- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 73
- 1/48двое суток
- 83
- 1/72трое суток
- 90
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/u9vefFYPyWo?si=KFEoa_m_gGwh2C87
ፅንሰታ ለማርያም እንኳን ለነሐሴ7 ፅንሰታ ለማርያም በዓል በሰላም አደረሳችሁ ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር: እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱጻድቃን ደጋግ ሰዎች ነበሩ:፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረላቸውባለጸጎች ነበሩ::ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅአልነበራቸውምና መካን ነበሩ:፡ አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን: አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት::እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳአንስ ላደርገው በልቡናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቀኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለዱ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቶአችኋል በሳህሉ መግቧቸኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳችሁ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ ከቤታችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው: እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች:ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርምእንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት ;ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም: ይህቺም ሃና በስርዓት አደገች፡፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧት:: እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ:፡ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡- ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋየምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች:፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች:፡እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተእግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው: ምልአቱ: ስፍሃቱ:ርቀቱ: ልእልናው: ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:፡ ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታበራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው::ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው: ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየንነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንናሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡: እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበትመግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሐት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይን ፣ምድርን፣ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች:: ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን- አሜን ፡፡
без подписи
💒ሰአሊ_ለነ_ቅድስት (ሠዐሊ ለነ ቅድስት)" "ቅድስት ሆይ ለምኝልን" (ቅድስት ሆይ ሣይልን) ሰአለ ማለት ለመነ ፣ማለደ ፣ጠየቀ ማለት ሲሆን ሠዐለ ማለት ደግሞ ሣለ(ለሥዕል)፣ቀረፀ ማለት ነው። የመጀመሪያው ቅድሰት ሆይ ለምኝልን፣ ማልጅልን፣ ከፈጣሪያችን ምህረትንና ይቅርታን ጠይቀሽ አሰጭን ሲሆን ሁለተኛው ምሥጢር አእምሮ (ዕውቀት) ፣ ለብዎ( ማስተዋል) ጥበቡን በልቡናችን ሣይብን አሳድሪብን ማለት ነው። "ቅድስት" ማለትም ንጽሕት፣ክብርት፣ፅንዕት፣ ልዩ ማለት ነው። 💒ንጽሕት ተብላ ስትጠራ እንደሌሎቹ ፍጡራን ፣እንደሌሎች ሴቶች አይደለም፣ ሌሎች ሴቶች ከገቢር(ኃጢአት ከመሥራት) በነጹ ከነቢብ(በአንደበት ከመበደል) አይነጹም፣ ከነቢብ ቢነጹ ከኀልዮ(በሀሳብ ኃጢአት መስራት) አይነጹም እመቤታችን ግን በዘህ ንጽሕት ናትና " ዐቀባ ጰራቅሊጦስ እምከርሠ እማ ወኢረኲሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ እምፅቡር ጽሩየ ገብራ ድንግል በኅሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ" " ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ጠበቃት፣ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን አላደፈችም፣ከአፈር ንጽሕት አደረጋት፣ እርሷም በሀሳቧና በሥጋዋ ድንግል ናት" እንዲል። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንን መስክሯል ሉቃ 2:27፣ ኤልሳቤጥም እንዲሁ። 💒ክብርት ፦ ሌሎች እናቶች ነገሥታትን ፣ጳጳሳትን ካህናትን ......በመውለዳቸው ይከበራሉ እመቤታችን ግን አምላክ፣ንጉሠነገሥት፣ሊቀ ካህናት ..... ኢየሱስ ክርስቶስን ስለወለደች ክብሯ ልዩ ነው፣ ስለዚህም ክብርት ትባላለች። 💒ፅንዕት ፦ ማለት የፀናች ማለት ነው፣ሌሎች ሴቶች ቢፀኑ እስከ ጊዜ ተፈትሖ ማኅፀን ነው ከዛ በኋላ ፅናት የላቸውም እመቤታችን ግን ከመፅነሷ በፊት፣ ከፀነሰችም በኋላ፣ከመውለዷ በፊት ከወለደችም በኋላ ለዘለዓለም ፅንዕት ናት። 💒ልዩ ፦ እናትነትን ከድንግልና፣ድንግልናን ከእናትነት አስተባብራ ይዛ የተገኘች ብቸኛ ሴት ናት፣ የሥላሴን ዙፋን የተሸከመች፣ መላእክት በሰማይ እየራዱ እየተንቀጠቀጡ የሚያመሰግኑትን አምላክ እርሷ 9 ወር ከ5 ቀን በማህፀን ተሸክማዋለች፣አዝላዋለች፣አቅፋዋለች፣ እርሱንም ተሸክማ በግብፅ በረሃ ተንከራታለች፣ የእኛ የሕይወት ምግብ የሆነው እንጀራችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሷ በኩል አልፎ፣ ተጋግሮ፣በስሎና ጣፍጦ የመጣ ነው ልዩ ናት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ የልጅዋ ቸርነት ይጠብቀን። ሀገራችንንም ሰላም ያድርግልን አሜን።
без подписи
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን 🌿ጾመ_ፍልሰታን_ለምን_እንጾማለን ? ጾመ ፍልሰታ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ተብሎ ተወስኖ ይጾማል። 🌿ፍልሰታ ፈለሰ- ፈለሰ :- ፈለገ፣ ተሰደደ (ተገለጠ) ፣ መከፈት፣ መገለጥ፣ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሳኤ ያመለክታል። 🌿የጾሙ ዋና ምክንያት ሐዋርያት የእመቤታችንን የእረፍቷን ነገር አስመልክተው የጾሙት ፆም ነው። 🌿ታሪኩን በአጭሩ እንዲህ እንመለከታለን :- 🌿እመቤታችን በጥር በ21 እሁድ ቀን አርፋለች ። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሴማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል። ዛሬ ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ስለዚህ አስክሬኗን በእሳት እናቃጥላለን ብለው ተነሱ 🌿ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሯን ጨበጠው መልአኩ ሁለት እጁን ቆረጠው፣ እጁ ከአጎበሩ ተንጠጥሎ ቀረ ከዚህ በኋላ መላዕክት የእመቤታችንን አስከሬን ወስደው በገነት አኑረዋታል። 🌿በ8 ወሩ በነሐሴ ሐዋርያት ከነሐሴ1-14 ጾም ጸሎት ይዘው አስከሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎት እና በምህላ እሑድ ሥጋዋን ቀብረዋታል። ማግሰኞ ተነስታለች። ከመትንሳኤ ወልዳ/ እንደ ልጇ ትንሳኤ ያሰኘው ይህ ነው፡፡ በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይም ከ12 ቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ አልነበረም። 🌿ቅዱስ ቶማስም ደመና ጠቅሶት ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት፣ ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ/ ከሚጓዝበት የደመና ጉዞ ላይም ለመውደቅ ወደደ ተበጠበጠ፣ ቀድሞ የልጇን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ፣ አይዞህ አትዘን ወንድሞችህ ሐዋርያት ትንሳኤዬን እንጂ ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ፣ ተነሳች አረገች ብለህ ንገራቸው ብላ ምልክት ይሆነው ዘንድ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። 🌿 ከዚህ በኋላ ቶማስ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው አግኝተን ቀበርናት አሉት፣ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይሄ ነገር አይመስለኝም አላቸው። 🌿 ቅዱስ ጴጥሮስም አንተማ ልማድህ ነው ፣ አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም አንተ እየተጠራጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው። 🌿እርሱም የያዘውን ያውቃልና ፀጥ ብሎ ይሰማቸዋል። ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፍተው አጣት፣ ደንግጦ ቆመ፤ አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነስታ፣ አርጋለች አላቸው የያዘውን ሰበን ሰጥቶአቸው ለበረከት ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተበታትነዋል። 🌿 በዚህ ምክንያት በአመቱ ቶማስ ትንሳኤሽን፣ ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ቅዱሳን ሐዋርያት ነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ ሱባኤ በጀመሩ በ14 ተኛው ቀን ትኩስ በድን አድርጎ ሰጣቸው ከቀበሯትም በኋላ በነሐሴ 16 ቀን በክብር ተነስታለች። 🌿 በዚህ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሶ እመቤታችንም ከልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህቺን ጊዜ ትጾማለች። 🌿እኛም ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሱባኤውና በጾሙ ስንጠነክር የእሷ አማላጅነት የልጇ የመድኃኔዓለም ቸርነት ከመከራ ስጋና ከመከራ ነፍስ አድኖ ለንስሐ ጥሪ እንደሚያበቃንና ቅዱስ ስጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንደሚፈቅድልን አምነን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባናል ። 🌿ጾሙን -የበረከት -የጤና -የጽድቅ -የመተሳሰብ -የፍቅር -የሰላም ያድርግልን ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክቡር ።
без подписи
ስለምን ይጨነቃሉ? ፩•ስለ ኃጢአትዎ?-አይጨነቁ "ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።" ይላል (ኢሳ ፩÷፲፰)- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።"(ማቴ 11÷28) ፪• ስለ ሞት?-ምንም አያስቡ " ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።* (ዮሐ 11÷26) -" ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።" (ምሳ 13÷14) ፫• ስለ ፍርድ ቀን? ፣በጭራሽ " ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።" ይላል ( ማቴ24÷44) - "ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።" ተብሏል(ዮሐ 6÷40) ፬• ስለ መከራ? ፣ አያስቡ ቅዱስ ጳውሎስ "እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ክፉም ደጉም ለበጎ መሆኑን ያስታውሱ።" ፣ብሎዎታል (ሮሜ 8÷28) ፭• ስለ ጤንነትዎ ? "ምን በወጣዎት " ልብሱን ብቻ የዳሰሰው እንደሆነ እድናለሁ ያለችውን ሴት ያስታውሱ ••• ልብ ይበሉ ።" የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች። ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ ብላለችና። ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ። ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ።" ( ማር 8÷27-30) ፮•ስለ ሀብት?: የሚያሳስብዎ አይሁን! " ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።፤ ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።የተድላ ምድር ትሆናላችሁና አሕዛብ ሁሉ ብፁዓን ብለው ይጠሩአችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።"( ት•ሚል፫÷፯-፲፪) ፯• ስለ ሥልጣን? አይቸገሩ " በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፣ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤ እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" ፣የሚለውን ያስታውሱ ( ማር 10÷43-44) ፰• ስለትዳር ፣? ሐሳብ አይግባዎ ።" የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።"፣(ዘፍ 24÷7) ብሎ ባሪያዎቹን የላከ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ መልካም ሚስት እንዳገኘለት አይዘንጉ።ስለዚህ ለእርስዎም እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አጋዥ ያገኛሉ እርስዎ ግን በጸሎት ይትጉ! ጠቢቡ ሰሎሞን " ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።"ይላል ( ምሳ ፲፱÷፲፬) ፱•ስለ ቤተሰብዎ ? ችግር የለም ። -በጸሎት በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አቅርቡ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ይላል ( ፊልጵ ፬÷፮) ፲• ስለ ሰዎች? በፍጹም አይጨነቁ:ቅዱስ ጳውሎስ " በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል።የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።"ይላል ሮሜ ፲፬÷፩-፭) እነዚህ የተጠቀሱት ነጥቦች በጣም ጠቃሚ የሆኑ ናቸውና በተረጋጋ ሁኔታ ሆናችሁ እንብቡት በያላችሁበት የሰላም አምላክ ሰላሙን ያብዛላችሁ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ። 🌿ሁል ጊዜ ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇። 💠በዩትዩብ https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ 💠በፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/ 💠በቴሌግራም https://t.me/hameretsidk 💠በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1
https://youtu.be/wklq5Xp74yE?si=Cr2mKIexwCt-l42I
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። ❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው። ❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡ ❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡ ❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡ ❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል። ❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ዐምስት መቶ ሦስት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨ 🌿ሁል ጊዜ ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇። 💠በዩትዩብ https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ 💠በፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/ 💠በቴሌግራም https://t.me/hameretsidk 💠በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1
без подписи
https://youtu.be/i7lU4c4DOmE?si=WlX4ip3EWeNTpfmK
ጠቃሚና ወሳኝ የሆኑ ትምህርቶቾ የሰው ልጅ በመጀመሪያ በሕገ ልቦና እንዲሁም በሕገ ህሊና በሕግ ሊጸና ለእግዚአብሔርም ሊታዘዝ ተፈጥሮ ነበር: ይህን ማድረግ ባለመቻሉ በጧትና በማታ እያነበበ: እያየም ሰው የሆነ ሁሉ እንዲጠብቀውና እንዲፈጽመው እግዚአብሔር አምላክ ስለፈቀደ ሕጉን በጽሁፍ ሰጠው እነዚህ በጽሁፍ የተላለፉ የብሉይ ኪዳን ሕግጋት ለክርስቲያኑ ህዝብ አሁንም አስፈላጊዎች ናቸው። + ከአሠርቱ ቃላት ዘጠኙ ተጠብቀው አንደኛው እንኳን ከፈረሠ አሠርቱ ሕግጋት ሁሉ እንደፈረሱ ይገመታል እንጂ የዘጠኙ መጠበቅ ምንም ዋጋ የለውም። ለምሳሌ አሥር በር ያለው ቤት ቢኖር ዘጠኙ በሮች ቢዘጉና አንዱ ክፍቱን ቢያድር: ሌባ ክፍት በሆነው በአንደኛው በር ገብቶ ንብረቱን ሁሉ ከወሰደው የዘጠኙ በሮች መዘጋት ምንም ጥቅም አላስገኘም ማለት ነው የአንደኛው መከፈት ለንብረቱ መጥፋት ምክንያት ሆኗልና። አሠርቱ ቃላትም በትክክል ካልተጠበቁ ዋጋ የማያሰጡ መሆናቸውን ሐዋርያው ያዕቆብ እንዲህ ሲል ያስረዳል:- " ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ። አትግደል ብሎአልና፤" (የያዕቆብ መልእክት 2:10) ።።።።።።። 10ቱ ትዕዛዛት እነማን ናቸው ።።።።።።። >አንቀጽ 1:- " ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።" (ኦሪት ዘጸአት 20:3) ።።። >አንቀጽ 2:- " የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። " (ኦሪት ዘጸአት 20:7) ።።። >አንቀጽ 3:- " የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።" (ኦሪት ዘጸአት 20:8) ።።። >አንቀጽ 4:- " አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።" (ኦሪት ዘጸአት 20:12) ።።። >አንቀጽ 5:- ፤ አትግደል። (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 20:13) ።።። >አንቀጽ 6:- ፤ አታመንዝር። (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 20:14) ።።። >አንቀጽ 7:- ፤ አትስረቅ። (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 20:15) ።።። >አንቀጽ 8:- ፤ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር። (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 20:16) ።።። >አንቀጽ 9 ፤ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ። (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 20:17) ።።። >አንቀጽ 10 " ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ " (ኦሪት ዘሌዋውያን 19:18) ++++++ ።።3።። ስድስቱ ሕግጋት (ትዕዛዘተ) ወንጌል:- እንደ ብሉይ ኪዳን እምነት ስርዓት ህግን እንደፈፀመ የሚቆጠረው ፍፁምም አይሁዳዊ ነው የሚባለው አሠርቱ ቃላተ ኦሪትን የጠበቀው ነበር። በሐዲስ ኪዳንም አሠርቱ ቃላተ ኦሪት ምንም ሳይነኩ እንደተጠበቁ ሆነው በተጨማሪ ሌሎችም አዲሶች ሕጎች አስፈለጉ። አሠርቱ ቃላተ ኦሪት መጠበቃቸውንና እንዳሉም መጽናታቸውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5:17-18) ሲል ግልጽ አድርጎ ተናግሯል። +ከዚህ በተጨማሪ ግን እነዚህኑ አሠርቱ ቃላትን በስድስቱ አንቀጽ አጠቃሎና አሳጥሮ ቃላተ ወንጌል ወይም ትዕዛዛተ ወንጌል ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ግን እላችኋለሁ እያለ አጥብቆ: አጽንቶና ወስኖ ተናግሮ ይገኛል። አሁንም የሐዲስ ኪዳንን ህግጋት ስናቀርብ እነዚህ የብሉይ ኪዳን ህግጋት ለሐዲስ ኪዳን መሸጋገሪያ ሆነው አጥረውና ተጠቃልለው በስድስት ቃላት ይቅረቡ እንጂ አሁንም መሠረቶቹ አሠርቱ ቃላት ናቸው። ሆኖም አጥረው: ተጠቃለው ከበድም ብለው ለሐዲስ ኪዳን መታወቂያ መለያም ሕግ ሆነው የቀረቡ ሲሆን እነዚህን ሕግጋት ለይቶ: ጠንቅቆ ማወቅና መጠቀም በጣም አስፈላጊ በመሆኑ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል:- ።።። >አንቀጽ 1:- አትግደል ላለው " ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።" +++++++ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።" (የማቴዎስ ወንጌል 5:21÷22) ።።። >አንቀጽ 2:- አታመንዝር ላለው " አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል።" +++++++ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።" (የማቴዎስ ወንጌል 5:27÷28) ።።። >አንቀጽ 3:- መፍታት እንደማይገባ ፤ ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ። ++++++ ፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5:31÷32) ።።። >አንቀጽ 4:- ፈጽመህ አትማል ላለው ፤ ደግሞ ለቀደሙት። በውሸት አትማል ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ እንደተባለ ሰምታችኋል። +++++++ ፤ እኔ ግን እላችኋለሁ። ከቶ አትማሉ፤ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤ ፤ በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ ፤ በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። ፤ ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5:33-37) ።።። >አንቀጽ 5:- "ክፉውን በክፉ አትቃወሙ" ፤ ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። +++++++ ፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5:38-39) ።።። >አንቀጽ 6:- "ጠላትህን ስለመውደድ" ፤ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። +++++++ ፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ፤ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ፤ ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ፤ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5:43-48) +++++++ ።።4።። አሥሩ አንቀጸ ብፁዓን:- ስድስቱ ቃላተ ወንጌል የአስርቱ ቃላተ ኦሪት መጠበቂያ እንደሆኑ አንድም አሠርቱ ቃላት በስድስት ቃላተ ወንጌል እንደጸኑ ስድስቱ ቃላተ ወንጌል ደግሞ በአሥሩ አንቀጸ ብፁዓን ይታጠራሉ: ይጸናሉ: ፍጹምነታቸው እንዲታወቅ ይሆናል።
እንኳን ለሐምሌ7 አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ✤✤✤ ሐምሌ ሥላሴ፡፡ በዚህ በሐምሌ 7 ቀን ቅድስት ሥላሴ ለአብርሃም የተገለጹበት ነው፡፡ ይኸውም ስለ 3ት ምክንያቶች ነው፤ 1ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል/ ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጎ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበርና)፡፡ እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ (ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤ ለዳንኤል በአረጋዊ፣ ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፣ ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል)፡፡ ምግብ የማይመገቡ ሥላሴም በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤ ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡ ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤ አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡ 2ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያለው ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡ 3ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈን በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤ ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤ ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤ ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡ በማለት አመስግኗል በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን በመባረክ ጉድለቱን ሁሉ የሞሉ ሥላሴ የኛንም ጉድለት በበረከት እንዲሞሉ እኛም መልካም ሥራ ሠርተን እንደ አብርሃም በረከት ተቀባዮች እንድንሆን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን አሜን ። 👇 🌿ሁል ጊዜ ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇። 💠በዩትዩብ https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ 💠በፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/ 💠በቴሌግራም https://t.me/hameretsidk 💠በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1
без подписи
ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ✝ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡ ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ✝ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን። ጴጥሮስና ጳውሎስ ጽኑዕ ነው ፍቅራቸው፤ በተጠሩ ጊዜ ሞትም አልለያቸው፤ ፍቅራቸውን አውቆ አንድ ቀን ጠራቸው፡፡ ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ✝ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ። 🌿ሁል ጊዜ ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ 👇 💠በዩትዩብ https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ 💠በፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/ 💠በቴሌግራም https://t.me/hameretsidk 💠በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1
ሐመረ ጽድቅ: እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት እንዲሁም ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርኃዊ በዓል አደረሳችሁ፡፡ ✤ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ ✝ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ፤ በገሊላ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ የአባቱ ስም ዮና የእናቱ ስም ሃውኒን ይባላል፡፡ ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነው የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም እንዳወጣችለት ይነገራል፡፡ ✝ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ፤ ነገዱ ከዕብራውያን ከብንያም ነገድ ነው አባቱ ዮስኤል ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ጠርሴስ በንግድ የታወቀች የኬልቅያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሐገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀ የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ፡፡ በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዐት እየተማረ እስከ 3ዐ ዓመቱ ቆየ፡፡ በ3ዐ ዓመቱ የአይሁድ ሸንጐ አባል ሆኖ ተቈጠረ፡ ✝ለአገልግሎት_አጠራራቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረው መረቡን ታንኳውን እንዲሁም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶን ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ይህን በጽርዕ ቋንቋ «ዐለት» ማለት ነው በአራማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሐዋርያ ነው፡፡ ማቴ 26፥34 ነገር ግን 3 ጊዜ ጌታችንን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ዶሮ በጮኸና አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ ንስሐ ገባ፡፡ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለየው ጊዜ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱን ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለትም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኃዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንስሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፥15-17 ✝ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመኾኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣማ> ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡ በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ካገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል፥ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኃኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ 9፥1 የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡ ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር መሄዱን ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2,ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፤ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም. ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ54 ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያሳለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡ ✝እረፍታቸው
без подписи
https://youtu.be/t6Qv07psUDA?si=7MU4oIu_gESkFrNc የሐምሌ 7ወረብ
https://youtu.be/ZFVPbGHdzxQ?si=XhagDfXsE09uLLRN