TIKVAH-ETH
Статистика- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 38
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 460
- 1/48двое суток
- 2 819
- 1/72трое суток
- 3 040
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በቻይና በመነሳቱ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ከቤታቸው ለቀው ወጡ ዶልፊን' የተሰኘው ኃይለኛ አውሎ ንፋስበቻይና ምሥራቃዊ ክፍል ላይ መነሳቱን ተከትሎ፣ የቻይና ባለሥልጣናት የፋይናንስ ማዕከል የሆነችውን ሻንጋይን ጨምሮ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን ከቤታቸው አስወጥተዋል። አውሎ ንፋሱ ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለ ሲሆን በመላው ክልሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲስተጓጎል አድርጓል። ሰኞ ዕለት ብቻ በሻንጋይ ብቻ ወደ 1,000 የሚጠጉ በረራዎች ተሰርዘዋል።ባለሥልጣናት፣ አውሎ ነፋሱ ወደ ሰሜን ሲንቀሳቀስ ኃይለኛ ዝናብ፣ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ እስከ ረቡዕ ድረስ እንደሚከሰት ማስጠንቀቃቸውን ቀጥለዋል። የቻይና ባለሥልጣናት ቀደም ሲል ዶልፊን የተሰኘውን አውሎ ንፋስ በተመለከተ ከፍተኛውን የቀይ ማስጠንቀቂያ አውጥተው ነበር፣ ይህም በዚህ ዓመት ቻይናን የመታው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ነው። እሁድ በዠይጂያንግ ግዛት ዩሁዋን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አውሎ ንፋሱ ሲመታ፣ በሰዓት 150 ኪ.ሜ ከፍተኛውን የንፋስ ፍጥነት አስተናግዷል፣ ይህም ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ በዌንዙ ከተማ ሁለተኛ ዝናብ መጣሉን የሜትሮሎጂ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሰኞ ዕለት በሻንዶንግ፣ ሄናን፣ ሁቤይ፣ አንሁዊ፣ ጂያንግሱ፣ ዠይጂያንግ እና የሻንጋይ ከተማ ግዛቶች ከባድ ዝናብ እንደሚዘንብ ተንብየዋል። @Tikfahethiopia
በፈረንሳይ እና ስፔን የተቀሰቀሰዉ ከባድ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን ቀጥሏል የፈረንሳይ ባለስልጣናት በደቡብ ምዕራብ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኘውን የካፕ ፌሬት ባሕረ ገብ መሬት በሙሉ ነዋሪዎች ለቀዉ እንዲወጡ አዘዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በጀልባ ከአካባቢው ወጥተዋል። የእሳት አደጋ ተከላካዮች በጊሮንዴ ክልል ለቀናት የቆየውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት እየተጉ ቢሆንም የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዉ ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ በሳውሞስ የተከሰተው እሳት 8 ሺህ 700 ሄክታር መሬት በእሳት ቃጠሎው አውድሟል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ አቅራቢያ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ሰደድ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ የስፔን መንግስት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አውጇል። በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ማክሰኞ ዕለት በቦርዶ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በተነሳ እሳት ሕይወታቸው አልፏል። በአትላንቲክ የባህር ዳርቻ፣ በፈረንሳይ ላንዴስ ክልል፣ በቢስካሮሴ ከተማ ዙሪያ፣ ሐሙስ ከሰዓት በኋላ የጀመረው ሌላ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ከ23,000 በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል። በቢስካርሮሴ 18,000 የሚሆኑ ሰዎች እንዲሁመር በፓሬንቲስ-ኤን-ቦርን ከተባለ ስፍራ 5,000 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸውን፣ የካምፕ ቦታ፣ የነርሲንግ ቤት እና የበጋ ካምፕን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ዛሬ አርብ ከክልሉ የተገኘ ዜና እንደሚያሳየው የቢስካርሮሴ ማዕከል በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ለቀዉ እየወጡ ነዉ፡፡ @Tikfahethiopia
አስገራሚ መረጃ‼️ እስራኤል እስር ቤቶቿን በአዞ ለመጠበቅ ጉድጓድ መቆፈር ጀመረች። 👉በሀማስ እና ጋዛ እስረኞች ላይ ተጀምሯል። የእስራኤል ሚዲያዎች እንደዘገቡት በደቡብ እስራኤል በሚገኘው የሃማስ እና የፓላስቲኒያን እስረኞች በሚገኙበትና ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የእስር ቤት ክንፍ ዙሪያ ለአዞዎች መቀመጫ የሚሆን ጉድጓድ እየተቆፈረ ይገኛል። እነዚህ ጉድጓዶች በኬትዚዮት እስር ቤት ዙሪያ እየተቆፈሩ ሲሆን ወደ 170 ሜትር የሚረዝሙ ይሆናሉ። እስር ቤቱ የሚገኝበት የራማት ኔጌቭ የክልል ምክር ቤት ባለስልጣን ጉድጓዶቹ በእስር ቤቱ ውስጥ በልዩ ክንፎቹ ዙሪያ እየተቆፈሩ መሆናቸውን እና ከውጭ ማየት እንደማይቻል ተናግረዋል። "በእርግጥ እዚያ አዞዎች ይኖሩ እንደሆነ ማንም አያውቅም፣ ነገር ግን ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው" ሲሉ ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለስልጣን ተናግረዋል። የእስራኤል ብሔራዊ የደህንነት ሚኒስቴር ለአዞዎች በተመደቡ ቻናሎች ላይ ሥራ መጀመሩን አረጋግጧል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል። የእስራኤል የእስር ቤት አገልግሎት አዞዎቹን ለመንከባከብ፣ ለመቆጣጠር እና ለማስተናገድ እቅድ አዘጋጅቷል፣ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ደግሞ አዞዎቹን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ስልጠና ወስደዋል፣ ፕሮጀክቱም 21 ሚሊዮን ሰቅል (6.3 ሚሊዮን ዶላር) ተመድቧል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል። @Tikfahethiopia
без подписи
በቀይ ባህር ሁለት ግዙፍ የነዳጅ መርከቦች በሁቲ ማስጠንቀቂያ ጉዟቸውን ቀየሩ። ከሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ጭነው በቀይ ባሕር በኩል ሲቀዝፉ የነበሩ ሁለት ግዙፍ መርከቦች ከየመን ሁቲ ኃይሎች በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ምክንያት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ መደረጋቸው ተዘገበ። የሳዑዲን የነዳጅ ምርት ጭነው ወደ ቻይና እና ሕንድ ሲጓዙ የነበሩት ሁለቱ መርከቦች ወደ መጡበት የተመለሱት ሁቲዎች በሳዑዲ አረቢያ ላይ የባሕር እንቅስቃሴ ዕቀባ መጣላቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው። ከሳዑዲ ጋር በጠላትንት የሚተያዩት የኢራን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ሁቲዎች ማንኛውም ወደ ሳዑዲ የሚያቀኑ እና ከሳዑዲ ወደቦች የሚነሱ መርከቦችን ዒላማ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል። ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሳዑዲ የተነሱት ሁለቱ መርከቦች ከሁቲ ታጣቂዎች ማስጠንቀቂያ በኋላ ወደ ደቡባዊ የቀይ ባሕር መስመር መጓዛቸውን በመተው ፊታቸውን በማዞር ወደ ሱዩዝ ካናል አቅንተዋል። አሜሪካ እና ኢራን በሚያደርጉት ጦርነት በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ኢራን በፈጠረችው ስጋት የተናጋው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዘይት አቅርቦት የዋጋ ጭማሪ ያስከተለ ሲሆን፣ አሁን በቀይ ባሕር ላይ የተፈጠረው ስጋት የበለጠ ቀውሱን ያባብሰዋል ተብሎ ተሰቷል። በሁቲዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ ከተደረጉት መርከቦች መካከል ዢ ሎነግ ያንግ የተባለው እጅግ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ሁለት ሚሊዮን በርሜን ነዳጅ ጭና ሰኞ ዕለት ከሳዑዲ የቀይ ባሕር ዳርቻ ያንቡ ወደብ በመነሳት ወደ ቻይና እያቀና ነበረ። ሁቲዎች በቀይ ባሕር በኩል ከዚህ ቀደም ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸን መርከቦችን በማጥቃት የሚታወቁ ሲሆን፣ የተወሰኑ መርከቦችም መስመጣቸው አይዘነጋም። መረጃው የቢቢሲ ነው። ሃምሌ 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
❗️ብልጽግና ፓርቲ በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ጽምጽ በማግኘት አሸነፈ ብልጽግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በማግኘት የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ መሆን መቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ በምርጫው ውጤት ይፋ ማድረጊያ መርሀግብር እንደገለጹት፥ ለምርጫው ከተመዘገቡ ከ54 ሚሊዮን በላይ በምርጫው ከተመዘገቡት ዜጎች 96.2 በመቶ የሚሆኑት ድምጽ ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት ብልፅግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በማግኘት ማሸነፋን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በተለያዩ አካባቢዎች ባደረገው ተሳትፎ በድምሩ 13 የፓርላማ ወንበሮችን ማግኘት መቻሉም ተገልጿል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ክልል ባደረገው ፉክክር 6 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮችን ማሸነፋም ተመላክቷል። በሲዳማ ክልል ፥ መድረክ 3 የፓርላማ መቀመጫዎችን ማግኘቱንና ፣ ሌሎች ፓርቲዎችም በየክልሉ በወከሉአቸው እጩዎቻቸው የፓርላማ መቀመጫዎችን ማግኘታቸውም ተገልጿል። የፓርላማ ወንበሮችን ያገኙ የግል ተወዳዳሪዎችም መኖራቸው ተነግሯል። ብልጽግና ፓርቲ የ11 ክልሎችና የሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤቶች አብላጫ ወንበር ማሸነፉም ተገልጿል። @Tikfahethiopia
ጭንብል ለብሶ አፈሳ❗❗❗ በትግራይ የጭምብል ታጣቂዎች የታገዘ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ ስጋት ፈጠረ‼ በትግራይ ክልል ዓብይ ዓዲ እና አካባቢው በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫዎች ላይ፣ የክልሉ ኃይሎችና ፊታቸውን የሸፈኑ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ አሰቃቂ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ እያካሄዱ መሆኑን ቢቢሲ ትግርኛ በምርመራ ዘገባው ይፋ አደረገ። ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ700 በላይ ወጣቶችና የዕለት ጉልበት ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ላይ በድብደባና በኃይል ታፍሰው፣ ልብስና ስልካቸውን እንኳ ሳይይዙ ማይቅነጣል ወደሚገኝ ወታደራዊ ማሠልጠኛ መወሰዳቸውን ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል። የትግራይ ኃይሎች (አርሚ 60) ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዘልዑል ማቲዮስ በአካባቢው "የማዕድን ወረራን ለመበተን እርምጃ ወስደናል" በማለት ድርጊቱን ያመኑ ቢሆንም፣ ወጣቶቹ ወደ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ስለመወሰዳቸው ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ቢቢሲ ትግርኛ @Tikfahethiopia
без подписи
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገበ። ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር። ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikfahethiopia
ለፌደራል መንግሥት የ2019 በጀት ከ2.3 ትሪሊየን ብር በላይ ቀረበ! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለፌደራል መንግሥት ለቀጣዩ 2019 ዓ.ም. በጀት ከ2.3 ትሪሊየን ብር በላይ አጸደቀ።ዛሬ ሰኔ 2/2018 ዓ.ም. በተካሄደው 56ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በቀረበው የፌደራል መንግሥት የ2019 ረቂቅ በጀት ላይ "በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል" ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተገልጿል። ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግሥታት ድጋፍ እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሦስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቦ መጽደቁ ተገልጿል።የፌደራል መንግሥት ለ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የመደበው 1.93 ትሪሊዮን ብር ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መግለጫ የ2019 ዓ.ም. የፌደራል መንግሥት በጀት የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት "የፕሮግራም በጀት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ" መዘጋጀቱን ይገልጻል።በቀጣይ ሊኖር የሚችለው "የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች" እንዲሁም በመንግሥት የተቀመጡ "ግቦችን ለማሳካት የመንግሥትን የፋይናንስ አቅም እና አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮ እና ኃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም" ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተመልክቷል። ምክር ቤቱ ከ2019-2023 ዓ.ም. በሚኖረው የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ እንደተወያየ ጠቅሶ፤ "የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉበት ተግዳሮቶች እየተላቀቀ እና የኢኮኖሚው መሠረቶችም እየተጠናከሩ መጥተዋል" ብሏል።"በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል" እንዲሁም "ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ታሳቢዎች ላይ በመመሥረት" የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት በጀት መነሻ መሆኑም ተጠቅሷል። @Tikfahethiopia
ኤርትራ ስለ ፅምዶ የፃፈችው ደብዳቤ‼️ ኤርትራ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ (ዩኤንኤስጂ) የላከችው ደብዳቤ ምስጋና በማቅረብ የጀመረ ሲሆን፤ በኤርትራ እና ትግራይ "በማህበረሰብ ላይ የተመሰረተ ከአንድ አመት በላይ ተከታታይ የህዝብ ለህዝብ ውይይት፣ የማህበረሰብ ውይይቶች፣ የባህል ልውውጦች እና በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ተግባራት “ጽምዶ ንሰላም"(መተሳሰር ለሰላም) በሚል ሀገር በቀል መሪ ቃል መጀመሩን ገልጿል። ይህ ህዝባዊ ዘመቻ እምነትን መልሶ ለመገንባት፣ ማህበራዊ ትስስርን ወደነበረበት ለመመለስ እና በአመታት ግጭት እና መለያየት ህይወታቸው በእጅጉ የተጎዳ ማህበረሰቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል። የፅምዶ ጠቀሜታ በእንቅስቃሴው ላይ ብቻ ሳይሆን በኦርጋኒክ እና በአካባቢው ባለቤትነት ላይ ነው፣ በእራሳቸው የማህበረሰቡ አባላት የሚመራ፣ በዋናነት በጋራ ድንበሮች የሚኖሩ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ቤተሰቦች፣ በውይይት እና ቀጥተኛ ሰብዓዊ ተሳትፎ መግባባትን፣ ፈውስ እና አብሮ መኖርን ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነትን ያሳያል ብሏል። ውጥኑ የተባበሩት መንግስታት ሰላምን ለማስቀጠል እና ህዝብን ያማከለ የሰላም ግንባታን የሚደግፉ መርሆዎች ትርጉም ያለው ምሳሌ ይሰጣል። ለዚህ ማሳያ ይሆናል የተባለ ተጓዳኝ ቪዲዮ ከደብዳቤው ጋር አብሮ መላኩን በደብዳቤው ላይ ተጠቅሷል። @Tikfahethiopia
በዓፋር ሰደድ እሳት መነሳቱን ተዘገበ በአፋር ክልል በራህሌ ወረዳ ዳትጋራብ ጫካ ውስጥ ሰደድ እሳት መነሳቱን ወረዳው አስታውቋል። የአደጋው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም ብለዋል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው ባለመኖራቸው አደጋውን መቆጣጠር አልተቻለም ተብሏል። @Tikfahethiopia
ነዳጅ በሁለት ዶላር ቀነሰ። የነዳጅ ዋጋ በአለማቀፍ ደረጃ መጠነኛ ቅናሽ አሳየ። የዋጋ ቅናሽ የተስተዋለው እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። አንድ ብሬንት ነዳጅ በርሚል 67 ሳንቲም ወይም 0.69 % ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል። በ97.14 ዶላር ሲሸጥ የነበረው አንድ በርሚል ነዳጅ ወደ 95.40 ዝቅ ማለቱ ተመላክቷል። @Tikfahethiopia
ችሎት ውስጥ የተፈፀመ አሰቃቂ ግድያ‼ ዛሬ ረፋድ ላይ በሆለታ ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት፣ የዕለቱን የችሎት ውሳኔ በማንበብ ላይ የነበሩ ዳኛ እና አንዲት ተከራካሪ ህይወታቸው ማለፉን አክሰስ ቱ ጃስቲስ ኢኒሼቲቭ - ኢትዮጵያ አስታውቋል። እንደ ምንጩ መረጃ፣ የቤተሰብ ክርክር ጉዳይን በመመልከት ላይ የነበሩት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ የፍርድ ውሳኔውን እያነበቡ ባሉበት ወቅት፣ ተከሳሹ በድንገት ባወጣው ሽጉጥ ዳኛዋን በጥይት በመምታት ህይወታቸውን ቀጥፏል። በዚሁ አጋጣሚ በችሎቱ ላይ በጉዳዩ ላይ ይከራከሩ የነበሩት (ተከራካሪዋ) በተመሳሳይ ሁኔታ በተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል። የሕግ ባለሙያዎችና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን በጽኑ ያኮነኑ ሲሆን፤ ዳኞችና የሕግ ባለሙያዎች በሥራ ገበታቸው ላይ አስተማማኝ የደህንነት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በርካቶች በመጻፍ ላይ ይገኛሉ። “አንድ ግለሰብ ታጥቆ ወደ ፍርድ ቤት አዳራሽ መግባት መቻሉ፣ የፍርድ ቤቶችን የጸጥታና የፍተሻ አሰራር ምን ያህል ደካማ እንደሆነ በአሳዛኝ ሁኔታ አሳይቷል” በማለት አክሰስ ቱ ጃስቲስ ኢኒሼቲቭ የድርጊቱን አሳሳቢነት ገልጿል። @Tikfahethiopia
ኬንያ ውስጥ በደረሰ አሰቃቂ የትምህርት ቤት ቃጠሎ ዘጠኝ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ በኬንያ በሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ 16 ተማሪዎችን ለሞት የዳረገውን ቃጠሎ አቅደዋል እና ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ዘጠኝ ሴት ተማሪዎች እስከ 21 ቀናት ድረስ በቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ተወሰነ። መርማሪዎች ምርመራቸውን እንዲያጠናቅቁ እና ክስ መመስረት አለመመስረታቸውን እንዲወስኑ ተጠርጣሪዎቹ በሕፃናት ማቆያ ማዕከል ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ይደረጋል። ጉዳዩ የመላው ሀገሪቱን ትኩረት ስቧል። ቃጠሎዉ ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ በ90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጊልጊል፣ ናይቫሻ አቅራቢያ የሚገኘውን እና 2መቶ2 ተማሪዎችን የያዘውን የኡቱሚሺ የሴቶች ትምህርት ቤት የመኝታ ክፍልን አውድሟል። ዘጠኙ ተጠርጣሪዎች ሁሉም በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ፤ከተማሪዎች የተገኘ የምስክርነት ቃል እና የደህንነት ካሜራ ምስሎችን ከመረመሩ በኋላ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ቃጠሎው የተነሳው ተማሪዎቹ በመኝታ ክፍሉ መውጫ ላይ የሚገኝ ፍራሽ በክብሪት እና በጋዝ በመለኮሳቸው እንደሆነ ተገልጿል። ለዚህ የቃጠሎ ጥቃት እስካሁን ምንም ዓይነት ምክንያት አልተገለጸም። ለመለየት በሚያስቸግር ሁኔታ የተቃጠሉ አንዳንድ አስከሬኖችን ማንነት ለማረጋገጥ የሚደረገው የዲኤንኤ ምርመራ ውጤት ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። @Tikfahethiopia
ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በ85ኛው መደበኛ ስብሰባው ላይ ለ81ኛው ጠቅላላ ጉባኤ መሪ የሚሆኑ አካላትን የመረጠ ሲሆን፣ የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኤርትራ የከፍተኛ አባል ሀገራትን ድምጽ በማግኘት ከ16 ሌሎች አገራት ጋር በመሆን የጉባኤው ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች። ኤርትራ ከተመረጡት እንደ አፍጋኒስታን፣ ፊንላንድ፣ ግብፅ፣ ሊባኖስ፣ ፓራጓይ እና ዚምባብዌ ካሉ ሀገራት እንዲሁም ከጸጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ አባላት ጋር በመሆን የጠቅላላ ጉባኤውን ቢሮ በጋራ የምትመራ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዕለት በምስጢር በተደረገ የድምፅ አሰጣጥ የባንግላዲሹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካሊሉር ራህማን ተፎካካሪያቸውን የቆጵሮሱን አንድሪያስ ካኩሪስን በ99 ለ 91 ድምፅ በማሸነፍ የ81ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሥራቸውን በይፋ የሚረከቡት ሚስተር ራህማን ድርጅቱ ከባድ የፋይናንስ ቀውስ እና ዓለም አቀፍ የእምነት ማጣት እየገጠመው መሆኑን ጠቅሰው፣ አባል ሀገራቱ የጠፋውን እምነት ለመመለስ በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል። @Tikfahethiopia
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи