tgindex
Sankofa_Readers_Association

Sankofa_Readers_Association

Статистика
@sankofabooksКнигианглийский

Read, Change, Share እናንብብ፤ እንለወጥ፤ እናካፍል ፡ This is the channel of sankofa readers association working with the motive "reading leads to change then to nearest perfection in doing art."comment is welcomed Contact: @Poco_L0c0 @markrylos https://t.me/sankofab

Последний пост
31 мая
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
35
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 314
−2 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 391
35 постов
Вовлечённость
105,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 35
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 31 мая821343

    🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ሳንኮፋ የአንባብያን ማህበር ትናንት በደረሰው ታላቅ ሀዘን ህይወታቸው ላለፉት ወንድሞቻችን እና በህክምና ላይ ስላሉት ሁሉ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መፅናናትን ለነብሳቸውም አፀደገነትን እንመኛለን። የተቀረነው ተማሪዎችም ራሳችንን እንጠብቅ ! 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

  • 21 мая964201

    ሳንኮፋ፣ አንድ ደሴት፣ ብዙ ትዝታ!!

  • 30 апр.1 23671

    #የመጽሐፍ ውይይት (Book discussion) መጽሐፍ: ባሕራን ቀን: ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ቦታ: አዲስ አበባ፣ ቦሌ ሩዋንዳ (Taste of Nardi) ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ https://vt.tiktok.com/ZS9PF8shP/ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

  • 15 апр.1 1307

    መጽሐፍትን ለግሱን🙏🙏 https://vt.tiktok.com/ZSHnd1H3q/

  • 8 апр.1 16069

    📚ርዕስ:- ዳኛው ማነው 📝ደራሲ:- ታደለች ኃ/ሚካኤል 📜ዘውግ:- የብርሃነ መስቀል እና የታደለች ሕይወት በኢሕአፓ የትግል ታሪክ 📖የገፅ ብዛት:- 442 📅ዓ.ም:- 2012

  • видео или голосовое, без подписи

  • This movie presents medical and ethical dilemmas, including a debate over euthanasia. The film will give a good motivation, and a chance to re-think about some closed topics. 👨‍⚕️👨‍⚕️👩‍⚕️👩‍⚕️👨‍⚕️👨‍⚕️👩‍⚕️👩‍⚕️ "Dr. John"ን የኮርያ ፊልም አድናቂ ለሆናችሁ የጤና ተማሪዎች ልጋብዛችሁ። ፊልሙ የሚያጠነጥነው ያልኖረውን ህመም ተረድቶ Palliative care ላይ በሚሰራ፤ በእውቀቱና በስራውም እጅግ የተደነቀ ዶ/ር የስራ እና የፍቅር ህይወት ላይ ነው። በፊልሙ ውስጥ በኛ ሀገር የማይደፈረውን "euthanasia" ፣ ህመም ያለማወቅ ምንነትን እንዲሁም ጥሩ ተነሳሽነትንም ስለምታነገኙበት ተጋበዙልኝ።

  • https://vm.tiktok.com/ZMAmX1Q8W/

  • видео или голосовое, без подписи

  • የሳንኮፋን የቲክቶክ ገፅ ይከተሉ ለጓደኛዎትም ሼር ይበሉ @sankofa.readers.a Sankofa readers association ላይክ ኮሜንት ማረግ ሳይዘነጉ ሳንኮፋን ዝነኛና ሀብታም ያድርጉ https://vm.tiktok.com/ZMAUKwmME/

  • Let's feel alive! Let's celebrate our dedicated souls for the respected human lifes! Let's  celebrate 🥂 our brave choices to be health students ! Cheers 🥂 Today Saturday night in front of students Union office. Every student is invited! (there will be fun games and a chance to communicate with real health students 🥰)

  • видео или голосовое, без подписи

  • የሰከነች ቡና ☕ በብዙ በተወደደጅበትና በታወቀችበት ሰዓት ከሰው አይን ጠፋች እና ሰከን ያለ ኑሮዋን እየኖረች፣ የምትወደውን ሙዚቃም ካለማንም የሀሳብ ጫና ድንገት በዓመታቶች ብቅ እያለች ለወዳጆቿ ማስደመጥን ቀጠለች። አንዳንዴ ያለንበት system የሚፈልገውና የልባችን ሀሳብ ወዲና ወዲያ ይሆናሉ። ልባችን ላይ ያለውን ትተን ሌሎች በፈለጉበትና ባሰመሩት ብንጓዝ ደግሞ በዓለም አትርፈን ከነፍስያችን ግን እንጎላለን። ብቻ ይህቺ ሴት እውቅናን፣ ገንዘብን ትታ ራሷን መርጣ በጥቂቱ መሸሸግን የመረጠች ሆነች። ለምታውቋት የሰከነች ቡናችን ወ/ሮ Lauryn Hill አዲስ አበባ ገብታለች ፣ ለማታውቋት ፣ሙዚቃ፣ ጠለቅ ያለ ግጥም እና ውብ ድምጽ አጀብ የሚያሰኛችሁ ከሆነ ደግሞ እስቲ በበይነ መረባችሁ ሙዚቃዎቿን አድምጡትማ። የሚያውቋት አብዝተው የሚወዱላትን "Tell him" ን ደግሞ እኛው እንጋብዛችሁ Peace✌

  • 🎉🌼እንቁጣጣሽ🌼🎉 የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት "እንቁጣጣሽ" ...... መስከረም ሲጠባ ፤ ምድር በአደይ አበባ ታጅባ ፤ ፀሐይ ከቦታዋ ስትገባ ፤ "የጎመን ድስት ይውጣ የገንፎ ድስት ይግባ "...."እዮሃ አበባ መስከረም ሲጠባ🌼" እየተባለ በዜማ ሲታወጅ ፤ አበባ የመሰሉ ህፃናት አበባን ይዘው ከአበባ ጋር አበባ አየውሽ 🫣ሲጫወቱ ፤ እነ ባቢ የመልካም አዲስ ዓመት ምኞትን በስዕል ሲያዞሩ ኧረ ምኑ ቅጡ…

  • 🎉🌼እንቁጣጣሽ🌼🎉 የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት "እንቁጣጣሽ" ...... መስከረም ሲጠባ ፤ ምድር በአደይ አበባ ታጅባ ፤ ፀሐይ ከቦታዋ ስትገባ ፤ "የጎመን ድስት ይውጣ የገንፎ ድስት ይግባ "...."እዮሃ አበባ መስከረም ሲጠባ🌼" እየተባለ በዜማ ሲታወጅ ፤ አበባ የመሰሉ ህፃናት አበባን ይዘው ከአበባ ጋር አበባ አየውሽ 🫣ሲጫወቱ ፤ እነ ባቢ የመልካም አዲስ ዓመት ምኞትን በስዕል ሲያዞሩ ኧረ ምኑ ቅጡ ከሁሉም ግን ዶሮ ወጡ ፤ ጠጅ ጠላው መጠጣ መጠጡ ፤ ድፎ ዳቦ ቁርስ የቡና ፤ ዳንስ ጭፈራ በሸነና.....ብዙ ብዙ አዲስ ዓመት መጣ በሚል ሰበብ ሁልጊዜም ጥንታዊ አዙሪት....አምናም ታች አምናም አበባየውሽ ፤ እዮሃ አበባ ፤ መስከረም ገባ ፤ ክትፎ በጣባ ፤ ቡናው ባጀባ በቃ ደስታ እና ፌሽታ... ታድያ ይሄ ሁሉ ወደ ጤና ትምህርት ሲገባ ይቀየራል። አዲሱ ዓመት ለጤና ተማሪ ሁሌ ባያጓጓውም ሁሌም አዲስ ነው። አዲስ የቤተሰብ ናፍቆት ፤ ትኩስ የድፎ ዳቦ ፣ የጠላ የጠጅ...የቤት ምግብ መጠጥ ጥማት። ....አዎ የጤና ተማሪ ጋር አበባ አየውሽ የሚለው መዝሙር ብዙም ላይዘመር ይችላል። ይልቁንም ቁንጣን ያሳመመው ፤ ለዶሮ የተሳለ ቢላ የቆረጠው ፤ ጠላ አስክሮት ዱላ ያጋጠመው ፤ ቀን ጎሎበት በዓልን በህመም የዋለ ፤ በአዲስ ዓመት መስከረምን ወይም አዲሱን ለመውለድ የመጣች የማርያም አራስ የሚያሰሙት ድምፅ እንጂ ዶክተር እስቲ እይልኝማ ፤ ነርስ እዚጋ በጣም ታሞብኛል ፤ ኧረ የሆነ ሰው ታደጉልኝ ....ግን ምንድን ነው አዲሱ ዓመት ሁሌም እንደምናስበው አዲስ እና ቆንጆ አይድለም ግን እድሜ ለጤና ባለሞያዎች የታመመውን አዲስ ዓመት ፤ የተሰበረውን ፤ የተጨነቀውን ፤ የተቀደደውን ብሎም የተጨማደደውን ዓመት አዲስ ያረጉታል። ምክንያቱም ለታመመ ሰው መስከረም መጥባቱም ሆነ አደይ አበባ መፈንዳቱ ደንታ አይሰጠውም። 🥂ቺርስ የሰዎችን ጤና እንደ አበባ ለምናፈካ ለእኛ 🥂ቺርስ በአዲስ ዓመት በስራ ውጥረት ለምንሰክር ለእኛ 🥂ቺርስ ለአዲስ ዓመት ዲስቻርጅ የሚል ስዕልን ለምናድል ለኛ 🥂ቺርስ አበባየውሽ ማለት ባንችልም ፔሸንቶቻችንን ሳንታክት ለምናይ 🥂ቺርስ በበዓል ቤተሰብ ቢናፍቀንም ጤና ለናፈቀው ጤናውን ለመመለስ ለምንሮጥ። 🌼🌼🌼ቺርስስስ👨‍⚕👩‍⚕💉🥼🌼🌼🌼 🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼 ሳንኮፋ የአንባብያን ማህበር

  • #Muchachos ለአንዳንዶች የምንግዜም ድንቅ ተጫዋች(The goat) ሲሆን ለሁሉም የዘመኑ የእግር ኳስ ተመልካች ግን ድንቅ ከሚባሉ የእግርኳስ ተጫዋቾች አንዱ ነው ሊዮኔል ሜሲ። ባሳለፍነው ሀሙስ ምናልባትም በሀገሩ ምድር የመጨረሻ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን አድርጎ በ2022 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ያደረጋቸውን የሀገሩን ሰዎች ተሰናብቷል። ዶክመንተሪ መመልከት ለምትወዱ የዓለም ዋንጫ በተጠናቀቀ በዓመቱ የተለቀቀውን    እ.ኤ.አ በ2022 በሊዮኔል ሜሲ የተመራውን የአርጀንቲና እግር ኳስ ቡድን የዓለም ዋንጫ ጉዞ እና በዋናነት የአርጀንቲና ደጋፊዎች  ያሳለፉትን መንገድ፣ ስሜቶች፣ የሀገር ፍቅር እና የስፖርት በተለይም የእግር ኳስን ሀይል  የሚያስቃኝ  " Muchachos" የተሰኘውን ዶክመንተሪ እንድትመለከቱት እንጋብዛለን። እናም እንደ አንድ የእግር ኳስ ተመልካች              Gracias por todo Leo!              ስለሁሉም እናመሰግናለን ሊዮ(🦁)

  • September Birth & Death...🙇‍♂ ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ Rabbi moo namumaa Kan seera jallisee ? Haati teenya takkaa Maaltu addaan nu baasee ? አምላክ ወይንስ ሰው ፤ ሕግን ያጣመመው ? የአንድ እናት ልጆች ነን ፤ የሚለያየን ማን ነው ? In the city of Dire Dawa, Ethiopia, on September 29, 1950, a voice was born—smooth as silk, bold as heritage. His name? Ali Birra. A legend in Oromo music, a bridge between cultures, and a man whose songs could make even the toughest hearts soften like injera in coffee. Ali didn’t just sing—he translated souls. Whether in Oromo, Amharic, or Somali, his lyrics carried the weight of love, loss, and liberation. He was the kind of artist who made you feel proud of your roots, even if you didn’t know where they were planted. .............. And just like a poetic full circle, Ali Birra passed away in September 2022, leaving behind a legacy that still hums through Ethiopia’s hills and headphones. Born in September. Departed in September. A life framed by the same month🙇‍♂

  • በሚወዱት ልብ ውስጥ(In the heart of a true  lover) "You can study God through everything and everyone in the universe, because God is not confined in a mosque, synagogue or church. But if you are still in need of knowing where exactly His abode is, there is only one place to look for him: in the heart of a true lover." ኤሊፍ ሻፋክ "40 rules of Love" የተሰኘ  ድንቅ መጽሐፍ ጸሀፊ ነች። በዚህ መጽሐፏ በሰፊው በ12 ክ/ዘመን በተነሳው በእውቁ ሱፊ ሩሚ(Rumi) እና በወዳጁ ሻምዝ ታብሪዚ(Shamz Tabrizi) ላይ ያተኮረ ሲሆን በዛ ውስጥ 40 የፍቅር ህግጋትን ከህይወታቸው ጋር  እያዋሃደች ትጽፋለች፣ ከዛ ውስጥ ሶስተኛው ህግ እግዚአብሔር የት ይገኛል አሊያም ይፈለጋል የሚለው ሲሆን የህጉ መልስም በእውነት በሚወዱት ሰዎች ውስጥ ይነበባል ወይም ይገኛል ነው ። በብዙ ሀገራት የሚገኙ ሱፊዎች የሚመሳሰሉበት ነገር በደንብ የእስልምናን ህግ የተማረ እና ነፍሱ የተዋበን መምህር ፈልገው ከእርሱ ስር መማር ነው በእርግጥ ለምን ይሄን ያደርጋሉ የሚለውን 3ኛው ህግ ይመልሳል ነፍሱ የተዋበ ሰው ውስጥ እግዚአብሔር ያገኙታልና ነው። ለዚህም ብዙ ሱፊዎች በእነርሱ ዘንድ በተደነቁ እና ቅዱስ የተባሉ መምህሮቻቸውን በሚገርም ግጥሞቻቸው ከአምላካቸው ቀጥለው ያወድሳሉ። እናም ለእኛ ነፍሳቸው ከተዋቡ ወደ አምላካችን መንገድ ከሚወስዱን ሰዎችን ጋር መወዳጀት ደግ ነው። Happy Mawlid☺️

  • ተዘክሮ ሞት Dear Milena, "I wish the world were ending tomorrow. Then I could take the next train, arrive at your doorstep in Vienna, and say: "Come with me, Milena. We are going to love each other without scruples or fear or restraint. Because the world is ending tomorrow." Perhaps we don't love unreasonably because we think we have time, or have to reckon with time. But what if we don't have time? Or what if time, as we know it, is irrelevant? Ah, if only the world were ending tomorrow. We could help each other very much." - Kafka ጋሽ ካፍካ እንግዲህ የታወቁ እና የተደነቁ ጽሐፊ ሲሆኑ በህይወታቸው ሚሌና ለተባለች ሴት የጻፉት ደብዳቤዎች ታትመው ለንባብ የበቁ ናቸው። በዚህ በተቀነጨበች ደብዳቤ ላይ ጋሽ ካፍካ ነገ ባይኖር ዛሬ ላይ የፈሩትን ግንብ ሁሉ አፍርሰው ደስታ ካሉት ከሜሌና ጋር መኖርን ይመርጡ እንደነበር ያትታሉ እና ይሄን  ሀሳብ  በገዳም የሚኖሩ መነኮሳት አስፍተው "ተዘክሮ ሞት" ይሉትና እንደ ጋሽ ካፍካ ነገ ሳይሆን ዛሬን ልንሞት እንችላለን በሚል ሰበብ እና ሞትን ሁሌ በማሰብና በመዘከር ዛሬን ንጹህ ሆኖ መኖር(ጠብቆ) እንዳለበት ካልሆነ ሞት ዛሬ ቢመጣ ለነገ ከአምላካቸው ጋር ዘላለማዊ ኑሮን እንደሚያጡት ያምናሉ። ሞትን በየእለት መዘከር ላወቀበት ራሱን ከዓለማዊ ጭንቀቶች የሚፈታበትና ዛሬን በሰላምና በደስታ የሚኖርበትን መንገድ የሚጠርግለት ጥበብ ነው። ጋሽ ካፍካ ግን ከሚወዷት ሚሌና ጋር ተገናኝተው ይሆን? እንጃ! ለእኛ ግን ነገ እንደሌለን በማሰብ ለነገ ያልነውን መውደድ፣ ሰላምና ደስታ ለራሳችን ብንሰጥ ደግ ይሆናል።   ምናልባት ነገ ላይኖር ይችላል..

Sankofa_Readers_Association — tgindex