tgindex
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) ️

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) ️

Статистика

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Последний пост
10 дек.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
27 374
−66 за 5 дн.
Сутки
−21
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
9 857
23 постов
Вовлечённость
36,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 дек.10,6 тыс7520

    በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ የሚኒስትሪ ተፈታኞች አፋን ኦሮሞ እንደሚወስዱ ተገለጸ ውሳኔው ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶችንም ያካትታል ተብሏል። ዘንድሮ በአዲስ አበባ በሚሰጡ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተናዎች አፋን ኦሮሞ እንደሚካተት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው በአዲስ አበባ ለሚገኙ አሥራ አንዱም ክፍላተ ከተሞች የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ማሳወቁን ሪፖርተር የተመለከተው ደብዳቤ ያሳያል፡፡ ደብዳቤው በመንግሥት፣ በግልና በዓለም አቀፍ (International) አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች ተፈጻሚ እንዲሆንና ትምህርት ቤቶቹም ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡ ለ8ኛ ክፍል አማርኛና አፋን ኦሮሞ እንደ አንደኛ ቋንቋ እንደሚሰጡ በደብዳቤው ሲመላከት የሒሳብ፣ የእንግሊዝኛ፣ የሳይንስና የዜግነት (ግብረገብ) ትምህርቶችም ይሰጣሉ ይላል፡፡ የ6ኛ ክፍል ፈተና በአማርኛ ሥርዓተ ትምህርት ለሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች አማርኛ እንደ አንደኛ ቋንቋ ሲሰጥ፣ አፋን ኦሮሞ ደግሞ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይሰጣል፡፡ የ6ኛ ክፍል ፈተናን በአፋን ኦሮሞ ሥርዓተ ትምህርት ለሚያስተምሩት ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ አንደኛ ቋንቋ ሲሰጥ፣ አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይሰጣል፡፡ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ሒሳብ፣ እንግሊዝኛ፣ አካባቢ ሳይንስና ግብረገብ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ደብዳቤውን የፈረሙት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኢል ጫላ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ተጠይቀው፣ ‹‹ጉዳዩ የሚመለከተው ሌላ ሰው ነው፤›› ብለዋል፡፡ የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት አቶ አበበ ደግሞ፣ ‹‹ስለጉዳዩ ማጣራት ይኖርብኛል›› በማለት ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ © ሪፖርተር ጋዜጣ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • 10 окт. 2025 г.14,7 тыс528

    ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸው ትክክለኛ መረጃ ካላቀረቡ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሀላፊዎቻቸው ከስራ ይባረራሉ ተባለ። ይህንን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው። በቀጣይ 6 ወራት ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ሌሎችም ጉዳዮች መረጃ በትክክል ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ አለባቸው ተብሏል። ይህንን ያላደረገ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በስራው አይቀጥልም ብለዋል። ይህንን ስራ እኔ በቀጥታ እከታተለዋለሁ ሲሉም የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የዩኒቨርስቲ ውጤት በተመለከተ የስምምነት ውል በተፈራረመበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ምደባ ቀስ በቀስ ይቆማል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ ዩኒቨርስቲዎች በራሳቸው ጥረት ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ እኛ የተማሪ ምደባ ስራን እየቀነስን እንመጣለን፣ ያ ሲሆን ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ መርጠውና በተቋሙ ብቃት ለይተው መግባት ይጀምራሉ ብለዋል። በረከት አካሉ ሸገር ኤፍ ኤም ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • 8 окт. 2025 г.11,5 тыс2125

    የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ፦ ➡️ በዌብሳይት፦ https://student.ethernet.edu.et ➡️ በቴሌግራም ቦት @moestudentbot ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ገልጿል። የRemedial ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። #MoE ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • 7 окт. 2025 г.10,3 тыс1415

    የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ። ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል። 1.  በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • ማስታወቂያ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ (NGAT) የፈተና ጊዜን ስለማሳወቅ በ 2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ የተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ፤ ፈተናው የሚሰጠው ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል እንድትገኙ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ፤ •  ሁሉም ተፈታኞች በተመደቡበት የፈተና ማዕከል ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ እና በ https://ngat.ethernet.edu.et ፖርታል በኩል የተላከላቸውን Exam Entrance ቲኬት ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • ከ8.4% ወደ 8.9% 2017 ትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በፊዚክስ እና ኢኮኖሚክስ ትምህርቶች ቅሬታ ቀርቦ ከተስተካከለ በኋላ እንዲሁም የመግቢያው ውጤት ከ49.50 ወይም ከ297 ጀምሮ ከሆነ በኋላ ዩኒቨርስቲ በቀጥታ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ቀድሞ ከተገለፀበት 48,929 ወደ 52,279 በመቶኛ ከ 8.4 ወደ 8.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ከማስተካከያው በኋላ 3,350 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት ችለዋል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መስከረም 2018 ዓ/ም ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • የሰሞኑ ጉንፋን መሰል በሽታ ከተለመደው የተለየ እንዳልሆነ እና እስከ ታኅሳስ ወር አጋማሽ ሊቆይ እንደሚችል ተገለጸ   ‎ከሰሞኑ ብዙ ሰዎችን እያጋጠመ ያለው ጠንከር ያለ ጉንፋን ከተለመደው በተለየ ቫይረስ እንዳልከሰተና እስከ ታኅሣሥ ወር አጋማሽ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፤ ሕጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን እያጠቃ ያለው ጉንፋን መሰል በሽታ በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት እና ከዚህ ቀደም ከነበሩት ኢንፍሉዌንዛ ቫይረሶች የተለየ እንዳልሆነ  ተናግረዋል። ለቫይረሱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ የፈጠረው መስከረም ወር ሰዎች በብዛት ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱበት፣ በርካታ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩበት እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ ተሳታፊዎች የሚታደሙባቸው የአደባባይ በዓላት የሚከወኑበት በመሆኑ ነው ሲሉ ዶ/ር መሳይ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም፤ የሰዎች የመከላከል አቅም መቀነስ ቫይረሱ ጉልበት እንዲያገኝ እና ሕመሙ እንዲበረታ አድርጎታል ብለዋል። ብሔራዊ የኢንፍሉዌንዛ ማዕከል ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት አዲስ ዓይነት ቫይረስ አለመግባቱን ማረጋገጡን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የቫይረሱ ስርጭት እስከ ታኅሣሥ አጋማሽ ሊዘልቅ እንደሚችል ተናግረዋል። የጤና ሚኒስቴር በቅርቡ ስለ ኢንፍሉዌንዛ እና ሌሎች ጉንፋን መሰል ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰቱ በሽታዎች ሰፋ ያሉ መረጃ እንደሚያቀርብ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ሕብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድ መክረዋል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT

  • #AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ትምህርት ዘመን በመደበኛው የቅድመ ምረቃ መርሐግብር በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃ ትምህርት የመግቢያ መስፈርቶች መሠረት ቅበላ ያገኙ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት፦ ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች መስከረም 22 እና 23/2018 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል፡፡ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆነና ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ቀን መስከረም 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል፡፡ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ➫ የማደሪያ አገልግሎት (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች መስከረም 22 እና 23/2018 ዓ.ም በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡ አጠቃላይ ገለጻ ሰኞ መስከረም 26/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 27/2818 ዓ.ም ይጀመራል፡፡ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • ለመምህራን፦ ውጤትዎን ይመልከቱ! በ2017 ዓ.ም የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና ውጤታቸውን በኦንላይን መመልከት ይችላሉ። https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት TDP Results የሚለውን በመጫንና User Name በማስገባት ውጤት መመልከት ይቻላል። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ 297 ሆኗል በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል።  በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል። በዚህ ውሳኔ መሠረት 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑ ተገልፃል። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • 16 сент. 2025 г.11,2 тыс2517

    #update የተፈጥሮ ሳይንስ የphysics ውጤት ማስተካከያ ተደርጎበታል። ውጤታችሁን ድጋሜ መመልከት ትችላላችሁ። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • 15 сент. 2025 г.12,8 тыс1537

    አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ መመዘኛና መስፈርት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩ ይታወቃል። በመሆኑም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመስከረም 05-09/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው ፖርታል (https://portal.aau.edu.et) አማካኝነት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና የፈተና ማዕከላት በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ መገናኛ ገፆች እና በተቋሙ ይፋዊ ድረገፅ እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለተማሪ ነክ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ @NATIONALEXAMSRESULT

  • 15 сент. 2025 г.11,4 тыс1132

    ውጤት መታየት ጀምሯል። https://result.eaes.et ለተማሪ ነክ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ @NATIONALEXAMSRESULT

  • 15 сент. 2025 г.13 тыс2753

    ውጤት በዚህ ተመልከቱ የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆኑ፡፡ የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች #ዛሬ_ከሰዓት_ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡ ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡ አድራሻዎቹ፡ 1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et 2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot 3.  አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284 (የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት) ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በአዲስ የምዘና ሥርዓት መመዘን ከጀመሩበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2017 ድረስ በጠቅላላው 🎯 3,011,607 ለፈተና ተቀምጠዋል 🎯 የማለፊያ ነጥቡን (50%) ያገኙት 🎯 በጠቅላላው 142,514 ተማሪዎች ወይም 4.7% ብቻ ናቸው 🎯 2,869,093 የሚሆኑት ወይም 95.3 % ተማሪዎች ማለፊያውን ማግኘት አልቻሉም ለተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • ውጤት እስከ ነገ 6 ሰዓት ይፋ ይደረጋል ለተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • #update ዘንድሮ ያገኘነው ውጤት ስንጠብቀው የነበረውን ውጤት ነው። ያሰብነውንም በሙሉ መተማመን እያሳካን እንገኛለን። ለተማሪ ነክ መረጃ ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • ከፍተኛ ተማሪዎችን ያሳለፉ ክልሎች ፦ - አዲስ አበባ፣ - ሐረሪ - አማራ ክልል ናቸው። ዘንድሮ " የተፈታኙ ቁጥር ቀንሷል ያለፈው ተማሪ ቁጥር ግን ጨምሯል " ያሉት ትምህርት ሚኒስትሩ ዘንድሮ በአጠቃላይ 48,929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጸዋል። በጾታ ስብጥር ፦ 30,451 ወንድ ተማሪዎች አልፈዋል። 18,478 ሴት ተማሪ አልፏል። አማካይ ውጤት 87 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች 86 በመቶ ዓለማቀፍ ትምህርት ቤቶች 5.4 በመቶ የመንግስት ትምህርት ቤቶች 51 በመቶ የግል ትምህርት ቤት ውጤት ለተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • #update #ሬሚዲያል የሬሚዲያል መግቢያ ነጥብን ከፍ እያደረግን ቀስ በቀስ ሙሉ በሙሉ ሬሚዲያል የሚባል አካሄድ እናቆማለን። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT

  • #update #ሬሚዲያል የሬሚዲያል መግቢያ ነጥብን ከፍ እያደረግን ቀስ በቀስ ሙሉ በሙሉ ሬሚዲያል የሚባል አካሄድ እናቆማለን። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT