tgindex
Hana Hailu

መንቃት እና ማንቃት መብቃት እና ማብቃት የሰው ልጅ ልክ እንደውቅያኖስ ነው ስፋቱ እንጂ ጥልቀቱ አይታይም! በየቀኑ እማራለሁ- የተማርኩትን ላካፍላችሁ ወደድኩ! በዚህ ቻናል የተማርኩትን የገባኝን ከሌሎች ከራሴ ለእናንተ አካፍላለሁ! ራሴን እና ሌሎችን ለማንቃት እጠቀማለሁ አስተያየት @HanahailuEth ዌብሳይቴን ይጎብኙ Www.hanahailu.com

Последний пост
1 апр.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 798
−4 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,06%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 264
21 постов
Вовлечённость
125,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • 19 мар.1 280256

    አወዳደቃችሁን ያሳምርላችሁ..... በቤታችን 2ተኛ ነገስትን እያጠናን ነው። ዛሬ ምዕራፍ 13 ላይ ያለውን ስናነብ ይሄ ነገር በጣም ገረመን.....ስንወያይበትም ነበር..... አንድ ጊዜ እስራኤላውያን ሰው ሞቶ ሲቀብሩ፣ አንድ የአደጋ ጣይ ቡድን በድንገት አዩ፤ ስለዚህ የሞተውን ሰው ሬሳ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ ጣሉት፤ ሬሳው የኤልሳዕን ዐፅም እንደ ነካም ወዲያውኑ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ። 2 ነገሥት 13:21

  • 5 февр.1 565481

    የረዥም ጊዜ ህልሜ እውን ሆኗል። ከአመታት በፊት በጆን ማክስዌል ተቋም አለም አቀፍ አሰልጣኝ መሆን እንደሚቻል ሰምቼ ከአቅሜ በላይ ስለነበር ትቼው ነበር...... ታዲያ ከ2026 አዲስ አመት ጀምሮ እኔ እና ባለቤቴ ዶ/ር ዳራራ ጢሞቲዎስ (SJD) የማክስዌል አመራር ማዕከል በሚሰጠው እና አለም አቀፍ አሰልጣኝ፣ ተናጋሪ እና ኮች የሚያደርገውን ረጅም ጊዜ የሚወስደውን ስልጠና በመቀላቀላችን ደስታ ተሰምቶናል። ይህ ፕሮግራም ከሚሰጠው እውቅና ባሻገር የጆን ማክስዌልን የትምህርት ቁሳቁሶች ሙሉ እንድንጠቀም፣በድርጅቱ ካሉ አሰልጣኞች ጋር በመሆን የስራ እድል እንድናገኝ(freelancer) እና የህይወት ዘመን አባል እንድንሆንም እድል ፈጥሮልናል! በዚሁ መንገድ ሀገራችንን ሆነ ሌላውን ህዝብ በተሻለ መጥቀም እንደምንችል አምናለሁ! የምትችለውን ሁሉ ዋጋ ከፍለህ ህልሞቼን ወደ ህይወት እያመጣህ ስለሆነ ፤ ይሄንን ጉዞ ደሞ አብረን ስለምንጓዝ ፣እንድማር ፣እንዳውቅ ፣እንዳድግ በየእለቱ ስለምትረዳኝ ከልብ አመሰግናለሁ - Darara T Gubo Maxwell Leadership #MaxwellLeadership #training #coaching #speaking #leadeeship

  • 30 дек.1 691403

    እንዲ ተሰምቷችሁ ያውቃል? ከዚህ በላይ ምን መሆን ነበረብኝ? 📚📖 From my diary / ከማስታወሻዬ ውስጥ አለኝ ከምለው የኔ ብቻ ከሆኑት ነገሮች ሁሉ የምደነቀው በማስታወሻ ደብተሮቼ ነው። የልደቴ ሰሞን ሲሆን ፣ አዲስ አመት ሲመጣ እና የህይወት የስሜት መለወጥ ሲገጥመኝ ወይ ገልጬ አነባቸዋለሁ ወይም ገልጬ እፅፍባቸዋለሁ። የዛሬ አራት አመት በ25ተኛ አመቴን ለማክበር በዋዜማው ላይ የፃፍኩት እዚህ ገፅ ጋር ቆም እንድል አደረገኝ...... እንደቀድሞው መልካም ነገር ሳይሆን ለራሴ ግራ የተጋባሁበትን ጥያቄ ነበር የፃፍኩት! በዚህ እድሜዬ ላይ ድርጅት ከፍቼ ፣ሰራተኞች ቀጥሬ፣ ራሴን ችዬ ፣እንደውም ሌሎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እንዲሁም በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን በገንዘብ ጭምር መርዳት ጀምሬ ነበር። ሰውነቴን ከመንከባከብ ( ስፖርት ከመስራት ፣ የምበላውን ከመምረጥ .....)እንዲሁም በየአመቱ ቀጣይ አመት አገባለሁ እያልኩ ብፅፍም (ሁለቱ እቅዶቼ ብዙ ጊዜ ተፅፈው ያልተሳኩት ነበሩ) ፈገግታዬን ከሚነጥቁኝ ሀሳቦች ውስጥ ግን ይሄ ዋነኛው ነበር. .... ብዙ ጊዜ ደስታዬን የሚነጥቀኝ ነገር ከራሴ ብዙ መጠበቅ ነው። የሞላልኝ ፣የተሳካልኝ ፣የደላኝ ቢመስል እንኳን ገና ይቀርሻል የሚል ድምፅ ገኖ ይሰማኝና ራሴን አስጨንቃለሁ.....የሆኑ ወዳጆች አሉ.... ከአንዱ አንድ ከፍታ ወደ ሌላው ስትሻገሩ የደረሳችሁበትን ለአፍታ ሳታጣጥሙት ገና ካንቺ ከዚህ በላይ እንጠብቃለን ይሏችኋል! ክፋት እኮ አስበው አይደለም ግን በቃ እኔ ጋር ሲመጡ በውስጤ ትልቅ ጎጆ ይሰራሉ። እኔም ሰዎችም ከራሴ ብዙ ስንጠብቅ የቆጡን አወርድ ብላ እንደሚባለው የብብቴን ይዤው ሳልጠቀምበት አይኔን እንደገና የቆጡ ላይ እጥላለሁ? በራስ ስኬት ባለመርካት ብዙ ተጠቅሜያለሁ ፣ብዙ አድጌበታለሁ ግን ደሞ ራሴን ብዙ ያሰቃየሁ ይመስለኛል። ከደረሳችሁበት በላይ ለመድረስ ስትንጠራሩ ዛሬ እንዳያመልጣችሁ በያዛችሁት መደሰት እንዳይቀርባችሁ! ቀጣዩን ጉዞ ከመጀመራችሁ በፊት ባላችሁበት ቦታ ጥቂት እረፍት ውሰዱ ለማለት ነው።

  • 9 нояб.1 89320

    ይሄስ አይገርምም? እንዲህም ታዘንል እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ። ኤፌሶን 4:29

  • без подписи

  • በመከራችሁ እስቅባችኋለሁ! መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ! መዓት እንደ ማዕበል ሲያናውጣችሁ፣ መከራም እንደ ዐውሎ ነፋስ ሲጠራርጋችሁ፣ ሥቃይና ችግር ሲያጥለቀልቃችሁ አፌዝባችኋለሁ! ትላለች ለምን? ስንቶቻችን ይሆን በየእለቱ እግዚአብሄር ምን ይላል ብለን መጽሐፍ ቅዱሳችንን የምናነበው..... ዝም ብዬ ሳስበው በምድር ያለው ኑሮ ሲያበቃ ሊቆጩን ከሚችሉ ነገሮች ዋነሻው.....በስተርጅና ወደ እግዚአብሄር እጠጋለሁ. ...ቃሉንም አጠናለሁ ማለታችን አልያም ደሞ በእሁድ ቀን ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ እርሱም ይበቃኛል ብለን መገመታችን ሊሆን ይችላል። ይሄ ስለእኔ ስለራሴ ነው! ለብዙ አመታት መጽሐፍ ቅዱስን እየሳምኩ እና አቧራውን ከሽፋኑ ፡እያፀዳሁ ከማስቀመጥ ያለፈ ህይወት አልነበረኝም። አንድ ቀን እንዲህ የሚል ነገር፡ከሆነ ሰው ሰማሁ "መጽሐፍ ቅዱስ ስሙኝ እንጂ ሳሙኝ አይልም!" ደነገጥኩ ያሉት ነገር ነውር እና የተሳሳተ መሰለኝ ግን የሚመር እውነት ነው......መድሀኒት እስካልዋጣችሁ ድረስ እንደማይጠቅማችሁ ቃሉንም እስካላነበባችሁት ድረስ አይጠቅማችሁም..... ከአመታት በፊት ጥቂት ገፆች ከፍቼ በማንበቤ ህይወቴ በብዙ አቅጣጫ ስርዓት ይዟል። የሴጣን ትልቁ ስራ ገልጣችሁ እንዳታነቡ ማድረግ ይመስለኛል.... እናም በቃሉ ውስጥ ያለችው ጥበብ ስሙኝ እያለች ትጣራለች.....እኛ ግን ብዙ የምንሰማው ድምፅ ስላለን ችላ ብለናታል። ሀዘን ውስጥ ናችሁ? የገንዘብ እጥረት ውስጥ ናችሁ? ሰው ትቷችኋል? ደስታ ውስጥ ናችሁ? ተስፋ ቆርጣችኋል? ሰላም አጣችሁ? "ጥበብ በጐዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፤ በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤ ዉካታ በበዛባቸው ጐዳናዎች ላይ ትጮኻለች። በከተማዪቱም መግቢያ በር ላይ እንዲህ ትላለች፤ “እናንት ብስለት የሌላችሁ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው? ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እንቢ ስላላችሁኝ፣ እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣ ምክሬን ሁሉ ስለ ናቃችሁ፣ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፣ እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤ መዓት እንደ ማዕበል ሲያናውጣችሁ፣ መከራም እንደ ዐውሎ ነፋስ ሲጠራርጋችሁ፣ ሥቃይና ችግር ሲያጥለቀልቃችሁ አፌዝባችኋለሁ። “በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም። ዕውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርንም መፍራት ስላልመረጡ፣ ምክሬን ለመቀበል ስላልፈለጉ፣ ዘለፋዬን ስለ ናቁ፣ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ። ብስለት የሌላቸውን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤ ተላሎችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፤ የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።” ምሳሌ 1:20

  • በአካል በተገናኘን በአራተኛው ቀን ነው ቀለበት ያደረግነው..... እንዴት? ከመቼው ያላችሁት ነገር ይኸውና..... እንዴት እንደተገናኘን ፣እንዴት እንደተጋባን ያሳለፍነውን ሁሉ ለእግዚአብሄር ክብር ይሆን ዘንድ እንመሰክራለን! እንድተሰሙት ጋብዣችኋለሁ.... https://youtu.be/53rRtBWjuWs?si=Z6FFf1-lAJ1Z1XyU

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 4 Days Left ምን እንደገባኝ ታውቃላችሁ? ሄዋን የአዳም የትግል ውጤት አይደለችም። ረዳት እንደሚያስፈልገው እንኳን he had no clue... የእግዚአብሄር እጅ ሲሰራ አዳም ተኛ ሄዋን ተሰጠችው! አዳምም የሄዋን የፍለጋ ውጤት እንዲያውም ጥያቄዋም አልነበረም....! የሰውም ሆነ የእናንተ እጅ የሰራው ነገር ሲሆን እጅ እጅ ይላል! ነገራችሁን ለእግዚአብሄር እጅ አሳልፋችሁ ስጡት በእውነት ያስደንቃችኋል። ሁሉን በጊዜው ውብ አድርጎ ሰራው የሚባለው ለዛ ነው። በእናንተ ጊዜ የተሰራው ውበትም ሆነ እረፍት የለውም ....እግዚአብሄር ልባችሁን ያሳርፍላችሁ! ለማንኛውም 7:00 - 9:00 ብቻ ለ2 ሰዓታት በሚቆየው የቃልኪዳን ስነ ስርዓታችን ላይ ተገኙልን! ቅዳሜ ግንቦት 23 ከቀኑ 6:30 መገናኛ ከኔክሰስ ሆቴል ጀርባ ባለው ትልቁ አዳረሽ በቤዛ አፍሪካየምስጋና ማዕከል

  • ሰርግ እና ሞት - ሰው በቀብር ቀን አያረፍድም ሰዓቱን ጠብቆ ይመጣል! - ደግሞም አልተጠራሁም አይልም የመጠሪያ ካርድም አይፈልግም መስማቱን ብቻ እንደጥሪ ይቆጥራል! - የትም ቦታ ቀብር ቢሆን ግድ የለውም እርሙን ለማውጣት፣ መቀበራችሁን ለማረጋገጥ፤ ሀዘን ለመካፈል ይገኛል! ሰርግ እና ሞት አንድ ነው እየተባለ ሲዘፈን ሰምቻለሁ?..... ይሄም ትዳር ያልፋል ነገር ግን የማያልፈው አምላክ ያበጀው ትዳር እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ! ሀዘን ቢያጋጥመኝ ልትደርሱኝ የምትችሉ ወዳጆቼ እያንዳንዳችሁን ለመጥራት ሞክሬ ስላልሆነልኝ ደስታዬ፡የሚያስደስታችሁ አለኝ በምለው በደስታዬ ቀን ሳታረፍዱ ልያችሁ..... ያከበረኝን በሚያልፍ ቀን የማያልፍ ነገር የሰራውን አምላክ በጋራ እናመስግን! ቅዳሜ ግንቦት 23 ከቀኑ 6:30 መገናኛ ከኔክሰስ ሆቴል ጀርባ ባለው ትልቁ አዳረሽ በቤዛ አፍሪካየምስጋና ማዕከል አመሰግናለሁ

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • #Glorytobe #ጌታ_እኮ_ነው! They call it Bride to be and I call it Glory to Be! God is very very Good - ክብሩን ለማየት እናፍቃለሁ ማንም ሰርፕራይዝ አያረገኝም የሚለውን ድፍረቴን ሰብራችሁ ተሳክቶላችኋል.....! ጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ ከልብ አመሰግናለሁ..... ልዩ ምስጋና #KalEvents #TeeCakes

  • የመብላት እና የመጠጣት ሱስ ያለበት ወዳጅ ያለን እንዲ ተብለናል? ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ ሥጋ ከሚሰለቅጡ ጋር አትወዳጅ፤ ሰካራሞችና ሆዳሞች ድኾች ይሆናሉና፤ እንቅልፋምነትም ቡትቶ ያለብሳቸዋል። ምሳሌ 23:20-21 መልካም እሁድ