Lideta Manufacturing College
СтатистикаThis channel belongs to Lideta Manufacturing College
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 34
- Всего постов
- 47
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 295
- 1/48двое суток
- 338
- 1/72трое суток
- 364
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የሰልጣኞች ቅበላ አቅሙን ለማሳደግ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው መሰረት በኮሌጁ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር እና የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት መርሃ-ግብር አከናወነ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ባዘጋጀው በዚህ መድረክ፤ የበርካታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን፣ የዩኒት ሊደሮች እና የሙያ አሰልጣኞች ታድመዋል። የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን አቶ እንድሪስ መሐመድ በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የስምምነቱ ዋና ዓላማ የተማሪዎችን ተግባራዊ ክህሎት ለማልማት እና የ2019 የትምህርት ዘመን የአዲስ ሰልጣኞች ቅበላን በጋራ ስራ ለማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ እንድሪስ አክለውም፣ ተማሪዎች ከወዲሁ የሙያ ስልጠናዎችን ተረድተው ኮሌጁን የመጀመሪያ ምርጫቸው እንዲያደርጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዕለቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚኖረውን የረጅም እና የአጭር ጊዜ የስራ ድርሻ የሚወስን "የቅንጅታዊ ትስስር ሰነድ" የተፈረመ ሲሆን፤ ይህም ተማሪዎች ወደ ኮሌጁ በመምጣት የስልጠና ክፍሎችን እንዲጎበኙና የሙያ አቅጣጫቸውን እንዲይዙ ያስችላል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተኩ ታዬ በበኩላቸው፤ እስከ አሁን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ጋር በተከናወኑ ቅንጅታዊ ስራዎች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን አድንቀዋል። ዋና ዲኑ አክለውም፣ የተጀመረው ትስስር በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለ2019 የትምህርት ዘመን የታቀዱትን ግቦች ለማሳካት ኮሌጁ በትኩረት እና በጋራ እንደሚሰራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በስነ-ስርዓቱ ማጠቃለያ፤ በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው መሰረት ከኮሌጁ ጋር ተቀናጅተው በመስራት፣ የተማሪዎችን ተግባራዊ ክህሎት ለማልማት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በኮሌጁ ስም የምስጋና እና እውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል። የስምምነቱ ታዳሚዎች በኮሌጁ የሚገኙ የስልጠና ክፍሎችንና የቴክኖሎጂ ወርክሾፖችን በመጎብኘት መርሃ-ግብሩን አጠናቀዋል።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи