tgindex
Tirita 97.6 FM Radio

Tirita 97.6 FM Radio

Статистика

ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ''ከልብዎ የቀረበ'' ትርታ ሚዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ ነው።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
44
Всего постов
100
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
1 354
+4 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
99
40 постов
Вовлечённость
7,3%
к подписчикам
Постов в день
6,3
всего 100
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
87
1/48двое суток
99
1/72трое суток
107

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው 8ቱም የአጀንዳ ቡድኖች ከስምምነት ደርሰዋል - ኮሚሺኑ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው፣ በዛሬው ዕለት የቀሩት 4 የአጀንዳ ቡድኖች ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ። በዛሬው ዕለት ከስምምነት ላይ የደረሱት ቡድኖች በሀገር ግንባታ፥ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ፥ በተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነት እና ሰብዓዊ መብት እንዲሁም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተመካከሩ መኾናቸው ታውቋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሺኑ በይፋዊ ገፁ ሁሉም የአጀንዳ ቡድኖች ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ባስታወቀበት ፤ ከሁለት ቀናት በፊት አራቱ የአጀንዳ ቡድኖች ከስምምነት ላይ መድረስ መቻላቸውን አስታውሷል። ከሁለት ቀናት በፊት በሰላም ግንባታ፥ በሃይማኖት ጉዳዮች፥ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በመንግስት አደረጃጀት እና የፖለቲካ ስርዓት ሲመካከሩ የነበሩ ቡድኖች መግባባት ላይ እንደደረሱ መገለፁ ይታወቃል። 🌕Facebook: https://www.facebook.com/Tirita97.6FM 🌕YouTube:  https://youtube.com/@tiritaradio?si=T9uLNGL6JLK7cWct 🌕Telegram :https://t.me/tiritaradio 🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6

  • የነገ፣ የዕለተ ዐርብ፣ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም. ትርታ ቁርስ መሰናዶዎችን እናስተዋውቅዎ። የዩክሬን ከተማዋንና በጥቁር ባህር ዳርቻ የምትገኘዋ ኦዴሳን በመዳረሻ ጥቆማችን እንቃኛለን። ከግዙፉ የቴክኖሎጂ ተቋም አፕል በመውጣት ፤ ውድቀቶችን ተቋቁማ ፤ የተቋማትን ያልዘመነ የሕግ ጉዳዮች አያያዝን ስለቀየረች ብርቱ እንስት የሕይወት ጉዞ በብርቱ ቀን መሰናዷችን እንቃኛለን። የክረምት ወቅት የአሽከርካሪዎችና የእግረኞች የትራፊክ ህጎች አከባበር ምን ይመስላል? በመንገድ ላይ መሰናዷችን ታዝበነዋል። የኪነጥበብና ስለሙዚቃ መሰናዶዎችን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና፣ ፖለቲካዊ የአገር ቤት ብሎም ዓለም አቀፍ ጉዳቶችን ሰንቆ ትርታ ቁርስ መሰናዶ ነገ ከማለዳ 12፡30 ጀምሮ እንድታደምጡት ተዘጋጅቷል። ስለምታደምጡን እናመሰግናለን። ትርታ 97.6 ኤፍኤም ከልብዎ የቀረበ 🌕Facebook: https://www.facebook.com/Tirita97.6FM 🌕YouTube:  https://youtube.com/@tiritaradio?si=T9uLNGL6JLK7cWct 🌕Telegram :https://t.me/tiritaradio 🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6

  • ምክረ-ሐሳቦችን የማጣጣምና ወጥ ሰነድ ማዘጋጀት ዛሬ ይጀመራል - ኮሚሺኑ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሺን፣ ከስምንቱ ዐበይት ቡድኖች በተወጣጡ አባላት የተዋቀረ አዲስ ቡድን መቋቋሙንና ሥራውን በዛሬው ዕለት እንደሚጀምር ገለፀ። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው  በታቀደው አግባብ እየተካሄደ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በ500 ተመካካሪ አባላት ያሏቸው ስምንቱ የአጀንዳ ቡድኖች በተመደቡባቸው አጀንዳዎች ላይ ሲመካከሩ የቆዩ መኾናቸው ሲታወቅ ፤ በአብዛኛው የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በምክረ-ሀሳቦቻቸው ላይ ፊርማቸውን በማስፈር ሥራቸውን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶች መስተዋላቸውም፣ የምክክሩን አስፈላጊነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። 8ቱ ቡድኖች የተስማሙባቸው ምክረ-ሐሳቦችን የማጣጣም ተግባር ከቡድኖቹ በተወጣጡ አባላት በተዋቀረ አዲስ ቡድን እንደሚከናወንም ተጠቁሟል። አዲሱ ቡድን ኃላፊነቱ ምክረ ሐሳቦቹ እንዳይቃረኑ ማጣጣም፣ አላስፈላጊ ድግግሞሾች እንዳይኖሩና የሚቀርበው ሰነድ ወጥነት እንዲኖረው ማድረግ እንደሆነም ጠቁመዋል።

  • የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያን ይፋ ተደረገ የፍትሕ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር ያዘጋጀውን የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያን ይፋ አደረገ። መምሪያው ለቤተሰብ፣ ሕጻናትና ተጋላጭ ዜጎች የሕግ ጥበቃን ለማረጋገጥና ማህበራዊ ፍትሕን ለማስፈን እንደሚያግዝ ተጠቁሟል። የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር)፣ በፍርድ ቤቶች ከሚቀርቡ ጉዳዮች መካከል በአራተኛ ደረጃ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ መኾናቸውን አንስተው ፤ ቤተሰብ የህብረተሰብ መሠረት በመሆኑ፣ መንግሥት የቤተሰብን ጥበቃ ለማጠናከር ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። መምሪያው በቀለብ፣ በልጆች አስተዳደግና ጉብኝት፣ በንብረት አስተዳደር፣ በፍቺና በንብረት ክፍፍል እንዲሁም ከቤተሰብ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የሕግ ጉዳዮችን እንደሚመለከት የኢዜአ ዘገባ አመልክቷል። ላይ የሚመራና የሚዳስስ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያው ከዳኞች፣ ከትምህርት ተቋማትና ከባለድርሻ አካላት በተውጣጡ ባለሙያዎች ኮሚቴ በማቋቋም መዘጋጀቱም የተዘጋጀ ተነስቷል። 🌕Facebook: https://www.facebook.com/Tirita97.6FM 🌕YouTube:  https://youtube.com/@tiritaradio?si=T9uLNGL6JLK7cWct 🌕Telegram :https://t.me/tiritaradio 🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6

  • ኦቪድ ሆልዲንግ ግሩፕ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ ኦቪድ ሪል እስቴት እና እህት ኩባንያዎች ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና ሰራተኞች 8ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ። በዚሁ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የተቋሙ ስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንደገለጹት ፤ መርሀ ግብሩ ተቋሙ የግንባታ ስራዎቹ አረንጓዴ ልማትን ለማድረግ የሚያከናውናቸው  ተግባራት አካል ነው። ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ፣ በኦቪድ ሪል እስቴት ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ፥ ከ4 ሺህ በላይ ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር ተካሂዷል። የችግኝ ተከላው የአንድ ወቅት ተግባር ሳይሆን የተተከሉት የችግኞች ክትትልና እንክብካቤ የማድረግ ባህል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የተሳተፉ የኦቪድ ግሩፕ ሰራተኞች በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ወሳኝ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም የተቋሙ ሰራተኞች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

  • አፍሪቃውያን በጋራ ገንዘብ መገበያየት የሚችሉበትን መላ መፍጠር አለባቸው ተባለ ​አፍሪቃውያን አኅጉራዊ እና ቀጣናዊ የንግድ ትስስራቸውን ለማጠናከር በጋራ ገንዘብ መገበያየት የሚችሉበትን አሠራር መፍጠር እንዳለባቸው ኬንያዊው የምጣኔ-ሀብት ባለሙያ አሳሰቡ። ​የዓለም-አቀፉ ንግድ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር እና የኬንያ ንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር የኾኑት ፓትሪክ ኦባዝ ከተርኒንግ አፍሪቃ ፎርዋርድ ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በተለይ በምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ ውስጥ የጋራ ገንዘብ መጠቀም አስፈላጊ ነው ብለዋል። ​ ቀደም ሲል በምሥራቅ አፍሪቃ ቀጠና ሀገራት የጋራ ገንዘብ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ያወሱት ባለሙያው፣ አሁንም ሀገራቱ ገንዘቦቻቸውን በማጣመር በአንድ የጋራ ገንዘብ መገበያየት የሚያስችላቸውን አሠራር መዘርጋት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። 🌕Facebook: https://www.facebook.com/Tirita97.6FM 🌕YouTube:  https://youtube.com/@tiritaradio?si=T9uLNGL6JLK7cWct 🌕Telegram :https://t.me/tiritaradio 🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6

  • ወደ አውሮጳ አሕጉር ለመሻገር በሚደረጉ የባሕር ጉዞዎች ሳቢያ በሕይወት ላይ የሚደርስ ጉዳት መጨመሩ ተገለጸ ​እ.ኤ.አ. በ2026 የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ ብቻ ወደ አውሮጳ ለማቋረጥ ሲሞክሩ ሕይወታቸውን ያጡ ስደተኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን በተባበሩት መንግሥታት የዓለም-አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቋል። ​በድርጅቱ መረጃ መሠረት፣ በእነዚህ አራት ወራት ውስጥ ብቻ በጥቅሉ 1 ሺ 65 ስደተኞች በማዕከላዊና ምዕራብ ሜዲትራኒያን የባሕር መስመሮች ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል ወይም ደብዛቸው ጠፍቷል። ​ይህ አኃዝ አደገኛ በሆኑ የባሕር ጉዞዎች ላይ የሚከሰቱ አደጋዎች መጨመራቸውን የሚያሳይ እንደኾነ ያመለከተው መረጃው፥ ዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ የሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችን መረብ ለመግታትና የስደተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ መቅረቡን ጠቅሷል።

  • የኋይት ሀውስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከኃላፊነታቸው ሊለቁ መኾኑ ተገለጸ ​በአሜሪካው ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራምፕ ኹለተኛ አስተዳደር ዘመን የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩት ካሮሊን ሊቪት ከያዙት ከፍተኛኃ ኃላፊነት ሊለቁ መኾኑ ተሰምቷል። ​ከተለያዩ የዜና ምንጮች የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፤ ሊቪት ከኃላፊነታቸው የሚለቁት በቤተ-መንግሥቱ አስተዳደር የውስጥ አሠራርና የሕዝብ ግንኙነት ቡድን ላይ በሚደረጉ አዳዲስ ሽግሽጎች ምክንያት ነው ተብሏል። ​በአሜሪካ ታሪክ በዕድሜ ትንሿ የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ተብለው የተሾሙት ካሮሊን ሊቪት፤ በቆይታቸው የመንግሥትን የፖሊሲ አቋሞች ለአገናኝ አካላትና ለብዙኃን መገናኛዎች በማቅረብ ረገድ ንቁ ሚና ሲጫወቱ መቆየታቸው ይታወቃል። ካሮሊን ሊቪት ላበረከቱት አገልግሎት ምስጋና ያቀረበው የነጩ ቤተ መንግሥት አስተዳደር፣ የእርሳቸውን ቦታ የሚተኩ አዲስ ቃል አቀባይ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል። 🌕Facebook: https://www.facebook.com/Tirita97.6FM 🌕YouTube:  https://youtube.com/@tiritaradio?si=T9uLNGL6JLK7cWct 🌕Telegram :https://t.me/tiritaradio 🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6

  • በኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በታሪክ የከፋው ሊኾን ይችላል - የዓለም ጤና ድርጅት የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ በኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከቀደሙት ወረርሽኞች የከፋ ወደ መኾን እያመራ መኾኑን አሳሰበ። በወረርሽኙ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ ሲያልፍ ፤ በመዛመት መጠኑ ፈጣኑ ኾኖ ተመዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ወረርሽኙ ዓለምን አስደንግጧል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በዚህ ፍጥነቱ ከቀጠለም እ.ኤ.አ. ከ2014 - 2016 በምዕራብ አፍሪካ ከተከሰተው ወረርሽኝ የከፋ ሊኾን እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። ለአኹኑ የወረርሽኙ ምክንያት የኾነው ቡንዱቡግዮ ቫይረስ የተረጋገጠ ክትባት አለመኖሩ ለመባባሱ አንዱ ምክንያት ሆኗል ሲል አሶሸትድ ፕረስ ዘግቧል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • የስጋ ወጭ ንግድ ቄራዎች ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ ተጠየቀ የስጋ ወጭ ንግድ ቄራዎች በራሳቸው አቅም ሊፈቷቸው የሚችሏቸውን ችግሮች በመቅረፍ ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ ተጠየቀ። ይኽ ጥያቄ የቀረበው የግብርና ሚኒስቴር የቄራዎቹን የ2019 በጀት ዓመት የሐምሌ ወር አፈጻጸምን በገመገመበት ነው። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በመንግስት በኩል አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የማድረግ ቁርጠኝነት መኖሩን ጠቅሰዋል። የስጋ ወጭ ንግድ ቄራዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷልም ብለዋል። የስጋ ወጭ ንግድ ዘርፍ የግብዓት አቅርቦት፣ ገበያ እና ታክስ ጋር የተያያዙ ችግሮችም ተመክሮባቸዋል። የግብዓት አቅርቦት ትሥሥርን፣ የማምረት አቅምና የመዳረሻ ገበያን ማሳደግ እንደሚገባም መነሳቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አሳይቷል። 🌕Facebook: https://www.facebook.com/Tirita97.6FM 🌕YouTube:  https://youtube.com/@tiritaradio?si=T9uLNGL6JLK7cWct 🌕Telegram :https://t.me/tiritaradio 🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6

  • видео или голосовое, без подписи