የተ/ኢ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል
Статистикаይህ የቴሌግራም ገጽ በቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል እና ጻ/አ/ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ተስፋ ኢየሩሳሌም ሰንበት ትምህርት ቤት ፈቃድ ለትምህርት ክፍል ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ተከፈተ ። በዚህ ገጽ - በአምድ የተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 114
- 1/48двое суток
- 130
- 1/72трое суток
- 140
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
እንዴት ሰነበታችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! ✨መንፈሳዊ የርቀት ትምህርት✨ የርቀት ትምህርት ሦስተኛ ዙር ምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት እሁድ ነሐሴ 10፣ 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ3:30-5:30 ሰዓት በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ ስለሚሰጥ ተገኝታችሁ እንድትማሩ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን! ለበለጠ መረጃ 👉 https://t.me/+Yc4bCggmYs81ZGZk የቴሌግራም ግሩኙን ይቀላቀሉ #ትምህርት ክፍል https://t.me/tmhrt12
видео или голосовое, без подписи
ለሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እውቅና የተሰጠው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ በተዘጋጀው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበረው የሥራ አመራር ምርጫ መመሪያ መሠረት በማድረግ ተስፋ ኢየሩሳሌም ሰ/ት/ ቤታችን ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የሥራ አመራርና የኦዲትና ኢንስፔክሽን ተመራጮች እጭዎች ጥቆማ በመቀበል ከፍተኛ ድምፅ ያገኙትን የመለየት ሥራ አጠናቆ መመሪያው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የጸሎት መርሐ ግብር ወደማስደረጉ ተገብቷል። እጩዎቹ በእጣ የመለየት ሥራ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:45 ጀምሮ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ የሰ/ት/ቤት አንድነት ታዛቢዎች፣ የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሚከናወን ይሆናል። ሰ/ት/ቤታችንን ለተከታታይ ለሦስት አመታት ሰ/ት/ቤትን የሚመሩ ወንድምና እህቶች በፈቃደ እግዚአብሔር በአባቶች ጸሎት በእጣ የሚመረጡ በመኾኑ ኹለም አባል በሰአቱ በመገኘት የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን። አስመራጭ ኮሚቴ
видео или голосовое, без подписи
ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ነሐሴ ፩ በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር 21 ቀን በ49 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ “እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ እንዳያውኩን በእሳት እናቃጥላት” ብለው በዓመፃ ተነሡ:: ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊም አጎበሩን ይዞ ሊያወርዳት ሲል የእግዚአብሔር መልአክ ሁለት እጆቹን ቀጥቶታል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ጨምሮ እመቤታችንን በደመና ነጥቆ ወደ ገነት ወስዶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣት፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም እመቤታችን ያለችበት ቦታ እንዲገለጥላቸው ባረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ከዚህ ላይ “ስምንት ወር ሙሉ ምን ይዘው ቆይተው ነሐሴ ላይ ሱባዔ ገቡ?” የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፡፡ በእውነቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ከስብከተ ወንጌል፣ ከጾም፣ ከጸሎት፣ ከገቢረ ተአምራት፣ ተለይተው እንደማያውቁ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ምስክር ነው፡፡ በመኾኑም እመቤታችን ካረፈችበት ቀን ከጥር ወር ጀምሮ እስከ ነሐሴ ድረስ ጥያቄያቸውንና ጸሎታቸውን ባያቋርጡም ከሰው ተለይተው ሱባዔ ገብተው ጾም ጸሎት የጀመሩት ግን ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ነው፡፡ ቀድሞስ የክብር ባለቤት የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ኾነው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተሠውራባቸው እንዴት ዝም ብለው ይቀመጣሉ? ሁለት ሱባዔ ካደረሱ በኋላም የነገሩትን የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታቸውን ሰምቶ ነሐሴ 14 ቀን የእመቤታችንን ሥጋ ሰጥቷቸው በክብር ገንዘው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡ በሦስተኛው ቀንም እንደ ልጇ እንደ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታለች፡፡ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘውም ይህ ታሪክ ነው:: ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሲሰብክ ቆይቶ ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ አገኛት፡፡ በዚህ ጊዜ “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን?” ብሎ ትንሣኤዋን ባለማየቱ ኀዘን ስለ ተሰማው ከደመናው ይወድቅ ዘንድ ወደደ፡፡ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” እንዲል፡፡ እመቤታችንም “አይዞህ አትዘን፤ ባልነጀሮችህ ሐዋርያት ያላዩትን ትንሣኤዬን አንተ አይተሃል” ብላ ከሙታን ተለይታ መነሣቷንና ማረጓን እንዲነግራቸው አዝዛ የያዘቸውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ እርሱም ትእዛዟን ተቀብሎ በክብር ከተሰናበታት በኋላ ወደ ሐዋርያት ሔዶ እንዳልሰማ እንዳላየ መስሎ “የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ?” አላቸው፡፡ እነርሱም “አግኝተን ቀበርናት” ሲሉት “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይኾናል?” አላቸው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ በፊት የክርስቶስን ትንሣኤ መጠራጠሩን ጠቅሶ እየገሠፀ ስለ እመቤታችን መቀበር እነርሱ የሚነግሩትን ኹሉ መቀበል እንደሚገባው ለቅዱስ ቶማስ አስረዳው ቅዱስ ቶማስም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ሲሰማው ቆየ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ተቈጥቶ የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ ለቅዱስ ቶማስ ለማሳየት ሔዶ መቃብሯን ቢከፍት የእመቤታችንን ሥጋ ሊያገኘው አልቻለም በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ ቆመ ቅዱስ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ አግኝቻታለሁ” ብሎ የሰጠችውን ሰበን ለሐዋርያት ሰጥቷቸዋል እነርሱም በእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት እየተደሰቱ ሰበኑን ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩን በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ ዲያቆኑ በሚይዘው መስቀል ላይ የሚታሠረው መቀነት መሰል ልብስ፤ እንደዚሁም አባቶች ካህናት በመስቀላቸው ላይ የሚያደርጉት ቀጭን ልብስና በራሳቸው የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው። በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት “ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?” ብለው ከየሀገረ ስብከታቸው ተሰባስበው ጌታችን ሥጋዋን እንዲሰጣቸው በጠየቁበት በዚሁ ወቅት ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ቢይዙ ጌታችን ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ እመቤታችንንም ሐዋርያትንም አቍርቧቸዋል እነርሱም እመቤታችንን በዓይናቸው ከማየት ባሻገር አብረው ሥጋውን ደሙን ተቀብለዋል፡፡ በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣ ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን፡፡ ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ፤ ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን፡፡
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እውቅና የተሰጠው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ በተዘጋጀው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበረው የሥራ አመራር ምርጫ መመሪያ መሠረት በማድረግ ተስፋ ኢየሩሳሌም ሰ/ት/ ቤታችን ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የሥራ አመራርና የኦዲትና ኢንስፔክሽን ተመራጮች እጭዎች ጥቆማ በመቀበል ከፍተኛ ድምፅ ያገኙትን በመለየት መመሪያው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የጸሎት መርሐ ግብር ወደማስደረጉ ተገብቷል። እጩዎቹ በእጣ የመለየት ሥራ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:45 ጀምሮ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ የሰ/ት/ቤት አንድነት ታዛቢዎች በተገኙበት የሚከናወን ይሆናል። በጥቆማው መሠረት ለሥራ አመራር እጩነት በአባላት አብላጫ ድምፅ በማግኘት የተመረጡት:- 1.ሀብታሙ ምናለ 2.ቤተልሔም ካሥዬ 3.አቶ አብርሃም ቲመርጋ 4.አቶ ኤርምያስ በዳዳ 5.ወ/ሮ የትናየት ወልዴ 6.አቶ ሳምሶን በለጠ 7.ወ/ሮ ሰናይት ሠጠኝ 8.ዲ/ን ሳምሶን ገሠሠ 9.ዘማሪት ቡርክታዊት በላይ 10. ዲ/ን በአንተዓለም ተመቸው 11. ዲ/ን ብንያም መኩሪያ 12. ዲ/ን ብንያም አድማሱ 13. አብርሃም መልኩ 14. ይድነቃቸው ሹምዬ 15. ዲ/ን የአብጸጋ ስዩም 16. ፍቅርተ ተክሉ 17. ሜሮን አሸናፊ ለኦዲትና ኢንስፔክሽን የተጠቆሙ እጩዎች 1.አቶ ዮሐንስ ደመቀ 2.ወ/ሮ መዓዛ ቀለመ ወርቅ 3.መ/ር ሀብታሙ አበበ 4.ኤልያስ ከበደ 5.ወ/ሮ ዮዲት በላይ 6.ዮርዳኖስ መታፈሪያ 7.ዲ/ን እስጢፋኖስ ግዛቸው 8.በኃይሉ ዘለቀ መሆናቸውን እያሳወቅን ሰ/ት/ቤታችንን ለተከታታይ ለሦስት አመታት ሰ/ት/ቤትን የሚመሩ ወንድምና እህቶች በፈቃደ እግዚአብሔር እንዲመረጡ፣ እግዚአብሔር ጸጋውን እንዲያድላቸው በጸሎት እንድታስቧቸው እናሳስባለን። አስመራጭ ኮሚቴ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи