EBS TV NEWS
СтатистикаGet the latest headlines and breaking news in politics, business, technology, sports, entertainment, and cryptocurrency. Join our channel for real-time updates and concise, reliable news delivered straight to your device!
- Последний пост
- 16 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Политика
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 457
- 1/48двое суток
- 1 669
- 1/72трое суток
- 1 800
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከአፈር ነዳጅ ለማዘጋጀት የተወጠነው ፈጠራ የት ደረሰ? "ፕሮጀክቱ ሳይቋረጥ አሁንም በላቦራቶሪ ደረጃ ቀጥሏል" - ተመራማሪው በኢትዮጵያ ከአፈር የባዮ-ነዳጅ ለማምረት ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ ሲካሄድ የቆየ የምርምር ፕሮጀክት በፋይናንስ እጥረትና በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ ፋብሪካ ደረጃ እንዳይሸጋገር እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ዋና ተመራማሪው ለአሚኮ ገልጸዋል። ከአስር ዓመታት በፊት በነዳጅ እና በሊቲየም ፈጠራ ሥራቸው የብዙዎችን ትኩረት ስበው የነበሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ መምህር እና ተመራማሪው አቡሃይ ውብሸት ብዙዎች ግኝቱ የት ደረሰ ብለው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ተመራማሪው ፈጠራው ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ባብራሩበት በዚህ ቃለ-መጠይቅ፦ - አሁን ላይ ከአፈር ነዳጅ የመፍጠር ፕሮጀክት፣ በላቦራቶሪ በሚሊ ሊትር ደረጃ ከነበረበት አልፎ አሁን በሊትር ደረጃ (ከ30 እስከ 40 ሊትር) ማምረት የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱን፤ - ለፈጠራው የፓተንት (የባለቤትነት) መብት ማግኘታቸውን፤ - የኢትዮጵያ የጥራት ኤጀንሲ ምርቱ ለተሽከርካሪዎች መዋል እንደሚችል የጥራት ማረጋገጫ መስጠቱን፤ - በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ነዳጁ ተመርቶ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን፤ - ለምርቱ ግብዓት የሚሆነውን «ዶቤ» የተባለ የአፈር ዓይነት ናሙናዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ለማጥናትና ወደ ፋብሪካ ደረጃ ለመሸጋገር የጸጥታ ሁኔታው አስቸጋሪ እንደሆነባቸው፤ - የፕሮጀክቱን አዋጭነት እና የጥሬ ዕቃውን ክምችት በሰፊው ለማረጋገጥ የሚረዳ የፋይናንስ እጥረት ማጋጠሙን ገልጸዋል። ተመራማሪው ፕሮጀክቱ ሳይቋረጥ አሁንም በላቦራቶሪ ደረጃ መቀጠሉን ጠቅሰው፥ ከባዮነዳጁ በተጨማሪ ለኤሌክትሪክ መኪናዎች እና ለወደፊት ኢነርጂ ወሳኝ የሆነውን የሊቲየም ማዕድን ማውጣት ሥራ ላይ ትልቅ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። ባለሀብቶች፣ የመንግሥት አካላት እና በጎ አድራጊዎች በጥናት እና በፋይናንስ ከደገፏቸው የጥሬ ዕቃ ክምችቱን አጥንተው ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተመራማሪው ገልጸዋል። ዘገባው የአሚኮ ነው። @EBS_TV_NEWS
1️⃣3️⃣ Telegram turns 13 today. For over half that time — the past 7,5 years — it's been one of the 10 most downloaded mobile apps in the world. A whole generation has grown up with it 💪 🎂 Happy birthday, Telegram!
በናይሮቢ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ በቤት ኪራይ ዕዳ ምክንያት መዘጋቱ ተገለጠ በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መንግሥት የናይሮቢውን ቢሮ የነሐሴ ወርን ጨምሮ የአራት ወራት የቤት ኪራይ ክፍያ ባለመክፈሉ ምክንያት መዘጋቱን የኬንያው ኬንያንስ እና ራዲዮ ታማዙጅ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። በናይሮቢ ኪሊማኒ ሰፈር የሚገኘው ይህ ኤምባሲ የተዘጋው ባለፈው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲሆን ይህም በኬንያ ውስጥ ለሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች የሚሰጠውን የቆንስላ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አስተጓጉሏል። የኤምባሲው የሥራ ባልደረቦች እንደገለጹት የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ያለበትን ውዝፍ ዕዳ እስካልከፈለ ድረስ መሥሪያ ቤቱ ዝግ ሆኖ ይቆያል።
በአዲስ አበባ የ2019 ዓ.ም የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ መደበኛ ያልሆኑ አሰራሮችን ለመግታት የ2019 በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ እንዲጸድቅ መወሰኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት የተወሰነ ሲሆን፣ በከተማዋ የተካሄደ ሳይንሳዊ ጥናትንና የነዋሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆኑ ተገልጿል። ውሳኔው አከራዮች ወቅታዊውን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ተከራዮች ደግሞ ካልተገባ የዋጋ ጭማሪና መፈናቀል ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ምዝገባና የውል እድሳት ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች በይፋ መጀመሩ ቢሮው አያይዞ ገልጿል። ቢሮው አክሎም፣ " ይህ አሰራር በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው " ብሏል።
ሰበር፡- አሜሪካ እና ኢራን ተስማሙ.... ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት በይፋ መጠናቀቁን እና የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በድጋሚ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል። ሰላም ለአለም ሁሉ
" አከራዮችን በሕግ ያስጠይቃቸዋል " - ቢሮው አዲስ አበባ ውስጥ ሰኔ 30 የሚያበቃውን የቤት ክራይ ውል ተንተርሶ አከራዮች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ለተከራዮች እያሳወቁ ነው። አንዳንዶቹ አከራዮሽ " ቤቱን እፈልገዋለሁ ውጡ / ቤቱ ተሽጧል ውጡ " በማለት ቤት ተከራዮች እንዲለቁ ግፊት እያሳደሩ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። ከቤት ኪራይ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምን አሉ ? " ተከራዮች በህግ የተሰጣቸው መብታቸውን በደምብ መጠቀም ይጠበቅባቸዋል። አከራዮችም መብትና ግዴታቸውን በአግባቡ መጠቀም ይኖርባቸዋል። ከተማችን ላይ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ የኪራይ ቤቶችን መዝግበናል ወደ ሲስተም አስገብተን ቋት ውስጥ ነው ያለው። የት ክ/ከተማ ፣ የት ወረዳ ፣ የትኛው የቤት ቁጥር ፣ ባለስንት መኝታ ቤት በስንት ብር ተከራየ ፣ ማነውስ የተከራየው የሚለው ዳታ አለ እጃችን ላይ። እውነት ነው አንድ ሰው ግዴታ ያለበት 2 ዓመት አንድን ሰው ሊያከራይ ነው። ግዴታው ሁለት አመት ነው ከዛ በላይ መጨመር ይችላል (ጊዜውን)። ስለዚህ አከራዩ ' ዋጋ ጨምር ' ማለት አይችልም። ዋጋ መጨመር የሚችለው መንግሥት ነው። በአመት አንድ ጊዜ ሰኔ 30 ላይ በመጣው የዋጋ ጥናት መሰረት ዋጋ መጨመር የሚችለው መንግሥት ነው። ለምሳሌ ፦ አንድ ቤት 1 ሺህ ብር ተከራይቶ ቢሆን 1,100 ብር ማድረግ የሚችለው መንግሥት ነው። የማርኬት አሰስመንት ሰርቶ በምን ያህል መጠን ዋጋ ከፍ እንዳለ አስልቶ የሚጨምረው በፐርሰንት መንግሥት ነው። 2017-2018 በጀት አመት ላይ አምና ዋጋ ተጠና የጨመረ ዋጋ ስላልነበረ በነበረው ነው የሚቀጥለው ብለን አሳውቀን በነበረው ነው የቀጠለው። ዘንድሮም ዋጋ እያጠናን ነው። ስለዚህ የዋጋ ጥናቱ በሚመልሰው መልስ መሰረት ወይ በነበረት ይቀጥላል አሁንም አልያም የጨመረ ዋጋ ካለ በይፋ መንግሥት ያሳውቃል። እስከዛ ድረስ አከራዮች ዋጋ ጨምሩ የማለት መብት የላቸውም ፤ አሰራሩም አይፈቅድላቸውም። ተከራዮችም መብታቸውን መጠቀም አለባቸው። አከራይ ' ዋጋ ጨምር ' ስላለው ብቻ ዋጋ መጨመር የለበትም። ውላቸው እኛ ጋር አለ። ውላቸው የሚያበቃው ከሰኔ 30 በኋላ ነው። ውላቸው ውስጥ ሆነው ዋጋ መጨመር ስለማይጠበቅባቸው እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም በቅርባቸው ወረዳ አለ ስራ አስፈጻሚ የሚመራው ፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አለ ፣ ክፍለ ከተማም አለ ወረዳው ካልፈታ ክፍለ ከተማ ይፈታል፣ ቢሮ እኛም ጋር አለ። እነዚህ ቦታዎች ላይ እየመጣ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል። አከራይ ዋጋ ጨምር ስላለው ብቻ የሚጨምር ተከራይ ካለ መብቱን እየተጠቀመበት አይደለም። መንግሥት በተከራይ እና አከራይ መካከል ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሰፊ ጥረት አድርጓል እያደረገም ነው፤ አሰራርም የተበጀተው ተከራዮች ቢያንስ 2 ዓመት የሆነ ቦታ ተረጋግተው እንዲቀመጡ ነው። አከራዮችም በተከራዮች በኩል የሚደርስባቸውን ያልተገቡ ነገሮች (ቤቱን ላልተገባ ነገር መጠቀም) መከላከል የመንግሥት ድርሻ ነው። አከራዮች ተገቢ አይደለም ፤ ' ውጡልኝ ' ከዛ ደግሞ ' ጨምሬ ነው የማከራየው ' የሚባል አሰራር ስለሌለ ይሄ በጥቆማ ቢደረስበት ከክልከላዎቹ ውስጥ አንዱ ስለሆነ በሕግ ያስጠይቃቸዋል " ብለዋል።
መርከቦች የኢራንን እገዳ ለማለፍ በጭለማ መጓዝ ጀመሩ በርካታ የነዳጅ መርከቦች የሆርሙዝ ሰርጥን ለመሻገር አውቶማቲክ የአሰሳ ስርዓቶቻቸውን አጥፍተው በጭለማ እየተጓዙ ነው። ይህ እርምጃ የተወሰደው የኢራንን ጥብቅ ቁጥጥርና ሊሰነዘር የሚችለውን ጥቃት ለማምለጥ ነው። መርከቦቹ ይህንን አደገኛ ጉዞ የሚያደርጉት ከአሜሪካ ባህር ኃይል በሚያገኙት የደህንነት መመሪያ እገዛ ነው። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ባለው ውጥረት ምክንያት የኢንሹራንስ ዋጋ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።
#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር " ወንድ አይደለህ ? " በማህበረሰባችን ለወንድነት ከሰጠነው መለኪያዎች መካከል የማያለቅስ፣ ስሜት አልባ፣ ምንም እንኳን ጫና ቢደርስበትም ወንድ ስለሆነ ብቻ ዋጥ እና ቻል አድርጎ እዲያልፍ ይጠበቅበታል። ይህ በተለምዶ ለወንዶች የተሰጠ ማንነት ነው። በአጋጣሚ ከአቅሙ በላይ ሆኖ ካለቀሰ " ወንድ አይደለህ ጠንከር በል እንጂ የምን መልፈስፈስ ነው " ይባላል። ታዲያ ይህ የማህበረሰብ ጫና የሚሰማውን እና እያሳለፈ ያለዉን ከመናገር በራሱ እንዲወጣው እና እልፍ ሲል እራሱ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ይገደዳል። በዓለማችን በየዓመቱ ራሳቸውን ከሚያጠፉ 700,000 በላይ ሰዎች መካከል ከ450,000 በላይ የሚሆኑት ወንዶች ናቸው። በሰዓት 60 ወንዶች፣ በቀን 1,500 ወንዶች ፣ በሳምንት 12,000፣ በወር 45,000 በላይ ወንዶች ራሳቸውን ያጠፋሉ። ይሄ ቁጥር ታዲያ ሙከራ የሚያደርጉትን ሳይጨምር ነው፡፡ ማልቀስ እና ስሜትን በግልጽ መናገር ሰው የመሆናችን ተፈጥሯዊ መገለጫዎች እንጂ የወንድነት መለኪያዎች አይደሉም። የሚሰማንን ለሌሎች ማጋራት የደካማነት መገለጫ አይይለም፤ እርዳታ መጠየቅ እና የአዕምሮ ህክምና ማድረግም ከወንድነት ጋር አይገናኝም። ስለዚህ ወንዶች በየትኛውም የህይወት ጫና ዉስጥ እያለፍቹ ቢሆንም ብቻችሁን አይደላችሁም፤እርዳታ መጠየቅ ደግሞ የሽንፈት ወይም ያለመቻል ምልክት አይደለም። የአዕምሮ ጤና ለሁሉም!! ቲክቫህ ኢትዮጵያ #የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር #MentalHealthAwarenessMonth
" 30፣ 40 አመት ያሽከረከረ አሽከርካሪ ምዘና ቢወድቅ ልጆቹን ወዴት ሊበትናቸው ነው? ግራ የሚያጋባ አሰራር ነው የመጣው " - አሽከርካሪ ከሰሞኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ፥ " ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲመዘኑና እንዲሰለጥኑ ይደረጋል " በማለቱ ቅሬታ እንዳላቸው አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አንድ አሽከርካሪ ፣ " እኔ እያሽከረከርኩ ነው ያለሁት፣ ከ10 አመት በላይ አሽከርክሪያለሁ። 10 አመት ሙሉ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ምንም አደጋ አጋጥሞኝ አያውቅም " ብለው፣ " እንዴት ነው አሁን ላሰልጥንህ ብሎ የሚወስደኝ ? " ሲሉ ጠይቀዋል። ሌላኛው አሽከርካሪ፣ " መሆን የሌለበት አሰራር ነው። 30፣ 40 አመት ያሽከረከረ አሽከርካሪ ምዘና ቢወድቅ ልጆቹን ወዴት ሊበትናቸው ነው ? ግራ የሚያጋባ አሰራር ነው የመጣው " ያሉ ሲሆን፣ በርካታ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ናቸው። አሽከርካሪዎቹ ምን አሉ ? " ሾፌር የብቃት ማረጋገጫ ይዞም መኪና አይጥልም (አደጋ አያደርስም) ማለት አይደለም። አደጋ በድንገት የሚመጣ እንጅ ታውቆ የሚደረግ አይደለም። 40 ዓመት ያሽከረከረ ሾፌር መኪና ይጥላል። ያ ግን የብቃት ችግር አይደለም በድንገት የሚመጣ ችግር ነው። ስለዚህ ይተገበራል የተባለው አዲሱ አሰራር እኛን ወደ ሌላ ብዝበዛ የሚከት አሰራር ነው። አሽከርካሪዎችን በምን እናሰቃያቸው አይነት ነገር ነው። ሳይማሩ ገንዘብ ከፍለው መንጃ ፈቃድ የሚወስዱ አሉ። መሰራት ያለበት የመንጃ ፈቃድ ትምህርት ቤት ላይ ነው። አሁን የታቀደው አካሄድ ግን አያስኬድም። ስልጠና መሆኑ ባልከፋ ነበር። የተመጣበት ሂደቱ ግን መጀመሪያ እታች መንጃ ፈቃድ አሰጣጡ እንደተዝረከረከ ባለበትና ባልጸዳበት ሁኔታ ነው። ብዙ ክፍተቶች እያሉ ስራ ላይ ያለን አካል ማሰልጠን ግዴታ ሊሆን ነው የሚል ዜና መስማት እንደ አንድ አሽከርካሪ ጤናማ ስሜት አይሰጥም። መንጃ ፈቃድ ይዞ እያሽከረከረ ያለን ሾፌር በምን መልኩ ነው ስልጠናው የሚሰጠው? ምን ያክል ጊዜ ነው ስልጠና የሚወስደው? የሚሉ ነገሮች ይፋ መደረግ ነበረባቸው። ራሱን ችሎ ጥናት የሚፈልግ ነገር ነው። ከቴክኖሎጂ ጋር ታግዘን የምንወስዳቸው ነገሮችም አሉ፤ በግላችን። ከዚያ ውጭ ግን እናሰልጥናችሁ ወይም እናስተምራችሁ የሚለው ነገር ገንዘብ ፍለጋ ወይም ሌላ ይዘት ያላቸው የሚመስሉ ናቸው። እንጂ እውነት አደጋ ለመቀነስ ከታሰበ ከመሰረቱ ከመንጃ ፍቃድ አሰጣጡ ነው መነሳት ያለበት " ብለዋል። ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ እንዳገኘን እናቀርባለን።
የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በሚገኙ የሶላር አምራቾች ላይ ክስ መሰረቱ የአሜሪካ የሶላር ፓነል አምራቾች ጥምረት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱት ቶዮ ሶላሬ እና ኦሪጅን ሶላር ኩባንያዎች ላይ ለአሜሪካ ንግድ ሚኒስቴር ይፋዊ የንግድ ክስ አቅርበዋል። እ.ኤ.አ. ትናንት ሜይ 13 ቀን 2026 የወጣው ይህ አቤቱታ፤ ኩባንያዎቹ የቻይና ምርት የሆኑ ግብዓቶችን በኢትዮጵያ በማቀነባበር በአሜሪካ የተጣለባቸውን ከፍተኛ የቀረጥ ታሪፍ ለማምለጥ ሞክረዋል የሚል ክስ ሰንዝሯል። ቶዮ ሶላር በኢትዮጵያ የሶላር ሴል ማምረቻ ፋብሪካ ያለው ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚላኩ የሶላር ምርቶች እ.ኤ.አ. በ2025 መገባደጃ ላይ ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር አድጓል። የአሜሪካ ንግድ ሚኒስቴር በቀረበው አቤቱታ ላይ በቀጣዮቹ 30 ቀናት ውስጥ ምርመራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፏ ስንዴ አምራች መሆኗ ተዘገበ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 33 ሚሊዮን ቶን ስንዴ በማምረት የአፍሪካን ቀዳሚነት ስፍራ መያዟን የዩክሬን የእህል ማህበር ዘገበ። ሀገሪቱ ከአምስት ሚሊዮን ቶን በላይ የምርት ጭማሪ ያስመዘገበችው በዘንድሮው የምርት ዘመን ሲሆን፣ ይህም ቀደም ሲል ከውጭ ለምታስገባው ስንዴ ታወጣው የነበረውን ከፍተኛ ወጪ የሚቀንስና ራሷን እንድትችል የሚያደርጋት ነው።
ሳውዲ አረቢያ የአየር ክልሏን መዝጋቷን ተከትሎ ትራምፕ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ የነበራቸውን እቅድ ቀየሩ ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ለመክፈት የነበራቸውን እቅድ በድንገት ለመቀየር የተገደዱት ሳውዲ አረቢያ አሜሪካ የሀገሪቱን ወታደራዊ ካምፖች እና የአየር ክልል እንዳትጠቀም መከልከሏን ተከትሎ ነው። ይህ የሳውዲ አረቢያ ያልተጠበቀ እርምጃ በትራምፕ የቀድሞ እቅድ ላይ ትልቅ እንቅፋት የፈጠረ ሲሆን፣ የአሜሪካ ጦር በክልሉ ያለውን የመንቀሳቀስ አቅም በእጅጉ እንደሚገድበው ኤንቢሲ ኒውስ ዘግቧል።
85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፤ የነጻነትና የጀግንነት ታሪካዊ መታሰቢያ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘውን 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ለመላው የሀገራችን ህዝብ እንኳን አደረሳችሁ እንላለን። ይህ በዓል የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወራሪ ኃይል በቆራጥነት በመመከት ሀገራችንን ከባዕድ አገዛዝ ነጻ ያወጡበትና ዳግም የሉዓላዊነትን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ያደረጉበት ታሪካዊ ቀን ነው። የአርበኞች ቀን የነጻነት፣ የክብር እና የማንነታችን ምልክት ከመሆኑም በላይ፣ ለወጣቱ ትውልድ ሀገርን የመጠበቅና ለታላቅነት የመስራት የጽናት ትምህርት የሚሰጥበት ዕለት በመሆኑ በታላቅ ኩራት ይታሰባል።
በአሜሪካ የተያዙ ኢራናውያን ተለቀቁ የፓኪስታን መንግስት በአሜሪካ የባህር ሃይል ተይዞ ከነበረው የኢራን የጭነት መርከብ ላይ የተወሰዱ 22 ኢራናውያን ሰራተኞችን በሰላም መረከቡን የአልጀዚራ ዜና ምንጭ ጠቅሶ ገልጿል። አሜሪካ መርከቧን በቁጥጥር ስር ካዋለች በኋላ እነዚህን ሰራተኞች ለፓኪስታን አሳልፋ የሰጠች ሲሆን፣ ድርጊቱ በወቅታዊው የባህር ላይ ፀጥታ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ አዲስ መነጋገሪያ ሆኗል
ባንኮች ለተለያዩ ዘርፎች የሚሰጡትን ብድር ፍትሃዊ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ አዲስ ህግ ሊወጣ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባንኮች ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በተለይም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡትን ብድር ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲያከፋፍሉ የሚያስገድድ አዲስ ህግ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ ገልጸዋል። ይህ እርምጃ የብድር አቅርቦት ስርጭትን ለማሻሻልና ለልማት ወሳኝ ለሆኑ ዘርፎች ትኩረት ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንሳይደር በዘገባው አመልክቷል።
Trump posted a picture calling it the "Trump Strait" not the Strait of Hormuz.
#ነዳጅ #ናፍጣ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ አሳወቀ። በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፈጠሩ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ወርዶ እንደነበር የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል። አሁን የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ ቀደመው 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ እንደሚጀመር ሚኒስትሩ ወደ ክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ መጓጓዝ ይጀምራል ብለዋል። እስካሁን የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ቀድሞ በነበረው መጠን እየቀረበ መሆኑን አመልክተዋል። ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ/ም
በታዬ ደንደአ ላይ ቀርበው የነበሩ ሦስት አዳዲስ ክሶች ተቋረጡ የፌደራሉ ዓቃቤ ሕግ በቀድሞው የሰላም ሚንስትር ደዔታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ የመሠረታቸውን ሦስት አዳዲስ ክሶች ማቋረጡን ዋዜማ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል። መንግሥትን በኃይል ለመጣል መሞከር፣ በመከላከያ ላይ ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት እና ስም ማጥፋት የሚሉ ክሶች የቀረቡባቸው አቶ ታዬ፣ ዛሬ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይጠብቁ የነበረ ቢሆንም ክሶቹ የተቋረጡበት ምክንያት ግን በችሎቱ ላይ አልተገለጸም። ቀደም ሲል በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞታ ወንጀል ተፈርዶባቸው የነበረው የ7 ዓመት እስራት በይግባኝ ወደ 4 ዓመት ዝቅ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ ጠበቆቻቸውም የአሁኑ ክስ የተቋረጠበትን ምክንያት ከፍርድ ቤት ለማጣራት እየሞከሩ መሆኑን ገልጸዋል።
#Iran #USA የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ መውደቋንና የሆርሙዝ ሰርጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት ፍላጎት እንዳላት ገለጹ። ፕሬዜዳንቱ " ኢራን በገንዘብ ረገድ እየፈራረሰች ነው። የሆርሙዝ ሰርጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት ይፈልጋሉ ፤ ጥሬ ገንዘብ ተርበዋል በቀን 500 ሚሊዮን ዶላር እያጡ ነው። የወታደርና የፖሊስ አባላት ' ደመወዝ አልተከፈለንም ' በሚል ቅሬታ እያቀረቡ ነው " ሲሉ ፅፈዋል። ትራምፕ ትላንት ከኢራን ጋር የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ሲያልቅ ተጨማሪ ጊዜ ማራዘማቸው ይታወሳል። በሌላ በኩል የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ሁለት የንግድ መርከቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት " MSC Francesca " እና " Epaminodes " የተባሉ የጭነት መርከቦች መሆናቸው ታውቋል። ኢራን መርከቦቹ " የባህር ላይ ደንቦችን ጥሰዋል " እና " ያለፈቃድ ለመንቀሳቀስ ሞክረዋል " የሚል ክስ አቅርባለች።
ከ50 ቀናት በኋላ የኢራን አየር ክልል በከፊል ክፍት ሆነ ከአሜሪካና እስራኤል ጥቃት በኋላ ለሃምሳ ቀናት ተዘግቶ የቆየው የኢራን አየር ክልል ከዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን ጀምሮ በከፊል ክፍት መደረጉን ተከትሎ የሀገር ውስጥ በረራዎች ተጀምረዋል። የኢራን ብሔራዊ አየር መንገድ (iኢራን ኤር) የመጀመሪያውን በረራ ከቴህራን ወደ መሸድ ከተማ ያከናወነ ሲሆን፣ የአየር ክልሉ ክፍት መደረግ የተሰማው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማራዘማቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው። ቢሆንም ግን በሆርሙዝ ባህር ሰርጥ ላይ ያለው ወታደራዊ ውጥረትና የአሜሪካ የባህር ላይ ከበባ ባለመቆሙ በቀጠናው ላይ ያለው ስጋት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።