- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 212
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 56
- 1/48двое суток
- 64
- 1/72трое суток
- 69
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
“ገድላቸውንም ለፈጸሙት ብፁዓን የጻድቃን ዋጋቸው፣ የኃጥአን ዕረፍታቸው ፣ የደከሙት ጉልበት፣ የነዳያን ሀብት፣ የንጹሓን መመኪያ፣ ያደፉትም ከርኩሰታቸው የሚነጹብሽ፣ ያዘኑትም የሚጽናኑብሽ፣ ደስ ያላቸው የተድላ ደስታቸው ፍጻሜ ።” ማር አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #orthodoxy
“ በክርስቲያን ሃይማኖት አጽኝኝ። ክርስቲያን አድርጊኝ ። ፣ ክርስቲያን ልባል ምስጋና በክበበ ትስብእት በመንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ክርስቲያን ሁኜ ልገኝ ።” አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #orthodoxy
ጾመ ፍልሰታ መጣችልን...የልጅነታችን 🤲❤😁 ❝ ድንግል ማርያም በአንቺ የምተማመነው በውቅያኖስ እና በጠፈር መካከል ካለው አልማዝ ድንጋይ ከተጠጋ ሰው በላይ ያንቺን መጠጊያነት እመካበታለው!። ለምን?❕ ከአንቺ የተወለደው ለዳንኤል አናብስት ያሰገደ ፥ ለሠለስቱ ደቂቅ እሳት ያጠፋ ፥ ለእስራኤል ባሕር የከፈለ ፥ ለዳዊት ጠላት ያጠፋ ነውና ፣ ምኑን እፈራዋለው?? አውሬ እንዳያስፈራኝ የአናብስቱ ጌታ! እሳትን አልፈራ የእሳቱ ጌታ! ባህርን አልፈራ የባህሩ ጌታ! ከአንቺ ማህጸን ተገኝቶልኝ ምን አይቼ እደነግጣለው።❞ ‒ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #orthodoxy
ይድርስ ለፍቅርትዬ ማዕዶት ፤ ይህንን ደብዳቤ የምፅፍልሽ ለትጋትሽ ፣ ለጽናትሽ ፣ ለብርታትሽ እንዲሁም በፈገግታሽ ውስጥ የሚሰማኝን ታላቅ ደስታ ና ላንች ያለኝ ክብር እና ፍቅር ለመግለጽ ብቻ ነው። እንደ ባለሞያ በሕይወቴ ብዙ የማልረሳቸው እና ሁሌም ከምናቤ የማይሰወሩ ከሕመማቸው ጋር ሲታገሉ የማውቃቸው ብዙ ጀግኖች እና በዚያ በጽኑ ሕሙማን ክፍል በሥራ ያሳለፍኩባቸው እነዚያ እጅግ እረጃጅም ሌሊቶች በቂ ምስክሮች ናቸው። አንች በየቀኑ fight የምታደርጊውን ሕመም እንደባለሞያ በሚገባ እረዳለሁ ። እያንዳንዱ ሕመምሽን እንደ ባለሞያ ፊል አደርገዋል /at least I feel your pain through psychologically/ ብል ማጋነን አይደለም። ለዚህም በየቀኑ የምታገኛቸው የስራ ባልደረቦቸ ምስክር ናቸው፡፡ ስለሆነም በዚህ እጅግ ፈታኝ በሆነው የካንሰር ህመም ውስጥ እያለፍሽ አንቺ ግን ለሁላችንም የብርታት፣ የተስፋና የፈውስ ትልቅ ምልክት ሆነሻል። እናመሰግናለን። በዚህም ስለ አንች በግሌ ኩራት ይሰማኛል። አንችም በዚህ ጥንካሬሽ ልትኮሪ ይገባል። ለብዙዎች መጽናናትን ምክንያት ሆነሻልና። በተጨማሪም በየቀኑ የምታሳይው የጽናት ፈገግታ በወላጆችሽ እና በወዳጆችሽ እንዲሁም በዚህ የሕይወት መንገድ እያለፉ ባሉ በየትኛውም እድሜ ለሚገኙ ጀግኖች ሁሉ ያለ ጥርጥር በአንች ኩራት ይሰማቸዋል። በዚህም በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች ልብ ውስጥ አዲስ ተስፋን እና የህይወት ብርሃንን እንደዘራሽ ፈጽሞ አልጠራጠርም። ልጅነትሽ የጨዋታና የደስታ ጊዜ መሆን ሲገባው ከከባድ ህመም ጋር መታገልሽን ስናይ ልባችን ቢታመምም 😥 የአንቺ አይበገሬነት ግን ሁላችንንም ያበረታል፤ ያጸናል። በድጋሜ ይኼን ሁሉ ዓረፍተነገር የማስረዝመው አንች ለማጽናናት አይደለም። አንቺ ከህመምሽ በላይ ነሽ! የደከሙትን የምታበረች ተስፋ የቆረጡትን የምታነቃቂ እና እውነተኛው ጥንካሬ በትንሽ ሰውነት ውስጥም #ሊኖር እንደሚችል ለመላው ሕዝባችን በታላቅ ጀግንነት ያሳየሽ ብርቱ መምህር ነሽ። በየቀኑ የምታልፊበት እያንዳንዱ ፈተና አልፎ ፤ ሙሉ በሙሉ ተፈውሰሽ፤ በፍቅርና በደስታ ተከበበሽ ህልሞችሽን ሁሉ አሳክተሽ ለማየት ያብቃን። 🙏 እግዚአብሔር የተሟላ ፈውስንና ጤንነትን እንዲሰጥሽ እንማጸናለን። በተረፈ ይኼን ለአፍታ እንኳ እንዳትዘነጊ እያንዳንዷ ቀን ለአንቺ የድል ቀን ናት! ሁልጊዜም ቢሆን በአንቺ እንኮራለን፤ እንወድሻለን! My formula for greatness in a human being is amor fati: that one wants nothing to be different, not forward, not backward, not in all eternity. Not merely bear what is necessary, still less conceal it... but love it. — Nietzsche with regards; Yalewayker / Anesthetist/ #orthodoxy #ማዕዶት🙏❤
ይህ የሐዋርያት እና የነብያት መንገድ ነው። የቀደመችውን መንገድ ተመልከቱ በእርሷም ሂዱባት ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁ" (Look for the ancient paths; walk in them and you will find rest for your souls). ¹Jeremiah, chapter 6, verse 16. ስለዚህች ሃይማኖት እየተጋደላችሁ ትኖሩ ዘንድ ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።" (I felt I had to write and urge you to contend for the faith).² Jude, verse 3. ማንም ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መረዳት ቢፈለግ የያሬድን መንገድ መከተል ግድ ይለዋል ይኼውም « ማየት፣ ማወቅ እና መውደድ (to see, to know, and to love) are a summary of a teaching or an interpretation of Orthodox theological concept). #orthodoxy
ክርስቶስ ስንኖርም ለዘለዓለም እንዳንጠማ የሚያደርግ ለዓለም የተሰጠ የህይወት መጠጥ እርሱ ነው። እንዳንራብ እራሱን ለዓለም የሰጠ የዘለዓለም የሕይወት ምግብ እርሱ ነው። በጎ ብናደርግ የምንወርሰው መንግስታችን እርሱ ነው። ለዘለዓለም የምንጠጋበት የነፍሳችን እረፍት እርሱ ክርስቶስ ነው። ለእኛ ሲል ከሰማያት ሲወርድ ከመላእክት ዝቅ ሲል አለቅነቱን እንደመቀማት አልቆጠረውም። በደሙ ፈሳሽነት የጎሰቆለ ተፈጥሮችን ወደ ቀደመ ክብሩ የመለሰ እርሱ ነው። የአዳምን አምላክ የመሆን መሻት የፈጸመ እርሱ ነው። ይኼንም በገሊላ አውራጃ በምትኖር በአንዲት ድንግል ማህፀን በአደረ ጊዜ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ሲዋሐድ /ሥጋዌ —incarnation / የሔዋን መሻት ተፈጸመ ። የነብያቱን ትንቢት የፈጸመ ፤ የአበውን ተስፋ ፤ የቅዱሳኑን ጸለቶ የተቀበለ እርሱ ክርስቶስ ነው። የሆነው ሁሉ በእርሱ የሆነ ፤ በጥቂቱ እንደ ሰው ያደገ ፤ ከላይ ከሰማይ ያልጎደለ ከታችም ያልተጨመረበት ፤ ከሐዋርያቱ ጋር በታንኳ ሲጓዝ ያንቀላፋ ፤ ማዕበሉን ፀጥ እንዲል ያደረገም እርሱ ነው። ከማርያም የተወለደ እርሱ በቀደመ ልደቱ ከአብ የተወለደውም እርሱ ነው። የመጀመሪያ እና የመጨረሻም እርሱ ነው። ከማርያም በመወለዱም ዘመን የተቆረጠለት እርሱ ነው። የነፍሳችን እረፈት እንወደው ዘንድ ስለ እኛ ደም ግባት የሌለው መድኃኒታችን እርሱ ክርስቶስ ነው። ወንጌላችንም ስብከታችን እርሱ ነው። #ማስያስ #orthodoxy
« ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት? » ብለህ እንዴ ሰሎሞን የምትጠይቀኝ ከሆነ « ወላዲተ አምላክ ማርያም » ብዬ እመልስልኃለሁ። #orthodoxy
ሥጋዌን/ incarnation/ የሰበከው መልአክ ገብርኤል ! ቅዱስ ቂርቆስ እና እናቱን ከእቶን እሳት የታደገውም እርሱ ነው። የነብያቱን የይወርዳል ይወለዳል ስብከት ፍጻሜ /ብስራት/ የነገረን መልአክ ገብርኤል ነው። ለዳንኤል እና ለሠለስቱ ደቂቅም የተላከ እርሱ ነው። እኛን ለማማለድ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ይኼው ቅዱስ መልአክ ገብርኤል ነው። Gabriel is sent to announce the birth of Christ. It is not any angel, but one of the highest rank, who is entrusted with this mission - ክርስቶስን ለመውለድ የምስራች ለማብሰር የተላከው ገብርኤል ነው። ይህንን ተልዕኮ በአደራ የተሰጠው ማንኛውም መልአክ ሳይሆን ከሊቃነ መላእክት መላእክት ለአንዱ ለገብርኤል ነው። — ኦሪገን ዘእስክንድርያ -አርጌንስ Gabriel, who stands in the presence of God, was sent to bring the message of joy to the Virgin, and through her to all mankind ‑ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ገብርኤል ለድንግል ማርያም የምስራቹን መልእክት አመጣ ፤ ይህ የምስራች በእመቤታችን በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ተሰብኳል። — ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታኦማቱርጉስ Gabriel, the pure one, was sent to the pure Virgin. He brought the message of peace, and the world received its Savior - ከንጹኃን አንዱ ገብርኤል ንጽሕት ወደሆነች ድንግል ተላከ ፤ የሰላምንም መልእክት አመጣ ፤ ዓለምም አዳኛዋን ተቀበለች። — ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ #orthodoxy #St.Gabriel #Incarnation
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ለሳምራዊቷ ሴት የተሰጠ ለዘለዓለም የማያስጠማ የሕይወት ውሃ ክርስቶስ ነው። የምንኖረው በእርሱ ነው ፤ የምንወርሰው መንግስታችንም እርሱ ነው። እርሱ በእኛ እኛም በእርሱ እንኖር ዘንድ ቃሉን ከፈጸምን /ሥጋውን ከበላን/ ቃሉን ይፈጽም ዘንድ የታመነ ነው። ፍጹም እውነት እና ሕይወት ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ወንጌላችን እርሱ ነው። ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ ይሁን ወንጌል የለንም። የምናምነው የምንሰብከው ወንጌላችን ፤ የምንሞትለት አምላካችን እርሱ ክርስቶስ ነው። ለሚጠሩት ስሙ ጣፋጭ ፣ ለሚጠጡት ለዘለዓለም የማያስጠማ የሕይወት ውሃ ፣ ለሚበሉት ለዘለዓለም የማያስርብ የሕይወት ምግብ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው። ፍጥረት ሁሉ የሚሰግዱለት የሆነው ሁሉ በእርሱ የሆነ ፤ ከሆነውስ እንኳ አንዳንች እንኳ ያለ እርሱ የሆነ ነገር የሌለ ፤ በሥጋ የተገለጠ ፣ በጥቂቱ ያደገ ፣ ለፍጥረቱ ሁሉ ሕይወትን የሰጠ ፣ አዳምን ከብልየት ያዳነው ፤ በመስቀል በፍቃዱ ስለ እኛ የሞተ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ከእርሱ በቀር ሌላ ስበከት የለም ፤ ከእርሱም በቀር ሌላ ትምህክት የለንም። ወንጌላችን እርሱ ሕይወታችንም አምላካችንም እርሱ ነው። የሕግ ፍጻሜ ፍቅር መሆኑን በሥጋ ተገልጦ በመስቀል ከዚህ የበለጠ ፍቅር ለማንም የለውም የተባለውን የፈጸመ ፤ እንዲሁ የወደደን አምላካችን እርሱ ክርስቶስ ነው። ይኼን ስም ለዓለም ለዘለዓለም እንሰብካለን። #orthodoxy
“ እመቤቴ ማርያም ሆይ ስምሽን ለማመስገን አንደበቴን ዝግጁ አድርጊው። ለሕግሽ ቦታ ዝሬ፣ ለትእዛዝሽ ተግባርም የሚገዛ አድርጊኝ። ልጅሽ ንጉሥ፣ ይቅር ባይ፣ ካህን፣ የበደልን ክብደት የሚያቀል፣ ኃጢአትን የሚያስወግድ፣ የሃይማኖት ውኃን የሚያጣጣና የሕይወት ኅብስትን የሚመግብ ነውና። ዋጋየን የሚከፍል፣ በደሌን የሚያስወግድና ልመናዬን ቸል የማይል ይሆን ዘንድ ስለ እኔ ለምኚው። ለዘለዓለሙ አሜን። ” እንዚራ ስብሐት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #orthodoxy
ይኼን ያደረገ ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ • ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር የተከራከረው ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ይሁዳ 1፥9)፤ • ለሕዝቡ ነጻነትን ይሰጥ ዘንድ ከፋርሱ ንጉሥ ጋር የተከራከረው ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ዳን.10፥13)፤ • የበለዓም አህያ ወደ ፊት እንዳትኼድ የከለከላት፣ በልዓምም ያንን ክፉ ሥራ እንዳይሠራ የከለከለው፣ በለዓም የሚናገረውን ባላወቀ ጊዜ ዲዳይቱን አህያ ጥበብን ሰጥቶ እንድትናገር ያደረጋት ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ዘኁ.22)፤ • የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጠለትና ኢያሱ ወልደ ነዌ ከኢያሪኮ ሰዎች ጋር እንደ ምን መዋጋት እንዳለበት የነገረው ይህ ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ኢያ.5-6)፤ • በአንዲት ሌሊት 185,000 አሦራውያንን የገደለ፣ አሕዛብን በተኙበት ያስቀረ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ኢሳ. 37:36)፤ • ነቢዩ ዕንባቆምን ከአናብስቱ ጋር በጉድጓድ ለነበረው ለዳንኤል በንፋስ ሰረገላ የወሰደውም ቅዱስ ሚካኤል ነውና (ዳን.14:32-42)፡፡ ቅዱሳን መላእክትን ማመስገን የተገባ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግኑታልና፤ ለሰው ልጆች ምሕረት ቸርነትን ያደርግ ዘንድም ይማልዱታልና፡፡ ዳግመኛም አጋንንትን ድል እናደርጋቸው ዘንድ የሚረዱን ናቸውና ቅዱሳን መላእክትን ከፍ ከፍ ማድረግ የተገባ ነው፡፡ — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ከሚካኤል_በቀር_የሚያጸናኝ_የለም #orthodoxy
« አቤቱ አስበኝ በጸራ ወርቅ ምንጭ ወንጌልህን ለማስተማር ደማቸውን ስላፈሰሱ ስለ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ አማላጅነት። » — ማር አባ ጊዮርጊስ #Orthodoxy
#ሐመር! « መነኵሴ የምንኵስናውን ሕግ ንቆ ከገዳሙ ቢወጣ፣ በዚያ ይኖር ዘንድ ወደ ከተማና ወደ ገጠር ቢሄድ፣ በዚያች ውስጥ ባሉት በሕዝባውያን መዓርግ ይኑር። በሕዝባውያን አምሳል እንጂ መነኮሳትን ይመስል ዘንድ አይገባውም። » (ፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 10፥425)። #Orthodoxy
«¹አቤቱ የጆሮየንም መስኮት ክፈት። ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት የሚሰማውን የድንግልን የምስጋናዋን ሹክሹክታ ያደምፅ ዘንድ ። ²አቤቱ ሆይ ያይኔን ጽጋግ ግለጽ ። የብርሃን እናቱ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ምሥጢሩን እመለከት ዘንድ ። ³ዳግመኛም እንደበቴን ክፈት አቤቱ ለእግዚአብሔር እናት እመቤታችን ለድንግልናዋ ምስጋና ። » ማር አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #orthodoxy
ዋሕደ ባሕርይ ወአካል ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስ “ሰው ካራቱ ባሕርያተ ሥጋና ፫ ግብራተ ባሕርይ፣ ለባዊትነት ነባቢትነት ሕያዊትነት ካላት ከነፍስ የተፈጠረ መኾኑ ሳይዘነጋ አንድ ሰው እንዲባል፤ ክርስቶስም ፍጹም ሰው የኾነ ፍጹም አምላክ መኾኑ ሳይዘነጋ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ማለታችን የማይካድ ነው። ይህንም የምንልበት ምክንያት መጻሕፍት በያንቀጹ የመለኮትንና የትስብእትን ተዋሕዶ በነፍስና በሥጋ ተዋሕዶ ከመሰሉ በኋላ ፩ዱ የሚል ቅጽል እንጂ ክልኤቱ የሚል ቅጽል የሚቀጽልለት ባለማግኘታችን ነው። ” #መድሎተ_አሚን #orthodoxy
╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ” (የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ፡፡ ╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ። #orthodoxy
ማር አባ ጊዮርጊስ ለንስጥሮስ እና ለመሰሉ ከጻፉት ....ለዛሬዎቹ «.... እኔስ የእግዚአብሔር ትዕግሥቱን አደንቃለሁ፣ ይህንን በተናገርህ ጊዜ የረገጥሀት ምድር ትውጥህ ዘንድ እንደምን አልተቀደደችም ይህንን በተናገርህ ጊዜ ይጫኑህ ዘንድ ሰማያት እንዴት አልፈረሱም የተራሮች መሠረቶችስ እንዴት አልተነዋወጡም። የገሃነም ውኆች እንዴት አልፈሉም የሲኦልስ ምንጮች ያሰጥሙህ ዘንድ እንዴት አልወጡም፡ የመብረቆች መገለባበጥ እንዴት ዝም አሉ እንዴትስ አላቃጠሉህም የእሳት ሰይፎችስ አንተን ለመቆራረጥ እንደምን አልተመዘዙም። የቤተክርስቲያን ጠባቂ ሚካኤል ይህን በተናገርህ ጊዜ እንዴት ዝም አለ። ማርያም መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይፀልልሻል ካንቺም የሚወለደው ቅዱስ ነው የልዑል ልጅ ይባላል ያላትን የምስራቹን ያሳበልህበት ገብርኤል እንደምን ዝም አለህ አንተ ግን በባሕርይህ ወደ ዘር ትውልድ መለስኸው ትውልድህ ከምድር ላይ ትነቀል ስምህም ከሕይወት መጽሐፍ ይፋቅ። መዝ፻፰፥፲፬ ሉቃ፩፥፴፬.. ይህ ርግማን ላንተ ለብቻህ አይደለም በሃይማኖትህ ለሚያምኑት ሁሉ ነው እንጂ....» #orthodoxy
#ጰራቅሊጦስ!! • ጰራቅሊጦስ አሸናፊ ነው ለሰማዕታት መመኪያ የተሰበሩትን የሚጠግን ነው ። • ጰራቅሊጦስ ፍጹም የከበረ የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወት ነው ። • ጰራቅሊጦስ መጉደል ወይም መጨመር ሳይኖርበት በህልውናውአምላክነው ። • ጰራቅሊጦስ እንደ አብና እንደ ወልድ በሰማየ ሰማያት በምድርም ሁሉ ላይ መንግሥቱ የመላ ነው ። • ጰራቅሊጦስ የማይዳሰስ የእሳት ነበልባል ነው ። • ጰራቅሊጦስ የነፍስና የሥጋ ጽንዕ ነው ። • ጰራቅሊጦስ የወርቅ ሐር ግምጃ የቅዱሳን የጌጣቸው ልብስ ነው ። • ጰራቅሊጦስ የጻድቃን የባለሟልነታቸው የራስ ወርቅ ነው ። • ጰራቅሊጦስ የምሥራችን በመያዝ ከኢየሩሳሌም ወደ ፋርስ የተላከ ንስረ ትንቢት ነው ። • ጰራቅሊጦስ በጽዮን አደባባይ በቶማስ ላይ በቅዱሱ ነቢይ ፊት የበራ ነው ። • ጰራቅሊጦስ ሐዲስ ወንጌልን ያስተምር ዘንድ ጳውሎስን የጠቀሱ የሕይወት መብረቅ ነው ። • ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን የወይን ጠጅ ሳይጠጡ ያሰከረ ነው • ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ያናገረ ነው ። •ጰራቅሊጦስ ፤ ቅድስት ለምሆትን ሦስተነቱ እንሰግድ ዘንድ ያስተምረናል ይመክረናል ። // ሰይፈ ሥላሴ // #orthodoxy
በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር የሚወጣባቸውን ካድራል ህንጻ ያላቸውን አብያተክርስቲያናት ለመዝረፍ ብቻ የሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት ይኼን ሕዝብ ከዘረፈ ብዙ ጥፋት ሊታደጉ አይችሉም። #አይጸልዩም የተሸኸሙት ሥጋ ለሰዓታት አያስቆምም ፤ #አያዝኑም ብሔራቸው የሚየዘርፉት ገንዘብ ና ያላቸው ያልተገደበ ሥልጣን ያን አይፈቅድላቸውም። #መገሰጽ አይችሉም መለካውያን ናቸው ፤ ለተሾሙለት ብቻ የሚሰሩ አረማውያን ስለሆኑ። #ለእውነት አይኖሩም ፈሪዎች ናቸው። እግዚአብሔርን ይጠሩታል እንጅ አያምኑትም። ስለነዚህ ቁራዎች ሲባል ከእግዚአብሔር ና ከቅድስቲቱ ቤተ ክርስቲያን እንድንርቅ አደረጉን። በቃ መባል ያለባቸው ባለ ጥቁር ካባ ገዳዮቹ ናቸው። እነዚህ ለመንጋው አረመኔዎች ...Of all bad men religious bad men are the worst እንዲል ሊዊስ!😥 #Arsi #Oromia #Ethiopia #Orthodox #Amhara😥😭
« የቤትህ ቅናት በልታኛለችና የሚላገዱህ መላገድ በላዬ ወደቀ። (መዝሙር ፷፱ :፱)» የሚለውን የነብዩን ቃል አፈ-በረከት አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ አርጋኖን እንደሚከተለው ተርጉሞታል። “ነቢዩ እንግዲህ አንቺን የእግዚአብሔር ቤት አለሽ የሚላገዱህ መላገድ በላዬ ወደቀ ያለውም የአይሁድ ተናግሮት ነው። ሰይጣን ካስተማራቸው ምቀኝነት የተነሣ በእግዚአብሔር ልጅ ላይ የተናገሩት ስድብ ነው። የዮሴፍ ልጅ ነው ሲሉ። (ሜቴ ፣ ፲፫ ፣ ፶፭ ). በናዝራዊው በልጅሽ ላይ የአይሁድን ልቡና ስላከፋበት ቀናሁ። የዓለም መድኃኒት ርሱን እንዲገድሉ ስላስጨከናቸው ቀናሁ። ስላንቺም ስድብ ስለ ልጅሽም ቀናሁ። በድንግልናሽ ላይ የስድብ ነገር ስለ ተናገረ ቀናሁ። መንፈሳዊውንም ፅንስሽን ስላሳበለ ቀናሁ ። በድንግልና መውለድሽንም ስለሰደበ ቀናሁ።” #Orthodoxy