tgindex
ጥበብ ምንድነው

ጥበብ ምንድነው

Статистика

ምሳሌ 13 ¹ ባለ አእምሮ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም። ² ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ የዓመፀኞች ነፍስ ግን ግፍን ትሻለች። ³ አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋትን ያገኘዋል። ⁵ ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ ኀጥእ ግን ያሳፍራል ያስነውራልም።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 301
−22 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
493
20 постов
Вовлечённость
37,9%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
67
1/48двое суток
76
1/72трое суток
82

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.941удалён 15 авг.

    видео или голосовое, без подписи

  • የህይወት ምልከታ በአንድ ቀዝቃዛና ብርዳማ የክረምት ወቅት ሙቀት ለጋሽ ልብሶችን ደራርቦ በመልበስ በመንገድ ላይ የሚሄድ ሰው #ሙላህ ነስሩዲን አንዲት ሸሚዝ ብቻ ለብሶ ሲሄድ ተመልክቶ በሁኔታው ስለተደነቀ እንዲህ ሲል ጠየቀው ፦ <<ሙላህ! እኔ ይሄን ሁሉ ልብስ ደራርቤ ለብሼ እንኳን ብርዱን አልቻልኩም ፡፡አንተ ግን በዚህች ሸሚዝ ብቻ ጎዳናው ላይ ስትሄድ ትንሽ እንኳን የመብረድ ስሜት አይታይብህም ? >> ሲል ጠየቀው ናስሩዲንም ፦ <<አየህ! አንተ ብዙ ልብሶች አሉህ ። እናም ብርድን የመቋቋም ብቃትህ ተወስዷል ። እኔ ደግሞ ከዚህች ሸሚዝ ሌላ የምለብሰው የለኝምና የብርድ ስሜት ቅንጦት ሆኖ ከውስጤ ጠፍቷል >> በማለት መንገዱን ቀጠለ ። ለዚህ ነው እውነት ለሁላችንም አንድ መስላ ብትታየንም እንደ ሕይወት ምልከታችን እና እምነታች ትርጉሟ የተለያየ ሆኗል ። 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • መስማት ከሚፈልገው በላይ ሰው ከነገርከው፤ ጠላት መባል እንደምትችል ቀድመክም እውቀው። 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • Animation ደስ ስላለኝ ነው በ lyrics የሰራሁላችው............ መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ ውድ ቤተሰቦች🌼🌻🌼🥀🌻🌼🥀🥀🌼🌼🥀🌻

  • እውነተኛ ፍቅር- ፕሌቶ ግሩም ከሆነ የፍልስፍና እሳቤዎች አንዱን ፕሌቶ ከክርስቶስ ልደት 385 ዓመታት በፊት በጻፈው The symposium መጽሐፍ ውስጥ እናገኘዋለን። ይህ መጽሐፍ በታላቁ የቲያትር ደራሲ አጋቶን ቤት ስለተዘጋጀ የራት ግብዣ ያካትታል። ብዙ ጠቢባን ጣፋጭ ምግብን ሊመገቡ፣ ወይን ሊጠጡ እና ቁምነገር ሊያወጉ ታደሙ፡፡ በወንበሮቻቸውም ላይ እንዳሉ የተጠበሱ ምግቦችን እና ጣፋጭ አትክልቶችን መመገብ ጀመሩ፤ ግማሾቹ የወይኑ ስካር በአናታቸው ላይ ይወጣ ጀምሯል። እናም የድግሱ አዘጋጅ የነበረው አጋቶን ሁሉም እየተነሱ ስለ ኤሮስ ወይም ስለ ፍቅር የሚስማቸውን እንዲናገሩ ጋበዛቸው፡፡ እናም ፕሌቶ ንግግር ማድረግ ጀመረ፤ ፍቅርን በሁለት ከፈለው - የመጀመሪያው ምድራዊ ፍቅር ሲሆን፣ ሁለተኛው ፍጹም ንጹህ የሆነ መለኮታዊ ፍቅር ነው፡፡ ምድራዊ ፍቅር የፍቅር መነሻ ነው፡፡ ልክ መስላል ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ እንደምንወጣው ሁሉ፣ ይህም ወደ ፍጹማዊ ፍቅር የሚያደርስ ጅማሮ ነው:: በውስጡም ወሲባዊ ፍላጎት እና ምኞትን ይይዛል። ይህ ፍቅር የሚገናኘው ከሰውነት አቋም እና ከፊት ማማር ጋር ስለሆነ፤ ቆዳ ሲሸበሸብ፣ ጸጉር ሲሸብት የሚጠፋ ፍቅር ነው። ንጹህ ፍቅር - በአንጻሩ ከነፍስያ ጋር ይቆራኛል። በዚህ ፍቅር ውስጥ ስንሆን ከፊት ገጽታም በላይ ጠልቀን የምንገባበት እና ስለ ሰውነት መቀየር ግድ የማይሰጠን እንሆናለን፡፡ ይህ ሁለት ነፍሶች በፍቅር የሚወድቁበት ቦታ ነው። ዛሬ ላይ እንደዚህ አይነቱን ፍቅር ለመግለጽ platonic love የሚል ቃልን እንጠቀማለን፡፡ ፕሌቶ የፍትወት ፍላጎትንም ይቅር አስፈላጊ አይደለም አላለም። ይልቁኑ አንድን ሴት በመልኳ ተማርከን ልንቀርባት እንችላለን፤ ሆኖም ይህን ምድራዊ ፍቅር ንጹህ ወደሆነው መለኮታዊ ፍቅር ማሻገር ይጠበቅብናል፡፡ ፍቅራችን ከሰውነቷ ጋር ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህም በላይ ነፍሶቻችን ሊቆራኙ ይገባል። በእርጅና ዘመናችን አብሮን የሚሆን እና ከውበታችን መክሰም ጋር የማይጠፋ ፍቅር ውስጥ መሆን አለብን። እውነተኛ ፍቅር እውር አይደለም፤ ሆኖም በማስተዋል እና በጥበብ ይመራል፡፡ ከመልክ፣ ከቁንጅናም በላይ ይሄዳል።የተጣመሩ ነፍሳት ፍቅራቸው ከምድራዊው ዓለም አይደለም:: 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • 27 дек.387удалён 14 авг.

    Check out Psycology - ስነ ልቦና አማካሪ ኤጀንሲ: https://t.me/Psycology_helpcenterbot

  • 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🆗አምነን መቀበል ያለብን እዉነታዎች! - አንዳንዴ ዘላቂ መሆኑን እርግጠኛ እስክትሆን ድረስ በሚስጥር መያዝ መልካም ነዉ፣ - እራስህን ለማግኘት የተወሰኑ ሰዎችን ማጣት ሊኖርብህ ይችላል፣ - አንድ ላይ መሆንን እንደቻልከዉ ሁሉ መለየትንም ትችላለህ፣ - የትኛዉም ነገር ሊሆን ይችላል የአእምሮ ጤናህን የሚያስከፍልህ ከሆነ እጅግ በጣም ዉድ ነዉና ሌላ ፈልግ፣ - ሰዎች አንተን በግል የማያቁህ እስከሆነ ድርስ ንግግራቸዉንም በግል አንተን የሚመለከት አድርገህ አትዉሰደዉ፣ - በፍፁም የጮኸን ነገር ጠንካራ፣ ዝም ያለን ደሞ የማይረባ አድርገህ መገመትህን አስወግድ። ''ያንተን ህይወት በተመለከተ የሌሎችን አስተያየት እየተቀበልክ የራስህን መታሠሪያ ቅጥር አትገንባ ሁሌም ውስጥህ የሚልህን አዳምጥ።''

  • 🎤#ቀደምንም_ዘገየንም_መጨረሻችን_መቃብር ነው፡፡ ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡ እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡ አስታውሳለሁ ፥ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝ ዝና ፥ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 አመት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡ አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡ ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡ እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡ 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . .  ሃዘንተኛ ሰው ሆናችሁ መኖር ከፈለጋችሁ ቀላሉ መንገድ ሁልጊዜ፣ በሁሉም ቦታና በሁሉም ሁኔታ፣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ሲጦዙ መኖር ነው፡፡ ማንም ሰው እንዳያዝንባችሁ፣ ቅር እንዳይሰኝባችሁን ሁል ጊዜ ሁሉም ሰው በእናንተ ሃሳብም ሆነ ተግባር ደስተኛ እንዲሆን የምትፈልጉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አደገኛ የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ከዚያም ትንሽ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ቀላላል እውነቶች . . . • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ሰዎችን ለማስደሰት ሌላ ሌላውን ሲኖር ራሱን ሆኖ መኖር አይችልም፤ ራሱን ሆነ የማይኖር ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡  • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ለማስደሰት በሚፈልገው ሰው ቁጥጥር ስር ይውላል፤ ሰው ተቆጣጥሮ እንደፈለገ የሚያደርገው ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡  • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚሯሯጥ ሰው በየሰዓቱና በየቀኑ የሚለዋወጥ የስሜት ውጣውረድ (ሙድ) ውስጥ ራሱን ያገኘዋል፤ ስሜቱ (ሙዱ) በየጊዜው የሚለዋወጥ ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡ • ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው “ሰዎችን ያስደስትልኛል” ከሚለው ሃሳብ አንጻር እንጂ ከዓላማ አንጻር መኖር አይችልም፤ ከዓላማ ውጪ የሚኖር ሰው ደግሞ ደስተኛ  መሆን አይችልም፡፡ በሕይወታችሁ ሰዎችን ማስደሰት እጅግ ደስታን የሚሰጥ ልምምድ መሆኑን ማስመራችንን ሳንዘነጋ፣ የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ግን ማንም ሰው ቅር እንዳይሰኝባችሁ፣ በክፉ እንዳያስባችሁ፣ እንዳያወራባችሁ፣ እንዳይገፋችሁ . . . ከሆነ የዚህች ምድር አጭር እድሜያችሁን በኃዘን የምታሳልፉ ሰዎች ናቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማይቻል ትደርሱበትና ያን ጊዜ ደግሞ ያንን የማይቻል ነገር ለመቻል ስትጦዙ ዓመታቶቻችሁን ስላባከናችሁ በመቆጨት ታዝናላችሁ፡፡ በሉ እንግዲህ፣ ማድረግ ወደምትችሉትና ወደሚገባችሁ እውነታ ተመለሱ! ማድረግ የምትችሉት፣ በገባችሁና በአቅማችሁ መጠን ለራሳችሁ ጨዋ ኑሮን መኖር፣ ለሰዎች ደግሞ መልካም ሰው መሆንና ሁልጊዜ ከስህተት ለመታረም የተዘጋጀ ልቦና ማዳበር መሆኑን አትዘንጉ፡፡ 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • "…ነገን ማሰብ ተገቢ ቢሆንም ፣ በዛሬ ጥረት ነገን የተሻለ ማድረግ አርቆ አሳቢነት ቢሆንም ዛሬን ገድሎ ነገን ለመውለድ ማሰብ፣ ዛሬን አበላሽቶ ነገን ማሳመር፣ ዛሬን አጨልሞ ነገን ማብራት ግን ሞኝነት ነው። ዛሬን አቆሽሸን ነገን ማፅዳት አይቻልም። ..." * * * በሁለንተናው ኃይል ቅጽበቷን ኑራት : ይህ ቀላሉ የደስተኝነት ሚስጢር ነው። ምንም ነገር ስታደርግ ያለፈው ሁኔታ በጭንቅላትህ እንዲሄድ አትፍቀድለት ፣ ለወደፊት ያለውም እንዲረብሽህ አትፍቀድለት። ምክንያቱም ያለፈው አብቅቷል ፣ የወደፊቱ ገናአልመጣም። በትዝታ መኖር ፣ የወደፊቱን በማለም መኖር፣በሌለ ነገር ላይ መኖር ነው። በሌለ ነገር ላይ ስትኖር አሁን ያለው ነገር እያመለጠህ ነው። በዚህም ብላሽ ትሆናለህ ምክንያቱም መላው ህይወትህን ትስታለህ። 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • #የሚያጠነክረን የምንበላው ምግብ ሁሉ አይደለም። በልተነው የሚዋሃደን ምግብ እንጂ! ➦ሀብታም የሚያደርገን የምናገኘው ገንዘብ ሁሉ አይደለም፡፡የምንቆጥበውና የምንሰራበት ገንዘብ እንጂ! ➦አዋቂ የሚያደርገን የምናነበው ሁሉ አይደለም፡፡አንብበን የምንገነዘበውና የምናስታውሰው እንጂ! #ክርስቲያኖች (ሙሲሊሞች)የሚያደርገን በንግግር የምንገልጸው አይደለም በሥራ የምናሳየው በጎ ምግባር እንጂ!!!!!!!! /ፍራንሲስ ቤከን/ 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • ከ"ሕማማት" መጽሐፍ የተወሰደ አዳም ረታ እንዳስነበበን................ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያውቃል ማለት አስቀድሞ ይወስናል ማለት አይደለም ። ነገሮችም የሚሆኑት እግዚአብሔር አስቀድሞ ስላወቃቸው ሳይሆን በተቃራኒው እርሱ ያወቃቸው ስለሚሆኑ ነው ። እግዚአብሔር ስለወደፊት ያለው እውቀት እኛ ስላለፈው ታሪክ የዓይን ምስክሮች ሆነን እንደምናውቀው ያለ ነው።.../ አስቀድሞ የተነገሩ ትንቢቶች እንዴት ይታያሉ መጀመሪያ ትንቢት እንደ መንስኤ ሳይሆን እንደ ውጤት ካልተረዳነው ነገሩን ለመረዳት እንቸገራለን ። ትንቢቶች የሚነገሩት ነገሮች ስለሚሆኑ ነው እንጂ ነገሮች የሚሆኑት ትንቢት ስለተነገረ አይደለም "ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድይህ ሆነ ተብለው የተጻፉት ቃላት ሁሉም የተጻፉት ትንቢቱ እንደተፈጸመ ከተረጋገጠ በኋላ ነው እንጂ ትንቢቱ እስከሚፈጸምባት እስከመጨረሻዋ ቅጽበት ድረስ ትንቢቱ የተነገረበት ሰው ትንቢቱን የመለወጥ እድል አለው ። እግዚአብሔር የተናገርኩት ከሚጠፋ ብሎ የሰዎችን የመዳን በር የሚዘጋ ጨካኝ አይደለም ስለሰው ልጅ መጥፋትና መዳን የሚነገሩ ትንቢቶች እንደሁኔታው ሊፈጸሙ የሚችሉ ትንቢቶች (conditional prophecies ) ናቸው እንጂ እንደ ሰማይ ምድር ማለፍ የማይለወጡ ትንቢቶች (fixed prophecies )አይደሉም ። 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏 Your AB 🎗          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • በጠባብ ደረት በዐጭር ቁመት! ብዙ ሰዎች የክርክር ምክንያት የሆነውን ቪዲዮ ለማግኘት ጠይቃችሁ ነበር! ቪዲዮው እነሆ! የተናጋሪው መሠረታዊ ችግር በነገረ መለኮቱ ዓለም “The Economic Trinity” የሚባለውን ፅንሰ ዐሳብ ከ”The Immanent Trinity” ጋር ክፉኛ ማምታታቱ ነው! “The Immanent Trinity” የአምላክ ኑባሬዊ ማንነት ሲሆን ይህ ጉዳይ በድነት ታሪክ ውስጥ (history of salvation) ለእኛ እንዴት እውን ሆነ ወይም ኢየሱስ ትስብእት ሲሆን የተነገረንን ጉዳይ ከአምላክ ማንነት አንጻር ማጣረሱ ነው! ስለዚህ "አብ "በእርሱ" የሆነ አንዳችም ነገር የለም እንዲሁም ወልድ "ከእርሱ" የሆነ አንዳችም ነገር የለም" የሚለው የግለሰቡ ንግግር ከላይ ያለውን መሠረታዊ ልዩነት እርስ በርስ ያጠናበረ ነው! 1ቆሮንቶስ 8:6 መሠረት ተደርጎ አብ "ከእሱ" ብቻ ነው "በእርሱ" አይደለም እንዲሁም ወልድ "በእርሱ" ብቻ ነው "ከእርሱ አይደለም ከተባለ "ከ" እና "ለ" በጥምረት ለአንድ አካል ብቻ የዋሉባቸውን ምንባባት ምን እናድርጋቸው? (ለምሳሌ ሮሜ 11:36 "ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።" እነዚህንም ክፍሎት ይመለከቷል:- ራእ. 5:12-14 ቆላ. 1:15-18 ዕብ. 2:10 ይሁዳ 1:25 ዕብ. 1:2-3 ኤፌ 4:5-6 ፊልጵ 2:9-11 ዮሐ 17:21-23 ማቴ 11:27 ይህ አንድ የሥላሴ አማኒ ነኝ የሚል ሰው ሊጠነቀቅበት የሚገባው ነጥብ ነው! ፍርጥም ብሎ መናገር ጥሩ ቢሆንም "ነገሩ እንዲህ ይሆንን?" ብሎ መጠየቅ ከወንጌል አገልጋይ ይጠበቃል! Disclaimer: ከላይ ግልጋሎት ላይ የዋሉት ሙያዊ ቃላት ዛሬ ቃሉ በደርዛዌ ነገረ መለኮት ውስጥ ግጋግሎት ላይ የዋለበትን ዐሳብ ተንተርሶ የቀረበ እንጂ በጥንታውያኑ ሊቃውንት ዘንድ የነበረውን ቀደምት ክርክር በሚያሳይ መንገድ ጥቅም ላይ የዋለ አይደለም! ስለዚህ አንዳንድ ችኩል ተቺዎች "Etymological Fallacy" እንዳይፈጽሙ ለማሳሰብ ነው! 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • ከአንዲት አህያ የተገኘ ትምህርት አንድ ቀን የገበሬ አህያ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀች። አህያዋ  ለሰዓታት ጮክ ብላ አለቀሰች፤ገበሬው አህያዋን  ለማውጣት የሚረዳው አንድ ነገር ለማግኘት ሞከረ፤ ጉድጓዱ ደርቆ የነበረ እና በማንኛውም ነገር መሞላት እንዳለበት ወሰነ፤  ጎረቤቶቹን ሁሉ እንዲረዱት ጋበዘ።  እያንዳንዳቸው አካፋ ያዙ እና ወደ ጉድጓዱ ውስጥ ቆሻሻ መጣል ጀመሩ። አህያው እየሆነ ያለውን ነገር ስለተገነዘበች በአሰቃቂ ሁኔታ አለቀሰች።  ከዛ ሁሉንም ሰው ያስገረመ ነገር ተከሰተ ከጥቂት አካፋዎች ቆሻሻ መሞላት በኋላ የአህያዋ ልቅሶ ጸጥ አለ። ገበሬው በመጨረሻ ቁልቁል ወደ ጉድጓዱ ውስጥ ተመለከተ እና ባየው ነገር ተገረመ ... በእያንዳንዱ አካፋ አፈር አህያው የማይታመን ነገር እያደረገ ነበር: ቆሻሻውን እያራገፈ  እይረገጠ ነበር ፤ ብዙም ሳይቆይ አህያዋ ወደ ጉድጓዱ አፍ እንደደረሰች፣ ከዳርቻው በላይ እንደወጣች ተመልክተው ሁሉም ተገረሙ።    ሩሚ       ወዳጄ ህይወት ቆሻሻዎችን ልትጥልብህ ትችላለች ፣ ሁሉንም አይነት ቆሻሻ!! ከጉድጓዱ የመውጣት ዘዴው እሱን አራግፈህ ወደ ላይ ከፍ ማድረግ ነው።  የእያንዳንዳችን ችግር አንድ ደረጃ ነው። ተስፋ ካልቆረጥን ከገባንበት ጥልቅ ጉድጓድ መውጣት እንችላለን ደስተኛ ለመሆን 5 ሕጎችን ያስታውሱ- 1. ልብህን ከጥላቻ ነፃ አድርግ። 2. አእምሮዎን ከሚረብሹ ነገሮች ነፃ አድርግ። 3. ህይወትዎን ቀላል አድርጋት ( ከአላስፈላጊ ውስብስበነት እራስህን አርቅ ) 4. ብዙ ይስጡ እና ያነሰ ይጠብቁ 5. አብዝተህ ውደድ እና... ቆሻሻውን አራግፍ ምክንያቱም በዚህ ህይወት ውስጥ ችግር ሳይሆን መፍትሄ መሆን አለብህ 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • አስተማሪ ታሪክ😀👇 ማታ ላይ ለአቶ ባል መልዕክት ይደርሰዋል፤ በስልክ፡፡ : ባልም ለወይዘሮ ሚስት “ነገኮ ዘመዶቼ እንመጣለን አሉኝ …” ብሎ የሰማውን ያጋራል፡፡ . ሚስትም ተበሳጭታ፦ “ቆይ ለምንድነው የሚመጡት …” . ባል፦“እሱንማ እኔ ምን አውቃለሁ … ጉዳይ ይኖራቸው ይሆናላ፤ ብቻ በሰላም ነው ብለውኛል …” . ሚስት፦ “ስንት ሆነው ነው የሚመጡት?” . ባል፦“እሱንስ አልጠየኳቸውም … እንዲሁ እንመጣለን ሲሉ እሺ አልኩ እንጂ …” . ሚስት፦“ታዲያ የመጡ እንደሆነሳ?” . ባል፦“አይ! … እንድንዘጋጅ ብዬ ነው፡፡ መቼስ እንግዳ ሲመጣ ዝም አይባል …” . ሚስት፦“እኔ ምንም የማዘጋጀው የለኝም … ቤቱን እንደሆነ ያውቁታል … አዲስ አይደሉም … ” . ባል፦“የሚገዛም ነገር ካስፈለገም ልገዛዛና ሰርተን እንጠብቃቸው እንጂ” . ሚስት፦“ምንም አያስፈልግም … ያለውን ይቀምሳሉ” . ባል፦“ምን አለ …” . ሚስት፦ “ውሃስ ቢሆን … ሌላ የማዘጋጀው የለኝም!” . ባል፦“ኧረ ተይ … ሰው አለን ብለው አይደል ወደኛ መምጣታቸው … እንደገቡ እንኳ የሚቀማምሱት ብናዘጋጅ አይሻልም …” . ሚስት፦“ይምጡና ያለውን አቀርብላቸዋለሁ" . . ይችኑ እንደተባባሉ ነጋ፡፡ ባልም በማለዳ ተነስቶ የቤቱን ሁኔታ ሲያይ ምንም የለም … ቁርስም የለም … ጭጭ … ጭጭ … ሚስትም ለጥ ብላ እንደተኛች አረፈደች፡፡ ባል ሹልክ ብሎ ወጣ፡፡ ወዲያው የሚስት እናት፣ አባት እና ሌሎችም ተሰባስበው ከተፍ አሉ፡፡ ደንግጣ ተነስታ ተቀበለቻቸውና ወደ ባል ደወለች … . ሚስት፦“ለምንድነው ዘመዶችሽ ይመጣሉ ብለህ ያልነገርከኝ” . ባል፦“እንዴ! ነግሬሽ የለ …” . ሚስት፦ “ዘመዶቼ ይመጣሉ ነውኮ ያልከኝ!” . ባል፦“አዎ! ያው ያንቺ ዘመዶችስ የኔ ማለት አይደሉ እንዴ!” . ሚስት፦“እሺ አሁን ምን ላድርጋቸው” . ባል፦“ሌላ ምን ታደርጊያቸዋለች አስተናግጃቸው እንጂ” . ሚስት፦“የተዘጋጀ ደህና ነገር የለማ” . ባል፦“ታዲያ ምን ይሻላል?” . ሚስት“በቃ … ከምግብ ቤትም ቢሆን የሚበላ ነገር ገዛዝተህ ና እንጂ …” . ባል፦“እኔ እንኳ አሁን መምጣት አልችልም፤ እቆያለሁ … አንቺን ምን አስጨነቀሽ … ለቤቱ እንደሆነ አዲስ አይደሉ … ያለውን ነገር ስጫቸው” . ሚስት፦“ምንም ነገር የለምኮ!” . ባል፦“ … ውሃም ቢሆን ስጫቸው … 😂 ዘመዶቼ መልካምነት ለራስ ነው። 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • ‹ፌሚኒዝም እና ቤተ ክርስቲያን› (እንደ መግቢያ) ‹ፌሚኒዝም› ስለሚባል እንቅስቃሴ ከዚህ በፊት ሰምተን የማናውቅ ሰዎች እንኖር ይሆን? ለማንኛውም ለነገሩ እንግዳ የምንሆን ካለን ፌሚኒዝም ሴቶች በፖለቲካው ፣በኢኮኖሚው እና በማኅበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ የአሸናፊነት (የበላይነት) ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚንቀሳቀስ ሴቶች መር ንቅናቄ ነው፡፡ በርግጥ ጉዳዩን በለዘብተኛነት ይዘው የሴቶችን አቅም ለማሳደግ የሚጥሩ ጥቂቶች በመካከል ቢኖሩም ፤ በአንጻሩ የፋክክር ስሜቱን እጅግ በማጦዝ ጠርዝ የረገጠ የሴትነት እሳቤ ይዘው የሚሞግቱ ግን ብዙዎች ናቸው። ይህም ንድፈ ሐሳብ በአጠቃላይ የሴት እኅቶቻችንን ማንነት እና የሥራ ድርሻ በተመለከተ በዓለሙ ላይ ትልቅ የሐሳብ መዛነፍን ፈጥሯል፡፡ በተለይ መረጋጋትና ማስተዋልን የተላበሱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ ይህ የባዕድ አመለካከት ጥላ ሲያጠላ መመልከት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተን እንድናጤነው ያደርገናል፡፡ በንድፈ ሐሳቡ አራማጆች የሚነሡ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ከመመልከታችን በፊት ፣ ለመሆኑ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን እንዴት ይታያሉ? የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አዳምና ሔዋን የፈጣሪን ሕግ በመተላለፍ የበደሉ ቢሆንም ፤ በሰይጣን ወጥመድ ቀድማ በመውደቅና የጠላትን ምክር በመስማት ሞት ወደ ዓለም እንዲገባ ምክንያት የሆነችው ግን ሔዋን ነች (1ኛ ጢሞ 2፡15)፡፡ ስለዚህም እርሷ ከሰይጣን አግኝታ ለባሏ በመከረችው ክፉ ምክር የገነትን ደጅ በፍጡራን ሁሉ ፊት እንዲዘጋ አደረገች፡፡ በመሆኑም እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ ለወንዶች የሚከፈቱ የዕድል በሮች ሁሉ በሴቶች ፊት ግን የታተሙ ነበሩ፡፡ ሴትን አክብሮ ርስት የሚያካፍላት ፣አምኖ ለምስክርነት የሚያቆማት ማንም አልነበረም፡፡ በሄደችበትም አንገቷን የምትቀብር እና ከቁም ነገር የማትቆጠር ሆናም ትኖር ነበር፡፡ ክብር ይግባውና ሕግን በመተላለፍ በሰው ልጆች ላይ የወደቀውን ርግማን ሊያነሣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሰው በሆነ ጊዜ የሴቶችን መዋረድ ሁሉ አስወግዶላቸዋል፡፡ በዚህም ሴቶችን የማክበር አምላካዊ ተግባር የሥራው መጀመሪያ ያደረጋት ለዓለም ሴቶች ሁሉ የመመኪያ አርማ የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ወንዶች ምንም ራሳቸውን ከሴቶች በላይ ከፍ ከፍ ያድርጉ እንጂ ከእነርሱ ግን አንዳቸውም ‹የእግዚአብሔር አባት› ተብለው የተጠሩ (በመሆን) አልነበሩም፡፡ ከሴቶች ወገን ግን በማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር አምላክን በመውለድ ‹የእግዚአብሔር እናት› ተብላ ትጠራ ዘንድ ለድንግል ፈቃዱ ሆነ ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ገና በማዳኑ ሥራ መጀመሪያ በብሉይ ኪዳን ተንቀው የነበሩትን ሴቶች ምን ያህል ከፍ ከፍ እንዳደረጋቸው በገሃድ አሳየ፡፡ አምላካችን ክርስቶስም በመዋዕለ ስብከቱ በሰማርያ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ከሳምራዊቷ ሴት (ብርስፌንያ) ጋር ሲነጋገር ሐዋርያቱ ባዩት ጊዜ እንደተደነቁ ተጽፏል፡፡ ከሴት ጋር መነጋገሩ ለምን አስደነቃቸው? ካልን በጊዜው ከሴቶች ምን ቁም ነገር ይገኛል በሚል ፈሊጥ ሴትን በአደባባይ ማናገርን እንደ ሐፍረት በሚያዩ የአይሁድ ማኅበረሰብ መካከል ሆኖ እርሱ ግን ከሳምራውያን ወገን የሆነች አንዲትን ሴት አክብሮ ማናገሩ ነበር(ዮሐ 4፡27)፡፡ በኪሩቤል ጀርባ ተጭኖ የሚበርር አምላክ በሰማርያ ሊያልፍ ግድ የሆነበት ምክንያት ከዚህች ሴት ጋር ተገናኝቶ እርሷን ለማሳመን እንደሆነ ቢያውቁ ኖሮ ሐዋርያቱ አሁን ከተገረሙት እጥፍ ድርብ ይገረሙ ነበር!፡፡ በሌላም ጊዜ ፈሪሳውያን ስታመነዝር አግኝተው የያዟትን ሴት ይፈርድባት እንደሆን በክርስቶስ ፊት አቁመዋት ነበር፡፡ ልብ አድርጉ ይህችን ሴት የያዟት ከወንድ ጋር ስታመነዝር ቢሆንም ለፍረድ ያቀረቧት ግን ብቻዋን ነው፡፡ አብሯት በዝሙት ኃጢአት እኩል ባለ ድርሻ የሆነውን ወንድ ምረው ፤ ሴቷን ግን በአደባባይ እያዋከቡ ወደ ክርስቶስ አቀረቧት፡፡ አምላካችን ክርስቶስም ፈሪሳውያኑ ያሰቡባትን ፍርድ (ውግራት) አስቀርቶ ‹እኔም አልፈርድብሽም ፣ሂጂ ከአሁን ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ› ብሎ በፍቅር ቃል አሰናብቷታል (ዮሐ 8፡11)፡፡ ጌታችን የአንቀጸ ብፁአንን ትምህርት ባስተማረበት ክፍል በአይሁድ ዘንድ ከሴቶች ጋር በተያያዘ ሥር ሰዶ የነበረውን ክፉ ኅሊና ሲያርም እናገኘዋለን፡፡ ይኸውም አንዳንድ አይሁድ ሴቶችን እንደ ፍትወት ማብረጃ ብቻ አድርጎ የማየት አባዜ ስለነበረባቸው ይህን በመንቀፍ ‹እኔ ግን እላችኋለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝርዋል› ሲል አስተምሯቸዋል (ማቴ 5፡28)፡፡ ይህም የመድኃኒታችን ቃል ሴቶች በተለያየ መንገድ ማበርከት የሚችሉትን ወሳኝ አስተዋጽዖዎች ወደ ጎን በመተው ፤ ለወሊድ እና ለጾር ቀንበር ማቅለያ ብቻ እንደተፈጠሩ እስኪመስል ድረስ እነርሱን በአንድ አቅጣጫ ብቻ መርዞ ማየት ኃጢአት መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡ 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • መሀመድ የተላከው ለመካ በጎች ነው Narrated Abu Huraira: The Prophet ( ﷺ) said, "Allah did not send any prophet but shepherded sheep." His companions asked him, "Did you do the same?" The Prophet ( ﷺ ) replied, "Yes, I used to shepherd the sheep of the people of Mecca for some Qirats." አቡ ሁረይራ እንደተረኩት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ነብይ የላከው ሁሉ በግ ጠብቋል።" ባልደረቦቻቸውም "አንተም እንዲሁ አድርገሃል?" ብለው ጠየቁት። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ መለሱ "አዎ እኔ ለመካ ሰዎች በጎችን በጥቂት ቂራጦች እጠብቅ ነበር።" ﺣَﺪَّﺛَﻨَﺎ ﺃَﺣْﻤَﺪُ ﺑْﻦُ ﻣُﺤَﻤَّﺪٍ ﺍﻟْﻤَﻜِّﻲُّ، ﺣَﺪَّﺛَﻨَﺎ ﻋَﻤْﺮُﻭ ﺑْﻦُ ﻳَﺤْﻴَﻰ، ﻋَﻦْ ﺟَﺪِّﻩِ، ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ ـ ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ـ ﻋَﻦِ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲِّ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗَﺎﻝَ " ﻣَﺎ ﺑَﻌَﺚَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻧَﺒِﻴًّﺎ ﺇِﻻَّ ﺭَﻋَﻰ ﺍﻟْﻐَﻨَﻢَ ." ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺃَﺻْﺤَﺎﺑُﻪُ ﻭَﺃَﻧْﺖَ ﻓَﻘَﺎﻝَ " ﻧَﻌَﻢْ ﻛُﻨْﺖُ ﺃَﺭْﻋَﺎﻫَﺎ ﻋَﻠَﻰ ﻗَﺮَﺍﺭِﻳﻂَ ﻷَﻫْﻞِ ﻣَﻜَّﺔَ Reference : Sahih al-Bukhari 2262 In-book reference : Book 37, Hadith 3 USC-MSA web (English) reference : Vol. 3, Book 36, Hadith 463 (deprecated numbering scheme) 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲

  • ......እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። .....ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። .....አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። ገላትያ 1 ፥ 7-9

  • ይሁዳ ምዕራፍ 1፦ ⁴ ..............ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። ⁵ ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ። ⁶ መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል። ⁷ እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። ⁸ እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ ጌትነትንም ይጥላሉ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ። 🤳Share 👇👇👇👇👇👇 ሼር  #SHARE 🙏🙏 #ሼር #SHARE 🙏🙏          ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜           ☞ @Booksshelf22 ☜  ━━━━━━✦✦━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ⇲⇲⇲