tgindex
JUECSF Counseling Official

JUECSF Counseling Official

Статистика
@juecsfcounselingанглийский

Christian counseling channel, dedicated to serve u, through prayer,biblical counsels, and audio messages. For anonymous counseling services @juecsfcounselingbot @naold2 @ayimofA @eyasudegu7 @bamaloy

Последний пост
1 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
45
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
706
+5 за 4 дн.
Сутки
+1
+0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 182
40 постов
Вовлечённость
167,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 45
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 1 июн.303203

    መክብብ መፅሃፍን ሰለሞን ሲፅፍ በእድሜው መጨረሻ አካባቢ ነው። እናም እኔም አንድን ነገር ተማርኩ 700 ሚስቶች እንድሁም 300 ቁባቶች ያሉት ፤ በጥበቡ የሚታወቅ ፤ ትልቅ ሀብታም የሆነችውን እስራኤልን በዘመኑ የመራ ፤ ግዛቱ ደግሞ የሰላም የሆነለት ሰለሞን በእድሜው መጨረሻ ከፀሃይ በታች ሁሉም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ካለ ሌላ ምን ማረጋገጫ ያስፈልገናል? ይልቁኑ በጊዜ የፀፀት ግዜ ሳይመጣ ውድ እግዚአብሔር መጠጋት እርሱን የበለጠ ማወቅ ይሁንልን። አሜን🙏🙏 መልካም ቀን ይሁንላችሁ 🤗🤗🤗 #hesedmultimedia                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • አስደናቂው የእስረኛ ልውውጥ ፦ በርባን ለጲላጦስና ለህዝቡ አደጋ ከመሆኑ ይበልጥ ኢየሱስን እንደ አደጋ የተመለከቱበት አጋጣሚ ነው፤ "ንፁሁን በነፍሰ ገዳዩ" ፤ አይሁዳውያን ጲላጦስን አስወግድ ያሉት ኢየሱስ የተከሰሰዉ  በሃሠት ክሶች ሲሆን የተፈታው ግን በትክክለኛ ክስ ወህኔ ቤት የገባው ሰዉ ነው። እዚህ ጋር የእግዚአብሔር ቃል ይህን አጋጣሚ ለኛ ሲያስቀምጥልን የተከፈለልንን ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ያሳየናል። አንድ ሰው ኢየሱስ ያለ ምንም ጥርጥር ከማንም በላይ ለኔ ሞቶልኛል ማለት ካለበት እሱም በርባን ነው ምክንያቱም የተፈታው ኢየሱስ በእርሱ ቦታ ሞት ተፈርዶበትና እሱ ነጻ ወጥቶ ስለሆነ፣  በርባን ምናልባትም ለብዙ ጊዜ በእስር ሊቆይ አልያም ሞት ፍርድ ተፈርዶበት ቀኑን እየተጠባበቀ ያለ ሰዉ ነው፡፡ አይሁዳውያን ነፍስ ገዳይ እንዲፈታላቸው መለመናቸው አስገራሚ ነገር ነው። አንዳንዴ ደግሞ ለብዙዎቻችን ይህ ልውውጥ ያን ያህል ትርጉም ላይሰጠን ይችላል ግን እኛ እራሳችን በርባን እንደነበረን ብናስብ ግን ይህን ነገር ለመረዳት በጣም ቀላል ነው፤ ጴጥሮስ እነዚን ሠዎች ወንጌልን ሲሰብካቸው "የህይወትንም ራስ ገደላችሁት" ብሎ ነበር፤ ይህ ሁሉ ቢሆንም  ግን እግዚአብሔር ይመስገን ኢየሱስ ሊስቀል በርባን እንደተፈታው እኛም ከሚጠብቀን የዘላለም ሞት ቅጣት ነፃ መውጣት ችለናል። #hesedmultimedia                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።” ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ምድር ሳለ ከመጨረሻዎቹ ትምህርት መካከል የሚገኝ ለተከታዮቹ የሰጠው ማሳሰቢያ  እንደሆነ ግልፅ ነው።  ታዲያ ለመለወጥም ሆነ ለንስሃ የማይመቸውን ይህን ቅፅበታዊ ጊዜ ''ቶሎ" ተብሎ በእግዚአብሄር ቃል በተለያየ ቦታ  ተፅፎ እናገኘዋለን ። "ቶሎ" መች ነዉ? ቶሎ በጣም ቅርብ ነው ፣ ቶሎ የማይታወቅ ድንገተኛ ጊዜ ነው ደግሞም በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ አመት ሺህ አመትም እንደ አንድ ቀን ነው። ስለዚህ በጣም በቅርቡ ለእያንዳንዳችን ዋጋችንን ይከፍለናል፤ ይህ ዋጋ ከዳንን በኋላ በምንሰራዉ ስራ እንደሚገባን የምንረከበው የእግዚአብሔር የፅድቅ ፍርድ ነው። ኢየሱስም ለዮሐንስ በስተመጨረሻ ስለሚሆነው  እንዲሁ ተናግሯል፤ ዛሬም ደግሞ ባለንበት ዘመን ደስ ያለንንና የወደድነው ማንኛውም ነገር  እንድናደርግ ሰዎች ፣ አስተሳሰቦቻችንና ፍልስፍናኦቻችን ይገፋፉናል አለምም ይህን ታስተምረናለች፤  ደግሞም ኢየሱስ እንደተናገረው አመፃን የሚፈልግ ወደፊት ማመፅን እንደሚቀጥል መርከስንም የሚፈልግ እንዲሁ ወደፊትም በእርኩሰቱ እንደሚቀጥል እንዲሁ ነው ወይስ እርሱ በምድር እንደተመላለሰው በጽድቅና በቅድስና እስከ መጨረሻው መቀጠል፤ ታዲያ እኛስ የቱን መቀጠል እንመርጣለን? ጌታ እንደሆነ መምጣቱ አይቀር... ለእኛ ግን እዉነት የሆነውን፣ ፅድቅ የሆነውን ፣ ንፁህ የሆነውን ፣ ፍቅር ያለበትንና መልካም የሆነውን ማሰብ እና ማድረግ እንዳለብን ቃሉ ያስታምረናል፤ ፀጋው ይርዳን። #hesedmultimedia                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • Hello everyone!We are excited to share this amazing book written in Amharic for the first time focusing on the issue of pornography. For anyone interested in getting a hard copy we still have a few copies remaining and you can buy one. @naold2

  • እዚህ የራዕይ ክፍል ላይ የሚገኙት ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል ህዝብ ስናስብ ያለፉትን መከራ ምን ያህል እንደሆነ ማሠብና መረዳት ልንቸገር እንችላለን ምናልባትም ደግሞ ማንኛውም ሠው በህይወቱ ሊገጥመው የሚችለው አይነት መከራ ያለፉ ሠዎች ሊመስሉንም ይችላል ፤ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ማንኛውም ሰው በምድር ላይ የደረሰበትና የሚደረስበት አይነት መከራ ያጋጠማቸው ሠዎች አይደሉም በታላቁ መከራ ያለፉ ሰዎች ናቸው፤ ታላቁ መከራ አለም ወደ ፍጻሜዋ ስደርስ እርሷን ለካዱና አዳኛቸውን ክርስቶስን ላሉ የምትሠጠው ታላቅ የመከራና የስቃይ ጊዜ ነው። ታዲያ እነዚህ ሠዎች እንደኛው በተለያዩ የህይወት ፈተናዎች ያለፉ ከዚህም በተጨማሪ እንደዚህ አይነት ጊዜንም ያለፉ ሰዎች ጭምር ናቸው፤ ምናልባት እኛ እነሱን ስናስብ ያላቸውን የእምነት ፅናት እንመለከታለን፤ ከዚህ ግን በበለጠ በህይወታችን ብዙ ጊዜ የተለያዩ ችግሮች ሲገጥመን እዚህ ክፍል ላይ እነዚህ ሰዎች የተገባላቸውን የተስፋ ኪዳን እያየን መፅናናት እንችላለን። አሁን ባለንበት ዘመን ሰዉ በተለያዩ ፈተናዎች ዉስጥ ቢሆን  እግዚአብሔር እጅግ የራቀዉ ቢመስለው መጠለያ አጥቶ ከቤት ቢወጣ በዚያን ጊዜ ጌታ በርሱ ለሆኑት በዙፋኑ አብረዉት እንደሚሆኑ ልክ የብሉይ ኪዳኗ መቅደስ ጌታ በሃልዎቱ እንደሚከልላት መጠለያም እንደሚሆንላቸው እርሱን እያዩ ፊቱ ቆመዉ እንደሚያመልኩት ተስፋን ሠጥቷል፤ መራብ መጠማት የሚባል ነገር በዚያ እንደሌለና ፤ አሁን ላይ ሠው በተለያዩ የህይወት ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ መሄጃን አጥቶ በፀሃይና ሃሩር መሃል ቢንከራተት እንደዚያ አይነት ነገር በዚያ አይኖርም፤ ምክንያቱም መልካም እረኛችን ኢየሱስ ወደ ህይወት ውሃ ምንጭ ይመራናልና አሁን ላይ ያነባነውን እንባ እግዚአብሔር የዛኔ ያብሰዋል ምክንያቱም ተስፋችን እግዚአብሔር ጋር ብቻ ነውና። ስለዚህ ሁልጊዜ ተስፋን በሚያስቆርጡ ፈተናዎች ስናልፍ ጌታ በዚህ ክፍል ላይ የገባውን የተስፋ ቃል ማሰብና መናፈቅ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ዉስጥ በእርሱ ሀይል ፀንተን እንድናልፍ ይረዳናል።  #hesedmultimedia                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • без подписи

  • እግዚአብሔር እኛን ብቻ ሳይሆን ከእኛ ግንኙነት ይፈልጋል። እርሱንና ለእርሱ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እንድንሻ ይፈልጋል። በጎ የሆነውን ስናደርግና ዘላለማዊ ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ስንፈልግ ለእኛ ያቀደልንን ለመስጠት እጅግ ደስ ይለዋል። ይኸውም ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወት ይሰጠናል፤ ሌሎች ሰዎች ላይም መልካም ተጽእኖ እንዲኖረን ያደርጋል። በሌላ አነጋገር ፈላጊው እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ይፈልጋል ማለት ነው! #hesedmultimedia                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 13 мая2 252114

    በዚህ ዓለም ውስጥ የመጨረሻ የስድብ ቃል ሞት ነው፡፡ ስለ ሞት ማሰብ አንፈልግም፡፡ ነገር ግን ሞት ሊተወን የማይችል እውነታ ነው፡፡ ጓደኞቻችንን እና ቤተ ሰቦቻችንን በሞት እናጣለን። ኢየሱስ ከማለፋችን በፊት ካልመጣ በቀር እኛም አይቀሬውን ሞት እንጋፈጣለን፡፡ ታዲያ ይህን የማናመልጠውን ስንጋፈጥ መተማመኛችን ምንድን ነው? እረኛችን ነው! በመንገዳችን ሁሉ አብሮን ይሄዳል፣ ይመራናል፣ ይጠብቀናል፣ ያጽናናናል። እንደ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህ ተስፋ ታላቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ መልካሙ እረኛችን በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብናልፍ እንኳ መጨረሻችን ሞት ሳይሆን ክብር እንደ ሆነ አረጋግጦልናል። #hesedmultimedia                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • እምነት የሚለው ቃል በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ከቃለ እግዚአብሔር በብዙ የሕይወት መስተጋብሮች ውስጥ እንደ መመሪያ ሊጠቀመው የሚገባ ነው።(2ተኛ ቆሮ 5፥7) ይህም የሆነበት ምክንያት “የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር የእግዚአብሔር መንፈስ ነው” ይላል። እና ይህን መንፈስ የሆነውን አምላክ እንዴት አውቀነው? ካወቀነው ደግሞ እንዴት እናመልከዋለን? የእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ በዕብራውያን 11፡6 “ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም” ይላል። በዚህ ምዕራፍ ብዙ የእምነት አባቶች እንዴት ደህንነትን እንደ ተቀበሉ እና ጌታን እንዴት እንዳስደሰቱ ይናገራል። ከዚህም በመነሳት እምነት ለደህንነታችንና በእግዚአብሔር ፊት ለመኖር እጅግ አስፈላጊ ነው። አምልኮን እግዚአብሔር የምንቀበለው በእምነት ስናቀርብ ነው። የቃሉ ትርጉም እርግጠኝነት (assurance) የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። በእግዚአብሔር ባህርይና በራሱ ላይ ምን ያህል እርግጠኛ ነን? በተገለጠው በክርስቶስ የማዳን ስራ ምን ያህል እርግጠኞች ነን? ይህ እርግጠኝነት ለክርስቲያን ታላቅ ተስፋ ይሰጣል! እንደገናም በጸሎት እንኳን ያለ እምነት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ሰው ምንም አይቀበልም። እምነት ያድጋል፤ ከሰው ሰው ይለያያል ይለያል፤ ይህም እግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ለመስጠት የሰጠን አቅም ወይም ችሎታ ነው ማለት እንችላለን። ደግሞም ከጽናት የተያያዘ ነው፤ እንደ አባቶች እግዚአብሔርን ፈጽመው በፈተና እንዲከተሉና እንዲጓዙ ያስቻላቸው በእምነታቸው መጽናታቸው ነው። “ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድርእምነትን ያገኝ ይሆን?”...እምነታችን ሊያናውጥ የሚፈልግ ብዙ ቢኖርም በጽናት ለማለፍ ጸጋው ይብዛልን። ተባረኩ! #hesedmultimedia                         @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 6 мая2 64322

    ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፣ በኢየሱስ ሆነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደዚሁ ያመጣቸዋል። 1 ተሰሎንቄ 4:14 መስቀሉ ምንም ያህል አስፈሪ ቢሆንም፣ የኢየሱስ የመጨረሻ ታሪክ ግን አልነበረም። ኢየሱስ ሞተ ከዚያም ከሞት ተነሣ። ኢየሱስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ሁለት ነገሮችን ማመን እንችላለን። በርሱ ለሚያምኑት ዳግም በድል ይመለሳል፤ ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ደግሞ የምንወድዳቸው በኢየሱስ ሆነው ያንቀላፉትን ትንሣኤ ይሰጣቸዋል፤ ዳግምም እንገናኛለን። በክርስቶስ ያላችሁ ውድ ወዳጆቼ ወደፊት ምንም ነገር ቢያጋጥመን ወይም አሁን ምንም ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን፣ እነዚህ ሁለት እውነቶች ርግጥ የሆነ ተስፋን ይሰጡናል። #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፤ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል። ምሳ 17÷17 "ወዳጅ" ለሚለው ቃል ሁላችንም ጋር የተለያየ ትርጉም ሊኖረው እንደሚችል አስባለሁ። "ወዳጅ" ማለት በአማርኛ መዝገበ ቃላት ትርጉም መሰረት ፍቅር፣ መተማመን እና መቀራረብ ያለው፣ የቅርብ ጓደኛ፣ አጋዥ፣ ወይም ተወዳጅ ሰው ማለት ነው። እንደዚህ ነው ወዳጅ እንግዲ። እና ይህን ሁሉ የሟላ የኛ ኢየሱስ በዘመን (በክፉ ቀን) ሁሉ የሚወድ እንደዚህ አይነት ወዳጅ አይደገምም። እና ሌላ ወዳጅ ፍለጋ ባንጥር ትርፉ ጉዳት ስለሚሆን።  ከእንግዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ አገልጋይ ጌታው የሚሠራውን አያውቅምና፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጽሁላችሁ ወዳጆች ብያችኋለሁ። ዮሐ15÷15 #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 29 апр.2 22544

    መዝሙር 91 በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር ታማኝነት የሚሰጠውን ጥበቃ እና መከላከያ ይገልፃል። በ 14-15 አንቀጾች ውስጥ ያለው መልዕክት ይህን በግልፅ ያረጋግጣል፤ እግዚአብሔር ለእርሱ የሚያምኑትን ሰዎች ያዳናቸዋል፣ ይሰማቸዋል፣ ከእነርሱ ጋር ይሆናል እና ያከብራቸዋል። እግዚአብሔር እራሱ ይናገራል፡ ይህ ጥቅስ ከመዝሙር 91 መጨረሻ ላይ የሚገኝ ነው። በዚህ ምዕራፍ አብዛኛው ጊዜ የሚናገረው የመዝሙር ደራሲ (በእግዚአብሔር ላይ ተማምኖ የሚኖር ሰው) ሲሆን፣ በመጨረሻ ግን እግዚአብሔር ራሱ ድምፁን ሰምቶ የሚንገረውን ተስፋ ያረጋግጣል። በሌላ አነጋገር "እኔ እሰራለሁ" በማለት ቃል ይገባል። መጽሐፈ ምሳሌ 22:4 (NASV) •••••••••• ⁴ ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሀብትን፣ ክብርንና ሕይወትን ያስገኛል። መጽሐፈ ምሳሌ ግን እንደሚያስተምረን እውነተኛ እና ዘላቂ ብልጫ (ሀብት፣ ክብር፣ ሕይወት) የሚገኘው እግዚአብሔር በእርሱ ፊት ትሕትናን በመቅረብ እና እርሱን አክብሮትን በመስጠት እንደ መንገድ ነው። ይህ በሃይማኖታዊ እምነት ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ስነምግባር እና አስተዳደር ላይም ጠቃሚ መርህ ነው። ትሕትናና ትሁትነት ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ ክብርን እና ተጽዕኖን የሚያስገኙባቸው ምስጢራዊ መንገዶች ናቸው። #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 27 апр.1 960224

    በዚህ አጽናፈ ዓለም ( Universe ) ላይ ወደ 2 ትሪሊየን የሚደርሱ ጋላክሲዎች ፤ ወደ 200 ቢሊየን ትሪሊየን ወይም ወደ 200 ሲክስቲሊየን ክዋክብቶች እንዳሉ ይገመታል ( እርግጠኛ ቁጥራቸዉ እስከዛሬ አልተደረሰበትም ) የእኛ አምላክ ግን ብዛታቸውን ይቆጥራል በስምም ይጠራቸዋል! በአእምሮአችን ከምንረዳው በላይ ትልቅ ሆኖ፣ ያልናቀን፣ የቀረበን፣ እና ስለእኛ እራሱን አሳልፎ ለሰጠን ጌታ በታላቅ አክብሮት እና በፍቅር መገዛት እና መኖር እንዲሁም በእርሱ መታመን ይሁንልን! #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 22 апр.1 96744

    መዝሙር 10:14 14 አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቍጣን ትመለከታለህና፥ በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፤ ድሀ ራሱን ለአንተ ይተዋል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ። አቅመ ደካሞችን፣ በችግር ውስጥ እያለፉ ያሉትንና በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ለራሳቸው ጥቅም የሚጠቀሙ ሰዎችን እግዚአብሔር ይቃወማል። ደካሞችን፣ ችግረኞችን እና የተጎዱትን የሚበዘብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ሥራቸውን እንደሚያይና ተጠያቂም እንደሚያደርጋቸው ማወቅ አለባቸው፡፡ በችግር ውስጥ ያሉ ደግሞ እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ጥለው እርሱ እንደሚያያቸው፣ እንደሚጠነቀቅላቸውና በትክክለኛው ሰዓት ርዳታን እንደሚልክላቸው ማመን አለባቸው፡፡ ከሁለቱም ወገን ያልሆነው ደግሞ በፈተና ውስጥ ላሉ ነፃ የሚወጡበት እና የሚባረኩበት ምክንያት ለመሆን መሥራት አለብን። ይህ የእግዚአብሔር ልብ ነው(መዝሙር 68፥5፣ ኢሳይያስ 10፥1-3)። #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 20 апр.2 10987

    ወጣት ስንሆን ብዙ የምናደርጋቸው ነገሮች አሉን። ብዙ አዝናኝ ነገሮች አስፈላጊ ነገሮችን ከማድረግ ሐሳባችንን ሊሰርቁት ይችላሉ። ስለዚህ ፍላጎቶቻችንን እና ኀላፊነቶቻችንን በጸጋ እንድንመራ እግዚአብሔር እንዲረዳን ልንጠይቀው ያስፈልጋል። እግዚአብሔር መልካም ለሚለው ነገር የወጣትነት ግለታችንን ልንጠቀምበት ይገባል። ማርጀት በአንድም ይሁን በሌላ ውስንነትን ያመጣል። ይህ ደግሞ አስደሳች አይደለም! ይህ እውነታ ሕይወት መጥፎ እንደ ሆነች አያሳይም። ይልቁንም ከማርጀታችን በፊት ቅድሚያ መስጠት ላሉብን ነገሮች ቅድሚያ ልንሰጥ እንደሚገባ ያሳያል። በወጣትነታችን መማር ያለብንን የእምነት ትምህርቶችን ወስደን ቀሪውን ዘመናችንን በብስለትና በጥበብ፣ ታናናሾቻችንንም በመርዳት እንኖራለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በዚህ መንገድ ስንኖር ከእኛ በኋላ ለሚመጡት መልካም ምሳሌ መሆን እንችላለን። #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 15 апр.1 871104

    በዚህ ዘመን የብዙ ሰዎችን ልብ የሚያርድ ነገር ቢኖር ከአንደበታችን ያለቁጥጥር የሚወጡ ያልተገቡ ቃላት ናቸው። እስቲ ትንሽ ጊዜ እናስብ ስንቶቻችን በአንደበታችን አንኳን የሰውን ልብ ያወረድን? የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይለናል ንሰሀ እንግባ እንመለስ። ማመዛዘን የጐደለው ሰው ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤ አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል።”   — ምሳሌ 11፥12 (አዲሱ መ.ት) #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 13 апр.1 90356

    ማቴ16:23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን:- ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። አንዳንድ ጊዜ በጣም የምንወዳቸው ሰዎች(ልክ ጼጥሮስ ኢየሱስን እንደሚወደው ማለት ነው..) የእ/ርን ፍቃድ እንዳናደርግ ሊያዘናጉን ይሞክራሉ(ምናልባትም ችግር እንዳይደርስብን ካላቸው ፍላጎት የተነሳ በመሆኑ ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ።) ከዚህ ይልቅ ግን የእ/ርን ፍቃድ ማድረግ  አለብን።ጼጥሮስ የሰውን እንጂ የእ/ርን አላሰበም። ኢሳ55:8-9 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው። #hesed multimedia                                                                                                          @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • 12 июн. 2025 г.1 1201из EvaSUE58

    ስልካችሁ ላይ ስንት ሰዓት ታሳልፋላችሁ! Share us Your Screen Time!

  • 24 мая 2025 г.1 13041из JUECS_Fellowship

    “እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።”   — ማቴዎስ 11፥28 (አዲሱ መ.ት) " 🗣️🗣️🗣️ደረሰ ደረሰ ደረሰ! በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው የfresh እና remedial Carnival  2017 በንጉሱ ማረፍ በሚል ርዕሰ ነገ ቅዳሜ  የሚካሄድ ይሆናል:: በዚህ carnival 👉የአንድነት 👉በህብረት እግዚአብሔር የምናመልክብት  👉ከቃሉ የምንማርበት 👉ማዕድ የምንካፈልበት 👉የተለያዩ ጨዋታዎች የምንጫወትበት 👉ፎቶ የምንነሳብት ይሆናል:: ማሳሰቢያ 🌟ሁሉም የfresh እና remedial ተማሪዎች ከ mom እና dads ጋር እንድትገኙ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን። 🌟በፕሮግራሙ ላይ በሚኖሩ activities አለመሳተፍ ፈፅሞ አይታሰብም😊 🌟ማርፈድም ሆነ መቅረት አይታሰብም 🌟የምንችል ጥላ እንያዝ     ቅዳሜ ከ3:00 ጀምሮ 💒MKC ፊት ለፊት ባለው ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ @juecsfcounseling @JUECS_Fellowship

  • без подписи