tgindex
Open reading 👐

Open reading 👐

Статистика
@sendeQ_shelfКнигианглийский

📚 Sendeq Shelf — an open reading forum. Where readers connect, share books, and grow. 📖 Borrow hard-copy (Physical) books 💼 Access job & economic opportunities 🤝 Connect with a reading community Inbox: 👉 @teds_walker Call us: 👉 0933758181

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14:41
Постов за неделю
1
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Книги
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 483
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
897
25 постов
Вовлечённость
60,5%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 25
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
160
1/48двое суток
183
1/72трое суток
197

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የኔ እንዳይደለሽ እያወኩኝ እቴ ምንይባላል እንዳላጣሽ መፍራቴ ኤዲያ     : ወለፈንዲ ነው ሀሳቤ ግራ የሚገባ ህይወት ነው ውዴ       : (አንቺ ትክክል ነሽ) ያልተገኘ ይታጣል እንዴ? ኤልያስ ሽታኹን From .. https://t.me/thiout

  • 15 февр.1 1512214

    በረኻ ነው ያሉት አበባ ይለብሳል ፤ ጨለማ ነው ያሉት ብርሃን ይወርሳል ፤ ተራራ ይኾናል ሜዳው ተገልብጦ ፤ በሜዳ ይተካል ተራራው ተውጦ ፤ ሁሉም እያደረ ይገለባበጣል፤ ከአፈር ሊመልሰኝ የኔም ቀን ይመጣል፤ እናም . . . 'ወድሻለሁ ብዬ እርግጠኛ አልኾንም ፤ ብቻ እየተጓዝን እንዬው ሁሉንም።

  • 25 янв.1 4172513

    “የልቤ” ባልኩሽ ሰው በድንገት ብከዳ ብዙም እንዳላዝን ብዙ እንዳልጎዳ… አንቺም ድንገት ነገ ፤ “የልቤ” ባልሽኝ ሰው በኔ ብትከጂ ብዙ እንዳተክዢ ብዙ እንዳትጎጂ። አየሽ… ከ እልፍኝ ያልዘለቀ ቀርቶ ከ በረንዳ ደፍሮ አይጎዳም ባዳ። ይልቅ… ከ በረንዳ አልፎ ከ እልፍኝ የዘለቀው ሽራፊ ሳትቀር ገመናን ያወቀው “የልብ” ያሉት ሰው ነው… በክህደት መዶሻ ልብን የሚያደቀው። ©Sendeq Shelf Facebook / TikTok / Telegram / linkedin

  • 23 янв.1 1592

    видео или голосовое, без подписи

  • 23 янв.1 1612

    видео или голосовое, без подписи

  • 23 янв.1 2282

    видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 23 янв.1 150142

    ሰላሞ ውድ የመፅሐፍ ወዳጆች.. "አቶ"እኔ.. የተሰኘ ልብ ወለድን፣ እውነተኛ ታሪክንና ሳይኮሎጂን(ፍልስፍናን) አጣምሮ የያዘ መፅሐፍ ፅፌ አጠናቅቄያለሁ! ይህን መፅሐፍ ለአንባቢያን ለማብቃት የምትኮሩበትን ተሳትፍ እንድታደርጉ እጠይቃለሁ። 1ሺህ ሰዎች 50, 50 ብር ቢያዋጡ ለማሳተም የጎደለው ብር ስለሚሞላ.. የመፅሐፍ ፍቅር ያላችሁ ፍቅራችሁን ግለፁልን ስል በመፅሐፍት ክብር እጠይቃለሁ🙏🙏። ልታወሩኝ ከፈለጋችሁ @Mr_lewi የቻናሌ link @lewi_derest Acc 1000514171328 Telebirr 0944240243

  • ላገባ ነው! ተንበርክኬ "ታገቢኛለሽ ወይ" አላልኳትም። ጥሎሽ አላንጋጋውም። ሽማግሌ አላሰማራሁም። ትዳር ወደተባለ ተቋም በዝምታ ተራመድሁ። በኔና ጋብቻ መካከል አንድ እርምጃ ቀርቷል። በዝምታ ዳሩ ግን በጥድፊያ ወደ ትዳር እተጓዝኩ ነው። ከሳምንት በኋላ አገባለሁ። "ፅኑ አፍቃሪ ነህ" ይሉኛል። ፈሪ እንጂ አፍቃሪ ባልሆንም እንደ አፍቃሪ መቆጠሬን ተቀብዬዋለሁ። ከቀደመችው ፍቅረኛዬ ከተለየሁ አስር ዓመታት አልፈዋል። አስር ብዙ ነው። አስር ጥቂት ነው። "እስከመች ነው ሳንጋባ የምንቆየው?" አለችኝ "ነገሮች ይስተካከሉና እንጋባለን" አልኋት። ትታኝ ሄደች። "ካንታጋ እድሜዬን አልፈጅም። እንዲረፍድብኝ አልፈልግም" ብላኝ ሄጀች። እውነት አላት። የኔ ነገር እስኪስተካከል ድረስ ጀምበሯ ይጠልቃል። የሚስተካከለው ነገሬ አንድ ነው። ድህነትን ሳላሸንፍ ማግባት አልችልም። ሽንቁሬን ሳልደፍን ትዳር ለመመስረት አልደፍርም። አፈቅራት ነበር። አንድ ነፍሴን እስክሰጣት ድረስ አፈቅራት ነበር። የፍቅራችንን አለት የድህነት መዶሻ ሰባበረው። መዋደዳችንን የማጣት ቡጢ ነረተው። ችጋር ለየን። እንዋደድ ነበር። እኔ ድህነትን እስካሸንፍ መታገስ ስለማይገባት ተለየችኝ። "ፍቅርህ አገባች እኮ" አሉኝ "ባገባች በአመቱ ወለደች" አሉኝ "ልጆች ደጋገመች" አሉኝ አስር ዓመት ስንት ነው? ከተለየኋት በኋላ በብቸኝነት ኖርኩ። ከሰው ሸሽቼ በራሴ ውስጥ መሸግኩ። ከራሴ አፈግፍጌ ከራሴ ተጣመርኩ። ከራሴጋ ሆንኩ ፥ ከራሴጋ ተለያየሁ። አስር ዓመት ድህነትን ለማሸነፍ ታገልኩ። "ከቀደመ ፍቅረኛው ስለተለያየ ከሰው ሀሉ ሸሸ" ይሉኛል። ፅኑ አፍቃሪ እመስላቸዋለሁ። ፍርሃቴን የማውቅ እኔ ነኝ። የድህነት ልጆች ያስፈራሩኝ እንደነበር የማውቅ እኔ ነኝ። "ከቀደመች ፍቅሩ ሲለያት ማዲያታም ሆነ" ይላሉ። የሚነረተኝን የችጋር ቡጢ የማውቅ እኔ ነኝ። አሁን ላጋባ ነው። በእኔና ትዳር መካከል አንድ እርምጃ ቀርቷል። ላገባ መሆኔን የሰሙ "ሰባራ ልቡ ተጠገነ" አሉ። "ዳግመኛ አፈቀረ" አሉ። የምሸሸው ድህነትን ነው። የሰበረኝ ድህነት ነው። ከአስር ዓመት በፊት ፍቅሬ "ጀምበር ልትጠልቅብኝ ነው" አለችኝ። እያለቀስኩ ሸኘኋት። ከአስር ዓመት በኋላ ለመሸነፍ መፈጠሬን ተቀበልሁ። በኮሳሳ እጅ አለትን ለመስበር ስታገል መኖሬን አመንኩ። ተሸነፍኩ። ድህነት ደጋግሞ አሸነፍኝ። ላገባ ነው። የማገባትን አላፈቅራትም። የምታገባኝ እንደማታፈቅረኝ እወራረዳለሁ። የሚያጓጓኝ ነገር የለም። ነገር አለሙ ጨላልሞብኛል። በየቀኑ ኑሮዬ በጥቂቱ እየተሸረፍኩ ነው። የማገባው ሙሉ ለሙሉ የምከስምበትን ጊዜ በጥቂቱ ለማርዘም ነው። ትላንት ከድህነት ለመውጣት ስታገል ነበር። የዛሬ ትግሌ ድሃ ሆኖ ለመቆየት ነው። ከድህነት በታች ተወርውሬያለሁ። ድሃ መሆን ቅንጦት ሆኖብኛል። ላገባ ነው። ከድህነት በታች ነኝ። የማገባትም ከድህነት በታች ነች። ሁለት አርፋጆች ልንጣመር ነው። ሁለት ኮስማኖች ልንጋባ ነው። ብዙ ሽንቁሮች አሉብን። ቀዳዳችን ብዙ ነው። ሁለታችን ብንጣምር ፥ ችግራችንን እናቀለው ይሆናል። በየግል ማሸነፍ የከበደንን ህይወት ተጣምረን እንገጥመዋለን። በተናጥል የከበደንን የቤት ኪራይ በጋራ እንፋለማለን። ላገባ ነው። ትላንት ድሃ ስለሆንኩ "አላገባም" አልኩ። የማፈቅራትን ሴት ተውኩ። ዛሬ ድሃ ስለሆንኩ "አገባለሁ"። የማላፈቅራትን ሴት እጣመራለሁ። ©Sendeq Shelf Facebook / TikTok / Telegram / linkedin

  • ደርጅታችን ለደንበኞቹ ለሚሠጠው አገልግሎት የሽያጭ እና የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር የሚፈልግ ሲሆን ከቢሮ ውጪ እየተዘዋወረች ለመሸጥ እና ለመስራት ፈቃደኛ የሆነች እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟላ አመልካች ስም፣ የመኖሪያ አድራሻ ፣ ስልክ እና ፎቶ ቀጥታ እንድትልክ እንገልፃለን ። መስፈርቶች – ፆታ – ሴት – የስራ ሁኔታ – out door sales -የክፍያ ሁኔታ— በኮሚሽን ክፍያ(ጠቀም ያለ) ለማመልከት፡ call - +251933758181      Inbox - @Teds_walker 🈴 Join us:    - https://t.me/Gfree_work    - https://t.me/Gfree_work

  • ❝ሎሚ ብወረዉር ደረቷን መታኋት፣ አወይ ኩላሊቷን ልቧን ባገኘኋት። ❞ **** ሴቶች ስንት ሎሚ ተወረወረባችሁ ግን 😉 ወንዶችስ ምን ያህል ወርውራችሁ ተሳካላችሁ??

  • ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!! ✨መልካም የጥምቀት በዓል! ©Sendeq Shelf Facebook / TikTok / Telegram / linkedin

  • የአባቴ ፍቅርና ትዝታ ለዘላለም ይኖራል! ዛሬ ስለ አባቴ ስለ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ሳስብ ልቤ በሀዘን ቢከብድም በእሱ ልጅነቴ ግን እጅግ እኮራለሁ።አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም!ለእናቴ ታማኝ ባል ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር!በሄደበት ሁሉ ፈገግታን የሚዘራ ለሰው አሳቢና እጅግ ሩህሩህ ሰው ነበር! አባዬ ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ።ሊገቡኝ የሚገቡ የህይወት ትምህርቶችን በትግስት አስተምረኸኛል!ከአባት የሚጠበቀውን እውነተኛ ፍቅርም ያለ ስስት መግበኸኛል!ያንተን ድምፅ አለመስማትና መለየትህ ለእኔና ለቤተሰቤ እጅግ የሚከብድ ቢሆንም አሁን አንተ ከፈጣሪህ ጋር በተሻለ ስፍራ ላይ እንዳለህ በማወቃችን እንፅናናለን።

  • በተወዳጁ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማኝን ልባዊ ሃዘን እየገለፅኩ  ለቤተሰቦቹና ለመላ አድናቂዎቹ ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ:: ነፂ ስላበረከትክልን ኪነጥበባዊ ውለታህ እጅግ አድርገን እናመሰግንሃለን :: እግዚአብሔር አምላክ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን ::                      ነፍስ ይማር !!!

  • ..."የሰው አዕምሮ በትክክል የሚዋኝበት ቢገኝ ከውቅያኖስ የጠለቀ...ከሰማይ የራቀ...ከሐሳብ የረቀቀ...በዋጋው ሁሉ የራቀ ...ተቆፍሮ ያልተደረሰበት ውድ ሀብት ነው። ግን የተቆለፈበት ቁልፍ ነውና ቁልፉን ለማግኜት ቁልፉ የተቆለፈበትን ደጃፍ ለመክፈት የሚያስችለውን ቁልፍ እስክናገኝ ተስፋ መቁረጥ የለብንም። ከቁልፉ ብዙ የራቅን አይመስለኝም!" ሲል መስማማቷን በደማቅ ፈገግታዋ ገልፃ አንድ እጁን ትክሻዋ ላይ እንዳለ በግራ እጇ ይዛ ሌላ እጁን ደግሞ በወገቡ ዙሪያ ባደረገችው እጇ ጠበቅ አድርጋ ያዘችና ልትጠልቅ የደረሰችውን ጀንበር እያዩ ወደፊት መራመዳቸውን ቀጠሉ። የተቆለፈበት ቁልፍ ምህረት እንደጻፈው

  • ከማጀቴ መጥቶ ፥ የሚዘልቀው ሁሉ የተኮታኮተ እመስላለሁ መሰል ሰባራ ልብ ጠጋኝ ፥ ጥበብ ያነገተ ጉድለቴን ባልገልጠው ፥ ሸራፋው ባይታይ ብቁ ነው ተባልኩኝ ፥ ሁሉ ሚችል ሰማይ ብዬ አልተናገርኩኝ ሰባራ ስራ አለሽ ፥ ወይ ፍራሽ አላድስ ህይወት እንደሆነ አያጣትም ለካ ፥ አሰሳ ግብስብስ ወስፌ ጅማት የለኝ መዘምዘሚያ ጣቶች ፥ ለሰጣቃ ልቦች ማቆያ 'ምለግስ በዚህ በዚያ ቡትርፍ ፥ የራሴን ቀዳዳ ማን ይወትፍ ማንስ? ከሀቅ ተናንቄ ፥ ብዬ እንዳልናገር ቃሌም እንደሆነ ፥ ዲዳነት ላይ ግግር ሰው ከነህመሙ ፥ ቆሟል ከደጃፌ ጆሮ እና መራራት ፥ በኣካሌ አንጥፌ ። ዝለቅ እለዋለሁ ክተት እለዋለሁ ሙሾን ልረከበው ከዕንባ ጋር ልዋየው። የስንቱን ሰው ዕንባ ፥ የስንቱን ሰው ሸክም መጋጃ ይመስል ፥ አረገኝ ጎባጣ ሰቆቃን ስለቅም የመጡትም ሁሉ ፥ ድነው ተመለሱ በረቀቀ ጥበብ ፥ ዓቅም ከእኔ አፈሱ ዳሩ ያኮራልም ፥ አያኮራም ደግሞ ከፈውሳቸው ግርጌ አናቴ ላይ ወጣ ፥ ቀውሳቸው ገግሞ። የራስ ባልሆነ ዕንባ ፥ ራስን መበደል ፈገግታ አይፀና ፥ በሀዘኔ ኪል-ኪል አረ ሰው በረታ ፥ በደከመው በኩል እየቦረቁ ነው የመጣው የሄደው ፥ በእኔ ላይ ምን ፈራ ስምኦን ገበሬው የሆንኩኝ መሰለኝ መስቀል ተሸክሜ የኔ ያልሆነው የምዞር መከራ። አለኝ በዪኝ እንጂ ፥ እንደ ጨው መዋዋስ እንጃ መሻገሬ ይኽ የሞት ጽላሎት ፥ የዛሬውን አድማስ። አረገኝ አንቺዬ በሄድኩበት ሁሉ ለሀዘን ማፈንደድ እኔስ ቸክኮኛል ብድር ልጠይቅሽ ላመል ታህል እንኳ ተድላ ይኖርሻል? ©Sendeq Shelf Facebook / TikTok / Telegram / linkedin

  • 📌በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሰርጉ ተሰረዘ በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የተሰማውና ብዙዎችን ያነጋገረው የሰርግ ታሪክ፣ በወጪ ብዛት ሳይሆን በፍጻሜው አስደናቂነት መነጋገሪያ ሆኗል። ሁሉም ነገር ተሰናድቶ፣ የሰርግ አዳራሹ አሸብርቆ፣ ምግብና መጠጡ ሞልቶ የተጠበቀው ሰርግ፣ በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። ኖር ሬድዮ ታሪኩን እንዲህ ይነግራችኋል  ለዓመታት በትውውቅ የቆዩትና ሙሽራው በውጭ ሀገር የሚኖረው እነዚህ ጥንዶች፣ ጋብቻቸውን ለመፈጸም የለፋ ወጪ አውጥተው ነበር። ለምሳሌ ያህል ለክትፎ ብቻ 450 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ (Advance) ተከፍሎ ነበር። ዲኮሩም ከትናንትናው ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ተሰርቶ አልቋል። ​ነገር ግን በሰርጉ ዋዜማና በዕለቱ በተፈጠረ አለመግባባት ነገሮች ተበላሹ። ሙሽሪት "ከጋብቻ በፊት የጤና ምርመራ ማድረግ አለብን" የሚል ጥያቄ ታነሳለች። ሙሽራው በበኩሉ ይህንን ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም ወይም ጊዜው አልፈቀደም ተብሏል። በዚህ መሃል "ሙሽራው ከዚህ በፊት ትዳር ነበረው፣ አምስት ልጆችም አሉት" የሚሉ ወሬዎችና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸው ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። ሽማግሌዎች ገብተው ለማስማማት ያደረጉት ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል። ​በመጨረሻም በሰርጉ ቀን ሙሽራውና ሚዜዎቹ ዘንጠው ተዘጋጅተው ቢጠብቁም፣ ሙሽሪት ግን "አልመጣም" በማለት ቀረች። ተጋባዥ እንግዶችም አንዳንዶቹ ጉዳዩን ሰምተው ሳይመጡ ቀርተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወጪ የፈሰሰበት ይህ ሰርግ፣ ሙሽራው ብቻውን ከሚዜዎቹ ጋር በባዶ አዳራሽ ፎቶ ተነስቶ ወደ ቤቱ በመመለሱ ተጠናቋል። Facebook / TikTok / Telegram / linkedin

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

Open reading 👐 — tgindex