የእኔ ማስታወሻዎች ✍🏽”
Статистикаከህይወት የተቀዱ ሃሳቦች እንጥፍጣፊ ስሜት ሽርፍራፊ ሀሳብ እይታ ምናባዊ ሀሳብ የብዕር ስሜ ኪያብ✍🏽 "መኖር ጥሩ ነው.... አስተያየት መስጫ: መወያያ group 👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾 https://t.me/mekiyab (ኪያብ) @itsmekiyab
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 80
- 1/48двое суток
- 91
- 1/72трое суток
- 98
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
ራሴን ብሎም ማንነቴን ለምወደው ሰው ከፍቼ ነበር፤ የምወደው ሰው ግን በእኔ ክፍተት ውስጥ በፍጥነት እጁን ሰደደና ህመሜን ቆፈረው!።
«አንድ ሰው ላይ ከሚደርሰው መጥፎ ነገር መካከል በናፈቀው ነገር ላይ አቅም ማጣት ነው። የሚቀርበውን ሰው ከልቡ ለማውራት አቅም ማጣት፤ ለረጅም ውይይትና ንግግር አቅም ማጣት፤ በሚያናድደው እና በሚያበሳጭ ነገር ላይ እራሱን ላለመውቀስ እስከመጨረሻው አቅም ማጣት። መነሻውም መድረሻውም በጸጸት የተከበበ ብቸኝነት ለብቻው ማስተናገድ!።» ፦ሙሐመድ ሹክሪ―Counting stars 📖
አዲስ የህይወት አቅጣጫ ልጀምር እንደሆነ እያሰብኩ ድጋሜ እንደማላይህ አሰብኩ። አይገርምህም ስንት ቅድሚያ ላስባቸው ከሚገቡ ነገሮች በፊት ደግሜ አይኖችህን እንደማላይ መቀበሉ busy አረገኝ። ሁለተኛው እና ሶስተኛው ቀን ላይ በመንገዴ ሳገኝህ እግዜር ተሰናበችው ብሎ እድል የሰጠኝ ነበር የመሰለኝ።ወይም እንቁልልጭ አታዪው እንደው ከዚህ በኋላ ያለኝ አይነት። እኔም በልቤ ተሰናበትኩ።"በቃ ቃል ይሄው ነው" አልኩና ራሴን አጀገንኩ።ለወደደ ጀብዱ መለየትን መቀበሉ አይደል ለመጨረሻ ጊዜ የመጨረሻዎቹን ሁለት ቀናት ምሽት እያየሁህ ከጀርባም ቢሆን አይኖችህን ሸኘሁ። የኔ መድረሻ ቀድሞ መሆኑ መልካም ነው አይደል ቀድሜ ለመቁረጥ እድሉን ሰጠኝ።በእኔው የተጀመረ ታሪክ በእኔው ተቋጨ። ከእንግዲህ አላይህም።ይሁን ተቀብዬ move on አድርጌያለሁ።ግን አሁን ለምንድነው የምትናፍቀኝ?ቀድሞ ያልተጀመረ ታሪክ ይቋጫል? ይሁን ቢቋጭስ ባር ባር ይላል? Kal
በመራራቅ ውስጥ በጣም የሚያስጠላው ነገር ይናፍቁህ ይርሱህ አለማወቅህ ነው ኖቫ
ብቻ እንዲህም ሆነ እንደዛ እንኳን ተወለድክ ለዮሀናን
ትርጉምን ስፈልግ የዋጋ ማንነት ሲያሳስበኝ ትንሽ ወደ ድሮ ሸርተት ማለት ያምረኛል፣ ብቻ ዛሬን ባልጠላውም እንዲያው ግን የማላውቀው ድሮ ይናፍቀኛል፣ ይሄም ዘመን የሚናፈቅ ድሮ ይኖረው ይሆን? እንጃ........
.......የተለያየ መንገድ ጀምረናል እንዴት እንደተለያየን እንጂ እንዴት ሁለታችንም በተለያየ መንገድ ተጉዘን ጭራሽ እስከማንተያይበት ድረስ ማዶ ለማዶ እንደተራራቅን አላውቅም...... ዓለም እንደመንደር ጠባለች" ብለው ነበር አይደል🤔 ......................................................... ✍✍ዮቶራዊት 🎤🎤 ኪያብ @itsmejerrymejerry
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ባይገርም አለሁ እየኖርኩ ነው አልወደኩም ወድቄም አልቀረሁም ልቤ ደከም ዛል ቢልም እየኖርኩኝ ነው ባለፈው ሳቄን አትመነው ብዬህ አልነበር ያው ነው አልተለወጠም ብወድቅ ባጣ ንቆኝ ለሚያልፍ ለሚፀየፈኝ ሰው ደሞ ተሰብሮብኝ የሰፋሁትን ልቤን ላሳየው አይሆንም ጥርሴ እስከፈቀደልኝ እስቃለው
ከራስ ሰው ጋር መንዘላዘል ትዝታውም ሁኔታውም ይጣፍጣል አድሓኖም ምትኩ
👁️ ማወቅ ወይስ ዝም ብሎ መኖር? በዚህ ምድር ላይ ሁለት አይነት ሰዎች ብቻ አሉ። የመጀመሪያዎቹ ዝም ብለው የተሰጣቸውን ህይወት የሚኖሩ፣ ማህበረሰቡ የጫነባቸውን እውነት ሳያጣሩ የሚቀበሉ እና በለመዱት መስመር ብቻ የሚጓዙ ናቸው። ሁለተኛዎቹ ደግሞ ለማወቅ የሚራቡ ናቸው። መማር ማለት በትምህርት ቤት ወንበር ላይ ተቀምጦ ወረቀት መሰብሰብ አይደለም። እውነተኛ መማር ማለት አእምሮህን ከተጋረደበት መጋረጃ መግለጥ፣ አለምን በራስህ አይን ማየት እና ትናንት ከነበርከው በላይ ዛሬ ማደግ ነው። "የማያውቅ ሰው ጨለማ ውስጥ ነው፤ ማወቅ የሚጀምር ሰው ግን የራሱን እሳት ያነድዳል።" 💡 ማወቅ ምን ይሰጥሃል? ፍፁም ነፃነት፦ ሳታውቅ ስትቀር የሰዎች ጥገኛ ትሆናለህ። ስታውቅ ግን ማንም ሰው ሊያታልልህ ወይም ሊመራህ አይችልም። የራስህ ጌታ ትሆናለህ። ልዩነት፦ አለማወቅ ሰዎችን ሁሉ አንድ አይነት (መንጋ) ያደርጋቸዋል። እውቀት ግን ካሉበት ረግረግ አውጥቶ ከፍ ያደርግሃል። የውስጥ ጉልበት፦ እውነተኛ እውቀት ያለህ ሰው ስትሆን ፍርሃትህ ይቀንሳል። ምክንያቱም ጨለማን የምትፈርደው ስለምታየው ሳይሆን ስታጣው ነው። ⚡ የእውነተኛ አዋቂ ሰው መንገዶች፦ ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን፦ "ሁሉንም አውቃለሁ" የምትልበት ቀን መማርህን ያቆምክበት ቀን ነው። እውነተኛ አዋቂ ሁሌም አዲስ ነገር ለመቅሰም ዝግጁ ነው። ከስህተት መማር፦ አለማወቅ ስህተት አይደለም፤ ካለማወቅህ ውስጥ ተምረህ አለመውጣት ግን ትልቅ ውድቀት ነው። በምክንያት መኖር፦ እያንዳንዱን የምታደርገውን ነገር "ለምን?" ብለህ ጠይቅ። ህይወትህን በምክንያት እና በእቅድ እንጂ በዘፈቀደ አትምራት። "መማር አእምሮን ፈጽሞ የማይደክምበት ብቸኛው ነገር ነው።" ማወቅህን አታቁም፤ አእምሮህን መገበውን ቀጥል። እውቀት የአንተ ትልቁ መሳሪያ እና ሀይልህ ነው! 🔥🧠
አይገርማቹም! ግን ከባድ የምንለው የትምህርት ቤት ፈተና እንኳን ሌላ የሚበልጠው አለ የህይወት ፈተና ህህህ ይሄ ፈተና ደሞ ክብደቱ በተግባር ነው ውድቀቱ ተግባር ነው
ያለህን ቦታ አለማወቅህ አለመረዳትህ ይገርማል የኔ ልብ ላይ ተከብረህ ተወድህ ተጠብቀህ ነበር ይገርማል አለማወቅህ
እምነግርህ የነበረኝ ኖረኸኝ በነበር ነው