tgindex
Physicians

Song of Physician Wisdom

Последний пост
12 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
976
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 335
19 постов
Вовлечённость
239,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12 июн.1 93371

    "የነጭ ልብሴ አቅም ያበቃበት ቦታ ውድ ኢትዮጵያውያን : እኔ ዶ/ር የሮም ጌታቸው እባላለሁ። ከ6 ዓመታት በላይ በሕክምና ሙያ ውስጥ ሰርቻለሁ። በየቀኑ የታመሙ ሰዎችን አክሜያለሁ፣ ለብዙ ቤተሰቦች ተስፋ ሆኜያለሁ፣ ሕይወት ለማዳን በቻልኩት ሁሉ ተግቻለሁ። ዛሬ ግን ልጄን ለማዳን እኔ ራሴ የሰዎችን እገዛ የምሻበት ወቅት ላይ እገኛለሁ። የ3 ዓመት ተኩል ልጄ በአጥንት ካንሰር ተጠቅቷል። ገና ሕይወትን መረዳት ያልጀመረ፣ ሕልሙን መናገር ያልቻለ፣ በእናቱና በአባቱ እቅፍ ውስጥ መጫወት የሚገባው ሕፃን ዛሬ የካንሰር ሕመምና የኬሞቴራፒ ስቃይ እየተሸከመ ነው። እንደ አባት ይህን ማየት ያማል። እንደ ሐኪም ደግሞ የበለጠ ያማል። ምክንያቱም ልጄ የሚያስፈልገውን የላቀ ሕክምና በሀገራችን ውስጥ ማግኘት አልቻለም። ለዓመታት በጤና ሥርዓቱ ውስጥ የሰራሁ ሰው እንደመሆኔ አንድ ሀቅ ልናገር። የሀገራችን የጤና ሥርዓት አሁንም ለእንደዚህ ያሉ ውስብስብ በሽታዎች በቂ አቅም የለውም። ብዙ ሕፃናትና ቤተሰቦች የመጨረሻ ተስፋቸውን ከሀገር ውጭ ባሉ ሆስፒታሎች ላይ እንዲጥሉ ይገደዳሉ። የበለጠ የሚያሳዝነው ደግሞ ሕይወት ለማዳን የሚሰሩ ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከእንዲህ ያሉ ከባድ የጤና ቀውሶች ለመታደግ በቂ የገንዘብ አቅም እንዳይኖራቸው የሚያደርግ እውነታ ነው። ለሌሎች ሕይወት የሚታገሉ ሰዎች ራሳቸው ሲፈተኑ የሚደግፋቸው ሥርዓት የለም። ዛሬ ልጄን ለማዳን እና ወደ ውጭ ሀገር ለሚደረገው ሕክምና ለማድረስ 3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገናል። ይህ ገንዘብ ከቤተሰባችን አቅም በላይ ነው። ከዚህም በላይ የሚያስጨንቀን ጊዜው ነው። ሐኪሞቹ የሰጡን ጊዜ አንድ ወር ተኩል ብቻ ነው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሕክምናውን መጀመር ካልቻልን የልጄ የመዳን እድል በእጅጉ ይቀንሳል። ስለዚህ ይህን መልዕክት እንደ ሐኪም አይደለም የምጽፈው፤ ልጁን ለማጣት የሚፈራ አባት ሆኜ ነው። እባካችሁ የምትችሉትን ያህል ድጋፍ አድርጉ። መልዕክቱን ለሌሎች አጋሩ። ለልጄ ጸልዩ። CBE - 1000149557982 Abay - 2091011011819814 Awash : 013201344371300 Tele birr: 0910119336 GoFundMe: https://www.gofundme.com/f/help-tsegabe-fight-cancer?lang=en_US&ts=1780047340 ለእናንተ ትንሽ የሚመስለው እርዳታ ለልጄ የመኖር እድል ሊሆን ይችላል። ዶ/ር የሮም ጌታቸው

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 30 мая1 9605

    ‛‛ዝም በል እባክህ! ድሮም ፍቅርህ የእውነት አልነበረም። ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ ፍርሃት ፍቅርን አያባርረውም’’ የሚል ጀብደኛ አይጠፋ ይሆናል። እኔም አንድ ሰሞን ማለቴ ዘመን እንዲህ አድርጎኝ ነበር። እናስ? እናማ ፍቅረኛዬን ከእኔ የደከሙ የሚመስሉ እናቷ አጠገቧ ቆመው አበረቷት። የጎበጠው ወገባቸው ከእኔ ልብ ይጠነክር ነበርና እሷን ደግፈው አቆሟት። ሰውነቷ ተመለሰ፣ ጤናዋ ተስተካከለ። ፈገግታዋን ቀርቤ ለማየት ባልደፍርም ከሩቁ አየሁት። ውብ ናት! ‛‛አታፍርም ደግሞ አማላጅ ትልክ ይሆናል’’ ትሉኝ ይሆናል። አዎ አድርጌዋለሁ! መልሷ ‛‛አይሆንም!’’ ነበር። ትክክል ናት! ዛሬ አግብታለች። ከምትወደው ሰው ልጅ አግኝታለች። እኔስ? እኔማ ሰው መሆኔን ተረዳሁ። ዛሬ ነው የገባህ? ትሉኝ ይሆናል። አዎ! ዛሬ ሰውነቴ ገባኝ። ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለሁም። ድካሜን በሂደት ያወቅሁ፣ ወኔና ዐቅም ያላቸውን ልዩነት ጠንቅቄ መናገር የምችል ወንድማችሁ ነኝ። አትፈሩብኝ። እሷን በማጣት ከተቀጣሁት በላይ ልቀጣ የምችለው ነገር ስለሌለ የትኛውም ፍርድ አያስፈራኝም። በትንሿ ልቤ የሚደርስብኝ በምችለው ልክ እቀበላለሁ። የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር

  • 30 мая4698из CraftofPhysician

    የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር

  • Channel photo updated

  • 27 мая2 259173

    📌📌ሞጣ ፣ አዶናይና ጃኒ ያክሙህ📌📌 ኮሜዲያን አማን ቢሰጠኝ የማለዳ ኮከቦች ላይ ሲወዳደር እንዲህ የምትል ዲያሎግ ነበረችው "ምሳህን ከኦማር ቤት ራትህን ደግሞ ከታያር ዱንዳር ቤት ሄደህ ብላ።" ያን ሰሞን ጥቁር ፍቅር የሚባል በቃና ቲቪ የሚተላለፍ ወረረሽኝ የነበረበት ወቅት ነበር። ስፔሻሊስትና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ዲ/ን ዶ/ር ታደሰ ፈንታ ቤት ተሰብስበው ኑ ስለ ጤናችን እንመካከር ሲሉ ባላዬ ባልሰማ ላሽ ብለህ ታልፍና ሞጣ ቀራንዮ ቤት ዘው ብለህ ትገባለህ። እዚህ ታብ ታብ ለማድረግ የሰነፈው ጣትህ እዛ አንበሳና ቀጭኔ ያወርዳል ። የሰው ሕይወት ለማትረፍ 36 ሰዓት የሚሠራ ሐኪም "ለ6 ወራት የሠራሁበት አልተከፈለኝም" ብሎ ሰልፍ በሚወጣበት ሃገር ምን ሠርቶ እንደፈመሰ የማይታወቅ ቲክቶከር መኪና ሲሸለም ቆመህ ታጨበጭባለህ። ያለ ደሞዝ ኢትዮጵያውያንን በማገልገል ላይ የሚገኙት አሜሪካዊቷ የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም የሚል ዜና ይሁን ዘነዘና የማይለይ ፖስት ስታገኝ እንዴት? ለምን? ብለህ በመጠየቅ ፋንታ የሀገርህ ሐኪሞች ላይ እንጀራ የቀደደው አፍህን ት-ከ-ፍ-ታ-ለ-ህ። እንገዲህ ስማ ያለ ምንም ደሞዝ የሚያገለግሉ ሐኪሞች በምድር ላይ የሉም(No free lunch) ። ያለ ደሞዝ ኢትዮጵያውያንን እያገለገሉ ነው የተባሉት ዶክተርም ከኮሚዩኒቲ የሚላክላቸው የሃገርህ ዶክተሮች በግልና በመንግሥት ለፍተው ከሚያገኙት ገቢ በእጅጉ ይበልጣል። አይ ያለ ምንም ደሞዝ የሚያገለግለኝ ሐኪም እፈልጋለሁ ካልህ ደግሞ ዘወትር አንበሳና ቀጭኔ የምታወርድላቸው ሞጣ አዶናይና ጃኒ ቤት ሂድና ታከም ። ላቦራቶሪውን ሀቢባ ላይ አሠርተህ መድኃኒቱን አይ ሾው ስፒድ ፋርማሲ መውሰድም ትችላለህ ። ©FB

  • 26 апр.2 250153

    ይህ የምትመለከቱት ሰው ዶክተር ነው። በእርግጥም እንዲህ የሚያለቅሰው ተቸግሮ ወይም የሚበላው በማጣቱ አይደለም። ነገር ግን ለሰብዓዊ ድጋፍ ሶሪያ ተገኝቶ የምግብ ድጋፍ በሚያድልበት ጊዜ  አንድ ታዳጊ ህፃን የተናገረው ንግግር ነበር። ልጁ ምግብ እየሰጠው ያለው ሰው ዶክተር መሆኑን ሲያውቅ"እባክህ ሁለተኛ እንዳይርበኝ መድሀኒት ወይም መርፌ ውጋኝ"?ሲል ይጠይቀዋል። ይህ ምን ያክል አሳዛኝ እንደሆነ መላው የሰው ልጅ ይገነዘበዋል።1

  • 22 мар.2 650122

    These days, spotting a male gold medalist in med school feels like finding a rare case 😄 What’s going on with us guys? ©debolteam

  • 14 мар.3 485142

    በሩሲያ የህክምና ታሪክ እጅግ አስገራሚ የተባለ እና በዘመናዊው የማይክሮ ሰርጀሪ ዘርፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ የእጅ ንቅለ ተከላ በሞስኮ በሚገኘው ስክሊፎሶቭስኪ የምርምር ኢንስቲትዩት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ ተነገረ። የሩሲያ ፌዴሬሽን የጤና ጥበቃ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት ናታሊያ ማንቱሮቫ እንደገለጹት፣ ይህ ስኬት ሰው ሰራሽ የሰውነት ክፍሎችን ለሚጠቀሙና እጃቸውን በልዩ ልዩ ምክንያት ላጡ ታካሚዎች አዲስ የህይወት ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ታሪካዊ የንቅለ ተከላ ሂደት በሁለት ታካሚዎች ላይ የተከናወነ ሲሆን፣ ውጤቱም እጅግ አበረታች ሆኖ ተገኝቷል።

  • 23 февр.3 090134

    ''እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ። ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል። ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች። ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል። ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው። ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል። ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል። እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን። ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው። ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል። ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው። የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ። እንደሚለወጥ ስለማውቅ። 'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው' ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው። አይመስልህም እንዴ?'' አዳም ረታ

  • 14 февр.2 62053

    እስከመቼ??

  • 6 февр.3 080104

    የህይወት ዘመን ተሞክሮዎቹን መሰረት አድርጎ በፃፈው ግለ ታሪክ ውስጥ ኬኔት ዎከር የተባለ ታላቅ ዶክተር እንደዘገበው ከሆነ ሰዎች ከሚመገቧቸው ምግቦች ውስጥ ግማሽ ያህሉ የተመጋቢዎችን ሆድ የሚሞላ ሲሆን፣ ቀሪው ግማሽ የሚሞላው ደግሞ የዶክተሮችን ሆድ ነው። እነዚህ ሰዎች ዘወትር ከሚመገቡት የምግብ መጠን ግማሽ ያህሉን ብቻ ቢመገቡ ግን ምንም በሽታ ስለማያጋጥማቸው ዶክተር እንደማያስፈልጋቸው ያትታል። ርዕስ፦ የነፍስ መንገድ ኦሾ

  • 27 дек.3 52032

    https://youtu.be/h4jWHMRe6s0?si=eHIvGIoT9gbOMteQ

  • 20 дек.2 6002

    https://youtu.be/cMzN5_lkhoI?si=Tjv6V2Hwaal5nBUs

  • 3 дек.3 190122

    በመከራ መጽናት *** Victor Frankl  በሙያው ሳይካትሪስት ሲሆን: በጀርመን ናዚ የአገዛዝ ዘመን ለአሰቃቂ አስር የተዳረገ፣ በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ብዙ ችግርና ስቃይን ያሳለፈ እና ቤተሰቦቹን በአሰቃቂው የ Auschwitz ካምፕ በሞት የተነጠቀ ሰው ነው:: ይህ ሰው Man's search for meaning የሚል የሰቀቀን ህይወቱን ያተተበት እንዲሁም ከዚያ ሁሉ መከራ በኋላ ተስፋ ሳይቆርጥ እንዲኖር የረዳውን እሳቤ ያጋራበት ድንቅ መጽሃፍ ጽፎልናል:: መጽሃፉም ለብዙ ሰዎች መጽናኛ መሆን የቻለና ጥልቅ የ existentialism የህይወት ፍልስፍናን የያዘ ነው:: Victor Frankl ተስፋ አለመቁረጡ ከ ማጎሪያ ካምፑ ሰቀቀን ወጥቶ ህይወቱን እንዲመራ አድርጎታል:: በአዕምሮ ህክምናው ዘርፍ Logo therapy የተባለን ድንቅ የስነልቦና ህክምናን ከማስተዋወቅ ጀምሮ ድንቅ መጽሃፍትን ሊያበረክትልን ችሏል:: ቪክተር ፍራንክል በመጽሃፉ እንዲህ ይለናል:- 1- በስቃይ እና በመከራ ውስጥም ብንሆን የህይወት ትርጉም ከመፈለግ መታከት የለብንም:: ለተረዳው ሰው: መከራም ቢሆን አንዳች ምክንያት እና ትርጉም አለው:: 2- ብዙ እኛ ልንቆጣጠራቸው የማንችላቸው ጉዳዮች ቢኖሩም: ለሁነቶች የሚኖረን ግብረ መልስ ግን በራሳችን ነጻ ፈቃድ እና አተረጓጎም የሚበየን ይሆናል:: 3- ወርቅ በእሳት ተፈትኖ እንደሚነጥር ሁሉ፤ መከራም ለሰውን ልጅ እንዲያ ነው:: በስነልቦናው Trauma Growth የሚባል ነገር አለ.. አንዳንድ መከራዎች ሊያስተምሩን እና ከፍ ሊያረጉን የተከሰቱ ሊሆኑ ይችላሉ:: ህይወት ሁሌ ተድላ እና ፌሽታ እንዳልሆነች፤ አንዳንዴ ለፈተናም እንደምትሆን አምኖ መቀበል እንዳለብን እና ራስን ለፈተና ማዘጋጀት እንደሚገባን ይገልጻል:: ቀድሞ መወጠኑ ድህረ-ፈተና ቶሎ እንድናገግም ይረዳናል:: 4- ከ Absurdism በተቃራኒ : ህይወትን በዘፈቀደ ሳይሆን በአጽንኦት እና ትርጉም ባለው መንገድ መመራት አለባት ባይ ነው:: 5- ነገሮችን ከግላዊ ምኞትና ፍላጎት ባሻገር መመዘን ተገቢ እንደሆነ ይመክራል:: አለም እኛ በወጠንነው ብቻ ትመራለች ማለት ዘበት ነው:: ሌሎች ሰዎችም የራሳቸው ፍላጎት እና ምኞት አላቸውና: የራስን ፍላጎት ከሌሎች አንጻር አጣጥሞ ማስኬዱ የውዴታ ግዴታችን ነው:: ይህ ለማህበራዊ ህይወት ወሳኝ ጉዳይ ነው:: የሰው ልጅ 'Rational Social Animal' ተብሎ ይገለጻል::  ፍራንክልም ማህበራዊ ህይወታችን ለህይወታችን ጣዕም ወሳኝ ግብአት እንደሆነ ፤ በዚህች አለም ስንኖር አንዳችን ካንዳችን ልንተሳሰብ፣ ልንዋደድ እና  ሃላፊነት ሊሰማን እንደሚገባ ይመክራል:: ** መውጫ :- የህይወት ጣዕሟ  በትናንት ትዝታ እና በነገው ተስፋ ይገለጣል:: የሰው ልጅ ተስፋውን የተነጠቀ ቀን የህይወት ወጋገን መደብዘዝ ይጀምራል:: ከብዙ ራስን ማጥፋቶች ጀርባ ከባድ ተስፋ መቁረጥ ጥላውን አጥልቷል:: ኢትዮጵያውያን በመከራ በመጽናት አንታማም:: ለዚህ የህይወት ፍልስፍና ብዙ አብነቶች ማንሳት ይቻላል:: ከነዚህ አብነቶች መሃል ተመስገን ባዲሶ አንዱ ነው:: ያለፋትን አመታት ከህመሙ ጋር ያለውን ግብግብ፣ የህክምና ሂደቱን፣ ከዚያም ባሻገር ያለውን ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ኑባሬውን በ ማህበራዊ ሚዲያ እያጋራን ይገኛል:: ታዲያ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ሁኖ ለፈጣሪው ያለው መታመን፣ ማህበራዊ ህይወቱን የሚያስኬድበት መንገድ፣ ጽናቱ.. ለብዙዎቻችን ትምህርት መሆን የሚችል ነው:: ይህ ሰው የ ቪክተር ፍራንክልን ፍልስፍና በምልአተ እየኖረው እንደሆነ ይሰማኛል:: አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

  • 2 дек.3 0301

    видео или голосовое, без подписи

  • https://youtu.be/bHANPGERiig?si=T0iYoQdhX4OLaext

Physicians — tgindex