tgindex
መንፈሳዊ ሕይወት

መንፈሳዊ ሕይወት

Статистика

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝ እንኳን ወደ "መንፈሳዊ ሕይወት" ቻናል በደህና መጡ! በዚህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን የጠበቁ ትምህርቶችን፣ መዝሙሮችንና መንፈሳዊ ምክሮችን ያገኛሉ። አምላከ ቅዱሳን ከሁላችን ጋር ይሁን🤲🤲❤

Последний пост
9 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 568
−7 за 6 дн.
Сутки
−2
−0,13%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
251
21 постов
Вовлечённость
16,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
88
1/48двое суток
100
1/72трое суток
108

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሰንበተ ክርስቲያን

  • ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 3

  • የእሁድ(የእለተ ሰንበት) ቅዳሴ ማርያም የተሰወረውን የምትገለጥፅ የተገለፀውን ሁሉ የምትሰውር ሆይ በውስጥ ያለውን የምታወጣ በውጭ ያለውን የምታስገባ ሆይ አሁንም በእውነት የሚጠሩህን የወገኖችህን ጩኸታቸውን ስማ። ድንግል ሆይ ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ፤ ጥፋትን አደለም ይቅርታን አሳስቢ መአትን አደለም ምህረትን አሳስቢ ፤ለጻድቃን አደለም ለኃጥአን አሳስቢ ለንጹሀን አይደለ ለተዳደፉት አሳስቢተ። ልመናዋ ክብራ የተወደደው የልጇ ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን በዕውነት አሜን።

  • 🕊 † እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !  † †  🕊 ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም  🕊 † † ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ አይቻልም:: ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ [ 7 ] አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው:: "ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን "ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ ፷፬ [64] ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም:: ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ፯ [7] ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት:: ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል:: - የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ:: - ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ:: - የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል:: † በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን:: † ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: - ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን:: †  🕊 ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ  🕊 † † እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው:: †  🕊  ቅዱስ ዮሴፍ ዘአርማትያስ  🕊 † † ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ [በመሲህነቱ] አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር:: †  🕊   ቅዱስ ኒቆዲሞስ   🕊  † † ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምሕር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል:: ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት:: እንዲህ እያሉ :- "ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!" - በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: "እየሳማችሁ አክብራችሁ እንደ ገነዛችሁኝ እኔም በሰማይ በእንቁ ዙፋን ላይ አስቀምጣቹሃለሁ" ብሏቸዋል:: "አነ አብረክሙ ዲበ መንበረ ሶፎር" እንዲል:: ጻድቃን አበው ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በተረፈ ዘመናቸው ወንጌልን ሰብከው: ከአይሁድ መከራን ታግሰው: በበጐ ሽምግልና ዐርፈዋል:: †  🕊  ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት  🕊  † † ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ ቅዱስ ዮስጦስና  ቅድስት ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው:: ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: ፫ [3]ቱም ከዙፋናቸው ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ:: በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ [ብስጣ] ይዘው አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም:: በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ አዙረውታል:: እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ  ቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ ፲፮ [16] ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል:: በተአምራቱና በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም ለሰማዕትነት አብቅቷል:: እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል:: † ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን:: ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን:: [   † ነሐሴ ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. በአተ ጾመ ፍልሠታ ፪. አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ፫. ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት ፬. ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ ፭. ቅድስት ሐና [የእመ ብርሃን እናት] ፮. ቅድስት ሐና ነቢይት [ወለተ ፋኑኤል] ፯. ደናግል ቅዱሳት [የንግስት ሶፍያ ልጆች] [   †  ወርኀዊ በዓላት    ] ፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት ፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ ፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር † " የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" † [ዮሐ.፲፱፥፴፰] (19:38) † " በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" † [ኢዩ.፪፥፲፭] (2:15) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

  • መንፈሳዊ ሕይወት pinned «በድጋሜ የተለጠፈ +++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++ ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው…»

  • በድጋሜ የተለጠፈ +++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++ ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ።  በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!" በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው? ዲያቆን አቤል ካሳሁን @menefesawihiwot.

  • "ጌታ ሆይ እርሻውን አቃጥለህ ሰብሉን ብትባርክ ምን ይጠቅማል? ዛፉንስ ቆርጠህ ቅርንጫፉን ብትባርክ ምን ይረባል? እናቴ እርሻ ናት እኔ ሰብል ነኝ:: እናቴ ዛፍ ናት እኔ ቅርንጫፍ ነኝ:: እባክህን እናቴ ብትክድ እኔ ባምን ምን ይጠቅማል:: ጌታ ሆይ የእናቴን ልብ በሃይማኖት አጽናልኝ" (ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ስለ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ የጸለየው ጸሎት) ቅዱስ ቂርቆስ ሆይ  አንተ ሕፃን ሆነህ ትልቅ ነበርክ:: ትልቅ ሆነን ሕፃን የሆንን እኛን በምልጃህ አስበን! "የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል" መዝ 19፥7 (#ከዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ_የተወሰደ)

  • ቅድስት ኢየሉጣን አላዊው ንጉሥ እስክንድሮስ "ስምሽ ማን ይባላል?" ባላት ጊዜ "#ክርስቲያን እባላለሁ፤ መዋቲ ስሜን ከፈለግህ ግን ኢየሉጣ ይባላል" አለችው። ልጇም ቅዱስ ቂርቆስም ተመሳሳይ ጥያቄ በተጠየቀ ጊዜ "ከማይደፈርስ ከንጹህ ምንጭ የተቀዳ ጥሩ ምንጭ ስሜ #ክርስቲያን ይባላል፤ መዋቲ ስሜን ከፈለግክ ግን ቂርቆስ ይባላል" አለ። እኛም ሕያው ስማችንን በገቢር መስክረን ርስተ መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ አምላከ ኢየሉጣ ወቂርቆስ ይርዳን!!

  • #ኪዳነ_ምህረት_እናቴ🥰 #አንቺ_ባትኖሪልኝ የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ የኃጢያት ሐረግ ሲንጠላጠልብኝ ሙቼ መራመዴ ለኔ ሲታወቀኝ ምን ይውጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ አልቅሼ ስነግርሽ አለሁሽ ባትዪኝ የመዳንን መድህን ልዑል ባትወልጂልኝ በምልጃ ፀሎትሽ ቤቴ ባይሞላልኝ በይቅር ባይነትሽ ኑሮ ባይቀናልኝ ማን ያስበኝ ነበር አንቺ ባታስቢኝ ኃጥያት ተፀይፈሽ ፊት ያላዞርሽብኝ ብርሃንን ወልደሽ ፀኃይ የሆንሽልኝ ለውለታሽ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ🥰 🥀የእናታችን ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ እናትነቷ ፍቅሯ ጣዕሟ ፆሎት ልመኗ ምልጇዋ ጥበቃዋን አይለየን 🙏🏼

  • ✞እንኳን አደረሰን! " ... ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዕደ እግርክሙ ጌሠ፤ ጽንዐ ኃይልክሙ ሰቀለ ንጉሠ፤ ወዕበይክሙ አስገደ አፍራሠ!" (አርኬ) ❖የቅዱሳን #ሐዋርያት ጌታ ቸሩ መድኀኔዓለም፦ ሰላሙን ፍቅሩን፤ ስምምነት አንድነቱን፤ በረከት ረድኤቱን፤ ዝናመ ምሕረቱን፤ ጠረ በረከቱን . . . አይንሳን! ከአርዕስተ ሐዋርያት ክቡራን #ጴጥሮስ #ወጳውሎስ ጸጋ ክብር ያሳትፈን!❤️

  • ነገ ቀኑኑ.......😊✨ 21 ነው። ዕለተ ሰንበትም ጭምር🥰 ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በ ሰኔ 21 ቀን ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንባዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን የለመነችበት ዕለት ነው :: ጌታችንም ልመናዋን ተቀብሎ ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ስለዚህ ነገ በዕለተ ቀኗ ሁላችንም እመቤታችን የፀለየችውን የሰኔ ጎልጎታን ፀሎት እንፀልይ 🙏🏻❤️ የነገ ሰዎች ትበለን🙏🏻🙏🏻🙏🏻

  • https://t.me/One0921607727

  • 27 июн.2431из Eletate

    እዩት ከወደዱት channelun ለሌሎችም ያጋሩ፤ አስተያየትም ካለ በዚኽ ስልክ ቁጥር ማውራት ትችላላችኹ፤ 0921607727

  • " በእኛ የነበረውን ጨለማ በአባትህ ፈቃድ አራክህልን  ፤ ከጨለማ ወደ ብርሀን አወጣኸን ፤ ከሞት አድነህ ህይወትን ሰጠኸን ፤ ከመገዛት ነጻ አወጣኸን ፤  በመስቀልህ በሰማይ ወዳለው ወደ አባትህ አቀረብከን  ፤ አቤቱ በወንጌል መራኸን በነብያት አፅናናኸን ..." [ፀሎተ ኪዳን]

  • 31 мая36213из Eletate

    ጾመ ሐዋርያት ሐዋርያት ያስተማሩን ጾም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ዕውቀትን እምነትን ቋንቋን ካጸናላቸው በኋላ፤ አባላቸውም ከበዛላቸው በኋላ ተሰበሰቡ፤ ሳንደክም ይኽን ቋንቋ እና ጸጋ ለሰጠን እግዚአብሔር ስጦታው ምንድነው አሉ፤ ሳንበላ የሚያጠግበን፤ ጠላትን የምንገዛበት፤ አጋንንትን የምናስወግድበት፤ መናፍቃንን ድል የምናደርግበት፤ ሙት የምናነሳበትን፤ ይኽን ኹሉ ሀብት ለሰጠን፤ ለአምላካችን ምንድን ነው ዋጋው ብለው ተጠያየቁ፤ በዚኽም ዋጋው ጾም እና ጸሎት ስግደት ነው ብለው ተስማሙ፤ ስለዚኽ እሁድ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ሰኞ ጾም ጀመሩ። ብጹዓን ጳጳሳትም ክህነት ድቁና ሲሰጡ ከዚኽ በመነሳት ሐዋርያት ዐርባ ቀን ጹመው ነው አገልግሎታቸውን የጀመሩት ፈጣሪን ያገለገሉት ብለው ዐርባ ቀን ጾም ይሰጣሉ፤ የሚቆርቡ ምእመናንም መቁረብ ሲጀምሩ ደገኛ ካህናት ጾም ይሰጧቸዋል፤ እንደዚኽ ያለው ጾም የበረከት የፍቅር ጾም ይባላል። ስለዚኽም እኛም ጾምን ጸሎት እና ስግደትን ገንዘብ እናድርግ፤  የታዘዘልን ጸሎት አለ፤ የታዘዘልን ስግደት አለ(ሰንበታት ፲፪ ፳፩ እና ፳፱ ን ሳይጨምር)፤ የታዘዘልን ጾም አለ (ከማታ ፫-፱ ሰዓት) ከዚኽም በተረፈ ምግባር ትሩፋት ለመተግበር ያብቃን። ሰኞ እና ማክሰኞ ግን የእመቤታችን በዓል እንዳለ ነውና ስግደት አይደረግበትም።

  • "አርእይኒ ገጸ ዚአኪ ማርያም ምእረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ" "ማርያም ሆይ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ" [መልክአ ማርያም]❤️

  • ☦️ ዳግማይ ትንሳኤ ☦️ ዳግማይ ትንሣኤ (ሁለተኛው ትንሳኤ) ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሑድ ደቀመዛሙርቱ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦ ትንሳኤው ምትሐት ያይደለ ፍጹም አማናዊ እንደሆነና እንደ ቶማስ የተጠራጠረውን ና ንካኝ በማለት ያሳመነበት ዕለት ነው፡፡ዳግማይ (ሁለተኛ) ያሰኘው መገለጡን ይዞ ነው፡፡ ✥  ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ትንሳኤ ባለፈ የሚመጣውን እሑድ ሰይማ ታከብረዋለች፡፡ /ዮሐ20፤24-30/ ✥ ጌታችን ስለምን ዳግመኛ ተገለ ጠ ✥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ቀድሞ በተዘጋ ግንብ ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ ተገልጦላቸው ነበር ዳግመኛም ሐዋርያው ቶማስ ባለበት ተገለጠላቸው ምክንያቱም ደግሞ ✥ 1ኛ.ካልዳሰስኩ አላምንም ያለ ሐዋርያው ቶማስን ሊያሳምነው ፡- ቶማስን ደቀመዛሙርቱ መጥተው ጌታችንን በመካከላችን ተገልጦ አየነው ብለው ሲነግሩት ‹‹የችንካሩን ምልክት በእጄ ካላየሁ ጣቱንም ወደ ተቸነከረበት ካልጨመርሁ እጄንም ወደ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም ››  ብሎ ነበርና ና ንካኝ ብሎ አሳምኖታል፡፡ ሌላው ቶማስን ‹‹ ና ጎኔን ንካ›› ሲለው በኋላ በዓለም ዞሮ ወንጌልን የሚሰብክ ነውና ሐዋርያ ከሆነ ዘንድ ደግሞ ‹‹ሐዋርያት እንዳሉት ጌታችን ተነስቷል›› ብሎ ያስተምር ዘንድ አይገባውም ይልቁንም እንደ ወንጌላዊው ዮሐንስ ‹‹በጆሮአችን የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውንን የተመለከትነውን እጆቻችን የዳሰሱትን እንነግራችኋለን ሕይወት ለእኛ ተገልጻለችና አየናት›› 1ኛዮሐ1፤1-2 እንዳለው ቶማስን ና ንካኝ ብሎታል ፡፡ ✥ 2ኛ.ሰንበትን ሲያጸናልን ፡- የክርስቲያኖች ሰንበት የምንላት ዕለተ እሑድ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳባት በመሆኗ የእረፍት የመንግስተ ሰማይ አምሳል ብለን እናከብራታለን፡፡ የዕለቲቱንም ክብርትነት እንድናስብና ዕለተ እሑድ በመጣች ቁጥር ጌታችን የተነሳባትና ለሐዋርያቱ ትንሳኤውን ደግሞ የገለጠባት እንደሆነ እንድናስብ ለአክብሮተ ሰንበት ደግሞ ተገለጠላቸው፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸ ዋለች። ✥  3ኛ.ትንሳኤው ምትሐት እንዳልሆነ ለማ ስረዳት፡- ጌታችን ራሱ የተገለጠበትን ዓላማ ሲነግራቸው ‹‹እጄን እግሬን እዩ ዳስሱኝም እኔ እንደሆንኩ ዕወቁ በእኔ እንደምታዩት ለምትሐት አጥንትና ሥጋ የለውምና››  ሉቃ24፤39 እንዳላቸው የጌታችን ትንሳኤ ምትሐት ያይደለ አማናዊ በቀደመው ተዋሕዶ ባለመለወጥ እንደተነሳ ለማጠየቅ ተገለጠላቸው፡፡ሲገለጥም በተዘጋ ግንብ መግባቱ መለኮት አለመለየቱንና ወደ ሥጋ መለወጥ እንዳላገኘው ያስረዳል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  • ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤     በዐቢይ ኃይል ወስልጣን፤          አሠሮ ለሰይጣን፤          አግዐዞ ለአዳም፤                ሰላም፤          እምይእዜሰ፤                  ኮነ፤          ፍሥሐ ወሰላም።     📖 ተነስቷል!  እንደ ተናገረ፤ ተነስቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ:: ማቴ (28:6) 📖 “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል እንጂ በዚኽ የለም" ሉቃ 24፥5 "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:20፤) እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን!❤️

  • ​​​​ዕለተ ዓርብ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕለት ዕለተ ዓርብ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት ክርስቶስ ከተሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ በክርስቲያኖች ዘንድ በጾምና በስግደት በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በመጀመሪያ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተሰቀለው ትንቢቱን ለመፈጸም ነው፡፡ ሙሴ "ስቅልተ ትሬእያ እስራኤል ለሕይወትከ ቅድመ አዕይንቲከ ወኢትትአመና" "እስራኤል ሆይ ሕይወትህ /ክርስቶስ/ በዓይኖችህ ፊት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ታየዋለህ፡፡ ግን አታምነውም፡፡" /ዘዳግ. 28/ ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስም "መጽአ ከመ በግዕ ይጠባሕ ወከመ በግዕ ዘኢይነብብ በቅድመ ዘይቀርጾ ከማሁኢከሠተ አፍሁ በሕማሙ በቅድመ እለ ይረግዝዎ፤ ወበ ኃጢአተ ሕዝብየ በጽሐ እስከ ለሞት፣ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ" አኮ በመልአክ ወአኮ በተንባል አላ ለሊሁ እግዚእ መጽአ ወአድኀነነ ተብሎ በሰፊው ተናግሯል፡፡ ጥቅሶቹ ብዙ ናቸው፡፡ ኢሳ. 53፡1-6 ነቢዩ ዳዊትም "አገቱኒ ከለባት ብዙኃን፣ ወአዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን" ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ ወኆ ለቁ ኵሎ አዕጽምትየ" "እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፡፡ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም" እንዳለው፡፡ 6666 ጊዜ በገረፉት ጊዜ አጥንቱ ተቆጥሮዋል፣ ይኸ አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ነው፡፡ 6666 ጊዜ ለመገረፉ ግብረ ሕማማት ይገልጻል፡፡ መዝ. 21/22 ቁጥር 17-18 ክርስቶስ ለምን ሞቱ በመስቀል ሆነ? ከመስቀል በሌላ ማዳን አይችልም ነበር ወይ? ቢባል በዘመኑ የነበረው የበደለኛ አገዳደል ሥርዓት እንደየሀገሩ ሁኔታ የተለያየ ነበር፡፡ ለምሳሌ የሮማውያን ሥርዓታቸው መስቀል ነው፡፡ የአይሁድ "ውግረተ ዕብን" ነበር፡፡ የባቢሎናውያን እሳት አንድዶ እዚያ መክተት ነው፡፡ ፋርስ ለአንበሳ መጣል ነው፡፡ ጌታም በሮማውያንም ሥርዓት ተሰቅሎ ሞተ፣ ለዚህም ራሱ ጌታ ሞቱ በመስቀል እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ ዮሐ. 3፡14፡፡ ባይሰቀል፣ ጎኑ ባይወጋ ማይ ለሕጽበት፣ ደም ለጥምቀት ባልተገኘ ነበር፡፡ ብለው መምህራን ተርጉመዋል፡፡ አይ፣ በውግረትም ደሙን አይታጣም ብለው ትንቢትን ለመፈጸም ተሰቀለ ብሎ አስታርቀውታል እንጂ፡፡ የአይሁድ ሥርዓት በድንጋይ ወግሮ መግደል ነው፡፡ ጌታ የተሰቀለው በሮማውያን ሥርዓት ነው፡፡ "ኲሉ ሰቁል ዲበ ዕፀመስቀል ርጉም ውእቱ" "ሠርቶ ቀምቶ የተሰቀለ ሰው የተረገመ ነው" ትላለች ኦሪት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም "ወፆረ መርግማ ለኦሪት" አለ፡፡ ርጉም ተብሎ የአዳምን መርገም ለማጥፋት በአዳም የተፈረደው ሁሉ ተቀብሎ አዳምን ከመርገመ ነፍስ አዳነው፡፡ "ወሠዓረ መርገመ እምኔነ" ከእኛ መርገመ ኃጢአትን ደመሰሰ፣ አጠፋ ያለው ስለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ክርስቶስ ከተሰቀለ፤ ልጅነት ከተመለሰ ወዲህ ወደ ሲኦል መውረድ ቀርቷል፡፡ ይህም ዮሐንስ አፈወርቅ ገልጦታል፡፡ "እንከሰ ኢንወርድ ታሕተ አላ ፈድፋደ ንተልዎ ለዘፈጠረነ ወንበውእ ኀበ ቦአ ሐዋርያነ ህየ ንበውእ ኵልነ" ይላል፡፡ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፋልን የተባለው አምኖ፣ ተጠምቆ ፣ ጥሩ ሥራ ከሠራ ወደታች መውረድ የለም ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡ ቀድሞ በዘመነ ብሉይ መልካም ሥራ ቢሠሩም እነ አብርሃም ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ሁሉ በሲኦል ነበሩ፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ አጠፋ የሚለው ስለዚህ ነው፡፡ "ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በሞትየ ወበመስቀልየ" ቀሌምንጦስ፤ "ወለትከ" የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ገድለ አዳም ገጽ 105፡125፡፡ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ገጽ 54፡8 ቀደም ብሎ እንደተገለጸው "ከመይሥዓር መርግማ ለኦሪት" በተባለው መሠረት አዳም ተርግሞ ነበር ወይ? ሲባል መልሱ አዎ ነው፡፡ ከገነት ሲኖር "ይችን ዕፅ የበላህ እንደሆነ ትመውት ሞተ" ሞትን ትሞታለህ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር ርደተ ሲኦል ያገኝሃል ነው ያለው፡፡ "ወአልበሶሙ አእዳለ ማዕስ" ያብርሃን የነበረው፣ እንደብርሌ፣ እንደ ብርጭቶ ንጹሕ የነበረው እሾኽ እማይወጋው፣ እንቅፋት የማይመታው፣ እማያደማው፣ ብርድ የሌለበት የነበር በኋላ መርገም ሲያድርብት እሾክ የሚወጋው፣ እንቅፋት የሚመታው፣ ብርድ የሚሰማው ልጅነት የሌለው ቁርበት አለበሰው፡፡ እሱ ባይረገም፣ ወደ ምድር ባይወርድ፣ በዘፍጥረት 1፡28 "ብዙ፣ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም" ብሎ ነበረ አዳም ባያጠፋ ኑሮ ሰው እንዴት ሊበዛ ይችል ነበረ ቢሉ? ይኸማ መጀመሪያ አዳም በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘ እንጂ ከሴት አልተገኘም፡፡ ሔዋንም ያለ ወንድ በሥልጣነ እግዚአብሔር ተገኘች እንጂ ሴትና ወንድ ተገናኝተው አልተፈጠሩም፡፡ ባይበድሉ በሥልጣነ እግዚአብሔር ወንድም በአዳም አምሳል፣ ሴቱም በሔዋን አምሳል በሥልጣነ እግዚአብሔር እየተባዛ፣ ዕፀ ሕይወትን እየበላ ሺህ ዘመን ሲሞላው መንግሥተ ሰማያትን ሊገባ ተፈጥሮ ነበር፡፡ እንግዲህ ለአዳም ዕፅዋትን ሰጠው፤ አንዱ የሚመገበው በመዓዛው ይጠግባል ሁለተኛው ሕግ ሊጠብቅለት ይችን ዕፅ አትብላ ብሎ፤ ሦስተኛው ሺህ ዘመን ኑሮ ያን ሲበላ ተሐድሶ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ፈጥሮት ነበር፡፡ ይኸንንም ሰሎሞን ገልጦታል "እግዚአብሔርሰ ኢገብረ ሞተ አላ ረሲአን ሰብእ አምጽእዎ በቃሎሙ ወዓርከ አምስልዎ" እግዚአብሔር ጥንቱን ሲፈጥረው ሞት እንዲሞት እንዲቀበር ወደሲኦል እንዲወርድ አልፈጠረውም፡፡ ሕጉን እንዲጠበቅ ሺህ ዘመን በሕይወት እየተቀመጠ ወደ መንግሥተ ሰማይ ሊገባ ተፈቅዶ ነበር፡፡ "ኢትብልዑ እምዕፅ" ይችን እንጨት አትብሉ ያለውን የዘነጉ አዳምና ሔዋን ሞትን፣ መቃብርን፣ ስበው ጎትተው አመጡት፡፡ "ወአርከአምስልዎ" ወዳጅ አስመሰሉት አለ ወዳጅ እንዳይለይ እንዳይለይ አደረጉት፡፡ ቀጥሎ ልጆቻቸውን፣ ይህንም ቅዱስ ጳውሎስ ገልጦታል፡፡ "ወሶበ ኵነኔ ኃጢአት ወጽአ እምላዕለ አሐዱ ብእሲ ተቀሰፈ ባቲ ኩሉ ፍጥረት" ሮሜ. 5፡12፡፡ ከአንዱ አዳም የተገኘች ኃጢአት ሁሉን /መላውን/ አደረሰች፣ ከአንድ ዛፍ በተቈረጠ ጨንገር ብዙ ሕፃናት እንደሚገረፋ ኃጢአትም ከአዳም ተገኝታ ሁሉን ያዘች፡፡ መባዛት በዘር በሩካቤ የሆነው ከመርገም በኋላ ነው፡፡ በገነት ሳሉ ወንድና ሴት መሆናቸው አይተዋወቁም፡፡ አዳም እኔ ብቻ ነኝ ሲል ረዳት እንድትሆነው ፈጠረለት እንጂ በዘር በሩካቤ ሊገናኙ አይደለም፡፡ ለምን ተባዙ አለ በሥልጣኑ ያበዛቸዋል። እግዚአብሔር ሁሉን አንድ አንድ ጊዜ ነው የተናገረው "ለታብቁል ምድር" አለ ይኸ መሬት ሁል ጊዜ ታበቅላለች፡፡ "ለያብርኁ ብርሃናት" አለ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ፣ ከያለበት ሲያበሩ ይኖራሉ፡፡ "ለታውጽእ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት" ሲል አዞ፣ ጉማሬ አንድ ጊዜ ሲባዙ ይኖራሉ፡፡

  • ++ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ++ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ፊት በዚያች ምሽት በጭንቀት ቆመዋል፡፡ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሠጠኛል ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ተጨንቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እያሉ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ተራ በተራ ጠየቁት፡፡ የቀሩት ሊሸጠው ተስማምቶ የመጣው ይሁዳና ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁዳ እኔ እሆንን ማለቱ ልቡ እያወቀ ስለነበር ከዐሥሩ ጋር አብረን አንቆጥረውም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ለጌታ ካለው የፍቅር ጥልቀት የተነሣ እኔ እሸጠው ይሆን? የሚል ሥጋት ስላልነበረበት ‘’ጌታ ሆይ አሳልፎ የሚሠጥህ ማነው?’’ አለ እንጂ እኔ እሆንን አላለም፡፡ የሐዋርያቱ የጭንቀት ጥያቄ በማግሥቱ መልስ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ይህንን ትሕትና የተሞላ ጥያቄያቸውን ለእኛ ሳይበጅ አይቀርም፡፡ በዙሪያችን ለተደረጉ ፣ ለሚደረጉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያቱ ምንድር ነው? ጥፋቱ የማን ነው? መነሻው ምንድርን ነው? ብንባል ሁላችንም ጣት የምንቀስርበት ሰው አናጣም፡፡ አዳም ዕጸ በለስን ለመብላቱ ‘’ም ክን ያቴ ሔዋን ናት ‘’ አለ ሔዋን ‘’ዕባብ አሳተኝ ‘ አለች ዕባብም ጠያቂ ቢያገኝ ሰይጣን ማለቱ አይቀርም ነበር፡፡ አንዳቸውም ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ማለት አልቻሉም፡፡ እንደ ዳዊት ‘’እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊትህ ነው’’ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ለሚሆኑ ነገሮች ሁሉ የምንከስሰው ሰው አናጣም:: መፍትሔው ግን ራስን ማየት ነው:: "እስመ አዕይንቲሁ ለጠቢብ ዲበ ርእሱ" (የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው) እንዲል ቅዱሳን በምንም ነገር ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር:: በገድላቸው ብዛት በሚጸልዩበት ሥፍራ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ሳለ እርሳቸውን እንዳይነካቸው በቆሙበት ሥፍራ እንዳይዘንም ያደረገላቸው ዳግማዊው ኤልያስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እናስታውስ:: በቆሙበት ሥፍራ ዝናም እንዳልዘነመ ሲያዩ "ይህችን መሬት በኃጢአቴ ዝናም አስከለከልኳት" ነበር ያሉት:: ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ይህም አይደል? የሙሴ ወንድም አሮን በእስራኤል ግፊት ጣኦት ሠራ፡፡ ከወርቅ አቅልጦ ጥጃ አምላክ አድርጎ ሠራላቸው፡፡ ከሠራ በኋላም መሥዋዕት ለጣኦቱ አቀረበ፡፡ ሙሴ መጥቶ ሲቆጣ ሲያይ  ግን አሮን ፈራና በሕዝቡ አሳበበ የራሱን ድርሻ በተመለከተ ግን እንዲህ አለ ‘ወርቅ ሰጡኝ በእሳት ላይ ጣልሁት ይህ ጥጃ ወጣ’ {ዘጸ 32፡24} ራሱ ከእጃቸው ተቀብሎ በመቅረጫ ቀርጾ የሠራውን ጣኦት ‘ስጥለው ጥጃ ሆነ’ አለ፡፡ ራሱ ሕዝቡን ‘ስድ ለቅቋቸው’ የነበረ በመሆኑ ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ብሎ ራሱን ሊከስስ ይጠበቅበት ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ሕይወታችን የማይረሱ ቀናት ግሬድ የሚለጠፉባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ከብዙ የመታወቂያ ቁጥር መካከል ውጤቱን ያየ ተማሪ በዚያ የትምህርት ዓይነት  A እንዳገኘ ሲያውቅ ለጓደኞቹ ‘’A አገኘሁ እኮ’’ ይላል፡፡ በተቃራኒው ‘F’ ያገኘ ከሆነ ‘’F ሠጠኝ’’ ይላል እንጂ ‘F አገኘሁ’ አይልም፡፡ A ከሆነ ያገኘው ተማሪው ነው ፤ F ከሆነ ግን በድክመቴ አገኘሁ ከማለት ይልቅ ጥፋቱ የመምህሩ ይሆናል፡፡ ነገሩን አልኩ እንጂ ሀገር ሰላም ብሎ የቆመ በር ጋር ስንጋጭም ‘በሩ መታኝ’ እንጂ መታሁት አንልም፡፡ እናም በሕይወታችን ለሆኑትና ለሚሆኑት ነገሮች ‘ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ትልቅ ጸሎት ነው፡፡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ታኅሣሥ 20 2012 ዓ ም አዲስ አበባ