Tikvah_University
Статистика- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 30
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Образование
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 186
- 1/48двое суток
- 1 359
- 1/72трое суток
- 1 465
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📢 Advertising in this channel You can place an ad via Telega․io. It takes just a few minutes. Formats and current rates: View details
#MekelleUniversity በ2018 ዓ.ም ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ የክረምት ስልጠና መርሐግብር ለመከታተል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መምህራን ምዝገባ ከሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዓዲ ሓቂ ግቢ ይካሔዳል፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ ● የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ የCOC IV ምስከር ወረቀት ዋናውና ኮፒው ● የመታወቂያ ካርድ እና ጉርድ ፎቶግራፍ
#AAU #GAT በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ሐምሌ 23 እና 24/2018 ዓ.ም በጠዋት እና ከሰዓት ፈረቃ ይሰጣል። ፈተናው ከግንቦት 30 እስከ ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ምዝገባ ላደረጉ አመልካቾች የሚሰጥ መሆኑን ከዩነቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ ከሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ምዝገባ የምታደርጉ አመልካቾች ፈተናችሁን ነሐሴ 07 እና 08/2018 ዓ.ም በሚሰጠው 2ኛ ዙር የGAT ፈተና የምትወስዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ለፈተናው የተመዘገቡ ማየት የተሳናቸው ተፈታኞች በሙሉ ዋናው ግቢ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ላብ 1፣ አርብ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም ከሰዓት ፈተናቸውን የሚወስዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በስህተት ሌላ የመፈተኛ ክፍል ተመድበው ከሆነ በቀጥታ ለአካል ጉዳተኞች ማዕከል ላብ 1 በዕለቱ ሪፖርት ያድርጉ ተብሏል፡፡ (የተፈታኞች ኮድ፣ ስም ዝርዝር፣ የመፈተኛ ቦታ ዝርዝር መርሐግብር እንዲሁም የፈተና መመሪያ በAAU Testing Center ይፋዊ አድራሻ መመልከት ይችላሉ፡፡)
#ጥቆማ አዲስ ሠልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክ አካዳሚ አሳውቋል። በኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ESL) ስር የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ፣ አዳዲስ ሠልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን የትምህርት እና የመሠረተ ልማት ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጿል። አካዳሚው ዘመናዊ የማስተማሪያ መሠረተ ልማት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ካሪኩለሞች እና ብቁ የማስተማር አቅም በማሟላት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ መሆኑን የአካዳሚው ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ገልፀዋል። ሲሙሌተሮች በመጠቀም እና በባቦጋያ ሐይቅ ላይ በሚካሄዱ የተግባር ስልጠናዎች በከፍተኛ የደህንነት እና የጥራት ደረጃ ለማከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ጠቁመዋል። አካዳሚው ከመሠረታዊ የባህር ላይ ደህንነት ስልጠናዎች ጀምሮ እስከ የመርከብ መኮንንነት ፕሮግራሞች በዓለም አቀፉ የባህር ድርጅት (IMO) መስፈርቶች መሰረት የተዘጋጁ ስልጠናዎችን ለመስጠት መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል። #ESL @tikevah_university
በቀዶ ሕክምና የስፔሻሊቲ ትምህርትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሔደበት ወቅት ነው። ጤና ሚኒስቴር ለስፔሻሊስት ሐኪሞች በሚሰጠው የቀዶ ሕክምና ትምህርት በAI የታገዙ ኮርሶችን አካቶ ለመተግበር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ሳህረላ አብደላ ገልፀዋል፡፡ የጤና ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተቃኘ እንዲሆን ሚኒስቴሩ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመሥራት ከስምምነት መድረሱን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ጤና ሚኒስቴር ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙ የጤና አገልግሎቶችን መተግበር መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሕክምና አሰጣጥን ለማሳለጥ፣ አንዳንድ የዲያግኖስቲክ ችግሮችን ለማወቅ የሚፈጀውን ጊዜ ለማሳጠር፣ የላቦራቶሪ ውጤት ትክክለኛነትን ለማሻሻል፣ በሰው ዓይን ሊታዩ የማይችሉ ነገሮች ጎልተው እንዲታዩ ለማድረግና በሌሎችም ሕክምናዎች ላይ ከፍተኛ ዕገዛ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ አብራርተዋል። ይሁን እንጂ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚሰጣቸው መረጃዎችን የማጥራት እንዲሁም የቁጥጥር ሥራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ #ሪፖርተር @tikevah_university
"ትምህርት ቢሮው የራሱን ፈተና አዘጋጅቶ ላልተፈተኑ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሰጣል።" - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ "ማንኛውም ክልል የሀገር አቀፍ ፈተና የማውጣት እና የመፈተን ስልጣን የለውም" - የፌዴራል መንግሥት የወረቀት ፈተናውን ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም ለመስጠት ታቅዷል። - የፌዴራል መንግሥት "ትምህርት ሚኒስቴር በወረቀት ለሚፈተኑ የትግራይ ተማሪዎች የፈተና ወረቀት አላከም" ያለው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ የራሱን ፈተና አዘጋጅቶ ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚሰጥ አሳውቋል። ሰኔ 29/2018 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ በወረቀት ሊፈተኑ የነበሩ 15,349 ተማሪዎች ፈተናው ከፌደራል መንግሥት ስላልተላከ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዳይጓዙ መደረጉን የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) ተናግረዋል። "ፈተናው በአውሮፕላን የሚመጣና በፌዴራል ፖሊስ የሚጠበቅ በመሆኑ፣ ወደ ትግራይ እንዳይላክ የሚያደርግ ምንም ዓይነት ምክንያት የለም" ያሉት ኃላፊው፤ "ውሳኔ ፖለቲካዊ ነው" ሲሉ ገልፀዋል። "የክልል ካቢኔ የፈተና ወረቀቱ በወቅቱ እንዲላክ ለፌዴራል መንግሥት ደብዳቤ አስተላልፏል። እስካሁን አውንታዊ ምላሽ አላገኘም" ብለዋል። በዚህም ትምህርት ቢሮው የራሱን ፈተና አዘጋጅቶ ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ አመልክተዋል። የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ "በራሴ ፈተና አዘጋጅቼ እፈትናለሁ" ማለቱን ተከትሎ፣ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፌዴራል መንግሥት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ታማኝ የመረጃ ምንጭ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል። እኚሁ ምንጭ "ይህን ፈተና የማዘጋጀት ስልጣን የፌዴራል መንግሥት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ ነው " ያሉ ሲሆን፤ ማንኛውም ክልል የሀገር አቀፍ ፈተና የማውጣት እና የመፈተን ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው ገልፀዋል። የትግራይ ክልል "እራሴ ፈተና አውጥቼ እፈትናለሁ" የሚለው አካሄድ ፍፁም ቅቡልነት የሌለው መሆኑን የገለፁት አመራሩ፤ "እንፈትናለን ብለው ከወሰኑና ፈተናውን ከሰጡ የፈተናው ውጤት ተቀባይነት ስለማይኖረው የተማሪዎችን ቀጣይ የህይወት ጉዞ ነው የሚያበላሹት" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ቀደም ብሎ በትግራይ ክልል በተካሄደው የኦንላይን ፈተና ወቅት የነበረውን ሁኔታ ያነሱት አመራሩ ፤ የፌዴራል ፀጥታ አካላትና ፈታኞች በአግባቡ ስራቸውን እንዳይወጡ ጫና ተደርጎባቸው እንደነበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። ለአብነትም ለጸጥታ ማስከበር ስራ የተሰማሩ አካላት እንኳን መሳሪያ እንዳይዙ የማድረግ ጫና እንደነበረባቸው ጠቅሰው፣ በወቅቱ የተማሪዎች ቀጣይ ህይወት ጉዞ እንዳይበላሽ ሲባል ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው በጫና ውስጥም ቢሆን ታግሶ እንዲሰጥ ማድረጉን አስታውሰዋል። የአሁኑ የወረቀት ፈተና አግባብ ባለው የፈተና አካሄድና ስርዓት ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም ድረስ እንዲሰጥ መታቀዱን እኚሁ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ይፋ ተደረገ። ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት መመልከት ይችላሉ። መጀመሪያ የተቀመጠውን ሊንክ ይጫኑ በመቀጠል 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤት መመልከት ይቻላል።
ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና አኃዛዊ መረጃዎች፦ 224,234 ➫ ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች 287 ➫ የቅድመ-ምረቃ የፈተና ዓይነቶች 47 ➫ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የፈተና ዓይነቶች 88 ➫ የፈተና ማዕከላት >5000 ➫ የፈተና አስፈጻሚዎች @tikevah_university
ተመራቂዎች ዲጂታል የጤና ሥርዓትን እንዲረዱ ዩኒቨርሲቲዎች ካሪኩለማቸውን ከአዲሱ ዲጂታል ሥርዓት ጋር እንዲያጣጥሙ ተጠየቀ የሚመረቁ የጤና ባለሙያዎች የሀገሪቱን ዲጂታል የጤና ሥርዓት በትክክል እንዲረዱ፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስርአተ-ትምህርት ወይም ካሪኩለማቸውን ከአዲሱ አሠራር ጋር እንዲያጣጥሙ የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። ሚኒስቴሩ ማሳሰቢያውን የሰጠው ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የጤና መረጃ በዲጂታል ሥርዓት ማካተቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። ይህም ማኅበረሰቡ ለተለያዩ በሽታዎች ያለውን ተጋላጭነት ለመለየትና ለፖሊሲ ግብዓትነት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ ይህ ውጤት ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር አንጻር ሲታይ ገና ጅምር ላይ የሚገኝ መሆኑ ተገልጾአል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በ6ኛው ሀገር አቀፍ የጤና መረጃ ሳምንት ላይ እንደገለጹት፣ መንግሥት የዲጂታል ጤና መረጃ አያያዝን ከጊዜያዊ ፕሮጀክትነት አውጥቶ ወደ ዘላቂ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ሥርዓት የመቀየር አቅጣጫ እየተከተለ ይገኛል። በመሆኑም ዛሬ ትምህርት የሚገኙ እና ነገ የሚመረቁ የጤና ባለሙያዎች በዚህ የዲጂታል ሥርዓት አቅማቸውን አጎልብተው ሊወጡ እንደሚገባ ሚኒስትሯ በጥብቅ አሳስበዋል። በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሂልተን ሆቴል ሲካሄድ የቆየውና በዲጂታል ጤና ሥርዓት ላይ ትኩረት ያደረገው ሀገር አቀፍ የጤና መረጃ ሳምንት ነገ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የካፌ አገልግሎት የማይጠቀሙ ተማሪዎች እየተከፈለን ያለው የምግብ ክፍያ እና የወጪ መጋራት ስሌት ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን በጽሑፍ ለቲክቫህ ባስገቡት ቅሬታ ገልፀዋል። "ዩኒቨርሲቲው ያልተቀበልነውን ገንዘብ በመመዝገብ ለከፍተኛ የገንዘብ እዳ ተጋልጠናል ሲሉ ተማሪዎቹ አስረድተዋል። ተማሪዎቹ ከመስከረም እስከ ጥር 2018 ዓ.ም ድረስ (1ኛ ሴሚስተር) በድምሩ 12,800 ብር ብቻ የተቀበሉ ሲሆን፤ በተማሪዎች ፖርታል ላይ የተመዘገበው የወጪ መጋራት ዕዳ 15,000 ብር እንደሆነ ያሳያል። በዚህም ያልተቀበሉትን 2,200 ብር ዕዳ ተደርጎባቸዋል። በ2ኛ ሴሚስተር (ከየካቲት ጀምሮ) በፖርታሉ ላይ 15,000 ብር ዕዳ ተመዝግቧል። የተቀበሉት ግን 9,000 ብር ብቻ ሲሆን፤ በግንቦት ወር ዕዳው ተስተካክሎ 6,000 ብር ሊላክልን ይገባል ብለዋል። "አንድ ተማሪ በዓመት በአማካይ ከ3,000 እስከ 6,000 ብር ያልተጠቀመበትንና በእጁ ያልገባን ገንዘብ እንደ ዕዳ እንዲከፍል መገደዱ ከፍተኛ የፋይናንስ ጉድለትና የአሰራር ብልሹነት ነው" ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። "ያልተጠቀምንበትን የመክፈል ግዴታ የለብንም" ያሉት ተማሪዎቹ፤ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን መፍትሔ ለመስጠት ፍቃደኛ የሆነ አካል አለመኖሩን ተማሪዎቹ ጠቁመዋል። ትምህርት ሚኒስቴር እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጉዳያቸውን እንዲመለከትላቸው ተማሪዎቹ ጠይቀዋል። ቲክቫህ የተማሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት አድርጓል። ይሁን እንጂ አመራሮቹ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር/አመራሮች የሚሰጡንን ምላሽ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።
#Grade12 #NationalExam ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። አገልግሎት መ/ቤቱ ፦ 1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል። 2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል። 3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል። 4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
видео или голосовое, без подписи
" ስቅለት " በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው። ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦ ✝ ዓርብ ጠዋት ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። ✝ በ3 ሰዓት ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው። ✝ በ6 ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው። ✝ በ9 ሰዓት በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው። ✝ 11 ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи