tgindex
Wanaw Media - ዋናው ሚዲያ

Wanaw Media - ዋናው ሚዲያ

Статистика

Media - ሚዲያ

Последний пост
16 июл.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 630
−4 за 4 дн.
Сутки
−2
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
846
25 постов
Вовлечённость
32,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ### የአሜሪካው አምባሳደር ጎንደር ገቡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለሥራ ጉብኝት ጎንደር ገብተው ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። አምባሳደሩ በቆይታቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልንና የአሜሪካን ኮርነር ማዕከልን የሚጎበኙ ሲሆን፣ በትምህርት፣ በጤና እና በሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ ከከተማውና ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይመክራሉ።

  • በደቡብ አፍሪካ የፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ መሪ የነበረው ግለሰብ ተገደለ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው ፀረ አፍሪካውያን ስደተኞች እንቅስቃሴን ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆነው አንዲሌ ሶምጋዳ ባልታወቀ ሁኔታ መገደሉ ተሰምቷል። በሀገሪቱ የፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴውን የበለጠ ሊያባብሰው እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። ሕገ ወጥ የተባሉ አፍሪካውያን ስደተኞች ከደቡብ አፍሪካ እንዲባረሩ ባለፉት ወራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሶምጋዳ 'ማርች ኤንድ ማርች' የተባለውን እንቅስቃሴ ከሚመሩት መካከል እንዱ ነበር። ጋውቴንግ በሚባለው አካባቢ የሚካሄዱ የፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ መሪ ወይም አስተባባሪ እንደሆነ የሚነገረው ግለሰቡ ባለፈው ሳምንት ከሚኖርበት ቤት አካባቢ ነበር በጥይት የተመታው። ቢቢሲ ይህ ግለሰብ ከጥቃቱ በኋላ ሆስፒታል ለበርካታ ቀናት ከቆየ በኋላ ሕይወቱ ማለፊ ተሰምቷል ብሏል።

  • ላይኛው ደሴ ነው ታችኛው ኮምቦልቻ ወሎ ፍቅር እንጂ አያውቅም ጥላቻ ።  የወሎ ሰው እንግዳ ሲመጣበት  በስሙ አይጠራውም ወርቄዋ፣ ሸጋዬዋ፣ አንገትዋ፣ የምወድህዋ፣የምወድሽዋ፣ አካሌዋ፣ ለስላሳዬዋ፣ ብላለኝ አቦ፣ ጠጣልኝ አቦ፣ እያለ ነው  ወሎ የቦርከና ወንዝ መገኛ፣ የሼኽ ሁሴን ሀገር፣ የብሄር  ብሄረሰቦችና ሁሉም ሀይማኖቶች ተቻችለው የሚኖሩበት፣ የእስልምናና የክርስትና ሀይማኖቶች የእውቀት አባቶች የፈለቁበት፣የአራቱ የሙዚቃ ቅኝት መገኛ፣  ሰው ሰው ስለ ሆነ ብቻ ያለ መስፈርት ሚወደድበት፣ ''ይምጣብኝ አቦ'' እንጂ ኬት መጣህ? ማይባልበት፣ የቆንጆዎች መፍለቂያ፣ የእውነተኛ ፍቅር፣ የሙሃባ፣የዱዓ፣የመቻቻል፣ የገራገሮች ሀገር ወሎ ወሎ እስልምናና ክርስትና አንድ አምሳልና አንድ አካል ሆነዉ ለዘመናት አብነት የዘለቁበት ሰፊ ሚስጥር በውስጣቸው ይዘው ሁለቱን ሀይማኖቶች አቻችለዉ ትዉልድ ያዘለቁ የእነ መምህር አካለ ወልድ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲያሰሩ ፣ መስጊዱን አብረዉ የሚያሳንፁ የእነ ባህታዊ አባ ምስክርና የእነ ሀጂ መሀመድ ገታ ቃል ኪዳን ያለበት ነዉ። ሙስሊሙ ከክርስቲያኑ ክርስቲያኑ ከሙስሊሙ የሚጋባበት፣ የስም አወጣጥ ባህሉ ድንበር የሌለዉ ፍቅርን የሚያንፀባርቅ የወሎ ምድር ነዉ። ልጅየዉ ሰለሞን አባቱ መሀመድ፣ ምንኛ ደስ ይላል ወሎ ላይ መወለድ የተባለበት.... ሰናይ ምሽት!

  • "በአውቶቡስ ላይ ድንጋይ በወረወሩ እናቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን" የመቀሌ ከንቲባ በመቀሌ ከተማ በግዳጅ የታፈኑ ወጣቶችን በጫነ አውቶቡስ ላይ ድንጋይ በወረወሩ እናቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀይሌ አረጋዊ ገለጹ። ከንቲባው በሰጡት መግለጫ፣ ሰሞኑን በቀበሌ 05 የተከሰተውና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው የቪዲዮ ድርጊት "የወጣቶች መገደድ ሳይሆን፣ የትግራይን አጀንዳ ለማደናቀፍ በፀረ-ትግል አካላት የተቀናጀ ሴራ" ነው ብለዋል። በድርጊቱ ላይ በተሳተፉት አካላት ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል።

  • ጥቆማ inbox❗️❗️❗️ ለሚ ናሽናል ስሚንቶ ለመጫን ኩፖን ተቆርጦልን ከቀቆምን 4ኛ ቀናችን ነው ፤ሌሎች ከኋላችን እየመጡ እኛ ቁመን እየገቡ ነው። አዲስ አበባ እያሉ ይቆረጥላቸዋል ።እኛ ቁመን እየገቡ ይጭናሉ ለሚመለከተው አካል ብታደርሱልን ሌላው ከተማ ላይ ግዳጅ ሳይኖር ግዳጅ እያሉ የሚያንገራግሩ ህግ አካላት አሉ ግዳጅ በሌለበት በግዳጅ ሽፋን የተለየ ጥቅም ለማግኘት የሚጥሩ ላይ ክትትል ማድረግ ቢቻል መልካም ነው።

  • без подписи

  • ለጣሊያን ሀገር የሥራ ዕድል የምዝገባ ጥሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር በሆቴልና መስተንግዶ (Hospitality) ዘርፍ የሰው ኃይል ይፈለጋል። የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ጣሊያን ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን። 🏨 የሥራ መደቦች፦ 🔹ጸሐፊ(Commis de Rang / F&B Server) – 19 ቦታዎች 🔹 የፅዳት ሰራተኛ (Room Attendant / Housekeeping) – 20 ቦታዎች 🔹 ረዳት ሼፍ (Commis Chef) – 13 ቦታዎች 🔹 የእቃ አጣቢ (Kitchen Steward / Dishwasher) – 11 ቦታዎች 🔹 የወለል ረዳት (Floor Porter / Houseperson) – 3 ቦታዎች 🔹 የቢሮ አስተናጋጅ (Front Office Agent / Receptionist) – 4 ቦታዎች 🔹 የጥገና ቴክኒሺያን (Maintenance Technician) – 1 ቦታ 🔹 የስፓ ቴራፒስት / የማሳጅ ባለሙያ (Spa Therapist / Masseuse) – 1 ቦታ 📌 የማመልከቻ መስፈርቶች ✅ ከስራው ጋር ተያያዥ የስራ ልምድ ያላቸው ተመራጭ ናቸው። ✅ ለአብዛኛዎቹ የስራ መደቦች የእንግሊዝኛ እና/ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ እውቀት ያስፈልጋል። ✅ ለአንዳንድ የሙያ መደቦች ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫ ወይም የሆቴል እና መስተንግዶ ትምህርት ተመራጭ ነው። 📅 የሥራ ቆይታ አብዛኛዎቹ የስራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የስራ መደቦች ዓመቱን ሙሉ ወይም በበጋና በክረምት ወቅት የሚሰሩ ናቸው። ✅ ለመመዝገብ 1.Labor ID ካሎት በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ያመልክቱ። 2.Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦ 1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ። በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ። 1. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/ ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ። ማሳሰቢያ • ምዝገባም ሆነ ስምሪቲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን ሲሆን ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን እንገልፃለን። • ምንም አይነት ክፍያም የለውም https://www.facebook.com/share/p/1V7Hgpj8U2/

  • 28 июн.1 3001

    без подписи

  • 28 июн.1 1901

    без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ሰበር ዜና፦ በሳዑዲ እና ፈረንሳይ በደረሱ አደጋዎች የ25 ሰዎች ሕይወት አለፈ ​በሳዑዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ በተከሰቱ ሁለት የአየር ላይ አደጋዎች የ25 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ። 📌​የሳዑዲው አደጋ፦ የሳዑዲ አራምኮ ኩባንያ የሆነ ሄሊኮፕተር በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ‘ራስ ታኑራ’ የነዳጅ ማዕከል አካባቢ ተከስክሶ የ14 ሳዑዲውያን ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል። አደጋው የተከሰተው ማዕከሉ ከዩኤስ-ኢራን ግጭት ጋር ተያይዞ ለ4 ወራት ተቋርጦ ሥራ በጀመረ በሁለተኛው ቀን ላይ ነው። 📌​የፈረንሳዩ አደጋ፦ በተመሳሳይ ዕለት በፈረንሳይ በደረሰ የሲቪል አውሮፕላን መከሰከስ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ከአደጋው የተረፈ ሰው አለመኖሩ ታውቋል። ​የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት የአደጋዎቹን መንስኤ ለማወቅ ጥልቅ ምርመራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

  • ሰበር‼️ ኢራን አፀፋዊ ምላሽ ሰጠች‼️ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገሪቱን የባህር ዳርቻዎች ኢላማ ያደረገ የአሜሪካ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ የኢራን ወታደራዊ ኃይል በአካባቢው በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል። በፓኪስታን አደራዳሪነት የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለአደጋ የዳረገው ይህ ድንገተኛ ግጭት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሻክር ያደረገ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የሁኔታውን መባባስ በስጋት እየተከታተለ ይገኛል። (Al Jazeera)

  • 25 июн.1 0992

    በትግራይ ክልል አከራካሪው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ አዋጅ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ታዘዘ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ በተካሄደ ምርጫ ተቋቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት፣ ያጸደቀው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ አዋጅ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፏል። የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ምኅረት ሃጎስ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሰኔ 17 ቀን በጻፉት ደብዳቤ፤ አዋጁ በክልሉ ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ የክልሉ የፍትሕ አካላት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ፖሊስ ኮሚሽን በጊዜያዊነት በሕጉ እየሠሩበት እንዲቆዩ አዘዋል። ይህ አዋጅ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራውና በቅርቡ የተቋቋመው ማዕከላዊ የጸጥታ ዕዝ በበላይነት ያስፈጽመዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) የትግራይ ባለሥልጣናት ይህንን የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ አዋጅ “በዝባዥ” ሲል መኮነኑና በአስቸኳይ እንዲያነሱት ሰሞኑን በይፋ መጠየቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የክልሉ ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ግፊቶችን ወደ ጎን በመተው አዋጁ በፍጥነት መሬት ላይ እንዲወርድ ማዘዙ በክልሉና በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሰላም ሂደት ላይ አዳዲስ ውጥረቶችንና ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል።

  • "ለ31 ሰዎች ሞት ለበርካቶች የአካል ጉዳት ምክንያት የሆነው በኮምቦልቻ (ሀረጎ) አከባቢ የደረሰው የመኪና አደጋ በፍጥነትና በተሽከርካሪው አሮጌነት የተከሰተ መሆኑን መረጃ አሰባስቤያለሁ።"ፖሊስ መረጃው ፦የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ነው።

  • የቀድሞዋ  ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተሾሙ‼ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ሳህለወርቅ ዘውዴን በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ (UNOWAS) የዋና ስትራቴጂያዊ ገምጋሚ አድርገው መድበዋል። በቀጠናው ባላቸው ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ልምድ የተመረጡት ሳህለወርቅ፣ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ለማካሄድ ኃላፊነታቸውን በዚህኛው ወር (ጁን) ማብቂያ ላይ በይፋ ይረከባሉ ተብሏል።

  • ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የሸቀጦች ዋጋ በበለጠ ከመንግስት ለሚያገኙት አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ እየፈተናቸው ነው ተባለ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት አገልግሎቶች ላይ የሚታየው የታሪፍ ማሻሻያ እና ተገልጋዩ አገልግሎት ለማግኘት የሚጠየቀው ወጪ ከፍተኛ መሆን የነዋሪውን ኑሮ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎበታል። በዚህ ምክንያትም የሸማቹ መብት እየተጣሰ በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል። የመንግሥት አገልግሎቶች ትርፍ ማጋበሻ ሳይሆኑ ዜጎችን ለመደገፍ፣ ማኅበራዊ ፍትሕን ለማረጋገጥና በሕግ የተጣሉ ግዴታዎችን ለመወጣት የሚቀርቡ መሠረታዊ አገልግሎቶችና መብቶች ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት በጅምላ እየታዩ ያሉ የዋጋ ጭማሪዎች ሸማቹን ማኅበረሰብ ተስፋ የሚያስቆርጡ፣ ወደ ከፋ ድህነት የሚገፉና ዜጎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ በማድረግ በሚከፍሉት ግብር የመገልገል የዜግነት መብታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ድርጅቱ፡፡ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ያደረጓቸው የዋጋ ጭማሪዎች የማክሮ-ኢኮኖሚውን ሕመምና የሕዝቡን የደመወዝ ወለል ያላገናዘቡ፣ የሸማቹን ኪስ ሙሉ በሙሉ የሚያራቁቱ መሆናቸውን ያነሳ ሲሆን ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአዲስ ፓስፖርት ክፍያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ዋጋ፣ የቴሌኮም አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች ላይ የታወጣን ጭማሬ እንደማሳያ አንስቷል፡፡ በእነዚህ እና በሌሎች የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ጭማሬዎች አገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ እየፈተነው እንደሆነ ተመልክተናል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል፡፡ ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው

  • ሂውማን ራይትስ ዎች ለትግራይ ባለስልጣናት ጥሪ አቀረበ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች፣ በትግራይ ክልል በቅርቡ ሥራ ላይ የዋለው የውትድርና አገልግሎት ሕግ መሰረዝ እንዳለበት አሳሰበ። ድርጅቱ ሕጉ ለግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ መንገድ የሚከፍት እና ተቃውሞን ለመቅጣት ሊያገለግል የሚችል መሆኑን በመግለጽ ትችቱን አቅርቧል። ባለፈው ወር በትግራይ ክልል ምክር ቤት የጸደቀውን ሕግ በተመለከተ የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ምክትል ኃላፊ ላቴሺያ ባድር፣ ባለስልጣናቱ ሲቪል ዜጎችን ለውትድርና በማስገደድ እና ተቃዋሚ ድምፆችን በመጫን ለክልሉ የፖለቲካ ውጥረት መፍትሄ ማምጣት እንደማይቻል ገልጸዋል። ሂውማን ራይትስ ዎች በተጨማሪም ሕጉ ከኤርትራ የግዴታ ብሔራዊ አገልግሎት ሥርዓት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በመጥቀስ፣ የዜጎች መብት እና ነፃነት እንዲጠበቅ ጥሪ አቅርቧል።

  • IRAN እና PAKISTAN የንግድ ልውውጣቸውን ከ3 ቢልየን ዳላር ወደ 30 ቢልየን ዶላር ከፍ ለማድረግ ተስማምተዋል:: 2ቱ አገራት ስምምነት ላይ የደረሱት የኢራን ጠቅላይ ሚንስትር ዛሬ PAKISTANን በጎበኙበት ወቅት ነው::

  • የበርካታ ዩኒቨርስቲዎች የሚቀጥሉት ቀናት ተማሪዎች ምረቃ መርሃግብር🔥 በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በዚህ ሳምንት ያስመርቃሉ። ከማክሰኞ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ተከታዮቹ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ፦ •አርሲ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 16/2018 ዓ.ም) •ራያ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 16/2018 ዓ.ም) •ሠመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 17/2018 ዓ.ም) •ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) •ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) •ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) •ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) •ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) •አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •አዲስአበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ዲላ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •አክሱም ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ጂንካ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ወራቤ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) •ወልድያ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)