📃ከብጥስጣሽ ወረቀቶች📄
Статистика📌 ምን ሆናችኋል 🤔 መጀመሪያ ከሰውነታችሁ በላይ አይምሯችሁን ገንቡ እንጂ🃏 📍አንድ ነገር እንድትጀምሩም ሆነ እንድትጨርሱ የተገነባ አይምሮ ያስፈልጋችኋል 😎 ↘️ማጋራት አይዘንጋ↗️ 🚸 ቻናላችንን ይቀላቀላሉ 📢 🔶https://t.me/From_broken_papers 🔸https://t.me/From_broken_papers
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 407
- 1/48двое суток
- 466
- 1/72трое суток
- 503
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እንጋባ ቀለበት ሳናስር፣ድግስ ሳናበዛ ቬሎ'ና ሱፍ ሳንል፣ወሬ ሳናንዛዛ ቤተሰብ ሳያውቁ፣ፍቃድ ሳንጠይቅ እኔ'ና አንቺ ብቻ፣ከአለም እንርቀቅ። ጎጆም ሳንቀልስ፣አንድ ቤት ሳንገባ ለማንም ሳንነግር፣ቶሎ እንጋባ😁። ሚዜም ሳያስፈልግ፣ወጪም ሳናወጣ በርበሬ ቀንጥሰን፣ለሰርግ ሳናሰጣ ቤትሽን ሳለቂ፣ከቤቴም ሳሎጣ ብቻ እንጋባ፣ከዛ የመጣው ይምጣ። "ተጋብተናል"ብለን፣ስለ ልጅ ሳናልም🫣 ባንድ አልጋ ሳንተኛ፣ሰማንያ ሳንፈርም😊 ግጥሜንም እንደ ቀልድ፣ቆጥረሽ ሳትስቂ ዝም ብለሽ አግቢኝ፣ጥሎሽ ሳጠብቂ።። #ታገቢኛለሽ ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
ዘንድሮ ውጪ ካለው ዘመድህ ይበልጥ ቀበሌ ሚሰራው ጎረቤትህ ይጠቅምሃል 🙌 📌ማጋራት አይዘንጋ
. ༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ༻ ✧༝ #ክፍል_6 ༝✧ ...ውጤቱን እስክሰማም ጨንቆኛል ግን ለምን ወጥቼ እንደሄድኩ እንጃልኝ። ልክ አስፋልቱን ተሻግሬ በር ላይ ስደርስ ማክቤል በር ላይ ቆሞ በፈገግታ ተቀበለኝ የኔ ፊት ግን ጭራሽ አልተፈታም። አቤት ምንድነው አልኩት ከፊት ለፊቱ ቆሜ: አትኮሳተሪ እንጂ ጉዳዩን ደግሞ ግቢና እነግርሻለሁ በናትሽ አልገባም እንዳትይኝ ብቻ መቼም እዚህጋ ቆመን እናውራ አትይኝማ አለ የመማፀን ፊት እያሳየኝ እሺ ብዬ አልፌው ገባሁ ከፊቴ ቀደመና የሆነ ወንበር ስቦልኝ ተቀመጥኩ ምን ልታዘዝ አለችኝ አስተናጋጇ ነበረች አይ ምንም አልፈልግም በቃኝ ስል.. ማኪያቶ አምጭላት አለ ማክቤል :: እሺ ምን ፈልገህ ነው ንገረኝ አሁን እቸኩላለሁ አልኩት። ተረጋጊ እንጂ እስቲ የሆነ ነገር ቅመሺ አለኝ እየሳቀ ነበር ወዲያው አስተናጋጇ ማኪያቶውን ይዛ መጣች እንደዛ የምወደው ማኪያቶ ገና ሲሸተኝ አቅለሸለሸኝ ፉት ለማለት ወደ አፌ እንኳን ማስጠጋት አቃተኝ አጎንብሼ ልውጣ አልውጣ እያለ የሚታገለኝ ነገር እየከበደኝ አፌን በሶፍት አፍኜ ስጠባበቅ ትንሽ መለስ ሲልልኝ በቃ ንገረኝ ልሄድ ነው ብዬ ቀና ስል በጣም የምታምር የደም ግባት ያላት ልጅ የማክቤልን ትከሻ ተደግፋ ቆማለች ተዋወቁ ፍቅረኛዬ ነች አለ በማፌዝ አስተያየት እያየኝ ልጅቷ ፈገግ ብላ እጇን ዘረጋችልኝና መርሀዊት እባላለሁ አለች ስትስቅ ዲንፕሏ ጎላ ብሎ ይታያል ውበቷንም በእጥፍ ይጨምርላታል ውስጤ ቅጥል እያለ ሰላም እባላለሁ ብዬ ጨበጥኳት እጇን ለቀኳትና በጣም እንደምታምር ነግሪያት ተነስቼ ወጣሁ ማክቤል መጣሁ ብሏት ተከተለኝ በህይወቴ እንደሱ ወራዳ ሰው አይቼ አላቅም በጣም ጠላሁት ከኋላዬ መጥቶ እየሳቀ ቆንጆ ናት እንዴት አየሻት ሲለኝ ድምፁ ሊያስታውከኝ ምንም አልቀረውም ነበር ዝም ብዬ ወደፊቴ ሄድኩ እሱ እየተከተለኝ ይለፈልፋል እንዴት ነው ፍቅረኛሽ ሸመጠጠሽ እንዴ አብራችሁ አትታዩም ወይስ ተከራይተሽው ነበር ብቻ ምላሱን ብቆርጠው በምን እድሌ መጨረሻ ላይ ትግስቴ ሲሟጠጥ በርጋታ ወደሱ ዞርኩና ፍቅረኛህ በጣም ቆንጆ ናት በጣም ደስ ትላለች ግን ደሞ ታሳዝናለች እንዳተ አይነት ሰው ላይ ስለጣላት ለማንኛውም ያዝልቅላቺሁ እኔን ግን ተወኝ እኔኮ በቃ እርግፍ አድርጌ ትቼሀለሁ እኔ የራሴን ህይወት ጀምሬሀለሁ አንተን ከሰው እኩል እንኳን መቁጠር ካቆምኩ ሳምንታቶች አልፈዋል ሰርግህን እንዳትረሳኝ ከቀደምኩህ አረሳህም ብዬው በቆመበት ጥዬው ሄድኩ ልክ ልኩን ስለነገርኩት አልተከተለኝም ብቸኝነት ሲሰማኝ የምሄድበት የሆነ ቦታ አለ እዛ ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ የምርመራ ውጤቱም አለ ለካ ..... ብቻዬን ቁጭ ብዬ ማብሰልሰል ጀመርኩ :: ማክቤል ከኔ የበለጠች ቆንጆ ስለያዘ የሆነች ቅናት ብጤ ተሰምታኛለች እኔምኮ ከሱ የበለጠውን ይዣለሁ ብዬ እራሴን ላፅናና ሞከርኩ ግን ልዑሌ የኔ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም ።። ትንሽ ቆየሁና ተነስቼ ወደሆስፒታል ሄድኩ ይቅርታ ተራዬ አልፎኛል መሰለኝ ውጤቱ አንቺጋ ስለሆነ ብትነግሪኝ አልኳት ውጤት ለመናገር ስትጣራ የነበረችዋን ዶክተር ኦኦ አንቺ ነሽ ስምሽ ሲጠራ የጠፋሽው ነው ግቢ አለችኝ ። ገባሁ ቁጭ አልኩኝ መጀመሪያ ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀችኝ ከማንጋ ነው ምትኖሪው ስራ አለሽ ፍቅረኛ አለሽ ወይ የኑሮ ሁኔታሽ እንዴት ነው ብቻ ብዙ ከጠየቀችኝ ከመለስኩላት ቡሀላ ወጤቱን ነገረችኝ ..... የምርመራ ውጤቴን ሳየው እዛው ነበር እራሴን የሳትኩ ስነቃ ዶክተሮቹ ከበው ደህና ነሽ ደህና ነሽ ይሉኛል መልሴን እራሴን ከፍ ዝቅ በማድረግ መልሼላቸው ካላጋ ላይ ወረድኩ እንባዬ ዝም ብሎ ይፈሳል አንዷ ዶክተር ሶፍት ሰታኝ እንድረጋጋ ነገረችኝ መረጋጋት ግን አቃተኝ:: ደና እንደሆንኩኝ ነግሪያቸው ዝም ብዬ ወደቤቴ ሄድኩ እቤት ታናሽ እህቴ ብቻ ነው ያለችው ስታየኝ ደንግጣ እሮጣ መታ አቀፈችኝ ዝም እንድትል አስጠንቅቂያት ወደ ክፍሌ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ:: ክፍሌ ተጠቅልዬ ሳስብ ሳለቅስ ስገላበጥ አመሻሽ ደርሶ እናቴ ወደ ቤት መጣች እቤት ስትገባ ከሳሎን ስታጣኝ ወደ ክፍሌ መጣች ብታንኳኳ ብታንኳኳ ዝምታ ነበር መልሴ የበሩ ድብደባና ድምጿ በጣም ሲረብሸኝ ተነስቼ ከፈትኩላት ስታየኝ ደነገጠች ምነው ልጄ ምን ሆንሽብኝ እያለች ፊቴን ስታሳሸኝ እንባዬን መቋቋም አቃተኝ ፊቴን አዙሬ ወደ አልጋዬ ሄድኩ ተከትላኝ ገባችና አልጋዬ ላይ አረፍ ካለች ቡሀላ ወደሷ ጎትታ ጉልበቷ ላይ አስተኛችኝ በይ አሁን በርጋታ የሆንሽውን ሁሉ ንገሪኝ አለች ከናቴ ምንም ነገር አልደብቃትም ከልጅነቴ ጀምሮ እንደ ልብ ሚስጥረኛ ጓደኛ ሆና ነው ያሳደገችኝ ሌላው ቀርቶ ትምህርት ቤት እንኳን የፍቅር ደብዳቤ ሲሰጠኝ ከናቴጋ ነበር ከፍቼ ማነበው የሚጠቅመኚንና ማይጠቅመኝን ከሷ የተሻለ የሚያውቅ ሰው አለ ብዬ ስለማላስብ ነው ምንም ነገር ማልደብቃት አሁንም ሁሉንም አፍረጥርጬ ልነግራት ነበር ግን እንደማልችል ገባኝ እናቴ ይሄን ብትሰማ ምን ያህል እንደምታፍር ሳስበው ሰቀጠጠኝ እናቴ በቀላሉ እንደማትፋታኝ ስለገባኝ የሆነ ታሪክ ፈጥሬ ልነግራት እያሰብኩ እያለ ድንገት ልኡል አይምሮዬ ውስጥ ብልጭ አለ ። እእእ ....ንገሪኛ.. ልጄ አለች በለሆሳስ ድምፅ ጠየቀችኝ ምን መሰለሽ ማም ፍቅር ያዘኝ አልኳት እየተቅለሰለስኩ :: አላመነቺኝም 💀ፍቅር ስለያዘሽማ እንዲህ አትሆኚም ።ደሞስ ዛሬ ነው እንዴ ፍቅር የያዘሽ እእእ ይሄን ያህል ጊዜ ከማክቤልጋ ስትቆይ ፍቅር እንደያዘሽ ነበር ማቀው እኔ እናትሽ ስታይኝ ህፃን ልጅ ነው እንዴ ምመስልሽ በይ አሁኑኑ እውነቱን ተናገሪ ብትዋሽኝ አውቅብሻለሁ እሺ አፋጠጠችኝ። እኔም ድርቅ ብዬ እማዬ ከማክቤልጋ ተለያይተናል ከሌላ ሰው ነው ፍቅር የያዘኝ .... 🔮ይቀጥላል🔮 ላይክ እና ሼር 😉 ማድረግ አንርሳ....! ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
ስንቶቻችንነን #በትላንትናው ጠባሳችን ፍቅር እየገፋን ያለነው ? ስንቶቻችን ነን በትላንትናው ህይወታችን ምክንያት በፍርሀት ሰው ማቅረብ ማመን የተውነው?? ሰንቶቻችን ነን መልካም ሰዎች እንዳሉ ማመን ያቃተን በትላንትናችን ምክንያት ? ስንቶቻችንነን እሚወዱን እንዳሉ መቀበል ያልቻልነው ? ሁሉም ነገር ልክ አለው እራሳቹን አክሙ ለመዳን አንድ እርምጃ ተራመዱ<<< ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራም ለሚመጣው እንጂ ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
ክፍል 3 እንዲቀጥል like and share ቻናሉ 3k እንዲገባ እናድርገው ❤❤ ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
. ༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ༻ ✧༝ #ክፍል_5 ༝✧ ...ስለዚህ በሆነ ነገር ልፈትነው አሰብኩ::.. ልክ እንደተገናኘን በመጣደፍ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህማ አልኩት መቼም አንዴ ሲፈጥረኝ እርጋታ ብሎ ነገር አልፈጠረብኝም...:: እሺ ሞልቃቂት አለ እየሳቀ ሲስቅ አንዳች ሰውነትን ስንጥቅ የሚያደርግ ምትሀት ነገርማ አለው ) በቃ ተወው ስንወጣ መኪና ውስጥ እነግርሃለሁ ብቻችንን ስንሆን አልኩት እሺ እንደተመቸሽ አለኝ ደሞኮ ሲያወራ ቃላቶቹ አንቺ ቅደሚ አንቺ የሚባባሉ ነው የሚመስለው አቤት እርጋታቸው ። ልክ መኪና ውስጥ ስንገባ ወደፊት ንዳው አልኩት የት እንደሚሄድ ባያቅም ይነዳዋል ብቻ ዞር ስል ትንሽዬ ቦታ አየሁ አቁመው አቁመው ሳይታወቀኝ አንባረኩበት እሺ ተረጋጊ እንጂ ሰላም አለ ። እሺ ወደ ታች ታጠፍ አልኩት ታጠፈ ትንሽ ተጉዘን ከመኪናው ወረድን ለሁለታቺንም በደንብ እየተያየን ለማውራት የሚመቸንን ቦታ ከመረጥን ቡሀላ ቁጭ አልን እሱ ትንሽ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ እግሩን ከፍቶ ተቀመጠ እኔ በእግሮቹ መሀል ገብቼ ቁጭ ልል አልኩና ድፍረት ይሆንብኛል ብዬ ከጎኑ ወደሱ ዞሬ ቁጭ አልኩኝ.... እሺ አጂሪት ቀጥይ አለ። ለመስማት እንደጓጓ የሆነ ነገር ሹክ ብሎኛል ። ምን መሰለህ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር አልኩ ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ እየገባኝ እኮ ነው ። ጠይቂኛ ብቻ አፈቅርሀለሁ እንዳትይኝ እንጂ አለ አነጋገሩ የቀልድ አይመስልም ማለት አልኩት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም ቀጥይ አለ። እሺ ብዬ የራሴን ጥያቄ ልግባው 😂😂😂😂😂😂 በቃ ለምሳሌ መንገድ ላይ እየሄድክ አንድ የኔ ቢጤና አንድ ሚሊየን ብር ብታገኝ ቀድሞ ልብህ የትኛውን ይከጅላል አልኩት :: መልሱን እስክሰማ ተጨነኩ እእእ በቃ ለዚህ ነው እዚህ ድረስ ያመጣሺኝ ብሎ አፍንጫዬን ጎተተኝና.... ወደ መልሱ ስገባ እኔ የኔ ብጤውን እመርጣለሁ ምክንያቱም እኔ የብር ችግር የለብኝም ይሄንን ጥያቄ ለ1 የኔ ቢጢ ብታቀርቢለት መልሱ ገንዘቡን ይልሻል እኔን ስጠይቂኝ ደሞ ሰውዬውን አልኩሽ ሰው የሌለውን ነገር ነው የሚመኘው እኔ ገንዘብ አለኝ ፍቅር ግን የለኝም ባሁን ሰአት ከገንዘቡ ይልቅ አንድ የልቤን ሚማርከው እውነተኛ ሰው ባገኝ ነው ምመርጠው እኔ ሚስት ማግባት ብፈልግ ገንዘቧን አይቼ አይደለም ማገባት ለምን መሰለሽ በቤት ላይ ቤት በመኪና ላይ መኪና በገንዘብ ላይ ገንዘብ እንጂ ፍቅርን አትሰጠኝም አንዲት ሴትን ሳፈቅራታ ክፍተቴን እንድትሞላልኝ እፈልጋለሁ የኔ ክፍተት ገንዘብ አይደለም የኔ ክፍተት እውነተኛ ፍቅር ነው ገንዘብ ሳላጣ ጤነኛ ሆኖ በሚኖረው ሰው እቀናለሁ :ሁሌ እየሳቀ በሚኖረው እቀናለሁ :የልቡን ሁሉ ዝርግፍ እያደረገ ለልብ ጓደኛው ሲያማክር ሳይ እቀናለሁ: ምክንያቱም አሁን የጠቀስኩልሽ ነገሮች ሁሉ የለኝም እነዚህ ነገሮች ያሏቸው ሰዎች ግን ለነሱ እንደተራ ነገር ናቸው እነሱ በእጃቸው የሌለውን እሩቅ አሻግረው ሲያዩ የተሰጣቸው ነገር ሳያመሰግኑበት ሳይጠቀሙበት ያልፍበታል ተመለሰልሽ ብሎ ጉንጬን ነካ ነካ እስኪያደርገኝ ድረስ አፌን ከፍቼ ነበር ምሰማው አንዳንድ ጥያቅዎችን ተፈጥረውብኛል ግን ዝም አልኩኝ ። ልኡሌ አነጋገሩ ውስጤ ነበር የገባው እውነት ፈልጎ ያጣውን ክፍተቱን እኔ ብሞላለት ብዬ ተመኘሁ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሱን ለማስደሰት ለራሴ ቃል ገባሁ ።ሳየው ሁሉ ነገሩ ነው የሚያሳሳኝ ከንፈሩ አይኑ ብቻ አላቅም ወደሱ የሚጎትተኝ ብዙ ነገር አለ በጭራሽ መቋቋም የማልችለው ። አንዳንዴ በጣም ያመኛል ምግብ እራሱ አይረጋልኝም በልቼው ወዲያው ይወጣል ያጥወለውለኛል ብቻ ሀኪም ቤት ለመሄድ እነሳና ምን እንዳስቀረኝ ሳላቅ እቀራለሁ። ዛሬ ግን በጣም ሲብስብኝ ሄድኩ ምርመራ አድርጌ ጨርሼ ልወጣ ስል ማክቤል ደወለ ግራ እየተጋባሁ አነሳሁት ሄሎ የኔ ውድ አለኝ አቤት አልኩ በመኮሳተር ድምፅ🙄😡😡 ፈልጌሽ ነበር ከቻልሽ አስቸኳይ ነው እባክሽ አለ። እኔም ምን ሊለኝ ነው ብዬ እያሰብኩ እዛው ከግሮሰሪያችሁ ፊት ለፊት ያለው ሆስፒታል ነኝ አልኩት ትንሽ እንኳን አልደነገጠም አስቸኳይ ነው ትመለሻለሸ ቶሎ ነይ አለኝ እኔም ውጤት ለመስማት ተራዬን እየጠበኩ ስለነበር ዝም ብዬ ወጥቼ ሄድኩ ። ውጤቱን እስክሰማም ጨንቆኛል ግን ለምን ወጥቼ እንደሄድኩ እንጃልኝ።......!!?? 🔮ይቀጥላል🔮 ላይክ እና ሼር ማድረግ አንርሳ....! ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
በጠዋት አከራዬ ምግብ ሲሰሩ ማነሽ .... እንደው ይሄ ልጅ ይሸተዋል ሂጂና .... በርህን ዝጋ በይው😁 መልካም ቀን ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
. ༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ༻ ✧༝ #ክፍል_4 ༝✧ ...በሰላም ነው የደወልከው?.....አዎ ላወራሽ ፈልጌ ነበር አለ:: ከተመቸኝ እሺ አልኩት.... በቃ ቻው ደህና እደሪ ስልኩ ጆሮዬ ላይ ተዘጋ:: ከትንሽ ደቂቃዎች ቡሀላ ወደ ልኡል ጋ ደወልኩ አያነሳም ልረብሸው ስላልፈለኩ ዝም አልኩ እንቅልፌ ሸለብ ከማድረጉ ስልኬ ጮኸ ልኡል ነበር አነሳሁትና በሰላም ገባህ..? አልኩት አዎ እየነዳሁ ስለነበር ነው ያላነሳሁት ይቅርታ አለኝ:: የተወሰነ ካወራን ቡሀላ ቻው ተባብለን ተኛሁ ጠዋት ከእንቅልፌ የተነሳሁት 3 ሰአት ላይ ነበር ቁርሴን በላልቼ ስጨርስ ወደ ጓደኛዬጋ ልወጣ ልብሴን ስለባብስ ስልኬ ጮኸ. ማክቤል ነው.. አነሳሁት ሄሎ አለኝ አቤት አልኩት ዛሬ እንገናኛለን ተባብለን አልነበር ከተመቸሽ አሁን ላግኝሽ በራቺሁ ጋ ነኝ አለ.. ጠብቀኝ ብዬው ከ10 ደቂቃ ቡሀላ ወጣሁ.. ተኮሳትሮ ነበር የጠበቀኝ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ምንድነው ልታናግረኝ የፈለከው አልኩት በውስጤ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ እኔም ትንሽ ከለመነኝ ቡሀላ እሺ እንደምለው ወስኜ ነበር... እሱ ግን የትናትናው ልጅ ፍቅረኛሽ ነው አለ ተኮሳትሮ ለምን ጠየከኝ አልኩት አይ እኔ እንድትጎጂ አልፈልግም ላስጠንቅቅሽ ብዬ ነው ማለት አልኩት ውስጤ ግራ ግብት ብሎታል እሱኮ በጣም ሀብታም ነው በጣም ታዋቂ መኪና አስመጪና ላኪ ድርጅት አላቸው ከወንድሞቹጋ..:: በዛ ላይ የራሱ የሆነ ምን የመሰለ ሆቴል አለው ስታስቢው ዝቅ ብሎ ካንቺጋ የሚሆን ይመስልሻል እኔ እንኳንኮ የራሴ የምለው ምንም ነገር ሳይኖረኝ ባባቴ ጎሮሰሪ ተኩራርቼ ነው አንቺን ደሀ ነሽ ብዬ የተውኩሽ..!!???። እስኪ እራስሽን ተመልከቺ አንቺም ሆንሽ ቤተሰቦችሽ ከዚህ ከቆመ የጭቃ ቤት በቀር የራሴ የምትሉት ምን አላቺሁ እና ተጠንቀቂ ብሎኝ በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ ብቻ አላቅም በስለት እንደተወጋሁ ነገር ሰውነቴን ሁላ ደነዘዘኝ የማቀው ማክቤል አልመስልሽ አለኝ ለአይኔ አስጠላኝ በጣም ቀፈፈኝ እስከዛሬ ፍቅረኛዬ መሆኑን ሳስብ ሰቀጠጠኝ ፈዝዤ በቆምኩበት የሆዴን ህመም መቆጣጠር አቅቶኝ መሬት ላይ ወደኩ ከየት መጣ ሳልለው የሆነ ሰውዬ መቶ አነሳኝ እራሴን ለማረጋጋት ከሞከርኩ ቡሀላ ወደ ቤት ገብቼ ተኛሁ ያለኝን በሙሉ ማሰብ ጀመርኩ ግማሹ ልቤ እውነቱን ነው አንቺ ተመርቀሽ እንኳን ስራ የለሽ የራሴ የምትይው የግል ቤት የለሽ ይለኛል ግማሹ ልቤ ግን ለፍቅር ገንዘብ መስፈርት እንደማይሆን እየነገረኝ ነው ብቻ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ደርሷል ሳወጣ ሳወርድ ከራሴጋ ስጣላ ስታረቅ ብቻ ክፍሌ ሆኜ በሀሳብ ሀገሪቷን ሳስስ ከሀሳቤ ልኡሌ ነበር ደውሎ የቀሰቀሰኝ እንደከፋኝ እንዲያቅ ስላልፈለኩ እንደመሳቅ ብዬ ሄሎ አቶ ልኡል ምን ነበር ስለው አይ ዛሬስ ፍቅረኛሽን አታስቀኚውም ወይ ልልሽ ነበር አለኝ ::በዛ እረጋ ባለ ድምፁ አይይ ታውቆብሀል በቀጥታ ላግኝሽ ነው ሚባለው አልኩት እየተፍለቀለኩ እሺ የት እንገናኝ እዛው የባለፈው ቤት ነዋ አልኩት እየተፍለቀለኩ ወዲያው ተነስቼ ከሌላ ጊዜው በተሻለ የሚያሳምረኝን ልብስ መምረጥ ጀመርኩ.... ልብሴን ለባበሼ ስወጣ ልኡልጋ ደወልኩ አነሳውና እዛው እየጠበቀኝ እንደሆነ ነገረኝ ሄድኩ ውስጥ ስንገባ ማክቤል የለም ለነገሩ አይኑን ማየት እራሱ ነበር ያስጠላኝ ልክ ስንገባ የሆነ ምግብ ሸተተኝ እና በጣም አማረኝ ለልኡል ልነግረው ነበር ግን ይታዘበኛል ብዬ ተውኩት ። አስታናጋጇ ትንሽ ቆይታ ስገባ የሸተተኝን ምግብ ባጠገቤ ይዛ አለፈች መቋቋም እስኪያቅተኝ ድረስ አማረኝ ስትመለስ አስተናጋጇን በእጄ ጠርቻት አሁን ባጠገቤ ይዘሽ የሄድሺውን ምግብ ይዘሽልኝ ነይ አልኳት ልኡልንም ምን እንደሚፈልግ ጠይቃው ሄደች... ምግባችንን ጨራርሰን እየተጎነጨን ዝም ብለን እያወራን ነው ልኡል በጣም ተጨዋች ነው ። አጉል እንደሀብታም አያካብድም በጣም እየገረመኝ ነው ጨራርሰን ልንወጣ ስንል ማክቤል ከፊት ለፊት መጣ አየተሳሳቅን ባጠገቡ አለፈን በግልምጫ አንስቶ አፈረጠኝ ቦታም አልሰጠሁትም የወደድኩትን ያህል ነው ያስጠላኝ ብቻ በቃ ከልኡሌጋ በጣም እየተቀራረብን ነው አንዳንዴ ሳስበው በጣም ነው ሚገርመኝ ፈጣሪ እንዴት ሁሉን ነገር አሟልቶ ለ1 ሰው ይሰጣል ብዬ አሰብኩ ከመልክ መልክ በሀብት ላይ ሀብት በፀባይ ላይ ፀባይ አላቅም ብቻ ይሄ ጎሎታል ማይባል እንደስሙ ልኡል የሆነ ሰው ነው አንዳንዶቹ ሀብት ካላቸው በጎነት ይጎላቸዋል በሀብታቸው ምንም ነገር ማድረግ የሚችሉ የሚመስላቸው ተራ ሰዎች በዚች አገር ላይ እልፍ ሰዎች አሉ አንዳንዶቹ ደሞ መልክ ካላቸው ፀባይ ይነሳቸዋል ብቻ ልኡሌ ከማቃቸው ሰዎች በብዙ ነገር ተለየብኝ አሁን አሁንማ ሳላገኘው ማደር እራሱ በጣም ጭንቅ ክፍት ይለኝ ጀምሯል አረ እንደውም በጣም ነው የሚያነጫንጨኝ ማክቤልን ከልዑልጋ ማወዳደር እየከበደኝ መጣ። ማክቤልን ማስታወስም ማየትም ስለማልፈልግ የነሱ ግሮሰሪ እግራችን ደርሶ አያቅም :: ከልኡልጋ በደንብ ማውራት ከጀመርን አንድ ወር አልፎናል ይመስለኛል የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ነው ነገር ግን እሱጋ ስደርስ አላስነቃም አንዳንዴ ልኡሌ እየተደበረብኝ ይመስለኛል ምክንያቱም ማክቤል ያለኝን ሳስታውስ እውነት እንደሱ ሀብታም ስላልሆነኩ ባይወደኝስ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ በሆነ ነገር ልፈትነው አሰብኩ ልክ እንደተገናኘን በመጣደፍ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህማ አልኩት......!!?? 🔮ይቀጥላል🔮 ላይክ እና ሼር ማድረግ አንርሳ....! ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
አንደ ተለያየን ያውቃል ሳር ቅጠሉ እንደ ረሳዋት ገብቶታል ሰዉ ሁሉ እንደ በቃችኝ.. እንደ ወጣችልኝ ሁሉም አውቆልኛል ሀገር አሳምኜ ልቤን ይቀረኛል😭
ወይ ይሳካልናል ወይ እየሞከርን እንሞታለን ተስፋ አንቆርጥም!!!🫡❤️🔥 በሰላም ታደረ ወገንታት መልካም ቀን🥀🤙 ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ༻ ✧༝#ክፍል_3༝✧ ...ሄሎ ጤና ይስጥልኝ ሰላም ነህ (ምን እንዳርበተበተኝ ፈጣሪ ይወቀው)። አብሮ ይስጥልን ሰላም ነኝ ማን ልበል? (ወይኔ ድምፁ ደስ ሲል ከዛ ከርከሮ ማክቤል ተብዬ አንፃርማ ይሄ).... እእእእ ይቅርታ ሰላም ነኝ እእ ባለፈው ሆስፒታል በር ላይ ገፍትረህ የጣልከኝ ልጅ። እእእ አወኩሽ ምነው አመመሽ እንዴ እእ??? አረ አደለም ሰላም መሆኔን ልንገርህ ብዬ ምናልባት ተጨንቀህ ከነበር አልኩት ቀልድ ማውራቴ ነው በኔ ቤት እሱ ግን በስሬስ እውነት ለመናገር አስቤሽ ነበር ግን በሰአቱ ስልክሽን አልወሰድኩም እና ቢያማት ትደውል ነበር ብዬ ዝም አልኩ። አለኝ። አረ አላመመኝም ደና ነኝ ግን ከይቅርታጋ 1 ነገር ላስቸግርህ ነበር ማለቴ ከተመቸህ ዛሬ ላገኝህ ነበር 1 ጉዳይ ላወራህ ነበር ። (አይና አውጣነቴን ከየት እንዳመጣሁት አላቅም) እእ ምነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ??? አዎ በሰላም ነው ግን ካልተመቸህ ችግር የለውም ተወው በቃ ። አልኩት አረ እንደዛ አላልኩም ወደማታ አካባቢ ስራ ከጨረስኩ አገኝሻለሁ ሰፈርሽ ባለፈው ያደረስኩሽ ቦታ ነው አደል??? አዎ አዎ እዛ ነው ደውልልኝ ቀደም ብለህ ማለቴ ከተመቸህ አልኩት ። እሺ እደውልልሻለሁ መልካም ቀን። ስልኩ ተዘጋ...... ቀኑ እየመሸ ሄደ ከ10 ሰአት ጀምሮ ስልኬን ሳነሳ ስጥል ቆየሁ ልክ 11.50 ሲል ደወለልኝ ውጪ ሰፈር መጥቻለሁ🙄 ክው አልኩ እንዴ ልብስ ሳልቀይር ሳልዘጋጅ ከራሴጋ እያወራሁ በፍጥነት ከሌላ ጊዜው በላይ ቆንጆ ሚያደርገኝን ልብስ መርጬ ለበስኩ : ፀጉሬ ከመጀመሪያውም ተሰርቼው ስለነበር ያን ያህል አላስቸገረኝም ። ይቅርታ አስጠበኩህ አደል?? የሴት ነገር የታወቀ ነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ ??? ቀጥታ ወደ ጉዳዩ ገባ ቀለል ያለ ሰው እኔም ቀለል አድርጌ እዚህ ነው እንዴ ምናወራው ባይሆን እኔ ከፍላለሁ ሻይ ቡና እንበል እንጂ !! ሳቀብኝ ምናልባት ከቸኮልሽ ብዬ ነው እንጂ እሺ ምታቂው ቤት አለ እዚህ አካባቢ ወይስ በኔ ምርጫ ልውሰድሽ ??? አይ እኔ ማቀው ቤት አለ አዛ ልውሰድህ አልኩት ። ቀጥታ እነ ማክቤልጋ ወሰድኩት ገባን ቁጭ አልን እሺ ለምን እንደፈለግሽኝ ንገሪኝ ከማዘዛችን በፊት አለኝ ። በቃ አጠር ቀልጠፍ አድርጌ እንባ እየተናነቀኝ የ6 አመት ፍቅረኛዬ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳይነግረኝ ከመሬት ተነስቶ እንለያይ አለኝ ሳላስበው እንባዬ ካይኔ ዝርግፍ ብሎ ፈሰሰ። አይዞሽ ብሎ ሶፍት ሰጠኝ ቀና ስል ማክቤል እያየኝ ነበር:: እሱ ፊት እንደዚህ መሆኔ በራሴ እየተናደድኩ ለመሳቅ ሞከርኩ... እንዴ ምነው አለኝ... ፍቅረኛዬኮ ፊት ለፊት እያየኝ ነው:: እንዴ እዚህ ምን ይሰራል? እዚህ እንደሆነ አውቀሽ ነበር እንዴ?? ብሎ ተከታታይ ጥያቄ ጠየቀኝ። አዎ ይሄ ቤት ያባቱ ነው እሱ ደሞ ከዚህ አይጠፋም ይቅርታ ግን ላናድደው ፈልጌ ነው እሱ ከማያቀው ሰውጋ ሆኜ ለሱ ደሞ ካንተ የተሻለ ሰው አላገኘሁም ማለቴ ላስቀናው ከፈለኩ ከሱ የተሻለ ቆንጆ ሰው መሆን አለበት ብዬ ሳስብ አንተ መጣህልኝ !!ቁጥብ ፈገግታውን ለገሰኝ ሲስቅ የሆነ ብቻ የሚያስደነግጥ ነገር አለው እኔ ምልሽ ካንቺ ምን አጥቶ ነው የተጣላሽ ????? መጀመሪያ ከኔ ምን ጎድሎት ነው የተጣላኝ ብለሽ እራስሽን ጠይቁ አለኝ። ማወቅ ምፈልገው እሱን ነው አልኩት እና ምግብ እንዘዝ አለኝ:: አስተናጋጁን ጠራነው እሱ የራሱን ምርጫ ሲያዝ እኔ የቀድሞ ፍቅረኛዬ አብዝቶ ሚወደውን ምግብ አዘዝኩ እየተመገብን እያለ ላጉርስህ ማለቴ ካልደበረህ??? አልኩት ምነው እያየሽ ነው እንዴ??.. አለኝ አዎ አይኑን ከኛ ላይ መንቀል አልቻለም አልኩት:: እሺ አለኝ በዙም ደስ እንዳላለው ያስታውቃል.. ግን የኔ አይና አውጣነት አጎረስኩት:: በልተን እንደጨረስን በቃ እንሂድ አለኝ:: እሺ ብዬ ተነሳሁና እጁን ያዝኩት የሆነ የገባው ነገር ነው:: ወደ እራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ ልክ ከበሩ እንደወጣን ልሸኝሽ አለኝ... ካላስቸገርኩህ አልኩት ደርሰን ልወርድ ስል ለካ እስካሁን ስሙን አላቀውም እውይ እረስቼው ስምህንኮ አልነገርከኝም አልኩት... የዛኔ ከት ብሎ ሳቀብኝ እንዴት ስሜን እንኳን ሳታቂ የጋበዝኩሽን ምግብ ትበያለሽ ደሞ ጭራሽ መኪናዬ ውስጥም ገብተሻልኮ አለኝ:: ከደበረህ ይቀራላ አትንገረኝ ተወው ብዬ ፊቴን ዘፈዘፍኩት:: ባክሽ አታኩርፊ ልኡል እባላለሁ አለኝ:: ስምን መለአክ ያወጣዋል ማለትኮ እንዳንተ ነው:.. በቃ ቻው አልኩት እሺ ብሎ ሄደ መኪናው ካይኔ ሲሰወር ወደ ቤቴ ገባሁ ልክ ሰገባ ማዘር ምነው ቶሎ መጣሽ ብላ ሙድ ያዘችብኝ ሰአቱን ሳየው2 ሰአት አልፏል ትንሽ ካወራን ቡሃላ ወደ ክፍሌ ገብቼ ጋደም ከማለቴ ስልኬ ጮኸ ሳየው ማክቤል ነው ። ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ አላነሳውም ትንሽ ይበሳጭ ብዬ ዝም አልኩት ድጋሜ ደወለ አሁንም ዝም በ4ኛው አነሳሁት ሄሎ አልኩ በመኮሳተር ድምፅ ምነው ስልክ አታናሺም አለ :: መጀመሪያ ሰላምታ አይቀድምም ስልክ ያላነሳሁት ደሞ ከፍቅረኛዬጋ ነበርኩ ምነው በሰላም ነው የደወልከው?..... ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
. ༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ✧༝ #ክፍል_2 ༝✧ ...ምሽቱን ሙሉ አይኔ ደም እስኪመስል ሳለቅስ አመሸሁ አንድም ቀን ካፉ ክፉ ቃል አውጥቶ አስቀይሞኝ አያቅም ይሄ ነው የምለው መጥፎ ፀባይ የለበት... በድንገት እንደዚህ ያደረገው ነገር ግራ ገባኝ አልቅሼምም አልወጣ አለኝ:: ማታ መሽቶ እናቴ ወደቤት መጣች ከእህቴጋ ሲያወሩ እየሰማኋቸው ነው:: እህትሽ ምን ሆና ነው በጊዜ ወደመኝታ ቤት ያመራችው ?? እኔጃ እማዬ ከመጣሁ ጀምሮ አላናገረችኝም እስቲ አንቺ አናግሪያት አለቻት። እኔም ምንም እንዳልተፈጠረ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ እናቴ አይታኝ ተያት በቃ እንቅልፍ ወስዷታል ብለው ከክፍሌ ወጡ። ሌሊቱን ሙሉ አንዴ ስነሳ አንዴ ስቀመጥ አንዳንዴም እንደ ህንድ አክተር ልግደለው እንዴ እላለሁ አንዳንዴ ደሞ በድንገት ቢሊየነር ሆኜ በየቲቪው ብታይኮ እራሱ እየለመነ ይቅርታ ይጠይቀኛል ብቻ ሌሊቱ እንዲሁ ነጋልኝ በሀሳብ ስብሰለሰል ። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ላይ ስነሳ ቤት ማንም የለም ከነጋ ቡሀላ ስለሆነ እንቅልፍ የወሰደኝ አርፍጄ ነው የተየነሳውት ቀጥታ ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ድፍት ብዬ አለቀስኩ የሆነ ሸክም ከላዬ ላይ እንደቀለለ ነገር ተሰማኝ ወደ ቤቴ ተመልሼ ምሳ ሰአት ሳይደርስ ቤቱን ፏፏ አድርጌ እናቴን ጠበኳት ተጨዋውተን ወደ ስራዋ ተመልሳ ሄደች ።እኔም ለባብሼ ወደነ ማክቤል ሬስቶራንት ሄድኩኝና አስጠራሁት ገና ሲያየኝ ፊቱን ቅይይር አደረገው ። ምንድነው?? ማክቤል መለያየታችን ይሁን እሺ ቢያንስ ግን ይሄ ነው ጥፋትሽ በለኝና ልወቀው እኔም ጭንቅላቴ እረፍት ያግኝ አልኩት። በቃ መለያየት ፈለኩ ተለያየን ሌላ ምክንያት መደርደር አያስፈልገኝም እየመጣሽ እንዳትበጠብጪኝ ክብርሽን ጠብቂ ። ይሄን ተናግሮ በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ እንባ እየተናነቀኝ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤቴ ሄድኩኝኝኝ ምሽቱን በሙሉ ከራሴጋ ሳልሆን መምሸቱም መንጋቱም ስለማይቀር መሽቶ ነጋ ዛሬም በጠዋት ተነስቼ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ። ቅዱስ ሚካኤል አባቴ ለኔ ካላልከው በቃ ከልቤም ከህይወቴም አውጣልኝና አንተ የተሻለውን እንደምታዘጋጅልኝ ስለማምን አንተን እጠብቅሀለሁ የራሴን ሰው እስክሰጠኝ አሱን ግን አባቴ ከነትዝታዎቹ ከሀሳቤም ከኔ ህይወት አውጣልኝ ብዬ ፀለይኩ።። ወደ ቤቴ ተመልሼ እንደተለመደው እናቴን ምሳዬን ሰርቼ ቤቴን አፀዳድቼ ጠበኳት ከሷጋ ተሳስቀን የልብ የልባችንን አውርተን ወደስራዋ ሄደች ። ልክ እናቴ ሄዳ ለብቻዬ ቁጭ ስል ቀጥታ ሀሳቤ ውስጥ ይመጣል ። አልጋዬ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ እንዴት ነው እሱን መበቀል ምችለው ???????? ከብዙ ሀሳብ ቡሀላ ጭንቅላቴ ውስጥ 1 ሰው መጣ የዛሬ ሳምንት ሆዴን በጣም እያመመኝ ተቸግሬ ነበር ። ለመታየት ወደ ሆስፒታል አመራሁ ልክ ከtaxi ወርጄ የሆስፒታሉ በር ላይ ስደርስ ከአንድ ልጅ ይሁን ሰውዬ ብቻ አላትሞ መሬት ላይ ዘረረኝ ። በጣም ደንግጦ ወይኔ ይቅርታ በሀሳብ ተውጬ ነው ተጎዳሽ የኔ እናት እእ በፈጣሪ ስም ደና ነሽ ብቻ ምን ልበላችሁ ተርበተበተ ከወደኩበት አነሳኝ ለጊዜው ትንሽ ቢያዞረኝም ያን ያህል ህመም አልተሰማኝም ነበር። ወዴት ነሽ እ ምን ልርዳሽ አለኝ ወደ ሀኪም ቤት ልገባ የነበርኩት ልጅ ወደ ቤቴ ነኝ አልኩት ። እሺ ነይ እኔ ልሸኝሽ አለኝ እንኳን ለመንዳት ለማየት ወደምታታሳሳው መኪናው ውስጥ አስገባኝ ። ይቅርታ አላየሁሽም ነበር እሺ ካመመሽ ወይ የሆነ የጉዳት ስሜት ከተሰማሽ ደውይልኝ ብሎ ቁጥሩን ሰጠኝ ወደ ቤቴ ሸኝቶኝ ተመለሰ ። ይኸው 1 ሳምንት ሙሉ ትዝ አላለኝም ነበር ዛሬ ግን ማክቤልን ለማስቀናት ለአንድም ይሁን ሁለት ቀን ይተባበረኝ ይሆናል ብዬ አሰብኩ። በሰአቱ ስሙን አልነገረኝም ነበር ስልኬ ላይ የገፈተረኝ ልጅ ብዬ ነው save ያደረኩት ያ በደንብ ለማስታወስ ያህል ማለት ነው😂😂 ስልኬን አነሳሁ ደወልኩ አያነሳም 😣 ወዲያው ስልኬን ከጄ ላይ ሳላስቀምጠው መልሶ ደወለ ። ሄሎ!!! ሄሎ ጤና ይስጥልኝ ሰላም ነህ (ምን እንዳርበተበተኝ ፈጣሪ ይወቀው)። አብሮ ይስጥልን ሰላም ነኝ ማን ልበል? (ወይኔ ድምፁ ደስ ሲል ከዛ ከርከሮ ማክቤል ተብዬ አንፃርማ ይሄ).... 🔮ይቀጥላል🔮 ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ༻ ✧༝#ክፍል_1༝✧ ሰላም እባላለሁ, ብዙዎች እንደ ስሜ ሰላም የሆንኩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል... ቅብርር ያልኩ የድሀ ልጅ ነኝ:: እናቴ እንደወንድም እንደሴትም ሆና ነው ያሳደገችኝ ፈጣሪ ይመስገን እንደማንኛውም ኢትዮጽያዊ ተመርቄ ስራ ይለኝም። በወጣትነት እድሜ ቤተሰብ ለፍቶ ስንት…
መሄዷ ላይቀር እኔ እንዲህ መታገሌ ላስቀራት ባልችል እንኳን ላዘገያት ነበር ሀሳቤ ደቂቃም እድሜ ነው እንዲሉ ጥቂት አብሪያት መሰንበት ብችል ብዬ.... 💔 ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
༺ ⟪ ሊነጋ ሲል ⟫ ༻ ✧༝#ክፍል_1༝✧ ሰላም እባላለሁ, ብዙዎች እንደ ስሜ ሰላም የሆንኩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል... ቅብርር ያልኩ የድሀ ልጅ ነኝ:: እናቴ እንደወንድም እንደሴትም ሆና ነው ያሳደገችኝ ፈጣሪ ይመስገን እንደማንኛውም ኢትዮጽያዊ ተመርቄ ስራ ይለኝም። በወጣትነት እድሜ ቤተሰብ ለፍቶ ስንት መስዋትነት ከፍሎ አስተምሮ ሲጨርስ ስራ አጥቶ ቤት ቁጭ ብሎ የነሱን እጅ እንደመጠበቅ የሚያም ነገር የለም:: በዚህ ህይወት ውስጥ ብቸኛ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ፍቅረኛዬን ማክቤልን ነው ። ከልጅነታችን ጀምሮ አብረን ነው ያደግነው የፍቅር ስሜት በመሀላችን አልነበረም:: እኔ 12 ስገባ እሱ ቀድሞኝ ተፈትኖ ውጤት አልመጣለትም ነበር እና የዛን አመት ነው አፈቅርሻለሁ አፈቅርሀሉ ሳንባባል እራሳችንን relationship ውስጥ ያገኘነው ። ይኸው አሁን 5 አመታችንን ጨርሰን ወደ 6 እየሄድን ነው:: ፈጣሪ ከፈቀደው እኔ ልክ ስራ እንዳገኘሁ እናቴን የተወሰነ የሰርግ ወጪ ማገዝ ከቻልኩ ለመጋባት ነው እቅዳችን ቢያንስ ካገባሁ ቡሀላ ከናቴ ላይ ሸክም ከመሆን እድናለሁ በራሴም እፍጨረጨራለሁ ብዬ አምናለሁ። ከናቴጋ ቡናችንን እየጠጣን የሞቀ ጨዋታ ላይ እያለን ማክቤል ደወለ አነሳሁት....... ሄሎ ሰላም ወዬ ማክ ሰፈር ነኝ የተለመደው ቦታ እየጠበኩሽ ነው ቶሎ ነይ !!! እሺ መጣሁ ብዬ እናቴን መጣሁ ቆይ ማክቤል ፈልጎኝ ነው ከቆየሁብሽ ወደ ስራሽ ሂጂ እሺ እናቴ ብዬ ስሚያት በዛው በለበስኩት ቱታና በነጠላ ጫማ ወደ ማክቤል አመራሁ (ለፍቅር አጋራችሁን በጣም ስትቀርቡት ስለለበሳችሁት ልብስ ግድ አይሰጣችሁም እዚጋ ዋናው ነጠብ እሱን ማግኘታችሁ ማውራታችሁ ለናንተ ከበቂ በላይ ነው) ማክ የተለመደው ቦታችንጋ ቁጭ ብሏል እንደለመድኩት ከኋላው ሄጄ ጥምጥም ብዬበት ሳምኩት ፍፁም የማቀው ማክቤል አልነበረም እጄን ከሰውነቱ ላይ መንጭቆ አነሳው በስማም እንዴ ምናባህ ሆነሀል መነጨከኝኮ አልኩት 😒 ካሁን ቡሀላ መተዛዘሉ አስፈላጊ አደለም ለትልቅ ጉዳይ ነው የፈለኩሽ አለኝ ፊቱ ደም መስሏል ደም ስሩ ሁላ ተወጣጥሯል አረ እያስጨነከኝ ነው የተፈጠረ ነከር ካለ በቀጥታ ተናገር ምን ሆነሀል ቆይ?? ከዛሬ ጀምሮ እኔና አንች መለያየት አለብን ካሁን ቡሀላ አጠገብሽ አልደርስም አጠገቤ እንዳትደርሺ አለኝ። ከት ብዬ በረጅሙ ሳኩበት አንተ ያምሀል እንዴ እኔኮ ምን ተፈጥሮ ነው ብዬ ደነገጥኩ አንተ ትቀልዳለሀ ደነዝ ጌታን ፊትህ ሁላኮ ተቀያይሯል እጄን ወደጉንጩ እያስጠጋሁ በድጋሜ አጄን ከፊቱ ላይ አነሳና መስፍን ይሙት አልቀለድኩም ለምን ብለሽ እንዳጠይቂኝ ዝም ብለሽ ከህይወቴ ውጭልኝ አለ አይኑ አዝሎት የነበረውን እንባ አፈሰሰው ምን አልክ መስፍን ይሙት እእ በአባትህ ማልክኮ እንዴ ምንድነው የተፈጠረው ያምሀል እንዴ ቆይ ምን አጠፋሁ ንገረኝ እንዴ ቆይ አቶደኝም አታፈቅረኝም 6 አመት ይቅርና 6 ወር የለፉበት ፍቅርኮ ያሳዝናል እእእ እንዴት ከመሬት ተነስተህ እንለያይ ትለኛለህ እናቴ የሰርጋችንን ቀን በጉጉት እየጠበቀች እኔ የምንጋባበት ቀኑ እርቆብኝ ሳለ እንደቀላል እንለያይ ትለኛለህ እእእእ ።( ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ነበር ልቤ ተከፍታ ለመውጣት ምንም አልቀራትም አንድ ቀን እንኳንኮ በመሀላችን አስታራቂ ገብቶ አያቅም ከፍ ያለ ፀብ ተጣልተን አናቅም አንድም ቀን ስለመለያየት አስበን አናቅም የመጀመሪያው ነኝ የመጀመሪያዬ ነው) የተፈጠረውን ነገር እንኳን አላብራራልኝም ፊቴን ቀና ብሎ አላየውም መናገር ሚፈልገውን ተናግሮ ሲጨርስ ሄደ ጥሎኝ እራሴን ችዬ መቆም እንኳን ስለከበደኝ እዛው ደገፍ ብዬ ቁጭ አልኩ መጮህ አማረኝ ማልቀስ አማረኝ አነዱ ልቤም አውቆ ነው አሁን ይመጣል ይለኛል አንዱ ልቤ ደሞ መቼም የውሸት በአባቱ አይምልም ይለኛል ግራ ገባኝ እንደምንም ተሟሙቼ ቤቴ ደረስኩ እናቴ ወደስራዋ ሄዳለች ማንም የለም እህቴም ብትሆን ውሎዋ ትምህርት ቤት ነው ቀጥታ ክፍሌ ገበሁ በቁም አልጋው ላይ ወደኩኝ አፌን በትራሴ አፍኜ ጮኩ ትራሴን ነከስኩት ምንም መፍትሄ የለም ስልኬን አነሳሁ ደወልኩኝ በሁለቱም ስልኩ block አድርጎኛል 😥.......... ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
በሰው ልጆች ከሚጠሩት ቃላት ሁሉ እጅግ የተዋበ ቃል "እናት" የሚለው ቃል ነው። እጅግ ቆንጆ አጠራርም "እናቴ" የሚለው ነው። በተስፋ እና በፍቅር የተሞላ፣ ከልብ የሚመነጭ ጣፋጭ እና መልካም ቃል ነው። እናት ሁሉንም ነገር ናት-በሃዘን ጊዜ መፅናኛችን፣ በስቃይ ጊዜ ተስፋችን፣ በደከምን ጊዜ ጥንካሬያችን ናት። የፍቅር፣ የምህረት፣ የርህራሄ እና የይቅር ማለት ምንጭ ናት። እናቱን ያጣ ያለ ማቋረጥ የምትባርከውና የምትጠብቀውን ንፅህት ነፍስ አጥቷል፡፡ ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
✍....እህቴ አንቺ ማለት ከወርቅ እና ከ ዳይመንድ በላይ ውድ መሆንሽን ብታቂ ከ መዳብ ጋር እራስሽን አታወዳድሪም ነበር።!!🍂 የማወራው ስለ ወርቅ እና መዳብ አይደለም ገባሽ ቆንጂት መልካም ቀን ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ
ፍቅር ማለት ልክ እንደ መጀመሪያው የማለዳ ጥሩ ቡና ነው። ያለ እርሱ ቀንህ ሙሉ አይሆንም፣ ልብህን ያደፋፍረዋል፣ ግን ትንሽ ከበዛ እንቅልፍ ይነሳሃል ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ