FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)
Статистикаይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 10
- Всего постов
- 171
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 343
- 1/48двое суток
- 393
- 1/72трое суток
- 423
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአቪዬሽንና በቴክኖሎጂ ዘርፍ አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያው ወጣት ዳዊት አዳነ፣ በቅርቡ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 «መለኛ» ፕሮግራም ላይ ያካፈለው የሕይወትና የሥራ ተሞክሮ ለብዙዎች መነሳሳትን የሚፈጥር ነው።
видео или голосовое, без подписи
ለዲዛይን ልዩ ፍላጎት ያለው ዳዊት፣ የ"Full-Stack Web Development" ክህሎቱን በመጠቀም ከጓደኞቹ ጋር "ሹክራን ቴክኖሎጂ"ን መሥርቷል። ከዚህም በተጨማሪ ለተማሪዎች የፈተና ዝግጅት የሚረዳ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚመራ ethioexam.et የተሰኘ ፕላትፎርም ሰርተዋል። ይህ ዌብሳይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ21 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት የቻለ ሰፊ የፈተና ባንክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ከአውሮፕላን ጥገና እስከ ቴክኖሎጂ ፈጠራ፡ የወጣት ዳዊት አዳነ አበረታች ጉዞ… በአቪዬሽንና በቴክኖሎጂ ዘርፍ አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያው ወጣት ዳዊት አዳነ፣ በቅርቡ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 «መለኛ» ፕሮግራም ላይ ያካፈለው የሕይወትና የሥራ ተሞክሮ ለብዙዎች መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። ለዲዛይን ልዩ ፍላጎት ያለው ዳዊት፣ የ"Full-Stack Web Development" ክህሎቱን በመጠቀም ከጓደኞቹ ጋር "ሹክራን ቴክኖሎጂ"ን መሥርቷል። ከዚህም በተጨማሪ ለተማሪዎች የፈተና ዝግጅት የሚረዳ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚመራ ethioexam.et የተሰኘ ፕላትፎርም ሰርተዋል። ይህ ዌብሳይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ21 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት የቻለ ሰፊ የፈተና ባንክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ወደፊት ethioexam.et ፕላትፎርምን ለሚሊዮኖች ለማድረስ ከማለም ባለፈ፣ ተማሪዎችን ለውጭ ስኮላርሺፕ የሚያዘጋጅ "Global Scholar" የተባለ አዲስ አገልግሎት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው። ዳዊት ለሌሎች ወጣቶች ባስተላለፈው መልዕክት፤ "ከመደበኛ ስራችሁ ጋር የሚጣጣምና ጊዜን በጣም የማይሻማ ተጨማሪ ስራ ጀምሩ፤ ካልሆነ ግን ሁኔታዎችን በጥናት መርምራችሁ አዳዲስና ተስማሚ የሆኑ ክህሎቶችን ተማሩ" ሲል መክሯል።
"ወጣቶች ተጨማሪ ስራ ሊሰሩ ይገባል" - ሚኪያስ ተስፋዬ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአርክቴክቸር ሙያ የተመረቀው ወጣቱ ሚኪያስ ተስፋዬ፣ በአንድ ዘርፍ ብቻ ሳይወሰን በግራፊክስ ዲዛይንና በፈርኒቸር ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ ውጤታማ መሆን የቻለ ሁለገብ ባለሙያ ነው።
"ወጣቶች ተጨማሪ ስራ ሊሰሩ ይገባል" - ሚኪያስ ተስፋዬ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአርክቴክቸር ሙያ የተመረቀው ወጣቱ ሚኪያስ ተስፋዬ፣ በአንድ ዘርፍ ብቻ ሳይወሰን በግራፊክስ ዲዛይንና በፈርኒቸር ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ ውጤታማ መሆን የቻለ ሁለገብ ባለሙያ ነው። ሚኪያስ ወደ ሥራው ዓለም ሲገባ የመነሻ ካፒታልና የስራ ቦታ እጥረት ቢገጥመውም፣ በተለያዩ የዲዛይን ዘርፎች ላይ ራሱን በእውቀት እና በክህሎት በማብቃቱ መሰናክሎቹን ማለፍ እንደቻለ ከመለኛ ፕሮግራም ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል። በመጨረሻም ሚኪያስ ለወጣቶች ባስተላለፈው መልዕክት፦ "በአሁኑ ጊዜ በአንድ የሥራ መስክ ላይ ብቻ መወሰን አስቸጋሪ ነው፤ ስለዚህ ወጣቶች ያላቸውን ተሰጥኦ እና ነፃ ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው በተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ሊሰማሩና ራሳቸውን በኢኮኖሚ ሊያጠናክሩ ይገባል" ሲል መክሯል።
ሳምንታዊው የ‹‹ሀምሳ ሎሚ›› የሬዲዮ ፕሮግራም በቅርቡ ባቀረበው መሰናዶ፤ በመቀሌ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ የነበሩ ወጣቶችን በማሳተፍ ዩኒቨርሲቲዎች የብዝሃነት፣ የአብሮ መኖር እና የጋራ ትርክት ግንባታ ማዕከል ስለመሆናቸው ሰፊ ዳሰሳ አድርጓል።
🎓 ዩኒቨርሲቲዎች “የትንሿ ኢትዮጵያ” ማሳያ፡ ወጣቶች በብዝሃነትና አንድነት ዙሪያ የጋሩት ተሞክሮ፡- ሳምንታዊው የ‹‹ሀምሳ ሎሚ›› የሬዲዮ ፕሮግራም በቅርቡ ባቀረበው መሰናዶ፤ በመቀሌ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ የነበሩ ወጣቶችን በማሳተፍ ዩኒቨርሲቲዎች የብዝሃነት፣ የአብሮ መኖር እና የጋራ ትርክት ግንባታ ማዕከል ስለመሆናቸው ሰፊ ዳሰሳ አድርጓል። 🤝 ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የነበረባቸውን የቋንቋ እና አካባቢን ያለማወቅ ፍርሃት ነበረባቸው፤ ከጊዜ በኋላ ግን ቋንቋ በመማማር፣ አዳዲስ ባህሎችን በማወቅ እና ጠንካራ ጓደኝነት በመመስረት የነበረውን የተሳሳተ አመለካከት መቅረፍ ችለዋል፡፡ 🤝 ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መሰባሰብ ትልቅ ሀብት መሆኑን ያነሱት ወጣቶቹ፤ "ማንነት እንደ አንድ ክር ነው። የተለያየ ቀለም ያለው ክር ተሸምኖ ውብ ልብስ እንደሚሰራው ሁሉ፤ የኛም ልዩነት ጥንካሬያችንን እና ውበታችንን ይጨምራል እንጂ የግጭት መንስኤ መሆን አይችልም" ነበር ያሉት። 🌎 ዘመኑ የዲጂታል እንደመሆኑ መጠን ወጣቱ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የሀሰትና አፍራሽ ትርክቶችን በንቃት በመለየት፤ ሚዲያውን ለሰላም፣ ለአንድነት እና እንደ ደም ልገሳ ላሉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ሊጠቀምበት እንደሚገባ መክረዋል፡፡ 📱 ወጣቶች የሀገር ተረካቢ በመሆናቸው በንግግር ማመንን፣ ችግሮችን በውይይት መፍታትን እና የሰላም አምባሳደር መሆንን ሊላመዱ ይገባል። 🗣 "ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም፣ ለሀምሳ ሰው ግን ጌጥ ነው!"
ህገወጡ የህወሓት ቡድን የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም የትግራይን ወጣቶች ለጦርነት እያዳረገ እንደሚገኝና ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር እያሴረ መሆኑ ተገልጧል። ከአፈናው ሸሽተው ያመለጡት ወጣቶች እንደገለጹት፤ በሽሬና አዲግራት ከተሞች "ጦርነት በቃን ፣ ሰላም እንሻለን" ያሉ ወጣቶች በአደባባይ እየተገደሉ ሲሆን፣ ታዳጊዎችም በጉልበት ለጦርነት እየተወሰዱ ነው።
የህወሓት እኩይ ሴራና በትግራይ ወጣቶች ላይ እየደረሰ ያለው አፈና … ህገወጡ የህወሓት ቡድን የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም የትግራይን ወጣቶች ለጦርነት እያዳረገ እንደሚገኝና ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር እያሴረ መሆኑ ተገልጧል። ከአፈናው ሸሽተው ያመለጡት ወጣቶች እንደገለጹት፤ በሽሬና አዲግራት ከተሞች "ጦርነት በቃን ፣ ሰላም እንሻለን" ያሉ ወጣቶች በአደባባይ እየተገደሉ ሲሆን፣ ታዳጊዎችም በጉልበት ለጦርነት እየተወሰዱ ነው። የቡድኑ አመራሮች ከኮንትሮባንድና ከወርቅ ንግድ በዘረፉት ሀብት የግል ጥቅማቸውን እያካበቱ፣ ለተራበው ሕዝብ የሚመጣውን ሰብዓዊ እርዳታም ለታጣቂዎቻቸው ቀለብነት በመቀማት ረሃብን የማንበርከኪያ መሣሪያ አድርገውታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለጹት፤ ህገወጡ ቡድን የትግራይን ሕዝብ ለሥልጣን ጥማቱና ለወንጀል መሸሸጊያነት በመጠቀም ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈፀመበት ይገኛል። የቀድሞ የህወሓት አመራር ዶክተር አረጋዊ በረሄ በበኩላቸው፤ ቡድኑ ከግብፅና ከሌሎች የራሳቸውን ሰላም ማጽናት ካቃታቸው አካላት ጋር በመሰለፍ "ጽምዶ" የተባለ የከሸፈ ሴራ በመጎንጎን ቀጣናውን ለማወክና ለጦርነት ለመዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል። የጥፋት ቡድኑ ተግባር ከትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን፣ ይህ ታሪክና ትውልድ ይቅር የማይለው የክህደት ጎዳናው በታሪክ ማኅደር ተመዝግቧል።
በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት ተግዳሮቶች እየበዙ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በአንድ ስራ ብቻ ተወስኖ መቅረት ለስኬት በቂ እንዳልሆነ የ24 ዓመቱ ወጣት ካሊድ አሊ ይናገራል። በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ የሚሰራው ካሊድ፣ በአሁኑ ሰዓት ወጣቶች የራሳቸውን የዲጂታል አካዳሚ በመክፈት፣ አዳዲስ ክህሎቶችን በማዳበር እና የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ስራዎች በመፍጠር ከዋና ስራቸው ጎን ለጎን ገቢ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት እንዳለባቸው ይመክራል።
በአዲስ አበባ የሜትር ታክሲ ሹፌር የሆነው ሰሎሞን አማረ ታክሲውን ወደ ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት በመቀየር የንባብ ባህልን እያበረታታ ነው። መጽሐፍትን እንዲያነቡና የሚወዷቸውን እንዲገዙ ያበረታታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአምስት ዓመታት በፊት የገቧቸውን ቃሎች መፈጸማቸውን ምሁራን ገለጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአምስት ዓመታት በፊት በመስቀል አደባባይ በዓለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቧቸውን ዋና ዋና ቃሎች ተግባራዊ ማድረጋቸውን ምሁራን ገለጹ። ኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉት የአዳማ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁር ዶክተር ገመቺስ መርሻ እና የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ጀማል መሐመድ እንደተናገሩት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል። እንደ ምሁራኑ ገለጻ፣ ከተከናወኑት አበይት ተግባራት መካከል፦ • ሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕ፦ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መቋቋሙ እና የሽግግር ፍትሕ አዋጅ መጽደቁ ለዘላቂ ሰላም እና የታሪክ ቁስሎችን ለማከም ትልቅ መሠረት ጥሏል። • ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፦ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጫናዎችን ተቋቁሞ የግድቡን ግንባታ ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ለቀጣይ ትልልቅ ፕሮጀክቶች መነሳሳትን ፈጥሯል። • የተቋማት ግንባታ እና የባህር በር፦ የመከላከያ፣ የአየር ኃይል እና የባህር ኃይል ማሻሻያዎች የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የማስከበር አቅም ያሳደጉ ሲሆን፣ የባህር በር ጥያቄም የአደባባይ አጀንዳ መሆን ችሏል። • የኢኮኖሚ እመርታ፦ ሀገራዊ ኢኮኖሚው ከግብርና ጥገኝነት ወጥቶ በብዝሃ ዘርፎች እንዲመራ የተደረገው ጥረት አወንታዊ ውጤት አሳይቷል።
“ብዙ ስራዎችን በአንድ ጊዜ” የመስራት ሚስጥሩና ወጣቱ ትውልድ… በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት ተግዳሮቶች እየበዙ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በአንድ ስራ ብቻ ተወስኖ መቅረት ለስኬት በቂ እንዳልሆነ የ24 ዓመቱ ወጣት ካሊድ አሊ ይናገራል። በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ የሚሰራው ካሊድ፣ በአሁኑ ሰዓት ወጣቶች የራሳቸውን የዲጂታል አካዳሚ በመክፈት፣ አዳዲስ ክህሎቶችን በማዳበር እና የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ስራዎች በመፍጠር ከዋና ስራቸው ጎን ለጎን ገቢ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት እንዳለባቸው ይመክራል። “ብዙ ስራ በአንድ ጊዜ መስራት ቀላል አይደለም” የሚለው ካሊድ፣ ለዚህም ዋናው መፍትሄ “ታይም ማኔጅመንት” ወይም ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም መሆኑን ያሰምርበታል። እያንዳንዱን ሰዓት በስኬጁል መከፋፈል፣ ማታ ማታ የሚኖሩትን ተጨማሪ ሰዓቶች ለራስ ስራ ማዋል እና በዲጂታል ዘመኑ ተፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን መቅሰም ለስኬት ቁልፍ መሳሪያዎች ናቸው። “ችግሮች ቢኖሩም መሞከር ውጤት ያመጣል” የሚለው ካሊድ፣ ወጣቱ ትውልድ በቴክኖሎጂ ታግዞ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች መጋፈጥ እንደሚችል እምነቱን ገልጿል። #ስራፈጠራ #ዲጂታልኢትዮጵያ #ወጣቶች #ስኬት #ታይምማኔጅመንት #ኢትዮጵያ #ካሊድአሊ
видео или голосовое, без подписи
ታክሲውን ወደ ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት የቀየረው ወጣት!! በአዲስ አበባ የሜትር ታክሲ ሹፌር የሆነው ሰሎሞን አማረ ታክሲውን ወደ ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት በመቀየር የንባብ ባህልን እያበረታታ ነው። መጽሐፍትን እንዲያነቡና የሚወዷቸውን እንዲገዙ ያበረታታል። በታክሲው ውስጥ ተሳፋሪዎች በጉዞ ላይ የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ተሳፋሪዎች በጉዞ ላይ ጊዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ ያበረታታል፤ እንዲሁም የሚወዷቸውን መጻሕፍት እንዲገዙና የንባብ ባህልን እንዲያዳብሩ ያነሳሳል። ከዚህ በተጨማሪ በSol Books በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ መጻሕፍትን በማስተዋወቅ ለወጣቶችና ለሌሎች አንባቢዎች የንባብ ፍቅርን ለማሳደግ ይሰራል። የእሱ ተነሳሽነት ትራንስፖርትን ከመጓጓዣነት ባለፈ የዕውቀትና የባህል ማዕከል ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳይ ተምሳሌት ሆኗል፡፡ በሊያ ተስፋዬ
የዘንድሮው የፌደራል መንግስት በጀት፣ ከባለፉት አመታት አንጻር ከፍተኛ እድገት በማሳየት 2.3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። ይህ ታሪካዊ የበጀት ጭማሪ፣ ሀገሪቱ በራሷ አቅም ለልማት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
видео или голосовое, без подписи