tgindex
Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

Статистика

መሐመድ ሐሰን

Последний пост
20 июл.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
769
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
364
22 постов
Вовлечённость
47,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
154
1/48двое суток
176
1/72трое суток
190

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • https://youtu.be/HQrFAGMTrLk?si=R-0nR0F0FMQc3Xn-

  • Part 1

  • https://youtu.be/Hnrt7fG4IQY?si=5dGYNRPWM70mYcWx

  • #walk እና #Talk አጋሮ ላይ‼️ #ከከንቲባው ጋር ዘለግ ያለና፣ በብዙ የሚያስደንቅ #ወግ፣ #ወክ እና #ፍለጋ አድርገናል። በዚህም አጋሮን ተሻግረን አዲስ አበባ: ቦሌና ባሻገርም እንዘልቃለን። ዛሬ ምሽት 2 ሰአት በ #Gasabmeda ቻናላችን ላይ ይጠብቁን።🙏 #ሀጉዞ #አጋሮ #ሀሳብሜዳ

  • https://youtu.be/LvSWYliaIYI?si=rYCjtxYKYUTSVQCU

  • የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ‼️ "ወታደር ነኝ" መፅሃፌ ዛሬ እጃችሁ እንደሚደርስ ቃል ገብቼ ነበር። ከህትመት እክል ጋር በተያያዘ፣ ለዛሬ ሊደርስ አልቻለም። በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እጃችሁ ይገባል። ቃላችንን ባለመጠበቃችን ይቅርታ እንጠይቃለን። አፉ በሉን። ሰናይ ቅዳሜ ለሁላችን🙏 #ወታደርነኝ #iamasoldier #mohamossen

  • ኢትዮጵያ ውስጥ እዚህም እዚያም ግጭት አለ፤ ይሄ ደግሞ ተቀባይነት የሌላችሁ መሆኑን ያሳያል ለማለትም ተጠቅመውበታል፡፡ ለዚህም የምንለው ‹‹ለልማቶቻችን አይናችሁን ጨፍናችሁ ግጭቶቹን የምትዘግቡልን ከግጭቶቹ ምን ትርፍ ስላገኛችሁ ነው?›› የሚል ጥያቄ እናነሳላቸዋለን፡፡ የኢትዮጵያ ፍላጎት መልማት፣ መበልጸግ፣ መሰልጠን መሆኑን እውቅና ሊሰጡ አልደፈሩም፤ እንዲያውም የወራሪነት ካባ ለማላበስ ሲሞክሩ ታይተዋል፤ ይህን አይን ያወጣ ጥላቻ ለመግለጽም የጠቅላይ ሚኒስትሩን መጻሕፍት እስከማሽሟጠጥ ደርሰው አይተናል፡፡ ለትዝብት ያህል የዛውን ጽሑፌን ከማጠናቀቄ በፊት እዲያው መህዲ ድብቅ ፍላጎቶች ባይኖሩት ኖሮ ብዬ ጥቂት የትዝብት ነጥቦችን ላንሳ - በትግራይ ሃይሎችና በፌደራ መንግስት የተደረገው ጦነት መነሻ ህወሃት በመከላከያ ላያ የደረገው ፍጅትና ሸፍጥ መሆኑን ለማንሳት ለምን አልደፈረም? ህወሃት በራሱ ወገኖች ላይ ሳይቀር ያደረሰውን ግፍ፣ በወልቃይት በኩል የፈጀውን ነዋሪ እንዲያው ለነገሩ ያህል እንኳ ጠየቅ ማድረግ ለምን ተሳነው? ህወሃት አሁንም ልክ ነው፣ የሚለውን ትርክት ለማስረጽ ይሄንን ያክል መጓዝ የተፈለገው ህወሃት ምን ጭነት ተጭኖ የት ድረስ እንዲጓዝ የተፈለገ ፈረስ ስለሆነ ነው? በተለያዬ ጊዜ ብዙ በደል ያደረሰ፣ ብዙ ወንጀል የሰራ፣ ሰነድ ጽፎ ከኤርትራ ጋር የሰራ፣ አሁንም ከኤርትራ ጋር እየሰራ ያለው ህወሃት ሆኖ ሳለ ህወሃትንና ኤርትራን ነጻ ትቶ የኢትዮጵያ የልማት ጥያቄዎች የተስፋፊነት ፍላጎቶች ናቸው ብሎ መተረክ ለምን ተፈለገ? - ብዙና ውስብስብ ፈተናዎችን ተቋቁሞ በማለፍ የዓባይን ግድብ ማጠናቀቅ ያስቻለንን ጥበብ ቢጠይቅ ምን ክፋት ነበረው? - የግንባታ ቴክኖሎጅ እምብዛም ባልተስፋፋበት፣ በቂ የበጀት አቅም በሌለበት ሌሎችም ፈታኝ ሁኔታዎች ባሉበት ሁኔታ ለመላው አፍሪካዊያን ምሳሌ የሆኑ ከተሞችና የከተማ መሰረተ ልማቶች በቀናት እና በሳምንታት ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቻለበትን ተሞክሮ ቢጠይቅ ምን ችግር ነበረ? አሰብን በጋራ ለመጠቀም ተስማምቶ አስፓልት መንገድ ከተሰራ በኋላ የኤርትራ መንግስት ያፈገፈገበትን ሁኔታ ቢያነሳ ምን ይሆን ነበር? በክፍል ሁለት እመለሳለሁ! #እንደማስታወሻ❗️ -በፅሁፉ ውስጥ ላሉ ግድፈቶች እና የጥራት ጉድለት ሁሉ አፉ በሉኝ።)🙏

  • እንደሚጎስም ስንደምርበት? መስመሮችን ለመገጣጠም እንደ ሁነኛ ማሳያ የቅርቡን ፓርላማ እናንሳ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው የአሁኗን ኢትዮጵያ ስኬቶች፣ ጉልበቶች፣ ብልሃቶችና እቅዶች ማብራሪያ በሰጡ በጥቂት ጊዜ ቃለ ምልልሱ መካሄዱ፣ የነመህዲንና መህዲ አቋማቸውን ይዞላቸው የመጡ ወገኖችን ፍላጎት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት የኢትዮጵያ የባህር በር ህጋዊ ባለቤትነት ጉዳይ በ1983 የተቋቋመው የሽሽግር መንግስትን ውሳኔ ኢ-ህጋዊነት የተንተራሰ ሆኖ ሳለ መህዲ ለማስረዳት የሞከረው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡና ከኢሳያስ ጋር እርቅ ሲፈጥሩ የኤርትራን ድንበር እውቅና ሰጥተዋል የሚል ነው፡፡ ይህ የሞኝ የመሰለ ግን አሳሳች የብልጥ እይታ ከኤርትራ ጋር ወደ ግጭት ያስገቡ በትግራይ ድንበር ያሉ አዋሳኝ ስፍራዎችን ለማስማማት በአልጀርስ የተፈረመ እንጅ አሰብን አሳልፎ ለመስጠት የተፈረመ አለመሆኑን ለምናውቅ ለእኛ የጠላቶቻችንን አሰላለፍ እንድናጤን አግዞናል፡፡ ባህሩን የፈለጋችሁት ለባህር ሃይላችሁ እንጅ ለወደብ ጉዳይ አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል፤ የባህር በር ታሪካዊና ህጋዊ መብታችንን ስለመሆኑ ያቀረብነውን ማስረጃ ይመኑልን እንጅ በመሬታችን ድንች ወይም በቆሎ መዝራት ያለብን እኛ እናውቃለን፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ነበረችበት ከፍታ ትመለሳለች›› የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ርዕይ ወደ ተስፋፊነትና ወራሪነት ትርጉሞ የለወጠው መህዲ እውነታውን ሳያውቅ ቀርቶ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያ ያሳካቻቸውና የወጠነቻቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች የተስፋፊነትና የአምባገነንነት መገለጫ አድርጎ ለማቅረብ መሞከር በርግጥም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከመፍራትም ከመጥላትም የመጣ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሄድ ቱ ሄድ ከይዘት አንጻር የመህዲ ጥያቄዎች ዞረው ዞረው የሚያርፉባቸው ማሰሪያ አንቀጾችና ገላጮች ዐቢይ አህመድን ዘር አጥፊ፣ ገዳይ፣ ጠቅላይ፣ ወራሪ፣ እብሪተኛ፣ ወዘተ. ማድረግ ላይ ነው፡፡ ነጥቦቹ በሙሉ፣ የአብይ ጠላቶች በተለያየ ጊዜ የነገሩን ናቸው፡፡ በዚሁ መድረክም ላይ የታደሙት ጭምር፣ ከመፅሀፍ እስከ ሚዲያዎች ድረስ ሲሰሩባቸው የኖሩና አስቀድመው የተነደፉ ናቸው። ምንም አዲስነት የሌላቸው አጀንዳዎች! ለዚያም ነው የአቢይን ማንነቶች በመካድ የተነሱት፡፡ አቢይ አህመድ ጌታቸው ረዳ ስለሰደበኝ ብሎ ፊት ያልነሳ ይቅር ባይ መሆኑን እውቅና ላለመስጠት፣ ጠያቂው የተጓዘበትን ርቀት ማየት፣ ለዚህ አስረጅ ይሆናል፡፡ በእህትህ ላይ ግፍ የፈጸመ አንተን ሊገድል የድሮን ጥቃት ያደረሰብህ እኮ ነው እያለ ከመሞገት አልፎ ‹‹አቢይ ዘርአጥፊ ነው በል›› እስከ ሚል ሙግት የደረሰው እንዲሁ አይደለም፡፡ ይልቁንም የትግራይ ህዝብ የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዲቆይ ኢትዮጵያም በዚሁ አዙሪት የደቀቀች ሀገር እንድትሆን ከመሻት እንጅ፡፡ ‹‹እህቴ በእሷ የደረሰው በማንም ላይ መድረስ እንደሌለበት ተረድታለች›› የሚለው የጌታቸው ረዳ ንግግር ውጥኑን ያከሸፈበት መህዲ ሌላ የሞኝ የሚመስል ሐሳብ ይዞብቅ ይላል፡፡ አንተም ሆንክ አቢይ ለሁለት አስርት አመታት ፖለቲካ ላይ ቆያችሁ ያመጣችሁት ለውጥ የለም፤ ለምን ጡረታ አትወጡም የሚለው የቂል የመሰለ ግን ብልጥ ጥያቄ የመህዲንና የወገኖቹን ውስጣዊ ፍላጎት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ለምን አቢይ የፓርቲ አባል የሆነበትን ሁለት አሰርት ለመቁጠር ፈለገ? ይልቁንም የፓርቲ መሪ የሆነበትንና አመርቂ ውጤት ያመጣበትን ያለፈውን ሰባት ዓመት ላለማዬት እንዲያውም የዘር ፍጅት አመታት አድርጎ ለማሳየት ሞከረ? ነገሩ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው፡፡ በተጨማሪ መህዲ በተደጋጋሚ ሲያነሳው የነበረው ያን የፈረደበት የኖቤል ሽልማት ነው፡፡ አቢይ የሰላም ኖቤል አይገባውም ለማለት፡፡ ከአመታት በፊት በግልጽ መልሶላቸዋል እኮ፤ በሽልማት የሚሸጥ ሀገር እንደማይመራ! ሌላኛውን የከሸፈ (ድኩም) ሴራ ደግሞ እንይ፡፡ ጌታቸውን እንዲህ ይለዋል መህዲ ‹‹አቢይ ከዘር ፍጅቱ በፊት ወዳጅህ ነበር፣ ከዘር ፍጅቱም በኋላ ወዳጅህ ነው፤ ስለዚህ በዘር ፍጅቱም ወቅት ወዳጅህ ነበር›› ይህ ኢንዳክት የተደረገ አመክንዮ ይመስላል፤ አሰላለፉን ላልዬ ሰው፡፡ የመጀመሪያ ጉዳይ ‹‹የዘር ፍጅት›› የሚለው ቃል አገልግሎት ላይ የዋለው በየትኛው ጥናት ተረጋግጦ ነው? ትልቁ ቁም ነገር ግን የቃሉ መሰረት ሳይሆን የመህዲና የጭፍሮቹ ውስጣዊ ፍላጎት መታዬቱ! ለነ መህዲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሁለት ጽንፎች ብቻ መኖር አለባቸው፡፡ አንደኛው ጽንፍ ያረጁ የህወሃት ቆሞ ቀሮች የያዙት ቆሞ ቀር አቋም ነው፡፡ ይኸውም ‹‹የዘር ፍጅት ደርሶብናል፣ ከፌደራል መንግስቱ ጋር አብረን አንሰራም፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት ፈርሷል ወዘተ›› የሚለው ነው፡፡ እነ መህዲ የሚፈልጉት ሁለተኛው ጽንፍ ‹‹እነዚህ ቆሞ ቀሮችን አሳድጀ ማጥፋት አለብኝ ለዚህም አዲስ ዙር ጦርነት ያስፈልገኛል›› የሚል የፈደራል መንግስት ነው፡፡ አቢይ ግን ከዚህ በላይ ነው፡፡ የቁሞ ቀሮችን ቆሞ የመቅረት ነጻነት በመጠበቅ አዲስ አተያይ አዲስ አስተሳሰብ ማሳየት፡፡ ለዚህ ነው ተራማጅ ከሆኑት ከእነ ጌታቸው ጋር በመስራት የትግራይን ችግር ለመፍታት እየተሰራ ያለው፡፡ መህዲ ግን ጌታቸው ከአቢይ ጋር መታረቁ ሰላም የነሳው ይመስላል፤ በጦርነቱ ጊዜም ወዳጅህ ነበር ማለት ነው የሚል ክስ የሚያነሳው ቆሞ ቀሮቹ እንደሚሉት ጌታቸው ትግራይን ክደሃል ለማለት ነው፡፡ ጌታቸው ደጋግሞ እንደተናገረው የትግራይ ችግር የሚፈታው ቆሞ ቀሮቹ በሚሄዱበት አካሄድ ሳይሆን አቢይ እየመራበት ባለው የሰከነ እና የበሰለ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ገለልተኛ የመሰለችው ግን ያልሆነችው ጸዳለ ደግሞ ቤኒዚን ይዛ ቀረበች ‹‹አንተ በምትለው መንገድ እንደማያዋጣ አይተናል፤ መች የትግራይ ህዝብ ካሳ አገኘና!›› የሚል ጥያቄ ለጌታቸው አንስታለች፡፡ እስከምናውቀው ድረስ ከፕሪቶሪያ ስምምነት ውስጥ የፌደራል መንግስቱ ያጎደለው አንዳች ነገር የለም፡፡ የካሳ ነገር ከተነሳ ግን ህወሃት በአማራና አፋር ክልል ላወደመው ምናልባት ሃያ ሳላሳ አመት መልሶ ለመስራት ለሚፈጀው ሁሉ መቼ ይሆን ካሳ የሚከፍለው? ፀዳለ ሌላም ውስጣዊ መሻት እንዳላት ጠቆም አድርጋናለች፡፡ ጌታቸው ተራማጅ መሆኑን ለማንኳሰስ፣ ቆሞ ቀሮቹ ልክ መሆናቸውን ለማሳዬት የተደረገ ሙከራ፡፡ ምንም እንኳ ብስራት ‹‹ይሄኮ ፕራግማቲዝም ነው›› ብሎ እዚያው በቂ ምላሽ ቢሰጣትም፣ የጸዳለንና የህወሃትን አሰላለፍ መልሰን ማየት ለምንችል ለእኛ የሚነግረን ነገር አለ፤ የማያባራ ግጭት ፍላጎት! ‹‹ጦርነት አይቀርላችሁም›› የሚለው ‹‹መግለጫ›› ሌላኛው ጎልቶ የወጣ ነጥብ ነው፡፡ ጦርነቱም ከኤርትራ ጋር ስለመሆኑ ነግረውናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ግን የጦርነት ፍላጎት እንደሌላቸው በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ እነ መህዲ ደጋግመው ያነሱት ኤርትራ በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ሃይሎችን እያስታጠቀች ነው ስለዚህም ጦርነት አይቀርላችሁም ነበር ያሉት፡፡ የእኛ መንግስት ደግሞ በፍጹም ጦርነት አልፈልግም ነው፡፡ ጦርነቱ እንደማይቀርልን በርግጠኝነት የነገሩን ከእነ ማን ጋር ስለሚሰሩ ነው?

  • ከብሄራዊ ቡድኑ እስከ ብሄራዊ ጥቅም⁉️ ከአልጀዚራው ግንባር እስከ ኳስ ሜዳው⁉️ ➖ እንደ አንድ ኳስ ተጫዋች፣ የቀድሞ ክለብህ ላይ እንኳን ስታገባ፣ ደስታህን መግለፅ ትፈራለህ። ታዝናለህ ወይም ደግሞ ከመፈንጠዝ ትቆጠባለህ። የእኛ ነገር ግን ግራ ይገባል። ብሄራዊ ቡድናችን፣ ብሄራዊ ጉዳዮቻችን፣ ብሄራችን ላይ ጭምር፡ ጎል ለማስቆጠር እንጋፋለን። ወይም እንዲገባብን እንናፍቃለን። ሲቆጠርብን ወይም ስንወድቅ እንፈነጥዛለን። ዛሬ ያለፈው ብሄራዊ ቡድናችንን ጨምሮ፣ ሰሞነኛ ፖለቲካችንን ብንመለከተው፣ የሆነውና የሚሆነው ይህ ነው። ከ27 አመት በሁላ ላለፈው ቡድናችን፡ እንኳን ደስ አላችሁ። ግን ዋነኛው ችግራችን መርሳት ነው። ለምሳሌ ከሰሞኑ በአልጀዚራው ግንባር የነበረው ፍልሚያ። በራስ ሀገር ላይ ለማስቆጠር የተደረገው የአደባባይ ግብግብ። አዎ እኔ አልረሳሁትም። አልረሳውምም። ስለዚህም እኔ ከዛሬ ጀምሬ በተከታታይ እሄድበታለሁ። በዚሁ ጉዳያችንም የሁሉንም ነገር አያያዛችንን አጮልቀን እንመለከትበታለን። መልካም ንባብ። አንድ - የአልጀዚራው ግንባር ፍልሚያ እና ሚስጥሮች! መህዲ ሀሰን በAJ ከUpfront እስከ Head to head ፕሮግራሞቹ ድረስ፣ በፍቅር የምከታተለውና የምወደው ጋዜጠኛ ስለመሆኑ ቀድሜ መናገር ይኖርብኛል። መህዲ ከአለጀዚራ በተጨማሪ አሁን ደግሞ በራሱ Zeteo በተባለ ቻናል ብቅ ብሏል። ሰሞኑን በአልጀዚራው ‹‹ሄድ ቱሄድ›› የመህዲ እንግዳ ሆኖ የቀረበው አቶ ጌታቸው ረዳም፡ በብዙ የፃፍኩበት ሌላኛው ሰው ነው። ከመፅሀፍ እስከ መጠነኛ ጥናት እና በርከት ያሉ አጭርና ረዥም ፅሁፎችን ፅፌበታለሁ። ሁሉም ማለት ይቻላል፣ አዎንታዊ አልነበሩም። ከአመትና ሁለት አመት በፊት፣ ከሰራነው ጥናታዊ ሰነድ ውጪ፣ ሌሎቹ ሁሉ፣ ክፉኛ ጌችን ያብጠለጠልኩባቸው ናቸው። ያም ሆኖ የዛሬ ጽሑፌ ትኩረት ዛሬ ግን ጉዳዬ መውደድ እና መጥላቴ ወይም ግለሰቦቹ አይደሉምለግለሰቦቹ ያለኝን ስሜት ማንጸበራቅ ሳይሆን፣ ሀሳባቸውን መፈተሸ ነው። የጽሑፌ መሰረት ሀገርን እና ብሄራዊ ጥቅምን ብሎም ሙያን መሰረት ያደረገ ነፃ አስተያየት ወይም ትንታኔ ነው። ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ መስጠቴ የጋዜጠኝነት ሙያዬ ግዴታ ነው፡፡ የምወደው መህዲም በሀገሩ ብሄራዊ ጥቅም ላይ የሚደራደር ሰው አይደለም። ዳሩ ግን ከእኛ ወገን በብሔራዊ ጥቅም የሚደራደሩ ‹‹ጋዜጠኞችን›› ይዞ ቀርቧል፡፡ እዚህ ጋ ምናልባት የሀገሩን ብሄራዊ ጥቅምም ታሳቢ አደርጎ በሀገሬ ብሄራዊ ጥቅም ላይ መምጣቱ ይሆን? የሚል መላ ምት ይዤ ለመነሳት ተገደድሁ፡፡ መልሱን ከሙሉ ፅሁፎቼ ውስጥ እንፈልግ። የሰሞኑን ቃለ ምልስ ተከትሎ በመበደበኛ፣ በማህበራዊ፣ በግል ሚዲያ ስም በሙያውም የሚነግዱት የኛዎቹ ጉዶች የመህዲህ መፈጠር ዛሬ መስማታቸው ይመስላል፡፡ የገዛ ሀገራቸው ላይ ሲዘምት ‹‹እንዴት›› ብሎ ከመፈተሸ ይልቅ የጀግና ካባ አለበሱት፤ አጨበጨቡለት። የጋዜጠኝነት ውሀ ልክ አድርገው ዘመሩለት። የነሱ ‹‹ጋዜጠኝነት›› ሀገር የለውምና። ‹‹ጋዜጠኝነታቸው›› ከብሔራዊ ጥቅም ወይም ከእውነት የሚቀዳ አይደም፡፡ ዕይታንና ተከታይን ከማፍራት እንጅ፡፡ ስለዚህ ‹‹እንዴት› እና ‹‹ለምን›› የሚሉ የሙያ አምዶችን ከመጠቀም ይልቅ ‹‹ነገረው!›› ‹‹አንጰረጰረው›› የሚሉ አዳማቂ ገለጻዎችን ለ‹‹ትንታኔዎቻቸው›› ፊት ገጽ ተጠቀሙ፡፡ ለባዳ ይዘምራሉ። ባንዳነት ጌጥ ሆኗልና! ወደ ዋናው ጉዳያችን እንዝለቅ። አልጀዚራ በዓለም ብዙ ተመልካች ካላቸው ሚዲያዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ይህ የሆነው ግን የሀሳብ መስኮት ስለሆነ ብቻ አይደለም፡፡ አዎ አልጀዚራ የሀሳብ መስኮት ብቻ አይደለም። እልም ያለ የውጊያ ግንባርም እንጅ። ያውም የዘመነና የዘመኑ አደገኛው የጦርነት ግንባር። የሰሞኑን የጌታቸው ረዳ ቃለ ምልልስ እና የመህዲን አንድምታዎች በዝርዝር እንይ! መህዲ ከጌታቸው ረዳ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ፍላጎትና አንድምታዎች! ጠቅለል ሲል፡ ፍጅት፣ ዘር ማጥፋት፣ መበታተን፣ መጠቅለል፣ መውረር፣ መስፋፋት፣ ዘር አጥፊ ወዘተ በሚሉ ቃላት የታጀቡት የመህዲ ጥያቄዎች፣ እውነትን የማወቅ ሳይሆን፣ አሳሳች ትርክትን የመፍጠር ሙከራዎች፣ እንዲሁም ቀድመው በመናበብ የተሰሩ መሰል ክሶችን የማስረገጥ ናቸው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያለችበትን ቁመና እና ፍላጎት የካደ፣ የጠቅላይ ሚንስትሩን ሰብዕና ለማንኳሰስ የሞከረ፣ በትግራይ ህዝብና በፌደራል መንግስቱ መኻል ያለውን መተማመንና (እምነት) ብሎም መተሳሰብ ለመደበቅ የሞከረ የ49 ደቂቃ አተካራ ሆኖ ያለፈው፡፡ እስኪ በዝርዝር እንየው፡፡ “ሄድ ቱ ሄድ” ከተሠራበት ወቅት አንጻር! አልጀዚራን ያክል ሚዲያ እንዲህ ያለ መነጋገሪያ የሆነን ቃለ መልልስ፣ እንዲሁ በአንድ አዳር ወስኖ የሚሰራ አይመስለኝም፡፡ ጌታቸው ረዳን ለመጋበዝ ሲያስብ እንደ ሀገር፣ እንደ ቀጠና እና አለም አቀፍ ጉዳዮችን ያጤናል፡፡ ወደድንም ጠላንም ይህ ሚዲያ የሚሰራለት የሆነ ወገን አለው፡፡ የዚያን ወደገን ብሔራዊ ወይም ቀጠናዊ ጥቅም ባማከለ መንገድ ፕሮግራሙን ሊቀርጽ እንደሚችል የሚያጠያቅ አይደለም፡፡ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ስንል ከእኛም ፈቀቅ አድርጎ ማዬት የሚገባን ይመስለኛል፡፡ አልጀዚራን የምታስተዳድረው ኳታር ናት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያ ቁርጠኛ የልማት አጋር ከሆኑ ሀገራት ውስጥ ዩናይትድ አብ ኢምሬት አንዷ ናት፡፡ ስለዚህ ኳታር በአልጀዚራዋ በኩል ምን ልትነገረን እየፈለገች ነው? የሰሞኑን ቃለ ምልልስ እና በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ እየሄደች ያለችባቸውን ልማታዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ መንገዶች ዞር ብሎ ማጤንና ይሄንን እንደ ሀገር፣ እምደቀጠና ሲልም እንደ ዓለማቀፉ አሰላለፍ መተንተን ይጠይቃል፡፡ የጎረቤት ሀገራት ሚዲያዎች ጨምሮ እንደ አልጀዚራ ያሉት ሰፋፊ ሚዲያዎች የኢትጵያ የባህር በር ጥያቄ እንዴት እየዘገቡት ነው? ሀገር ውስጥ ያሉ የውስጥ ጉዳዮቻችንን እንዴት እያራገቧቸው ነው? ሀገር ውስጥ የሆኑትን ብቻ ሳይሆን ሊሆኑ ይችላሉ የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዴት እየተነተኑልን ነው? ሀገር ውስጥ ኮሽ ሲል አንዴ የሃይመናት ካባ፣ አንዴ የብሄር ካባ አንዴ የፖለቲካ ካባ እያለበሱ ሊተነትኑልን የሚሞክሩት እንዴት ነው? ሌላው ቢቀር ሰሞነኛ የትምህር ሚኒስቴር አዳዲስ መመሪያዎችንና አዋጆችን የነገሩን ከአዎንታዊ ለውጥ አንጻር ወይስ ከጸብ አጫሪነት አንጻር? ከሴኩላር ትምህርት አንጻር ወይስ ከሃይማኖት አንጻር? በሌላም በኩል፣ ብዙ ሀገራዊ ስሀኬቶች ቢኖሩም ብዙዎቹ የዘገባ ወይም የትንታኔ ሽፋን ያገኙ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም የእኛ የስኬት ታሪኮች እንደ ቀጠና እንደ አለምም በእያንዳንዱ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም አይን እንጅ በእኛ አይን የሚታዩ አይደሉም፡፡ ይሄኔ ነው የእኛዎቹን ሞኞች ከቪውና ላይክ ይልቅ ብሔራዊ ጥቅም የምላቸው! ኢትዮጵያ አሁን ብዙ ጅምሮች አሏት፣ በፈጥነት ማጠናቀቅ ያሉባት፡፡ ታላላቀ ነገሮችን በጀመረች ቁጥር ረፍት የማያገኙት ‹‹ወዳጆቻችን›› የምርጫ ዋዜማ ላይ መገኘታችንን ለራሳቸው አላማ ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ። በማስረጃዎች ሁሉ እንደምናየው፣ ዋነኛ ተዋናዮቹ “ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም” ባዮቹ ወያኔ፣ አጃቢዎቿ እና “ነጭ ወያኔዎች“ መሆናቸውን ነው። ለዚህ ያመች ዘንድም ከአሁኑ ‹ለምርጫ የሚሆን በቂ ዝግጅት የለም›› ‹‹ሜዳው አልተስተካከለም›› ‹‹ይህ ካልሀፐነ በቀር ምርጫ አይደረግም›› የሚሉ ጩኸቶች እየሰማን ነው፡፡ ይህ ምን ታስቦ ለምን እንደሚባል ይገባናል፡፡ የህወሀት ሰሞነኛ የጦርነት ድለቃ እና ከማን ጋር ተቧድኖ ነጋሪቱን

  • без подписи

  • https://youtu.be/vgUrg4Kgdrg

  • እዚህ መንደር በተለይ ያለራስ እቅድ: ውሎ የማደር ትልቁ "ጥቅም"⁉️👇

  • #ከዓባይም በፊት #በጣና_በለስ⁉️ #ከአስመራ እስከ #ግብፅ እና #ሚዲያዎቹ? ኢሳያስ ዛሬ በካይሮ መገኘታቸውን እንደ ተራ እንድናልፍ ለሚለፉት። እንዳላየ ለሚያልፉት፣ ግን በኢትዮጵያ ስም ለሚተነትኑና ለሚታገሉት፣ አሁንም ትንሽ ማሳያ እንምዘዝ።

  • #ከዓባይም በፊት #በጣና_በለስ⁉️ #ከአስመራ እስከ #ግብፅ እና #ሚዲያዎቹ? ኢሳያስ ዛሬ በካይሮ መገኘታቸውን እንደ ተራ እንድናልፍ ለሚለፉት። እንዳላየ ለሚያልፉት፣ ግን በኢትዮጵያ ስም ለሚተነትኑና ለሚታገሉት፣ አሁንም ትንሽ ማሳያ እንምዘዝ።

  • አጃኢብ ነው መቼም እንዲህ ያለው መቅደም‼️ #አሰብ #የባህርበር #ቀይባህር #redsea #ethiopia #Eritrea

  • #ሌሊሴ = እውነት “ጤነኛ” ናቸው❗️ ክብርት ኮሚሽነሯን አወራሁአቸው። በጣም ጤነኛ ናቸው። እነሆ ቆይታችንንም፣ ማስታወሻዬንም እንደወረደ!👇🏾 ምናልባት ይህም አጋጣሚ ሌላኛው እድለኝነት ይመስለኛል። ከአራት ቀን በፊት፣ እሮብ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም። በሀገራችን ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 7፡48 ነበር ያወራነው። ይገረማችሁና ስናወራ፣ ይህ የመጀመሪያም የመጨረሻም ጊዜአችን ነበር። አሁንም የበለጠ የሚገርመው፣ ያወራነውን ስታውቁ ነው። ከዚህም በላይ አሁንም የበለጠ የሚደንቀው፣ አሁን በአደባባይ ከህዝብ ጋር በሰማሁት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፡ ይህን ያህል ማውራታችን ነው። አድራሻቸውን ስቀበል እኮ፣ ሀገር ውስጥ እንደሌሉ ተነግሮኛል። እኔም ወደ ስልካቸው ስደውል ይህንን አውቃለሁ። የጠበቅኩትም “ስመለስ አገኝሀለው”ን ነበር። ብቻም አይደለም። እንደ ሀገራችን የብዙ አመራሮች አሰራርም ቢሆን፣ የሚጠበቀው ይህና ከዚህም የባሰው ነው። እንኳን ታመው፣ ከሀገር ውጪ ከሆኑ፣ ሲጀመር አይመልሱም። ከመለሱም “ሀገር ውስጥ የለሁም። ስመለስ እናወራለን” ወዘተ ነው ልምዱ። እሳቸው ግን ከሀገር ውጪ ብቻ አልመበሩም ለካ። በሰማነው ትግል ውስጥም ናቸው። ታዲያ በዚህ ሁሉ ውስጥ ሆነው፣ መልስ ብቻ አልነበረም የሰጡኝ። አንዴም ብቻ አልነበረም የተመላለስነው። በስራ ላይ እንዳለ ሃላፊ ጉዳዬን ተረዱ። ከሚመለከተው ጋር አገናኙኝ። ብዙ ብዙ ርቀት ተጓዙ። ልብ በሉ እኔ ለሳቸው እንደ አንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቢሯቸው ጎራ እንዳለ ተራ ባለጉዳይ ነኝ። “ሰላም መሀመድ እንዴት ነህ? …” አሉኝና አጭር የማይባል መልእክት አሰሙኝ። … በድምፃቸው ውስጥ ፍፁም ጤንነታቸውን የሚያጠራጥር ድካም፣ መልፈስፈስ፣ መታከት ወዘተ ፈፅሞ አላስተዋልኩም። ከዛ ይልቅ ከሰዎች የምሰማውን አስገራሚ ትህትና ነበር ከነሙሉ ክብሩ ያገኘሁት። በአደባባይ እንደምናያቸው ከነፈገግታቸው ነበሩ። የጤና እክል ገጥሟቸው በስራ ላይ እንደሌሉ ነግረውኝ፣ በቀጥታ ወደሚመለከታቸው ጉዳይ መግባታቸው። ይህንንም በእርጋታና ትህትና መከወናቸው፣ እንዴት ዛሬ በአደባባይ የምንሰማው አይነት ትግል እንደገጠማቸው መገመት ያስችላል? አረ ክፉውን ማሰቢያ ፋታ እንኳን የሚነሳ ጉልበት ነው ከድምፃቸው ያደመጥኩት። የሳቸው ብቻም አይደለም። ተተኪ እንዳበቁም ከልውውጣችን ውስጥ ገመትኩኝ። ወደ ምክትላቸው አስተላለፉኝ። ለምክትላቸውም በዛው እለት ደወልኩኝ። እሳቸውም ወዲያው መለሱልኝ። ሳያንዛዙም በነጋታው ጠዋት ቢሯቸው እንድመጣ ቀጠሮ ያዙልኝ። …. አዎ ተቋም እንደተፈጠረ ወይም እየተፈጠረ እንደሆነ፣ ቢሮውም፣ ቢሮው የጀመረው ግዙፍ ስራም እንደሚቀጥል፣ በዚህች ጎበዝ እንስት አጭር ቆይታና ልውውጥ፣ የአደባባይ ተግባር፣ ከምክትላቸው የተረዳሁ መሰለኝ። እውነት እንዲሆን/ ትክክል እንድሆንም እመኛለሁ። ለካ ዛሬ ከናንተው ጋር በአደባባይ የሰማሁት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ነበር ይህንን ያወጋነው። በስራቸው ላይ እንዳሉ ሁሉ፣ ሳያዛንፉ ያስተናገዱኝ። እንኳን ከሀገር ውጪ ሆነው፣ እንኳን ታመው፣ እንኳን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝታችሁ፣ በስራ ላይ ሆነው፣ እያወቁን፣ ጤነኛ ነን እያሉ፣ የሚያጉላሉንን የሀገራችንን ጥቂት የማይባሉ ባለስልጣናትና ሃላፊዎች አሰብኩኝ። አዎ እነሱ የምር የታመሙትን! በክፉ ደዌ የተጠቁትን። እንጂ ኮሞሽነሯማ በሚያስቀና ጤነኝነት ላይ ናቸው። አዎ ክብርት ጤነኛ ናቸው። ግን ደግሞ ታመዋል። የሚገርመው ደግሞ፣ ቢታመᎀም አይሞቱም። እንዴት እንዲህ ያለ ሰው ሊሞት ይችላል? እንኳን ዛሬ ወደፊትም ሞተው የማይሞቱ ናቸው። ይልቅ ወንበር ላይ የተቀመጣችሁ፣ በየቢሮው የተሾማችሁ፣ ጤነኛ ነን የምትሉ። ግን የታመማችሁ። ሳትሞቱ የምትረሱ፣ ከሳቸው ተማሩ። የወደቀን/ የሞተን አወዳሽነት? ይህ መንደር እና የኛው ባህል፣ ሰውን በቁም ከማወደስ፣ ከማመስገን ይልቅ፣ እስክትወድቅ ወይም እስክትሞት ጠባቂ ነው። እኔም ይህንን ለመፃፍ የወደድኩት በዛ እሳቤ አይደለም። ይልቅስ በብዙ ልፅፍበት የምችለው፣ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ እሳቸው እና ቢሯቸው ያመጡት ድል፣ የሰሩት ስራ ከድንቅም በላይ ነው። እሱን ነው ክብርት አትሞትም ያስባለኝ። ሌሊሴ = እውነት (dhugaa) ሌሊሴ ማለት አመስጋኝነት። አመስጋኝም ናት። ደግሞም የምናመሰግናት። ደግሞም የእውነት ልጅ ነች። የdhuga ልጅ። እውነተኛ መሪ/ ዜጋ። የእውነትም የምናመሰግንበት። በእውነት የተመሰገነች። የአእውነት ምስክር መፈተኑ አይቀርም. . . እንደወርቅ እንዲያምር።። እኔም በእለቱ ስንሰነባበት። ዛሬ በአደባባይ የሰማሁት ትግል ላይ መሆናቸውን ሳላውቅ፣ የሚቀጥለውን በማለት/ በመመኘት ነበር የተሰናበትኳቸው። “እሺ ሌሊስ በጣም አመሰግናለሁ። በሰላም ተመለሺ። ፈጣሪ ይከተልሽ። ክበሪልኝ።” የሚል ነበር። አሁንም አላህ ጨርሶ ይማርሽ። ላንቺ ጤናሽን መልሶ፣ እኛ ላይ ግን ያንቺን ጤነኛ መንፈስ ያጋባብን። አሚን!! እንደ #ማስታወሻ- ማስታወሻዬን እንደወረደ ስላጋራሁ፣ ለግድፈቶቹ ሁሉ አፉ በሉኝ። “አንቱታው” ከተደበላለቀም ተረዱኝ። በስራቸው አንቱ የተባሉ ሰዎችን፣ አንቺ/ አንተ ማለታችን የፍቅር ነው። ሁላችንም በእድሜ/ በስልጣን ብቻ አንቱ ከመባል እንውጣ። በተግባራችን አንቱ ለመባል እንስራ። ዛሬ ስለሳቸው የምንፅፍም፣ ይህንን አንቱ ያሰኛቸውን ትጋት፣ ትህትና፣ ስራ እንውረስ።🙏🙏 #lelisedhuga #visitOromia #VisitEthiopia 🇪🇹

  • без подписи

  • https://youtu.be/m3Nx8h-PDxk