tgindex
Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
13 072
−25 за 4 дн.
Сутки
−7
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 340
22 постов
Вовлечённость
40,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
2 022
1/48двое суток
2 317
1/72трое суток
2 499

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 6 авг.1 4554

    ''አማራ እንደ አረጋ ከበደ የሚሠሩ የሚያሠሩ ርዕሰ መስተዳድር በታሪኩ አግኝቶ አያውቅም'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በባህዳር ከተማ ተገኝተው አዲሱን የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተርሚናል መርቀዋል። በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ በዳረጉት ንግግር አማራ በታሪኩ በተላይ ከባለፉት 30አመታት ወድህ እንዲህ እንደዛሬው ዘመን የአማራ ክልልም ሆነ ባህርዳር ራሱን በራሱ በተሟላ መንገድ የሚያስተዳድርበት ዘመን አልነበረም ብለዋል። አክለውም በተላይ ፕሬዝዳንታችን አረጋ ከበደ ከተሰጣቸው ስልጣን ጋር ያሻቸውን መወሰን የሚችሉ፣ የተከበሩ ፣ የሚሰሩ የሚያሰሩ ፕሬዝዳንት ናቸው ሲሉ አመስግነው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማራ በታሪኩም እንደ አረጋ ከበደ አይነት መሪ አግኝቶ እንደማያውቅም ጠቆም አድርገው አልፈዋል። ሀሳብዎን ያካፍሉን? ሰላም ለኢትዮጲያ ሰላም ለህዝባችን ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

  • 2 авг.2 279203

    ጦርነት ይብቃ! ጠላ ጠጪውን እንጂ ጠንሳሹን አያሰክርም። ታሪኩ ጋንካሲ (ዲሽታ ጊና) Stop civil war in Ethiopia!

  • 2 авг.2 2802

    https://youtu.be/n196BOXfjxc?si=NRSAPaUb8jilWxRu

  • 1 авг.2 295

    https://youtu.be/h2SndQXKnBw?si=3kUCsY_L6fKE6-pr

  • 30 июл.2 4132

    https://youtu.be/_8LU1gTdm60?si=DEUxEIk-Wa0Kqger

  • 29 июл.2 229141

    ''ጎጃም የኦሮሞ ነው'' ብአዴን "ወለጋ የአማራ ነው" ኦህዴድ ደግሞ "ጎጃም የኦሮሞ ነው" ብለው በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ሲፎጋገሩ ውለዋል አሉ😃 ''ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም የሚባለው ተረት ተቀይሮ "ልጅ ያመካከረው ለእራት አይበቃም!" ብለነዋል።'' የአገራችን ፖለቲካ በሄደበት ቁጥር አዳዲስ "ስክሪፕቶችን" እየፃፈ ሊያዝናናን ይሞክራል፤ ነገር ግን በጀርባው ያለው የህዝብ ህመም ሲታሰብ ቀልዱ ወደ እቅብት ይቀየራል። ሰሞኑን በሀገራዊ ምክክሩ የሚሰማውና የሚታየው የወሬ ገበያ ደግሞ የዚህኑ አስቂኝና አሳዛኝ ድራማ ሌላኛውን ምዕራፍ የሚገልጽ ነው፤ ብአዴን "ወለጋ የአማራ ነው"፣ ኦህዴድ ደግሞ "ጎጃም የኦሮሞ ነው" ብለው በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲከራከሩ አሰልጥኖ ድራማዊ ፉክክር የማስራት ጨዋታ ቀጥሏል። ይህ ድራማ በጥንቱ የአበው ብሂል ይደመደማል፦ "ልጅ ያመካከረው ለእራት አይበቃም!" ሀገሪቱ በበዛ የኢኮኖሚ ጫና፣ በዜጎች እንግልት እና በፀጥታ ስጋት ውስጥ እያለች፤ የፖለቲካው ልሂቃን የህዝቡን እውነተኛ ጥያቄዎች ለመመለስ ከመጨነቅ ይልቅ "የድንበርና የታሪክ ሰርከስ" ፈብርከው ሲያጫውቱን ይውላሉ። * ወለጋንና ጎጃምን የፖለቲካ ቁማር ማጫወቻ ማድረጉ የፖለቲካ በሰል አለማለትን ብቻ ሳይሆን፣ ህዝብን እንደ አሻንጉሊት የመቁጠር እጅግ የወረደ አካሄድ ነው። * እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚደረገው የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ሰላምን ለማስፈንና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንጂ የካቢኔ አባላትን "ተከራካሪ" አድርጎ መድረክ ላይ ማፎካከር አይደለም። የድራማው ዳይሬክተሮችና ተዋንያን ብአዴንም ሆነ ኦህዴድ በአንድ ጣሪያ ስር እየኖሩ፣ በአንድ ድርጅታዊ መዋቅር እየተመሩ፣ መድረክ ላይ ሲወጡ ግን የተለያየ ካባ ለብሰው እንዲጋጩ የማድረግ ስልት የቆየና የሰለቸ አካሄድ ነው። "በጓሮ አንድ ላይ እየበሉ፣ በመድረክ ላይ የድንበር ጠብ እንደሚመስል ገመድ ጉተታ ማሳየት ህዝብን 'ሞኝ ነው' ብሎ የመናቅ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።" የቀረበው "ሀገራዊ ምክክር" የህዝብን አውነተኛ ድምፅ የሚሰማበት መድረክ ከመሆን ይልቅ፣ ባለስልጣናት አስቀድመው ያዘጋጁትን ስክሪፕት የሚያነቡበትና የሰለጠኑበትን "ፉግግር (መፎጋገር)" የሚያቀርቡበት የቲያትር መድረክ ከሆነ ረጅም መንገድ አይሄድም። ህዝቡ ዛሬ የፖለቲከኞችን የውሸት ውዝግብና አስመሳይ ክርክር ጠግቧል። ድራማው ምንም ያህል በጥ በጥ ተደርጎ ቢሰራ፣ የተዘጋጀው ስክሪፕት ምንም ያህል ቢጠና፣ በውሸትና በትያትር የተገነባ የፖለቲካ ህንፃ መፍረሱ አይቀሬ ነው። የህዝብን አእምሮ በወሬና ''በፉግግር (በመፎጋገር)'' ማወናበድ የሚቻለው ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፤ "ልጅ ያመካከረው ለእራት አይበቃም" እንዲሉ! ማለት ነው። ሀሳብዎን ያካፍሉን? ሰላም ለኢትዮጲያ ሰላም ለህዝባችን ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

  • без подписи

  • 28 июл.2 7081

    https://youtu.be/7jB3oA35RGg?si=qmXIeoQPtlouZ7NX

  • 26 июл.2 6982

    https://youtu.be/5myHTB9Sazo?si=m9kC15_bJOoO4Vp6

  • 2 мая5 58752

    https://youtu.be/5wEpSRk6ymI?si=w9EOcZuEwO44tGUo

  • 28 апр.5 93251

    https://youtu.be/emYEbtwxOOI?si=VU42VRArA5rk_kyx

  • 15 апр.6 5279

    https://youtu.be/MMAxcIJSI_Y?si=T9eIVXT5Uh5VRxAn

  • 15 апр.6 06852

    https://youtu.be/jnfjCAz2DAw?si=2mg9aduHaLFI7b4s

  • 15 апр.5 33832

    https://youtu.be/_FkGBntx5uo?si=LYqUjFg6lxZ1Cjij

  • 15 апр.4 55222

    https://youtu.be/y0QU7gZTKuQ?si=eiS2BUlFY2Pdn4u6

  • 29 дек.11 тыс587

    ''አብይ ቀጥቅጦ አሸንፎናል'' የትግራይን ጀኖሳይድ የፈፀመው ፋኖ እና ሻቢያ ነው'' የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ልጅ ሁኘ እልኸኛ ነበርኩ ሰውም ልምታህ ካለኝ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብቼ ስስ ብልት ካገኘው ምናምን እልና ግን አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ ማሰብ አለብህ መጀመሪያ ዙር ትሞክርና ከቀጠቀጠህ ትመክራለህ ከዚያ የሆነ ሰአት ላይ ገላጋይ ቢመጣ ጥሩ ነው። ነገር ግን እየወደክ እየተነሳህ አሁንም ካልጣልኩት የምትል ከሆነ ስህተት ነው፣ አዕምሮ የለህም ማለት ነው በማለት tplfን ወርፈዋል። ባለፈው ጦርነት የTplf አመራሮች አድስ አበባ እንገባለን በሚል illusion (ቅዠት) ነው ጦርነት የገባነው። አሁንም የህወሃት አመራሮች አድስ አበባ እንገባለን በሚል ጦርነት ለማስነሳት እየቆሰቁሱ ነው ግን አይቻልም አድስ አበባ በባቡር መምጣት ይችላሉ እንጅ በጦርነት ግን አይሆንም በማለት የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በNBC ETHIOPIA ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። ጨምረውም አቶ ጌታቸው ረዳ የሰሜኑ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ''ጠቅላይ ሚስትሩ ግጭት ውስጥ ከገባን ሻቢያ ይጠቀምብናል ላስቆመው አልችል፣ ልዩነታችንን አቻችለን ብንሰራ ነው የሚያዋጣን ብለውን ነበር በሰአቱ ግን ማንም የተቀበላቸው አመራር አልነበረም በማለት የምስክርነት ቃል የሚመስል ከወትሮው የተለየ መልዕክት ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ የትግራይን ጀኖሳይድ የፈፀመው ፋኖ እና ሻቢያ ነው'' ትግራይ ውስጥ እኮ ያልገባ የለም እድል ገጠመኝ ያለ ማንኛውም የግል ሽፍታ የነበረ ሳይቀር ነው ትግራይ ላይ የተረባረበው በማለት መንግስትን ከትግራዩ ጀኖሳይድ ተጠያቂነት ገለል ለማድረግ በሚመስል አኳኳን ሀሳባቸውን በውይይቱ ተንፍሰዋል።

  • 24 дек.9 841171

    “ፋኖ ክዶናል'' ህዝቡ ካልታገለው ሰላም አይመጣም'' ብርጋዴር ጀነራል አዲሱ መሐመድ በ10% ነው የምንዋጋቸው መለቃቀም ነው የቀረን ሲሉ የነበሩ የጦር መሪዎች ዞር ብለው ህዝብ ካልታገላቸው አናሸንፋቸውም ብለው አረፉት፤ እንድህ ሳያስቡትም ቢሆን ለህዝብ እውነታው ማሳወቃቸው ጥሩ አጋጣሚ ነው። ያስተላለፉት መልዕክት እነሆ.......... የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዲሱ መሐመድ ጽንፈኛው ቡድን ኩሩውን ሕዝብ ያጎሳቆለ እና አንገቱን ያስደፋ ነው ብለዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ ሰላም የቆመ የሀገር ክብር ነው ያሉት አዛዡ ጽንፈኛው ግን በሀገር መከታው ላይ ክህደት ፈጽሟል ሲሉ የተደመጡ ሲሆን፤ የመኖር መብት እንዳይኖራችሁ ያደረጋችሁን፣ ምላስ የሚቆርጥን፣ እናት የሚገድልን፣ መስቀል የጨበጠ ቄስን አዋርዶ በጭካኔ የሚገድልን ቡድን ነው በማለት የፋኖ ኃይሎችን ወንጅለው፤ ለሰበሰቡው ህዝብ ደግሞ ፋኖን ካልታገላችሁ ሰላም አይመጣም በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል። አክለውም ቡድኑ የታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪ፣ ባንዳ እና ሀገር አፍራሽ መኾኑን ተናግረዋል። በሰላም እንዲገቡ ምከሩ፣ ገስጹ እምቢ ያለውን ግን አሳልፋችሁ ስጡ ነው ያሉት። ብርጋዴር ጀነራል አዲሱ መሐመድ በመርአዊ በተደረገ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ነው ይህን የተናገሩት ''በዚህ ንግግር ምን ይላሉ ሀሳብዎን ያካፍሉን??''

  • 12 дек.9 406253

    "ከኢትዮጵያ ተገንጥለን ከኤርትራ ጋር መዋሃድ እንፈልጋለን" ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ለአመታት በአዲስ አበባ ታስረው የነበሩት የቀድሞው የሜቴክ ሀላፊ ጀኔራል ክንፈ ዳኘው ጀነራሉ ብራኸ ሾው ከተሰኘ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አነጋጋሪ አስተያየት ይዘው ተከስተዋል። ከኢትዮጵያ ተገንጥለን ከኤርትራ መዋሃድ እንፈልጋለን"ሲሉ ተደምጠዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ ቅድመ ጦርነት ሁኔታ እየተመለሰች ያለችው ትግራይ የኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ስር መግባት የለባትም።በትግራይ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ብቸኛ የግንኙነት የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው።ከዚያ ውጭ ምንም አይነት ማሰሪያ የለም" ትግራይ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት።የሚፈጸመው በፖለቲካዊ ቁርጠንነትና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 መሰረት ነው፡፡ የትግራይን ሀገርነት ለማደናቀፍ የሚንቃቀስ አካል ካለ ለመመከት ወይም ለኃይል አማራጭ ለመጨረስ መዘጋጀት ያስፈልጋል። ሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች ትግራይን ወደ ሀገርነት ለማሸጋገር በጋራ መቆም አለባቸው።የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው ያሉትን የመገንጠል አጀንዳ እንደሚያቀነቅኑ ይታወቃል ብለዋል። ስለ አሁናዊ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይና ኤርትራ ውጥረት የተጠየቀት ጀነራሉ፣ ግጭት ከተቀሰቀሰ የውክልና ጦርነት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥት መካከል በባህር በር ጉዳይ ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ፣ ሌሎች ኃይሎችን በውክልና የሚያሳትፍ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡ ጀነራሉ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሊቀሰቀስ ይችላል ያሉት ጦርነት፣ ትግራይን የውጊያ ማዕከል ሊያደርግ እንደሚችለም ጠቁመዋል፡፡ ትግራይ የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የውክልና ጦር ሜዳ እንዳትሆን ከወዲሁ ስልታዊ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል፡፡

  • 30 нояб.11,6 тыс352

    ''አሳዛኝ ዜና:- ኮሜድያን ወንደሰን አውራሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ'' በጣም የሚያሳዝን ዜና.... ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ እንደሚታወቀው ለብዙ ዓመታት በኮሜድ ስራው ሲያስቀን የኖረ ወንድማችን መሆኑ አይዘነጋም ኮሜዲያን ወንደሠን እንደ ምንጮች ዘገባ ከሆነ በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ተሰምቷል። አስክሬኑም ለምርመራ በሚኒሊክ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገልጿል። ነብስ ይማር ለቤተሰቦቹ፣ለጓደኞቹ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን። Wollo Addis

  • 26 нояб.10,8 тыс357

    “አብይ ከጦርነቱም በፊት ጓደኛየ ነው አሁንም ጓደኛ ነን” የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ጌታቸው ረዳ የአልጀዚራው የፖለቲካ ጋዜጠኛ መህዲ ሀሰን ይጠይቃል?? ጋዜጠኛው:- በጦርነቱ ወቅት አብይ አህመድ ጀኖሳይድ ፈፅሟል እያሉ ሲናገሩ ነበር ያ አቋምዎ ከእርሰዎ ጋር አለ? ጌታቸው ረዳ:- አጋንኘ የገለፅኩት ነገር እንዳለ ሆኖ ሁሉም አይነት ወንጀሎች በትግራይ ላይ ተፈፅመዋል። ጋዜጠኛው:- አብይ አህመድ ጀኖሳይዱን ፈፅመውታል ወይ? ጌታቸው ረዳ:- ይህንን የምነግርህ እንደ ህግ ባለሙያ ነው፣ ይህንን ወይም ያንን የፈፀመው እከሌ ነው ልልህ አልችልም። ጋዜጠኛው:- በ2013 አብይ አህመድ ጀኖሳይድ ፈፅሟል ብለው ሲናገሩ ያኔ የህግ ባለሙያ አልነበሩምደ፤ ያኔኮ አብይ አህመድ በትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ ፈፅሟል ሲሉን ነበር። ጌታቸው ረዳ:- ያኔም የህግ ባለሙያ ነኝ ግን በተጋጋለና በ100ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሚሞቱበት ጦርነት ላይ ነበርኩ። ጋዜጠኛው:- ስለዚህ ጀኖሳይድ ተፈፅሟል አልተፈፀመም? ጌታቸው ረዳ:- በትግራይ ላይ ጀኖሳይድ ተፈፅሟል ብየ አምናለሁ ጋዜጠኛው:- በአብይ አህመድ? ጌታቸው ረዳ:- አሁን ለምናገራቸው ቃላት መጠንቀቅ አለብኝ ጋዜጠኛው:- ከዚህ በፊት የማይጠነቀቁ ነበሩ ማለት ነው? ጌታቸው ረዳ:- አሁንም በአቋሜ ለመገኘት ዝግጁ ነኝ ጋዜጠኛው:- ቆይ ቆይ አልገባኝም ለተመልካቾቸ ግልፅ ያድርጉላቸው? ጀኖሳይዱ እንደተፈፀመ ያምናሉ ግን አብይ ፈፀመ ብለው ለመናገር አይፈልጉም ይህን ነው እያሉ ያሉት? ጌታቸው ረዳ:- አወ ጋዜጠኛው:- ታዲያ ጀኖሳይዱ ዝም ብሎ በራሱ ጊዜ ተፈጠረ ነው? ጌታቸው ረዳ:- አይደለም በጦርነቱኮ በርካታ ተዋንያን ነበሩ ጋዜጠኛው:- እኮ አብይ አንዱ ነው? ጌታቸው ረዳ:- በትግራይ የተካሀደውን ጦርነትኮ የመራው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነው እሱማ ጋዜጠኛው:- ስለዚህ ጀኖሳይዱንም መርቶታላ? ጌታቸው ረዳ:- በዚህ ደረጃ ነጥለን መጥራት አያስፈልግም ጋዜጠኛው:- መጥራት አለብዎትኮ እርሰዎን የጠራሁት ለዚህ ነውኮ? ጌታቸው ረዳ:- ራሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሱን በፍርድ ቤትም ሆነ በአደባባይ የመከላከል መብቱን እተውለታለሁ ሲጀመርኮ አብይ ጓደኛየ ነው፤ ገና ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን ጀምሮ ጥብቅ ጓደኛየ ነው። ጋዜጠኛው:- ማነው የቅርብ ጓደኛህ ጌታቸው ረዳ:- አብይ የቅርብ ጓደኛየ ነበር ጋዜጠኛው:- ስትጠራው አልነበርደ የጀኖሳይድ ወንጀለኛ ጦረኛ ኢምፔሪያሊስት ስትለው አልነበርዴ? ጌታቸው ረዳ:- አወ ያኮ ጓደኛ ነበርን የሚለውን እውነት አይቀይረውም ጋዜጠኛው:- የሆኑ ግራ አጋቢ ጓደኛሞች ናችሁ? ከጀኖሳይዱ በፊት ነበር ጓደኛ ነበርን እያሉ ያሉት? ጌታቸው ረዳ:- አወ ጋዜጠኛው:- ከጀኖሳይዱም በሗላ ጓደኛ ናችሁ፣ ከጀኖሳይዱም በፊት ጓደኛ ናችሁ፤ እና በጀኖሳይዱ ወቅት ግን ጓደኛ አይደላችሁም? ጌታቸው ረዳ:- እርስበርስ እየተዋጋን ነበር 😁😁 ተመልካቾች ሳቁ '' ይህን የጀኖሳይድ ጉዳይ ባናሳንሰው ነው የሚሻለው ጋዜጠኛው:- እኔ አይደለሁም እያንኳሰስኩት እና እያሳነስኩ ያለሁት እርሰዎ ነዎት ጀኖሳይድ ፈፅሟል ሲሉት ከነበረው ሰው ጋር የቅርብ ጓደኛሞች ነን እያሉን ያሉት? .... እያለ ቃለ መጠይቁ ይቀጥላል። የእርዎ አስተያት ምንድነው ያካፍሉን?