ድብቁ ህሊና
Статистика🌟 Inspiration | Growth | Success ✨ ለተሻለ ማንነት እና ለታላቅ ስኬት! 🧠 ጥቅሶችና አነቃቂ መልዕክቶች በየቀኑ። 📩 ለማስታወቂያ (Ads): @Subconscious_admin 🌐 Buy Ads via Telega.io👇 https://telega.io/c/subconscious2023
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 819
- 1/48двое суток
- 938
- 1/72трое суток
- 1 012
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Train hard⚡️ Stay focused.🤝
⚠️ 5 ዓመት ወደኋላ መለስ ብለው አምስት ደቂቃ ያስቡ! ዛሬ የምንኖረው ህይወት ከ5 ዓመት በፊት ያቀድነው ነው ወይስ በዘፈቀደ የመጣ? አብዛኛው ሰው ጠዋት ተነስቶ ማታ የመተኛትን አዙሪት "ህይወት" ብሎ ሰይሞታል። ነገር ግን እውነታው ይሄ ነው፦ ስትሮጥ ውለህ ማታ የቆምክበት ቦታ ላይ የምትገኝ ከሆነ፣ እየሮጥክ ያለኸው በሌሎች ትራክ ላይ ነው። የገንዘብ ነፃነት እና የህይወት እርካታ የሚመጣው ጠንክሮ በመስራት ብቻ አይደለም፤ በትክክለኛው መንገድ እና በትክክለኛው ራዕይ ላይ በመልፋት እንጂ። ጉልበት እያለዎት፣ ጊዜው ሳይረፍድ የራስዎን የህይወት ካርታ ሊስሉ ይገባል። ዛሬ ካልቀየሩት፣ ቀጣዩ 5 ዓመትም ከዛሬው የተለየ አይሆንም! አትፈላሰፍ... ተግብር! 🔥 ስኬታማ ውሎ ተመኘን 🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
የመፍትሄ ሰው ሁን ! ማደግ ከፈለግህ የመፍትሄ ሰው ሁን "#መፍትሄ_ወዳለበት_ገንዘብ_ይፈሳል " ስለዚህ ምንም የምሰራው አጣው ካልክ ውጣ እና ዞር ዞር ብለህ አካባቢህን ቃኝ ምን ምን የጎደለ ነገር አለው? ሰዎች ምን አስፈልጎቸዎል? በዚህ ምድር ላይ ያለ ስራ ሁሉ የተፈጠረው መፍትሄ ለመስጠት ነው ህክምናው፣ ትምህርቱ ፣ ምግብ ቤቱ ፣ ልብስ ሰፊው ፣ ሊስትሮው ሁሉም የሰዎችን ችግር በመቅረፋቸው ሰው ወደ እነርሱ እየሄደ ገንዘቡን ያፈሳል ! #እድለኛነታችን_የእኛ_ሀገር_ብዙ_መፍትሄ_የሚፈልጉ_ጥያቄዎች_መኖራቸው_ነው ስለዚህ የመፍትሄ ሰው እንሁን! ያኔ ከእኛም ተርፈን ለብዙው እንሆናለን! መልካም ቀን ተመኘን 🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
ሁሌ ለበአል ሀገራችን ሰላም ከሆነች በግ አመጣለሁ ብሎ የሚሳል ልጅ አለ... ይሄው እሱ ብቻ ነው ከፍሎ የማያውቀው😂😂
📌 ዛሬህ ሊመለስ አይችልም ⏳ ትናንት አልፏል። ነገ እርግጠኛ አይደለም። ያለህ ዛሬ ብቻ ነው። መሽቶ ሲነጋ አንድ ቀን ህይወትህ ቀንሷል። ወደ #መጨረሻህ እየቀረብክ ነው። ታዲያ ዛሬህን እንዴት ትኖረዋለህ?በፍርሃት? በምኞት? ወይስ በድፍረት እና በአላማ? ህልምህን ዛሬ ኑር። ምክኒያቱም በዚህ ሳምንት ሰኞ ዛሬ ብቻ ያለህ ሌላ ሰኞ የለህም። 🔥 #ህይወት_አታባክን #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗ
ከአዲስ ጀምር ! አዲስ ነገር በህይወታችን እንዲፈጠር ከፈለግን አዎ የትላንት ነገሮቻችንን በሙሉ ትተን መነሳት ይኖርብናል ትላንት በነበረን ማንነት #የማንፈልገውን_የአሁን እኛን ሰጥቶናል ስለዚህ ልንለቀው እና ሙሉ ለሙሉ ከአዲስ እውቀት ከአዲስ እይታ ከአዲስ ማንነት መጀመር አለብን ! መልካም ሰንበት ተመኘን 🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
"እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!" አንዳንዴ የሆነ ቦታ ላይ የምንፈልገው ነገር ይኖራል ከእርሱ ውጪ ምንም ነገር የሌለ ይመስለናል ፤ አልተሳካም ማለት በቃ አለቀልን መንገድ ላይ መቅረታችን ነው ፣ የእኛ ነገር አበቃ ተበላሸ ይመስለናል ግን ደግሞ ከአጠገቡ ሌላ ትልቅ እድል ትልቅ ህይወት ተቀምጦ ይጠብቀናል የፈጣሪ አላማ እኮ ሁሌም ለእኛ #የሚበጀውን መስጠት ነው እንጂ ፈፅሞ #ሊጥለን_አይፈቅድም የአንዱን በር ሲዘጋብን ሌላውን ወለል አድርጎ እየከፈተው ነው ስለዚህ አትቁም ዞር ዞር ብለህ ተመልከት ይሄ ተዘጋ እንግድያው ያ ተከፍቷል በል መቼም አትቁም! መልካም ቀን ተመኘን 🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
ተስፋ የማይጠፋ ብርሃን ሕይወት ሁልጊዜ ቀላል መንገድ አይሆንም። አንዳንድ ጊዜ ዝናብ ይዘንባል፣ አንዳንድ ጊዜ ነፋስ ይነፍሳል ፣ አንዳንድ ጊዜም መንገዳችን በጨለማ ይሸፈናሉ። ነገር ግን ጨለማ ለዘላለም አይቆይም፤ ከእያንዳንዱ ሌሊት በኋላ ንጋት እንደሚመጣ ሁሉ፣ ከእያንዳንዱ ፈተና በኋላም ተስፋህ ይመጣል። ታላላቅ ሰዎች የተለዩት ችግር ስላላጋጠማቸው አይደለም፤ ችግርን ፊት ለፊት ተጋፍጠው ስላልተሸነፉ እንጂ። ውድቀት የመጨረሻ አይደለም፤ ዳግም ለመነሳት የሚሰጥ ዕድል ነው እንጂ። ዛሬ የምትጓዘው መንገድ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ነገ የምትኮራበት ታሪክ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በራስህ እመን፣ በተስፋ ኑር፣ በጥረትህም ቀጥል። የሚያበራው ሻማ ራሱን እየቀለጠ ነው የሚያበራው፤ እንዲሁም ትዕግሥትና ጥረት የተሻለ ሕይወት ያበራሉ። ተስፋህን አትልቀቅ፤ ምክንያቱም ታላላቅ ስኬቶች ብዙ ጊዜ ከታላላቅ ፈተናዎች በኋላ ይመጣሉ። #ዛሬን_በተስፋ_ኑራት መልካም ጁመዓ ተመኘሁላቹ 🥰🥰 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
💡ሰዎች በየቦታው ፍጹም ትክክል መስለው ሲታዩ ሰውኛ አይመስለኝም ። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል። ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ። ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም። ራስን መሆን ጥንቃቄ አያሻም። መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ። 💎እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል ። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ። ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም ። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል። 💡እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ሞኝ ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል ። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል ። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ። 📖 ጠበኛ እውነቶች ✍ሜሪ ፈለቀ ውብ ቀን ተመኘን 🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
የገንዘብ እውቀት ያለው ሰው አንድን ነገር ለመግዛት 1,000 ብር ሲያወጣ፣ የሚያየው የሚገዛውን እቃ ብቻ ሳይሆን ያ 1,000 ብር ኢንቨስት ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ወደፊት ሊያመጣው የሚችለውን ትርፍ ጭምር ነው። ለምሳሌ ዛሬ ለማያስፈልግህ ጌጥ የምታወጣው ገንዘብ፣ ከ10 ዓመት በኋላ ሊኖርህ የሚችለውን ትልቅ ሀብት የመሰዋት ያህል ነው። ማንኛውንም ብር ስታወጣ "ይህ ብር ኢንቨስት ቢደረግ ኖሮ ምን ሊያመጣ ይችል ነበር?" ብለህ ጠይቅ። 📕 ርዕስ፦ የገንዘብ ሳይኮሎጂ ✍️ ደራሲ፦ ሞርጋን ሃውሰል #መጽሐፉን በመጽሐፍት መደብር ያገኙታል! 📚 መልካም ቀን ተመኘን #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
አልኬሚስቱ አለም ላይ ብዙ ከተሸጠ እና ብዙ ከተነበብት መፅሀፎች ውስጥ ምርጥ 10 ውስጥ ያለ ነው የእውነት ጀምሩት
ሁሉንም ታልፋለህ! በሰዎች መካከል #ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን አስብ! #መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ #ብርሀን_ማየት_የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት! ሰናይ ማክሰኞ ተመኘን #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
የሚያቆምህ ነገር የለም ! ለፈጣሪህ የችግርህን ታላቅነት አትንገረው፤ በተቃራኒው ለችግርህ የፈጣሪን ታላቅነት ንገረው! ያኔ ችግርህን ከላይ ወደታች ማየት ትጀምራለህ። የሚያስገርም ለውጥ የምትፈልግ ከሆነ አይንህ ከገጠመህ ችግር ትልቀት ላይ አንሳውና የፈጣሪን ታላቅነት አስብ፤ ከዛ አንተን መቼም እንደማይተውህ እመን! ይሄን ስታደርግ የሚያቆምህ ነገር የለም! #መልካም ቀን #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
ተመስገን!🙏 ከፍ ዝቅ የሚሉ ስሜቶችን ታግሶ ለዛሬ መድረስ ቀላል አይደለም፤ ራስን #ለመለወጥ ወስኖ መንገድ መጀመር ቀላል አይደለም፤ ከባዱን እያደረክ ነው። ለውጥ የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ የሚጨርሱ ግን ጥቂት፤ #ከጥቂቶች አንዱ ለመሆን ምስጋናን የሚያክል ሀያል ነገር የለም። ስለዚህ በዚህ የለውጥ ጉዞ እስከ ፍፃሜ መጓዝ የሚፈልግ 'ተመስገን' ይበል! #ድንቅ_ሰንበት_ብለናል🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
መንጋቱ አይቀርም⛅️! ጓደኞችህ ሲሳካላቸው ስታይ እኔስ ግን መቼ ነው የምቀየረው ብለህ አትዘን ፀሀይ🌞ና ጨረቃ 🌝 እኩል አይወጡም ልፋትህ እንደ ፀሀይ የሚያበራ ከሆነ ጨረቃዋ እስክትገባ #ታገስ! ጥረትህን ካላቆምክ መንጋቱ አይቀርም! #ሠላማዊ_ቀን🕊 #ተመኘን!🙏 #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
ከውጥረትህ ውጣ! የሰው ልጅ የሚደክመው የሚረሳው የሚጨነቀው አዕምሮው እረፍት ሲያጣ ነው እንጂ አካሉ ስራ ስላበዛ አይደለም፤ የምትሰራው ስራ ወይም የምታስበው ሀሳብ ከበዛብህ ትንሽ ግዜ ለራስህ ስጠው ፤ እረፍት አድርግ ተረጋጋ ራስህን ሰብስብ እና ደግመህ ተነሳ ያኔ ሁሉም ነገር ካሰብክበት በላይ ሲቀልህ ታየዋለህ! የተሳካ ቀን ተመኘው #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
አትጓጓ! ለነገሮች በጣም የምትጓጓ ከሆነ ያ ነገር እንዳይሳካ መንገድ እየከፈትክ ነው፤ ቢሳካ ራሱ እንደጠበከው አትደሰትም። በጓጓህ ቁጥር አይምሮህ ውስጥ የዛ ነገር ምስል አለመጠን ይገዝፍና የተግባር #ሰው መሆን ይከብድሀል። ለህይወት ጣዕም እንድታጣ ያደረገህ መጓጓት ነው፤ አሁንም እየጓጓህ የሀሳብ ሰማይ ላይ መንሳፈፍ ካላቆምክ ብዙ ነገር ታጣለህ! ወዳጄ #አጥብቀህ_ፈልግ_ግን_አትጓጓ አለዚያ ስህተትህ በዝቶ ከመንገድ ትቀራለህ! ልዩ ዕሮብ ተመኘን #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ
አስታውስ ከዚህ በፊት ያላገኘኸውን ነገር ለማሳካት፣ ከዚህ በፊት ያላደረግከውን ነገር ማድረግ አለብህ፡፡ ከዚህ በፊት ሆነህ ወደማታውቀው ሰው መለወጥ አለብህ፡፡ የምትመኘው ምንም ይሁን ምን፣ መስዋዕትነት፣ ጊዜ መስጠት፣ጥረት እና ራስህን መገሠፅ ያስፈልግሃል። ምን ያህል ዋጋ እንደምታወጣ ወስንና ያንን ዛሬውኑ መክፈል ጀምር። 📓 ቢዝነስ ማይንድ ✍ብሪያን ትሬሲ ሰናይ ማክሰኞ ተመኘን #ድብቅ_ህሊና 🧠🔥 @Subconscious2023 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ 🔕 ˡⁱᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ