሶሪያ ወዘተ ለምን ይጨፈ--ጭፉናል ? ስለዚህ እነርሱ ስለ የበላይነት ሲሰብኩና ሲተገብሩ ትክክል ኢስላም ሲሰብክ ግን ስህተትና ነውር የሚሆንበት ሎጅክ ምንድን ነው ? አመለካከቶች ሁሉ ምድር ላይ የሚያደርጉት ጦርነት ለማሸነፍና የበላይ ለመሆን እስከሆነ ድረስ ኢስላምም ራሱን የቻለ እምነትና ስርአት ስለሆነ የመጣው ለበላይነት እንጅ ለእኩልነት አይደለም! አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል :- هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ «እርሱ (አላህ ) ያ መልዕክተኛውን በመምሪያ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት (ኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ የበላይ ሊያደርገው የላከ ነው፤ አጋሪ•ዎቹ ቢጠ|ሉም» (አስስፍ 33) ይህን የበላይነት ለምደንኮ ነው ስል እኩልነት ሲነገረን የበታችነት የሚሰማን! የቴሌግራም ቻናል : t.me/ismaiilnuru
без подписи
የሚደንቀው ይህ ብቻ አይደለም ።አሜሪካ ውስጥ 2 ሚስት አግብተህ ብትገኝ ትቀጣለህ ። እንደ ሁኔታው 10አመት በሚደርስ እስራትና የገንዘብ ቅጣት። በBF /GF ግን 20ም 30ም ሴት ጋር ብትማ-ግጥ ችግር የለውም፤ብቻም ሳይሆን መብትህ እንደሆነ ይታመናል። ሚስት ካልካቸው ግን በጣም ፀያፍ አስተሳሰብ እንዳመጣህ ነገር አፋቸውን በአግራሞት ይዘው How? ብለው ይጮሃሉ። ለዚህ ነው እስከቂያማ ድረስ ከምዕራባዊያን ጋር በትርጉም ከማንግባባቸው ጽንሰ ሀሳቦች አንዱ የዝሙት ትርጓሜ ነው ያልኩት። በጣም የሚያሳዝነው ምን እንደሆነ ታውቃለህ ? ለኛ ለኢስላም ልጆች የማህበረሰብ እሴት (community standards) የሚያወጣልን ይሄው ወሰኽ ማህበረሰብ መሆኑ! በጣም የሰለጠነ ማህበረሰብ ሆኖ¡ ይህ የማህበረሰብን ሞራል ስለሚነካ ይህን ቃል አትጠቀም ፣ ይህንን ድርጊት አትከውን፣ ይህን አስተሳሰብ አታራምድ እያለ የሚመክረንና የሚያስተምረን ማህበረሰብ እሱ መሆኑ! አላህ አላህ!! የቴሌግራም ቻናል ፡t.me/ismaiilnuru
без подписи
በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ለማጋራት ይህን ያውርዱ ።
без подписи
без подписи
50 ጊዜም ተፈቺ፤ ጋብቻሽ በሐላል እስከሆነ ድረስ አንች ንፁህ ነሽ! ትዳር ከአላህ የሆነ እድል እንደሆነው ሁሉ መፈታትም እድል ነው።በባህሪሽ ከሆነ ትምህርት ወስደሽ ታስተካክያለሽ፤ በባህሪው ከሆነ ሌላ አንችን ሰፍ ብሎ የሚጠብቅ አለ፤ አንች ሴት ነሽ! የዱንያ ደስታ ሁሉ ካላንች አይሞላም! እንዲያ ባይሆንማ የሰው ልጆች ሁሉ እናት ላይ ተመሳሳይ አቋም አይኖራቸውም ነበር! @ismaiilnuru
አንድ አዕራቢ ሐጅ ሄደ፤ ዐረፋ ላይ (ሲቆም) ምን ብሎ ዱዓ ማድረግ እንዳለበት አያውቅም ነበር ። እንዲህም አለ፦ «አላህ ሆይ! ዐረፋን ከፈጠርክባት ቀን ጀምሮ ለማኞች እዚህ ቦታ ላይ የለመኑህን ኸይር ሁሉ እለምንሃለሁ።» ሰዎችም አሉ :- 👉ለቀድ አብለገ ፊ ዱዓእ! «ሁሉንም ያካተተ ዱዐ አደረገ።» አላህ የዱዐህን ቤት መምታት ፣የቃላት መቀናጀት ምናምን አያይም ! የልብህን መሻት ብቻ በቻልከው አለማመን ለምነው ! ዐረፋ ላይ ስንቱ ነብይ፣ስንቱ ሲዲቅ፣ስንቱ ሷሊህና ስንቱ ሸሂድ ስንቱን ኸይር ለምኗል! Youtube: http://youtube.com/@ismaiilnuru Telegram: t.me/ismaiilnuru Facebook: fb.com/ismaiilnuru