ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
Статистикаበዚህ ቻናል ነባር እና አዳዲስ የጥበብ ሥራዎቼን የማቀርብበት ሲሆን እናንተም ሥራዎቼን በመመልከት ውስጣችሁን ታረኩበት ዘንድ እንሆ እላለሁ ። አስተያየትዎን ገንቢ ሃሳብዎን እንዲሁም ማሣል ሲፈልጉ ከታች ባለው መረጃ ይጠቀሙ። @zersh8 0929018509
- Последний пост
- 16 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ታሪክን_የኋሊት ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ መነኮሳቱና ዲያቆናቱ እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጠው ጀኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ነበር፡፡ ጀኔራል ግራዚያኒ የኢጣሊያ የምስራቅ ዕዝ አዛዥና በኋላም የኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ገዥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መነኮሳት ላይ የተለየ ጥላቻ ነበረው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ ኢትዮጵያ እንዳትገዛልን የሚያወግዙ፣ ስለነፃነት የሚሰብኩ፣ አርበኞችን የሚደግፉ ናቸው ፤ የሚል እምነት ስለነበረው ቤተ ክርስቲያኗን ለመበተን ይመኝ ነበር፡፡ የካቲት 12፣ አብርሃም ደቦጭ በቦምብ ካቆሰለው በኋላ ፣ሚስቱን ደብረ ሊባኖስ ገዳም መደበቁን ሰማ፡፡ ይኽም በካህናት መነኮሳት ላይ ያለውን ጥላቻ አጠናከረለት፡፡ ለሸዋ ጦር አዛዠ ፣ለጀኔራል ማልቲ፣ አደጋ የጣሉብኝ ሰዎች በግዛትህ ሲዘዋወሩ ባለመያዝህ ሀላፊነት ትወስዳለህ ብሎ ተቆጣው፡፡ በቴሌግራም ቁጥር 26320 በደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ላይ የግድያ ርምጃ እንዲወሰድ ከገዳሙ አለቃ ጀምሮ ያለምንም ምርጫ መነኮሳቱ ዲያቆናት እንዲረሸኑ ትዕዛዝ አስተላለፈለት፡፡ ጀኔራል ማልቲ፣ በርካታ ቁጥር ባላቸው ወታደሮች ታጅቦ ግንቦት 12 ደብረ ሊባኖስ ደረሰ፡፡ እለቱ የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓል የሚከበርበት ቀን በመሆኑ በርካታ ሰው ተሰብስቧል፡፡ የተራራውን ዙሪያ በወታደር አስከበበው፡፡ ወደ ገዳሙ ሲደርስ ፣ ሊቀበሉት የተሰለፉትን የካህናት “እናንተ ቁጥራችሁ ትንሽ ነው፡፡ ሌሎቹ ለምን አልተቀበሉኝም” ብሎ ተቆጣ፡፡ የተቀበሉትን በቅጥር ግቢው እንዲቆዩ አዞ ፣ሌሎቹን መምህራንና መነኮሳት ታድነው እንዲያዙ አዘዘ፡፡ 300 የሚሆኑ ሞታቸውን የሚጠብቁ አዛውንትና መነኮሳት፣ ዲያቆናትና የንግስ በዓል ለማክበር የሄደውን ሕዝብ እያስገደደ በመኪና ጫናቸው፡፡ ከገዳሙ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሽንኩርት ከተባለው ቀበሌ ሲደርሱ፣ ከመኪና አስወርዶ 300 የሚሆኑትን በጥይት አስደበደባቸው፡፡ ሌሎቹ በዓል ለማክበር ደብረ ሊባኖስ የተገኙትንና ዲያቆናትን ወደ ደብረ ብርሃን ትሄዳላችሁ ብሎ አሳፈራቸው፡፡ በመንገድም ላይ ሲደርሱ 129 የሚሆኑትን ዲያቆናት ገደላቸው፡፡ ጀኔራል ማልቲ ይኽንም ለአለቃው ለግራዚያኒ እለቱን ሪፖርት አደረገ፡፡ ከአሰቃቂው ግድያ በኋላ ወታደሮች ገዳሙን ዘረፉት፡፡ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ፣ መኳንንትና ዝና ያላቸው ኢትዮጵያዊውያን የተቀበሩበት ገዳም ስለሆነ አብሩዋቸው ወርቅ ተቀብሮ ይሆናል እያሉ ቀብራቸውን እየከፈቱ አዩ፡፡ ከሁሉም ብልጫ ያለው ንብረትና መፃህፍት የሚገኙበትን የደብረሊባኖስ ገዳም ጣሊያኖች ያገኙትን ሁሉ መዝብረው ወናውን አስቀሩት፡፡ ገዳሙ ለአገልግሎት ዝግ ሆኖ፣ ቁልፉ ለአካባቢው የኢጣሊያ ሹም መሰጠቱን ግራዚያኒ በቴግራም ለሮም አሳውቋል፡፡ በግራዚያኒ ትዕዛዝ 429 የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳት ፣ ካህናት መምህራንና ሲቪሎች ከተገደሉ ዛሬ 88 ዓመት ሆነ፡፡ እሸቴ አሰፋ ግንቦት 12/2018 የሸገርን ወሬዎች፣
https://vt.tiktok.com/ZS9p2B6Bp/
видео или голосовое, без подписи
ዜና_ዕረፍት ለበርካታ ዓመታት ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ቅዱሱን ሕያው ወንጌል በታማኝነትና በትጋት ያለዕረፍት ያገለገሉት መምህር_ዘለዓለም_ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከድካመ ሥጋ ዐረፉ። ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ ገብርከ ወልደ_ሰማዕት ሀገረ ሕይወት መንግስተ ሰማያት ያውርስልን፤ በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service
ማስታወቂያ ለኦርቶዶክሳዊያን ሠዓሊያን፣ ቀራጺያን፣ አርክቴክቶች፣ ግራፊክስ ዲዛይነሮች በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተና እና ችግር ላይ ናት። ይህንንም ፈተና በዘላቂነት ለመቅረፍና ጥበቧን ለቀጣይ ተውልድ ለማስተላለፍ ኅበረት አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሠዓሊያን ኅብረት ለመመስረት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ውድ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የሆናችሁ የጥበብ ሰዎች በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ በቅዱስ ሉቃስና በቅዱስ መብዓጽዮን ስም ጥሪ እናቀርባለን። ቦታ፥ ገርጂ ማርያም የሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ቀን፥ የካቲት 22፣ 2018 ዓ.ም. (እሑድ) 🕰 ከ 8:00 - 11:00 (ከሰዓት) በእለቱ መሳተፍ የምትፈልጉ እስከ የካቲት 20 2018 ዓ.ም. ከታች👇👇👇👇 ባለው መመዝገብ ትችላላችሁ። ፎርም https://forms.gle/G7bFf5D4bj7m9RBa7
በምሥራቅ አርሲ የኦርቶዶክሳውያን ግድያ እና የወጣቶች አፈና አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ የአካባቢው ምእመናን ገለጹ። EOTCMK TV ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ቅዱስ ገብርኤል በተባለ አካባቢ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ባሉበት በጥይት ተደብድበው በግፍ መገደላቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመላክታል ። ከተገደሉት ምእመናን መካከል ዲ/ን ኢዮብ እጅጉ፣ ጥላሁን ቦጌ እና ሕፃን ጻድቃኔ ሠራዊቱ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ይገኙበታል ። ሥርአተ ቀብራቸው በጠለታ ቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦርቶዶክሳውያኑ አፈናና ግድያን በተመለከተ መረጃ አቀብላችኋ በሚል ምክንያት የአካባቢው ወጣት ምእመናን ወዳልታወቀ ሥፍራ ታስረው እየተወሰዱ እንደሚገኝ ምእመናኑ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሥፍራው ላይ የጸጥታ ሓይል ቢኖርም ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ ፣ አፈናና ግድያውም ተባብሶ መቀጠሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ። ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወደ ሆነው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት ሴቶች እና ሕጻናት አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታም እየሸሹ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
"አታልቅሽ ተመልሰው መጥተው ይገሉሻል..."የእናት ማሳሰቢያ *** እንደ ህልም በእዛች በተረገመች ምሽት የተደረገውን አሰቃቂ ግድያ ታስታውሰዋለች። 3 ወንድም እህቶቿን ፣እናቷን እና ሌሎች ቤተሰቦችን ጭምር ይዘው ከእነከብታቸው ስም አልባ የሞት አበጋዝ የሆኑ ታጣቂዎች ነድቷቸው ከአንድ ጫካ ላይ ወስደው አሳረፏቸው። ከመኖርያ ቤታቸው አርቀው ጫካ ላይ ከወሰዱ በኃላ ሁሉም እንዲንበረከኩ አደረጉ። በያዙት መሣርያ ያለርህራሄ አርከፈኩባቸው ።ከተስማው የመሣርያ ጥይት ድምጽ በኃላ ሁሉም ጸጥ አሉ። ከጸጥታው ውስጥ ግን የሚጣጣር እና የሚያቃስት ሰው ድምጽ በትንሽ በትንሹ ይሰማል። እንደ ቤተሰቧ ይህቺ የ8 ዓመት ህጻን በትከሻዋ አከባቢ እና በጎድኗ በኩል ሁለት ጥይት በስቷት አለፈ። በአፈሙዝ ያልሞቱትን በገጀራ ለመጨረስ ሁሉንም መከታተፍ ጀመሩ። ይህችንም ህጻን ልጅ መሃል አናቷን ሰነጠቁ። በጎድኗ እና ትከሻዋ በኩል ዘልቆ ከገባው የመሣርያ ቀለሀ በተጨማሪ ሰይፍ ለእዚህች ህጻን በአናቷ ታዘዘላት። ይህን ድርጊት ከፈጸሙ በኃላ ታጣቂዎች ከስፍራው ሄዱ።ይህች ህጻን ግን ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ገላዋ በደም ረስርሶ ነቃች። ባልጠነከረ የስምንት ዓመት ገላዋ ላይ የገባው ቀለሃ እና ሰይፍ ድምጽ አውጥታ አስለቀሳት። በመሣርያ ተመተው በቆንጨራ ተጨፍጭፈው ከወደቁ አስክሬኖች መሃል የእዚህች እናት የልጇን ድምጽ ሰማች። በተኛችበት ወደ እርሷ ስባ "አታልቅሺ ድምጽሽን ከሰሙ መጥተው ይገሉሻል ዝም በይ " አለቻት። በእዛ ድቅድቅ ጨለማ እና ጫካ ውስጥ ልጅ የእናቷን ትዕዛዝ አክብራ ከህመሟ ጋር ዝም አለች። ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ግን ህጻኗ እናቷ ዳግም እንድታናግራት ለመሞከር ስትጥር ምንም መልስ አትሰጥም። ሞት አጅሬ ወስዳቷል። ጥዋት ላይ ከእስክሬን መሃል ተነስታ ወደ ህክምና ተወሰደች። እናቷን እና 3 እህት ወንድሞችን በእዛችን ቀን በሞት ተነጠቀች። ይህን መርዶ የሰማው አባቷ ጻዲቁ ኢዮብ አይደለም እና " እርሱ ሰጠ እርሱ ነሣ" ብሎ አምላኩን ማመስገን አቃተው። አማረረ። ማማረር ብቻ ሳይሆን ጨርቁን ጥሎ አበደ። የልጆቹ እና የሚስቱን አስክሬን እንኳን በክብር ሳይቀርብ ጨርቁን ጥሎ አበደ። እጆቹን ለሰንሰለት ዳረገ። የቀሩት የሟች ቤተሰቦች ተከፋፍለው የቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ወደ ቀብር ህሊናውን የሳተውን የሟች ልጆች አባት እና የእናታቸው ባል የሆነው አባወራውን ወደ ጸበል ይዘው ሄዱ። ይህ በእኛ ትውልድ መሃል የተፈጠረ ነፍስ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ አሰቃቂ ታሪክ ይህ ነው ። ከጭፍጨፋው በኃላ ሁሉም የአከባቢው ኦርቶለታሪክና ለትውልድ ይቀመጥ። Kune Demelash kassaye -Arba Minch
видео или голосовое, без подписи
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የኦርቶዶክሳውያን ግድያ መቀጠሉን ምእመናን ተናገሩ። የ75 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው ካህን ማንነታቸዉ ባልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። EOTCMK TV ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት በመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ንጉሴ ወልደ መድኅን ማንነታቸዉ ባልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ሌሊት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።። የ75 ዓመት አረጋዊው ካህን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከልጅነት እስከተገደሉበት ቀን ድረስ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከዲቁና እስከ ቅስና አገልግለዋል። በአገልግሎት ዘመናቸውም ዳሪሙ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተባበር አሠርተው ለአገልግሎት ማብቃታቸው ተጠቅሷል። የቀሲስ ንጉሴ ወልደ መድኅን ሥርዓተ ቀብር ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሮቤ ወረዳ እየተባባሰ የመጣዉን የኦርዶክሳዉያን መከራ እና ሞት የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸዉ በተደጋጋሚ ጊዜ የአካባቢው ምእመናን ጥሪ ቢያቀርቡም አሁንም ድረስ የኦርቶዶክሳውያን ግድያና መከራ እንዳላበቃ ከምእመናኑ አንደበት ተገልጿል፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
።።።።። +++ ።።።።።።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи