tgindex
Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1

Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1

Статистика

This is AradaFm 95.1 Official Telegram Channel አጭር የመልዕክት መቀበያ 8545

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
85
Всего постов
153
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 226
−2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
129
40 постов
Вовлечённость
3,1%
к подписчикам
Постов в день
12,1
всего 153
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
96
1/48двое суток
110
1/72трое суток
118

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ቅዳሜ ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! መልካም ቀን ! @Arada_Fm

  • ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርድዮቪች ሚቾን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በይፋ ሾመ ነሐሴ 8፣ 2018(አራዳ ኤፍ ኤም) የ31 ጊዜ የሊግ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ስኬታማ አሰልጣኙን ሰርድዮቪች ሚቾን በአምስት ዓመታት ውል ሹሟል። በሸራተን አዲስ ሆቴል በተደረገው መርሐግብር ላይ ከሰርብያዊው አሰልጣኝ በተጨማሪም ኢንስትራክተር ስዩም ከበደንም የቴክኒክ ዳይሬክተር በማድረግ ሹመት ሰጥቷል። በመድረኩ ላይ ሁለቱም በቀጣይ ሊሰሩ ያሰቧቸውን ዕቅዶች ያቀረቡ ሲሆን የክለቡን አካዳሚ በትክክለኛው መንገድ ከማዋቀር እስከ አፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ሻምፒዮንነት የሚደርስ ነው። ከ16 ዓመታት በኋላ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት የተመለሱት አሰልጣኝ ሚቾ የአሰልጣኞች ስታፍ አባላታቸውንም በገለፃቸው ወቅት ያቀረቡ ሲሆን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ እና የአካል ብቃት እና የፐርፎርማንስ አሰልጣኝ አማካሪዎች መካተታቸው ተገልጿል። ክለቡ አዳዲስ ያስፈረማቸው ተጫዋቾችም በመርሐግብሩ ላይ የተዋወቁ ሲሆን በመጪው ማክሰኞ በይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ላይ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን ይጀምራል። በመስከረም ወር የመጀመሪያ ሳምንታት ላይም ወደ አንድ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር በመጓዝ እስከ ሶስት የሚደርሱ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች እንደሚያደርግ ተገልጿል። በተጨማሪም በመድረኩ ላይ ለ17 ዓመት በታች ቡድኑ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። ሐብታሙ ምትኩ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • የደራሲ ቤተማርያም ተሾመ አዲስ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል   ነሐሴ 8፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የደራሲ ቤተማርያም ተሾመ ‘ቡናዬ እስኪሰክን…’ የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ነገ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ተገለጸ።   ምረቃው አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጽሐፍት ከሰዓት በኋላ በ8:30 ጀምሮ ይከናወናል።   መጽሐፉን በማንበብ እንዲሁም ከደራሲው ጋር በመገናኘት ሃሳብ ለመጋራት ፍላጎቱ ያላቸው የመጽሐፍትና የጥበብ ወዳጆች ሁሉ በቦታው ተገኝተው የዝግጅቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።     የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • የሳምንቱ ዓለም አቀፍ ዐበይት ዜናዎች ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም   የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና አዲስ የዋጋ ክብረ ወሰን አስመዘገበ   ነሐሴ 8፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) አንድ ኪሎግራም የኢትዮጵያ ቡና በ2 ሺህ 275 የአሜሪካ ዶላር በመሸጥ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።   ይህ የተመዘገበው በቅርቡ በሻንጋይ አዘጋጅነት በተካሄደው Solum SOURCING SHANGHAI COOWAY ዓለም አቀፍ የቡና ጨረታ ውድድር ላይ ሲሆን፥ ዋጋው በምንዛሪ ተመን ሲሰላ 364 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ነው።   ቡናው በሲዳማ ክልል በንሳ አካባቢ በጥንቃቄ የተመረተ ሲሆን በዘመናዊው “አናኢሮቢክ” የቡና ማቀናበር ዘዴ የተመረተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማህበር አስታውቋል።   ቡናው ያለው ተፈጥሯዊ ጣዕም፣ ልዩ መዓዛና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ በጨረታው ላይ በተገኙ የዓለም አቀፍ ቡና ገዢዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ማትረፉን መረጃው አመላክቷል።   የኢትዮጵያን ቡና ገጽታ ከማሳደግ፣ ለአርሶ አደሮች ከፍተኛ ማበረታቻ ከማስገኘት እና ከውጭ ምንዛሪ እድገት አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ተገልጿል።     የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • የሳምንቱ የሀገር ውስጥ ዐበይት ዜናዎች ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም   የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • без подписи

  • ኢትዮጵያና ማላዊ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ስምምነት ተፈራረሙ ‎ ነሐሴ 8፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ስምምነቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ ፈርመዋል። ‎ ‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ወቅት፥ ፍልሰት እድሎችም ተግዳሮቶችም ያሉት ውስብስብ ሂደት መሆኑን ጠቅሰዋል። ‎ ‎ፍልሰትን በአግባቡ ማስተዳደር ከተቻለ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠንና እና ቀጠናዊ ውህደትን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልፀዋል።   ‎ኢትዮጵያ ለፍልሰት ምንጭ፣ መጓጓዣ እና መዳረሻ ሀገር እንዲሁም ማላዊ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚወስደው ደቡባዊ መንገድ ዋና ኮሪደርና ወሳኝ የመጓጓዣ መስመር መሆኗን አንስተዋል። ‎ ‎የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለው ትብብርና አጋርነት የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱን ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።   ዜጎችን ለመታደግና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን ለማስቆም ማላዊ በቁርጠኛነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።     የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • без подписи

  • የቻይናው ‘ስካይ ኤክስ’ ተሽከርካሪ ነሐሴ 8፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ቻይናውያን በሰማይ መብረር እና በውሃ ላይ መንሳፈፍ የሚችል ተሽከርካሪን ይፋ አድርገዋል። ቻንግሻ ናይትሃውክ ኢንተለጀንት ቴክኖሎጂ በተሰኘው ኩባንያ የተሰራው ይህ ‘ስካይኤክስ’ የተሰኘው ተሽከርካሪ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሰራ ነው። የተሽከርካሪው ንድፍም ከ‘በራሪው ዓሣ’ የተቀዳ ነው። ተሽከርካሪው አየር ላይ ክንፎቹን ዘርግቶ የሚበር ሲሆን፥ ውሃ ላይ ደግሞ ክንፎቹን በማጠፍ ይቀዝፋል። ውሃ ላይ በሠአት 50 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት የሚጓዝ ሲሆን፥ በአየር ላይ ለ1 ሠአት ያክል መብረር ይችላለ ተብሏል። በርካታ የዲዛይን ሙከራዎችን እና ፍተሻዎችን ያለፈው ቴክኖሎጂ አሁን ላይ ለውሃማ አካላት ጥበቃና ቅኝት፣ ለመከላከያ እና ለአስቸኳይ ጊዜ አደጋ አገልግሎት ይሰጣል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical Telegram:-https://t.me/Arada_Fm Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm @Arada_Fm

  • ዛሬ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ከጠዋቱ 2፡00-9፡30 ጎፋ ዳታ ሴንተር፣ አይሱዙ ጋራዥ፣ ሶፉመር ብሎኬት ማምረቻ፣ ባቱ ኮንዶሚኒየም፣ መካነ ኢየሱስ፣ መካኒሳ ቆሬ መሄጃ እና አካባቢው፣   መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ አሚጎ ካፌ ፊትለፊት፣ ቫቲካን ኤምባሲ፣ መካኒሳ አቦ ቤ/ክ፣ የመከላከያ ሚ/ር መኖሪያ፣ ጥቁር አባይ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ፣ሰላም አስከባሪ እና አካባቢው፣ ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ፣ ካራ ከብት ተራ፣ ጥሩ መናፈሻ፣ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢው፣ ኮልፌ 18፣ አጠና ተራ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል፣አበበ ቢቂላ ስተድየም፣ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት፣ ታይዋን ገበያ እና አካባቢው፣ ቡራዩ አኔ ዲማ፣ ወታቤቻ፣ ጉዱ፣ ሙሎ፣ ከሚሴ፣ ድሬ ከአስፋልት በላይ፣መናገሻ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ እና አካባቢው፣ ከጠዋቱ 3፡00-10፡30 አያት ለገጣፎ ሰብስቴሽን ፊትለፊት ያሉ ኮንዶሚኒየሞች፣ ሸገር ዳቦ፣ ለገጣፎ፣ ሲዲሲ፣ ኮሰሮ፣ አርትስቲ፣ ዱከም እና አካባቢው፣ ከጠዋቱ 3፡00-8፡00 ቤላ ሰብስቴሽን፣ ሚኒሊክ ሆስፒታል ፣ ወደ 6 ኪሎ አንበሳ ግቢ፣ አራት ኪሎ፣ ፓርላማ፣ ግቢ ገብርኤል ቤ/ክ፣ ጣሊያን ኤምባሲ፣ ቤተ-መንግስት በፊል፣ ግንፍሌ እና አካባቢው፣ ከጠዋቱ 3፡30-10፡30 ሱሉልታ ከተማ፣ ሱሉልታ ቆዳ ፋብሪካ፣ ኮሶ በር፣ አቢሲኒያ ሲሚንቶ፣ ሙሎ እና አካባቢው፣ ጫንጮ ከተማ፣ ቆሬ ሮባ፣ ጫንጮ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ፣ ሆስፒታል ፣ ሞየ ጎጆ፣ ሰብስቴሽን አከባቢ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 በጭሮ ቀርሳ፣ ቁሉቢ፣ ላንጌ፣ ወተር፣ ኮሮሚ፣ ደደር፣ ጎሮ ጉቱ መልካ በሎ፣ ሜታ ወረደዎች እና አካባቢው፣ በአዳማ ቀበሌ፣ 01፣05፣ 12፣ ገንደ ኦዳ፣ ሞጆ ፣ጭሮ ከተማ፣ ቦርዶዴ፣ አንከር፣ ኮሞነ፣ ኮረ፣ ቤካ፣ ኢጂፈረ እና አካባቢው፣

  • без подписи

  • በ3 ሺህ ላሞች ላይ በተደረገ ጥናት በአማካይ 760 ሊትር ተጨማሪ የወተት ምርት ማግኘት ተችሏል - የኔዘርላንድስ ልማት ድርጅት   ነሐሴ 8፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ጥናቱ በኔዘርላንድስ ልማት ድርጅት (SNV)፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በምርምር ተቋማት በጋራ የተካሄደ ሲሆን፥ ጥናቱ በተተገበረባቸው አርብቶ አደሮች ዘንድ በአንድ የእርባታ ዑደት በአማካይ 760 ሊትር ተጨማሪ የወተት ምርት ማግኘት ተችሏል ተብሏል።   ላም ተኮር የምክር አገልግሎት አተገባበር በላሞች የወተት ምርታማነት ላይ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን በኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ኢትዮጵያ መሪ የኤክስቴንሽን ባለሙያ ተረፈ ታዬ ተናግረዋል።   ባለሙያው እንዳሉት የእንስሳቱን አጠቃላይ የእድገት ደረጃ ያማከለ እንክብካቤ ማድረግ መቻሉ ምርታማነቱን ከመጨመሩ ባሻገር የጥጃ ሞትን ለመቀነስና የኮርማ ፍላጎት ድግግሞሽን ለማስተካከል አስችሏል።   ይህ በሰባት ወር እርጉዝ ላሞች እና በ3 ሺህ 500 አርሶ አደሮች ላይ የተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ መሆኑ ተገልጿል።   የላሞቹ አካላዊ ብቃት በመስተካከሉ ድጋሚ ለፅንስ ዝግጁ የመሆን እድላቸው መጨመሩንም ገልፀው አሰራሩ ውጤታማ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በ10 ክልሎች በሚገኙ 80 ሺህ ላሞች ላይ እየተተገበረ እንደሚገኝ አመላክተዋል።   እንቁጣጣሽ ኃ/ማርያም     የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • የአራዳ የደቂቃ ስብስብ ዓለም አቀፍ ዜና ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም   የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • без подписи

  • አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ መታሰቢያ   ነሐሴ 8፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ልዩ የመታሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተዋል።   የኢትዮጵያ የቴአትር ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ቢንያም ወርቁ እንዳስታወቀው ደበበ እሸቱ ከ60 ዓመታት በላይ በቆየው የሙያ ጉዞው በቴአትር አዘጋጅነት፣ በተዋናይነት፣ በደራሲነት፣ በተርጓሚነት እንዲሁም በፕሮዲዩሰርነት በርካታ ድንቅ ሥራዎችን ሰርቷል።   በተጨማሪም በሲኒማው ዘርፍ በሃገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከታወቁ ባለሙያዎች ጋር በመስራት የሀገሩን ስም ያስጠራ ሲሆን፥ የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆንም አገልግሏል።   የአንድ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅቱም እሁድ ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 - 4:00 ሰዓት ጀምሮ ባለሙያው በተማረበት ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በቀድሞ ተማሪዎች የተዘጋጀ ልዩ የከበሬታና የመታሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳል።   ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የአርቲስቱን ሥራዎች የሚያስታውሱ የመድረክ ትርኢቶች፣ ዘጋቢ ፊልምና የፎቶ አውደ-ርዕይ እንደሚካሄድ የማህበሩ መግለጫ አመላክቷል።     የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • የአራዳ የደቂቃ ስብስብ የሀገር ውስጥ ዜና ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም   የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи