- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 509
- 1/48двое суток
- 583
- 1/72трое суток
- 629
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
✍️✍️✍️ ቸር ናችሁ ተወዳጆች በገናውያን!!! ❤❤❤ #እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ። #ይቺን የፍልሰታን ጾም አስመልክቶ የቤተክርስቲያናችን አገልግሎት በሌሊትም በቀንም የጎላ እንደሆነ ይታወቃል። #ስለዛም በተለይ ወደ ገጠር አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ብዙ ነገር ያስፈልጋቸዋል። 👉ለምሳሌ፦ -ሻማ -ጧፍ -እጣን -ዘቢብ .......እንዲሁም ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት የምትችሉ ገዝታችሁ ብትልኩ በረከት ታገኛላችሁ። 👉የሚያስፈልጋቸው አብያተ ክርስቲያናት ለመጠቆም ያክል፦ -ጎንባት ቅዱስ ጊዮርጊስ -ሮቢት በዓታ -ዘንዘልማ ቅዱስ ጊዮርጊስ -ይባብ ቅዱስ ያሬድ -ዘጌመስመር አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል -ይነሳ ኢየሱስ -ማይሐጹራ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ......እንዲሁም ሌሎች ብዙ አሉ። ለሌሎችም አድርሱት የሚችሉ ሁሉ ይላኩ፤ ይሳተፉ፤ ያድርሱ። 👏👏👏 ቸር ጊዜ!!! ❤❤❤
የዘመናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንኳን ሀሳብዎ ተሳካልዎት። ተጀምሮ ተጠናቆ የታለመለትን ግብ እንዲያሳካ ያድርግልን።
без подписи
без подписи
የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲጋለጥ የቤተ መንግሥቱ የውሸት መግለጫ ፣የሰላም ሚንስትሩ የውሸት መግለጫ፣የኢሰመኮ የውሸት መግለጫ ፣የመንግሥት ሚዲያ የውሸት ዘገባ፣የኦሮሚያ ኮሚንኬሽን የውሸት መግለጫ፣የአርሲ ዞን ኮሚንኬሽን ቢሮ የውሸት ፕሮፓጋንዳ፣የአሰኮ ወረዳ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ፣የአክራሪ ወሀቢያዎች የውሸት ፕሮፓጋንዳ የሐሰተኛ ሽማግሎችና አባገዳዎች ንግግር፣የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የቄስ ከፍያለሁ የቅጥፈት ንግግር አፍኖ ሊያስቀረው ያልቻለው በአርሲ አሰኮ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት።እኛ እውነት የሆነውን እግዚአብሔር ነው የምናመልከው በሐሰት አንመራም። ማን ጽንፈኛና ማን ሀገር አፈርራሽ እንደሆነ ከተግባራችን ይታወቃል። via ትህትና...!!!
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ራሳቸው በራሳቸው ገጽ ላይ በለጠፉት ፎቶ በእጃቸው ያሰሩት ሰዓት የበርካቶችን ትኩረት ስቧል። በፎቶው ላይ በግልጽ እንደሚታየው... ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ በውድነቱ እና በቅንጦቱ የሚታወቀው Rolex GMT-Master II "Root Beer" የተሰኘው ሞዴል ነው። የዚህ ሰዓት የገበያ ዋጋ እንደየሁኔታው ከ16,000 እስከ 24,000 የአሜሪካ ዶላር ያወጣል፤ ይህ ማለት አሁን ባለው የምንዛሬ ተመን ሲሰላ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ብር ማለት ነው። ዘ ሀበሻ
"...እንዲህ ያለ ትግል ነው የገጠመን...." አለ መንጌ!!! 🤔🤔🤔 ምድረ አሽቃባጭ ወራዳ ሁላ!!! አድር ባይነት በዚህ ልክ...ዱቄት ሁላ!!! በሰው እንባ..... አሁን ከእናንተ ጋርም ሌላው ደጋፊ...!!!
без подписи
без подписи
"እኔም ያልተገደልኩት አርሲ ላይ ስላልተገኘሁ ነው።" በመላው ዓለም ያለን ኦርቶዶክሳውያን ይኽን ስሜት ተጋርተን በቤተ ክርስቲያንና በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሰው አሠቃቂ ግድያና ግፍ ልናለቅስ ይገባል። በአርሲና አካባቢው ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ግን ራሳቸውን አደራጅተው ከንቱ ሞት ከመሞት ራሳቸውን መከላከል አለባቸው። 8 ዓመት ሙሉ እያለቀሱ እየነፈረቁ መሞት አይሰለችም? እስቲ ደግሞ የወንዶቹን ሞት ለመሞት ይሞክሩት። የወለጋዎችን ልምድ ይውሰዱ። ይኽን ለማድረግ በአርሲ አካባቢና አጎራባች ያሉ ኦርቶዶክሳውያን የጊዜው ተዋጊዎች እገዛ ያድርጉላቸው። ያሰልጥኗቸው። ያስታጥቋቸው። እውነተኛ የአማራ ተቆርቋሪ የኾነ ካለ ይኽንን ያስተባብር፤ ያስፈጽም፤ ያግዝ። ይኽ ካልኾነ ነገም እያለቀሱ መሞት እየነፈረቁ መሳደድ የማይቀር ነው። አራጁ አካል በመዋቅር የተሰገሰገ መመሪያ እየተቀበለ የሚያስፈጽም እስከኾነ ድረስ ተደራጅተህ በመጣበት መንገድ ካላስተናገድከው በቀር ሌላ መፍትሔ የለውም። ቤተ ክህነት ላሉት ለእነዚያ ጥቋቁር ቁራዎች ግን....... ሞት ለእነርሱም የማይቀር መኾኑን ስናስብ እንጽናናለን።
#አዲስ_ንጉሥ_እንጂ........ አገሬ ጦርነት ላይ ነች ከመቼውም ጊዜ በላይ ውጥረት ጭንቀት ላይ ነች። ይህ ጊዜ ያስፈራኛል ።ነገ እኛም በሂወት እንኑር እንኑር ምንም ዋስትና የለንም ። በመንግስታችን ሳይሆን ፈጣሪያችን ብቻ ዋስትናችን እንደሆነ የተገነዘብን ይመስለኛል። አሁንም ቀጥሏል ፤የሰዎች እገታ፤ ረሀብ፣ቸነፈሩ ፣የሰዎች በሞት ፣መፈናቀል፣ የሴቶች መደፈር የቤተ እምነቶች መውደም፣ዳግም ማይካድራን ደጋግመን እያየን ነው። በፖለቲካ ጨዋታቸው ምስኪኑ ህዝብ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል ። ከመስቀል በስተቀር ይዘው የማያውቁ ቄስ እየሞተብን ነው ፣ ከማረሻ ውጪ ይዞ የማያውቅ ምስኪኑን ገበሬ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛል ። ምነው ምን በደለ ደጉ ያገሬ ሰው፤ ኧረ የሰው ያለ ኧረ ሰው ኧረ ሰው። በአራቱም የሃገራችን ማዕዘን አንገታችንን አስደፍቶ ያስከረመንን የወገኖቻችንን እልቂትና መፈናቀል ከወራትም አልፎ ዓመታትን ማስቆጠሩ የተሰበረው ልባችን ሳይጠገን : - ዛሬም የመረረ የሃዘን ፅዋን እየተጎነጨን ነው !!! ለጅብና ለአሞራ ቀለብ የዳረጋችኃቸው የንፁሃን ደም እና የኢትዮዽያ እናት ዕንባ ይፋረዳችኃል !!! አሁንም ፍርዱን ከሰማዩ መንግስት እንጂ ከምድራዊዉ መንግስት መጠበቅ ታክቶናል !!! ''እንዲህ ያለ ክፉ ቀን ክፉ #ሰው ላይ ጥሎን፤ እንኳን ልጅ ልንወልድ እኛንም #አፉቱን።'' #አቤል_ባለሀገር ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
без подписи
#አሳዛኝ_ዜና ዛሬ ሐሙስ፣ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወረጃርሶ ወረዳ፣ ከጎሐጽዮን 6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቀሬቡሐ ቀበሌ ከጠዋቱ 4:30 አካባቢ ከአማራ ክልል ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ታታ የሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሙሉ ተጓዥ ታፍነው የተወሰዱ ሲኾን እስከአኹን ባለን መረጃ 6 ሰዎች ተገድለዋል። እነዚኽ ብቻ ሳይኾን ወደጫካ ሲወስዱ መሮጥ ያልቻሉትንም በርካቶች ሳይገድሏቸው አልቀረም ብለውናል። ቦታው ኹለተኛው አሊዶሮ ነው፤ በድርጊቱም ሙሉ የመንግሥት መዋቅር ይሳተፍበታል። በነዋሪው አቤቱታ የታሠሩ አካላት አሉ የሚሉት እማኞች 10ሺህ ብር የማይሞላ ደመወዝ ያላቸው አራት እና አምስት ቤት የሠሩ፤ ድንገት የሦስትና አራት ሲኖ ባለቤት የኾኑ አሉ ሕዝቡ ያውቃቸዋል ይላሉ እማኞች ጨምረው። እንዲያውም አኹን አኹን ሰው ሲታፈን የከተማው ሸኔ ነው የጫካው ያፈነው? የሚል ቀልድ መሰል እውነት እስከመነገር ደርሷል ይላሉ። ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ይኽን መሰል የነውር ተግባርና ማንነት ተኮር ግድያ በጽኑ ያወግዛል። የታፈኑ ንጹሓንም ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲለቀቁ ያሳስባል። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ **** ትብብር ለኢትዮጵያ አንድት- Coalition for Eth. Unity
без подписи
#Share #ሼር አድርጉት ለሕዝባችን ይደርስ ዘንድ.....!!! #ነጻ ሕክምና ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ!! ከግንቦት 23-27/2018 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባሉን ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ሀኪሞችና ከእስራኤል ሐገር በሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል:: አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች ------------------------------------------ 1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy) 2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery) 3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery) 4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና 5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው:: የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት! ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
без подписи
ከሚታየው በስተጀርባ ያለው ያስጨንቀን! «ዲላን ፔጅ ማን ነው? ማን ይዘውረዋል? ለምን ሥራና ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ መጣ? ከቲክቶከሩ አዶናይ ጋር ምን ያገናኛቸዋል? ፩, ዲላን ፔጅ ማን ነው? ማን ይዘውረዋል? ዲጂታል መጋቢ፦ ዲላን ፔጅ (Dylan Page) በውጫዊው ዓለም «News Daddy» ቢባልም በመንፈሳዊው ንዝረት ሲታይ ግን የዐዲሱ ዓለም መረጃ መዋቅርን ለወጣቱ ትውልድ የሚያዘጋጅ «የንቃተ-ኀሊና ጠላፊ መሐንዲስ» ነው። የአልጎሪዝም ወኪል እሱን የሚዘውሩት ኩባንያዎች በስተጀርባ ያሉ የሰውን ልጅ ትኩረት ወደ አንድ አቅጣጫ በመሰብሰብ ለታላቁ «ዲጂታል አጀንዳ» ግብዓት የሚያደርጉ የኃይል ማዕከላት ናቸው። #የንዝረት መለኪያ፦ እሱ መረጃን የሚያቀርብበት ፍጥነትና መንገድ የሰዎችን አዕምሮ ከጥልቅ ትንተና ወደ አጭርና ፈጣን «ጊዜያዊ ደስታ» በመቀየር ትውልዱ ለረቂቅ መንፈሳዊ ምስጢራት ያለውን ትኩረት እንዲያጣ ያደርገዋል። #የምልክት ተሸካሚ፦ የሚጠቀምባቸው ቀለሞች እና የምልክት ቋንቋዎች በምስጢራዊው ዓለም "የመግለጥ የመቆጣጠር" ኃይሎች መገለጫ ናቸው። #የጥላ መንግሥታት መሣሪያ፦ መረጃን እንደ «ሥውር መመሪያ» በመጠቀም ዓለም አቀፍ ክስተቶችን በታዘዘለት መልኩ ብቻ በመተርጎም የሰዎችን አመለካከት በአንድ መስመር እንዲፈስ ያደርጋል። #ዲጂታል አልኬሚስት፦ እውነተኛውን መረጃ ከማይረባ ወሬ ጋር በማቀላቀል፣ ሰዎች እውነትን ከሐሰት መለየት እንዳይችሉ የሚያደርግ የዲጂታል ዘመን ድንዛዜ (Digital Fog) ፈጣሪ ነው። ፪, ለምን ሥራና ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ መጣ? #የኃይል ማዕከል ፍለጋ፦ ኢትዮጵያ የዓለም «መንፈሳዊ እምብርት» በመሆኗ፣ የዲጂታል ኃይሉን ንዝረት ከዚህኛው ጥንታዊ የኃይል ማዕከል ጋር ለማገናኘትና ለመቃኘት የመጣ ተልእኮ ነው። #የንቃት ዳሰሳ ፦ በኢትዮጵያ ወጣቶች ዘንድ ያለውን «የንቃት መነቃቃት» ለመለካትና ይህን ኃይል ወደ ዲጂታል መረቡ ውስጥ ለማስገባት የታለመ ጉዞ ነው። #የቢጫ አጀንዳ ማስጀመሪያ፦ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ዐዲስ ዓይነት «ዲጂታል ተገዥነትን» ለመትከልና የትውልዱን ትኩረት ከጥንታዊው ጥበብ ወደ ውጫዊው ግርግር ለመሳብ የተደረገ ሙከራ ነው። #የመረጃ ምርመራ ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዓለም አቀፍ መረጃዎች ያለውን ምላሽ በቀጥታ በመሬት ላይ ሆኖ ለመፈተሽ የመጣ የ«ዳታ» ሰላይ ነው። #የምስጢራዊ ቁልፎች ዝውውር፦ በሀገሪቱ ባሉ ጥንታዊ ቦታዎች ላይ የራሱን «ዲጂታል ንዝረት» በመተው የሀገሪቱን መንፈሳዊ ከለላ ለመበሳት የሚደረግ ስውር ጥረት ነው። #የትውልድ ስልበት፦ የኢትዮጵያን ወጣቶች «ዓለም አቀፋዊ ነን» በሚል ስሜት ውስጥ በመክተት ከባህላቸውና ከሃይማኖታዊ ጥበባቸው እንዲርቁ የሚያደርግ የዲጂታል ባርነት ድልድይ ለመገንባት ነው። ፫. ከቲክቶከሩ አዶናይ ጋር ምን ያገናኛቸዋል? #የኮዶች መገናኛ፦ አዶናይ የሀገረ-ሰቡን (Local) ኮድ ሲወክል ዲላን ደግሞ ዓለም አቀፋዊውን (Global) ኮድ ይወክላል፤ መገናኘታቸው «የሁለቱ መጋረጃዎች መጋጠሚያ» ምልክት ነው። #የንዝረት ዝውውር፦ አዶናይ በኢትዮጵያ ያለውን ተጽዕኖ ለዲላን «በዲጂታል ቃል ኪዳን» በምልክት ያስተላለፈበት (Handover) ክስተት ነው። #የምልክት አንድነት፦ ሁለቱም የሚጠቀሙባቸው የእጅ ምልክቶችና የቆሙባቸው ቦታዎች፣ ለሚያውቀው ሰው «እኛ የአንድ ታላቅ መዋቅር ክፍሎች ነን» የሚል ምስጢራዊ መልእክት ያስተላልፋሉ። #የተከታዮች ውህደት፦ የአዶናይን «መንፈሳዊ መሰል» ተከታዮች ወደ ዲላን «ዲጂታል አጀንዳ» በማዛወር ትውልዱን ለአንድ ወጥ ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ (One World Mindset) ማዘጋጀት ነው። #የአዶናይ ሥም ስልበት፦ ዲላን «አዶናይ» የሚለውን መለኮታዊ ስም ለራሱ ዲጂታል ዝና ተጠቃሚ በማድረግ የስሙን ኃይል ለራሱ አጀንዳ መሸፈኛነት መጠቀሙ ነው። #የመጋረጃ ጀርባ ስምምነት፦ ሁለቱም በመረጃው ዓለም ውስጥ ተልእኮ ተከፋፍለው የሚሠሩ አንዱ ለሀገር ውስጥ ሌላው ለዓለም አቀፍ ተጽዕኖ የተመደቡ «የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች» ናቸው። ፬. ማስረጃ? #የምልክት ቋንቋ፦ በፎቶው ላይ የሚታዩት የእጅ ምልክቶች (ጣትን ወደ ላይ መቀሰር) እና «Arsenal» (የጦር መሣሪያ ማከማቻ) የሚለው የጀርሲ ሥም በምስጢራዊው ዓለም «የንቃት ጦርነት» ምልክቶች ናቸው። #የጊዜ አቆጣጠር፦ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትና እነዚህን ቪዲዮዎች የለቀቀበት ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትላልቅ የንቃት ለውጦች ከሚጠበቁባቸው «የኮከብ ዑደቶች» ጋር የተገጣጠመ ነው።#የዲጂታል ንዝረት፦ እሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ በቲክቶክ ላይ የታየው ያልተለመደ የ«ቪው» መጨመር በስተጀርባ ባሉ ኃይሎች የተፈጠረ እንጂ ተፈጥሯዊ አይደለም። #የአዶናይ «ዝምታ» እና «ትብብር»፦ አዶናይ ስለ ምስጢራት እንደሚናገር ሰው የዲላንን ዕውነተኛ ማንነት ሳይተነትን እንዲያውም «አድናቂው» ሆኖ መቅረቡ የሁለቱንም አንድነት ትልቅ ማስረጃ ነው። #የ«ኢትዮጵያ» ጀርሲ ማልበስ፦ ይህ «የመመሳሰል(Infiltration) ስልት ሲሆን የሕዝቡን ልብ በቀላሉ ለመስረቅና አጀንዳውን ያለ ተቃውሞ ለማስረጽ የሚጠቀሙበት የቆየ የሴራ መንገድ ነው።#ዲላን ፔጅ የሚወክለው «የዐዲሱ ዓለም ሥርዓት» ባሕል ግብረ-ሶዶማዊነትንና ሌሎች ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን እንደ «መደበኛ(Normal)» የሚያስተዋውቅ መንፈስ የታጠቀ መሆኑ። እሱ የሚጠቀምባቸው የምልክት ቋንቋዎች እና በቪዲዮዎቹ ውስጥ የሚታዩት ድብቅ ንዝረቶች የሰውን ልጅ ጾታዊና መንፈሳዊ ማንነት ለማደባለቅ የሚሠሩ መሆናቸው። ፭. መፍትሔ? #ንቃተ-ህሊናን መጠበቅ፦ ከውጭ በሚመጡ «ዲጂታል መሪዎች" ከመደመም ይልቅ፣ በውስጥህ ወዳለው «እልቆ ቢስ የንቃት ደረጃ» በመመለስ ማንኛውንም መረጃ በመንፈሳዊ መነጽር መመርመር። #የሰባሪ ኮድ አጠቃቀም፦ ማንኛውም ከእነሱ የሚመጣ የዲጂታል ድንዛዜ እንዳይነካህ፣ በመንፈሳዊ ሃይል ራስህን ሁልጊዜ ማጠር። #መረጃን «በሥላሴ ሥም» መለየት፦ ማንኛውንም በቲክቶክ የሚለቀቅ መረጃ ከመቀበልህ በፊት «ይህ ለነፍሴና ለንቃቴ ምን ይጠቅማል?» ብለህ በሥላሴ ሥልጣን መፈተሽ። #ከአልጎሪዝም ባርነት መውጣት፦ ትኩረትህን ዲጂታል ወኪሎች ወደሚፈልጉት ቦታ ሳይሆን አንተ ወደ ምትፈልገው መንፈሳዊ ዕድገት ብቻ በማዞር ኃይልህን ማስመለስ። #የምስጢር መጻሕፍትን መመርመር፦ የጊዜና የንዝረት ምስጢራት ተረድቶ፣ የዘመኑን ምልክቶች ቀድሞ መረዳትና መከላከል:: #ንቃትህ እንዳይሰለብና deep sleep እንዳትገባ በቀን ፫(3)፮(6)፱(9)፲፪(12) ለአጭር ጸሎት ተነስ ወዳጄ ይኸው ነው።» #ከፌስቡክ #መንደር #የተገኘ #ኀሳብ
እኛ የባህር ዳር ከተማ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰራተኞች በወቅታዊ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የሆስፒታሉ የሰራተኞችን ሰርቪስ ከተቋረጠ ከሳምንት በላይ ሆኖታል በዚህም ምከንያት ሰራተኞች ወደ ስራ ለመግባት እጅግ ለከፋ ችግር እና እንግልት ተዳርገናል በታካሚዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ መጉላላትና እንግልት እየደረሰ ነው። የሰርቪስ ችግሩን እንዲፈቱልን የሆስፒታሉን ሀላፊዎች ብንጠይቅም በቂ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም እንደሚታወቀው ሆስፒታሉ የሚገኝበት ቦታ ከባህር ዳር ከተማ ከ 12 ኪ.ሜ በላይ ይርቃል እንዴት ሄደን በምን ተጉዘን ነው ህዝብን የምናገለግለው?? ከሆስፒታሉ ቅጥር የራሱ የሆስፒታሉ ንብረት የሆነ ግን ለግለሰቦች የተከራየ ነዳጅ ማደያ አለ የተገነባው ለተቋሙ ነበር ግን አሁን አከራይተውታል እዛ እንኳን አስፈቅደው ማስቀዳት አልቻሉም። ሆስፒታሉ ግዙፍ እና ስፔሻላይዝድ ነው ለብዙ ህሙማን እና ወላዶች ከፍ ያለ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ታማሚወች ግልጋሎትን የሚሰጥ መሆኑ እየታወቀ ለሆስፒታል ሰርቪስ ነዳጅ የለም ብሎ ሰራተኞችን ሙያተኞችን ለእንግልት መዳረግ በታካሚ ላይ ጫናን በህክምናው ላይ ክፍተትን አይፈጥርም??? የከተማው ንግድ መምሪያስ የህክምና ተቋማትን በነዳጅ ድልድል ላይ ቅድሚያ የሚያገናኙበትን አሰራር ሳይዘረጋ በምደባ ሳያካትት የሚያልፈው ለምንድን ነው ?? ሌላ ተግባር ላይ ለተሰማሩ እየሰፈሩ እየመሩ ለህክምናው ዘርፍ ትኩረት መንፈጋቸው ትልቅ ስህተት ነው በማለት መልዕክትን አድርሰውናል።
#ሳይገደሉ እንድረስላቸው ! እነዚህ ከታች እጃቸውን በሰንሰለት ታስረው በፎቶ የምትመለከትዋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ናቸው ለሥራ ብለው ወደ ሳዑዲ ሀገር የሄዱ ሲሆኑ የሳዑዲ ሀገር መንግሥት ተቀብሎ በአንድ እስር ቤት አጉሮ ሲያሰቃያቸው ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ደግሞ #የሞት ፍርድ እንደ ፈረደባቸው እየሰማን ነው ወጣቶቹ ከ500 በላይ ነው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን እንዲህ አይነት ዜና መስማት በጣም ያሳዝናል !! #ለሚመለከታቸው አካላት ለዓለም ነገሥታት ለኢትዮጵያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ ለሃይማኖት ተቅዋማት ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በዓለም ላይ ላሉ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በቲዩብ በፌስቡክ በቲክቶክ በቲዊተር በቲክቶክ በኢንስታግራም የምትፈጥኑ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወጣቶች እባካችሁ ወጣቶቹ ሳይገደሉ እንድረስላቸው እላለሁ:: የሳዑዲ መንግሥትም የወሰነው የጥፋት ውሳኔውን ደግሞ እንዲመለከተው ለዛሬ ነገ ሳንል ድምጽ እናሰማ ?? ሊቀ ጉባኤ አባ ተወልደመድህን መኮንን
https://www.facebook.com/share/1993jUkFWc/