ማኅበረ ሰላም ሰንበት ት/ቤት
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 76
- 1/48двое суток
- 87
- 1/72трое суток
- 93
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ነሃሴ_7 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ቁጽረታ (ጽንሰታ)ለማርያም ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል። ስለ ምን ነው_ቢሉ :- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ። "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" - "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።" (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4) ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል። የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር። ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም። የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች። ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ። እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች። "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" - "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም) ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @mahbereselamm 💚 💛 @mahbereselamm 💛 ❤️ @mahbereselamm❤️
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ምስባክ ዘነሐሴ ፯ ዘቅዳሴ ፍልሰታ(ፅንሰታ ለእግዝእትነ ድንግል ማርያም) 👉 @mahbereselamm 👈
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ግጻዌ ዘነሐሴ ፯ ፍልሰታ(ፅንሰታ ለእግዝእትነ ድንግል ማርያም) 👉 @mahbereselamm 👈
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ምስባክ ዘነሐሴ ፮ ዘቅዳሴ ፍልሰታ 👉 @mahbereselamm 👈
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ግጻዌ ዘነሐሴ ፮ ፍልሰታ 👉 @mahbereselamm 👈
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ምስባክ ዘነሐሴ ፭ ዘቅዳሴ ፍልሰታ 👉 @mahbereselamm 👈
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ግጻዌ ዘነሐሴ ፭ ፍልሰታ 👉 @mahbereselamm 👈
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የመጽሐፍት ልገሳ ጥሪና ምስጋና! በዛሬው ዕለት በሰንበት ትምህርት ቤታችን ለሚገኘው ቤተ-መጽሐፍት ውድ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን የመጽሐፍት ልገሳ አድርገውልናል። ስለ መልካም ስጦታችሁና ደግነታችሁ በሰንበት ትምህርት ቤታችን ስም ከልብ እናመሰግናለን! ሌሎችም የዚህ በጎ አድራጎት ተካፋይ መሆን የምትፈልጉ አባላቶቻችን፣ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤታችንጽሕፈት ቤት በአካል በመምጣት የመጽሐፍት ስጦታችሁን ማበርከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ለበለጠ መረጃ፦ 📞 ስልክ፦ +251920326656 📍 ቦታ፦ የሰ/ት/ቤቱ የጽሕፈት ቤት
ነሐሴ 3/12/2018 ዓ.ም መዝሙር "ዮም ንወድሳ" #ምስባክ ፦ መዝ 86፥5-7 እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ወውእቱ ልዑል ሣረራ #ትርጉም ፦ ሰው ጽዮንን እናታችን ይላታል በውስጧም ሰው ተወልደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት 💚 @mahbereselamm 💚 💛 @mahbereselamm 💛 ❤️ @mahbereselamm ❤️
የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ሊቃውንቱ ያብራራሉ፡፡ የበረከት ጾም ያድርግልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🔅🔅🔅🔅🌿🌿🔅🔅🔅🔅 ምስባክ ዘነሐሴ ፪ ዘቅዳሴ ፍልሰታ 👉 @mahbereselamm 👈