Defence Construction Enterprise
СтатистикаDefense Construction Enterprise (DCE) is one of the leading construction companies in Ethiopia. We are different from other companies as we work in the most remote and difficult areas of the country. We are dedicated and devoted to build the country.
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14:30
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 514
- 1/48двое суток
- 589
- 1/72трое суток
- 635
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ኢንተርፕራይዙ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አዳዲስ ገልባጭ መኪኖችን አስገባ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ቅልጥፍናና ዕድገት ማሽነሪዎች ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። ይህንን ብሔራዊ ዓላማ በመከተል መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የ2024/ 2025 አዲስ ሞዴል 20 ዘመናዊ ገልባጭ መኪኖችን ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ገዝቶ ወደ ሥራ አስገብቷል። የኢንተርፕራይዙ የግንባታ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች አስተዳደር እና ጥገና መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ሀብታሙ ደሬሳ እንደገለጹት፦ በአሁኑ ወቅት የአንድ ገልባጭ መኪና ወርሃዊ ኪራይ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ መሆኑን ጠቁመው አዲሶቹ መኪኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ በዓመት ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ያስችላሉ። ተሽከርካሪዎቹ በጂፒኤስ (GPS) የታገዘ የደህንነት ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግላቸው በመሆኑ የብልሽት ቅነሳ እንዲኖር ያስችላሉ። ግዥው የኢንተርፕራይዙን የመፈጸም አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ ለሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ የደንበኞችን እርካታ እንደሚያረጋግጥ ተገልጿል። በመጨረሻም ተሽከርካሪዎቹ የሀገር ሀብት ጭምር በመሆናቸው፣ ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታቸውን ሳይጨርሱ ለብልሽት እንዳይዳረጉ ሠራተኞችና የሥራ አመራሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official
ዜና እረፍት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአምቦ ወሊሶ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ተሾመ ደምሴ ዳዲ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች በአቶ ተሾመ ደምሴ ዳዲ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን፡፡ ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአዋሽ ሰባት መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ ተካሄደ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአዋሽ ሰባት መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ። በምልከታው ላይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዴር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ እና የኢንተርፕራይዙ የሕንጻ ግንባታ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸናፊ ሐሰን ተገኝተው የፕሮጀክቱ ሥራ አፈጻጸም በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳና በጥራት እየቀጠለ መሆኑን ተመልክተዋል። የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቀሪዎቹን ሥራዎች በተያዘለት ጊዜ አጠናቀን ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በፍጥነት ጨርሶ ለማስረከብ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የአዋሽ ሰባት ማሰልጠኛ ማዕከል ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ኢንጂነር እሸቱ ታደሰ በግንባታው ሂደት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት የጣሪያ፣ የበርና መስኮት ገጠማ፣ የኤሌክትሪክ፣ የሳኒተሪ እና የመንገድ ሥራዎችን ጨምሮ ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። የግንባታ ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አካባቢ ከፍተኛ ሙቀትና የዲዛይን ማስተካከያዎች ቢኖሩበትም፤ የሥራ ሰዓትን እንደየአየር ሁኔታው በማስተካከል፣ እንዲሁም የሰው ኃይልና ቁሳቁሶችን በማሟላት ሥራው ያለምንም ማቋረጥ እየተከናወነ ነው ብለዋል። የማሰልጠኛ ማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ፤ ለ4,200 ሰልጣኞች የሚሆን መኖሪያ፣ ለ900 ሰልጣኞች የሚሆን መመገቢያና ዘመናዊ የምግብ ማዘጋጃ፣ 100 የአሰልጣኞች እና 10 የመኮንኖች መኖሪያዎች፣ 8 የቢሮ ሕንጻዎች፣ ሁለገብ መጋዘን፣ መጸዳጃ ቤቶች፣ የጥበቃ ቢሮ፣ የግቢ አጥርና በር፣ ለሰልጣኞች የምረቃ አገልግሎት የሚሰጥ መድረክ እንዲሁም ከመሠረተ ልማት ጋር የተያያዙ መንገዶችን ያካትታል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕና የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራሮችና ሠራተኞች በ8ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል። ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤትና የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ አመራሮችና ሠራተኞች በቢሾፍቱ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በጋራ በመገኘት አከናውነዋል። በመርሃ ግብሩ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው ኃይለማሪያም፣ የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ተክሉ ፀጋዬና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል። በተመሳሳይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራርና ሠራተኞች በዋና መሥሪያ ቤቱ እንዲሁም በተቋሙ በሚያከናውናቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለአካባቢው የአየር ፀባይ ተስማሚ የሆኑና በረሃማነትን ለመከላከል የሚያግዙ የአትክልትና የፍራፍሬ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች ተክለዋል። የተቋማቱ አመራርና ሰራተኞች እንደገለጹት፣ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር፣ የደን ሽፋንን ለመጨመር፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል። ዘገባው የክፍሎቹ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ https://dfmc.mod.gov.et/ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ https://www.facebook.com/fdredefense.official
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሐረሪ ሪጅን ዋና ጽህፈት ቤት ህንፃ ግንባታ ተጀመረ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ሀገራዊ የልማት አጋርነቱን በተለያዩ ጊዜያት በማስመስከር የሚታወቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሐረሪ ሪጅን ዋና ጽህፈት ቤት ሕንፃ ግንባታ በይፋ ጀምሯል። በግንባታ ማስጀመሪያው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ ኢንተርፕራይዙ በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በሰዓቱ የማጠናቀቅ የቆየ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ላይ በይፋ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሕንፃ ግንባታም በተያዘለት የጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና ማሽነሪ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አረጋግጠው፣ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ በጥራት ተጠናቆ እንደሚረከብ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ ወይዘሮ ለምለም ምስጋናው በበኩላቸው፣ ግንባታው በመከላከያ ኮንስትራክሽን እንዲከናወን መደረጉን ጠቅሰር አዲሱ የሪጅኑ ዋና ጽህፈት ቤት ህንፃ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቅ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። የሕንፃ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የኃይል አቅርቦትና የመሰረተ ልማት አገልግሎት ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አክለዋል። የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኻሊድ ጣሀ በበኩላቸው፣ የግንባታው ሥራ በተያዘለት ጊዜና የጥራት ደረጃ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል። በክልሉ የሚገነባው ይህ የተቋሙ ባለ አስር ወለል ህንፃ ለግንባታው ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበለት ሲሆን፣ በቀጣዮቹ 900 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ https://dfmc.mod.gov.et/ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ https://www.facebook.com/fdredefense.official
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи