- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 732
- 1/48двое суток
- 838
- 1/72трое суток
- 904
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሁሉም ጥሎህ ሲሄድ ከቀብርህ ስፍራ ፣ ካንተው ጋር ይቀራል የሰራኸው #ስራ።
ዘግይቶም ቢሆን ከአላህ የሚመጣ ችሮታ ያለፈን ሀዘንና ችግር የሚያስረሳ ፤ በረከተ ሰፊ እና እጅግ አስደሳች የሚሆን ነውና ፤ አብሽሩ ችሮታውን በትዕግስት ተጠባበቁ!
የምትለብሰው ልብስ የውጭ ገፅታህን ያሳምራል ፤ ጌታህን ማውሳት (ዚክር) ደግሞ ውስጥህን ያስውባል። እርግጥ ነው ሰዎች ዘንድ ሽክ ብሎ መታየት መልካም ነው ፤ ነገር ግን ልብህ አዛኙ ጌታህን በማውሳት መዋቡንና በርሱ ፍቅር መሞላቱን ጌታህ መመልከቱ እጅግ የበለጠ አስደሳች ነው።
ጌታየ ሆይ ጉዳዬን ገር አድርግልኝ
አህያን ከልክ በላይ መንከባከብ አንበሳ እንደሆነ እንዲያስብ ያደርጋል
ልብህን ማን እንደሚገባው ማወቅ ከፈለክ ያንተን ደስታ በህይወቱ ላይ ቅድሚያ ለሚሰጥ አድርግ ልቦች በቆንጆ ቃላት አይወሰዱም ስሜትን ጠብቀው ለደስታችን ልቦችን ለሚጠብቁ ነው ። ውዴታውን ለሁሉም ሁኔታወች ላይ ዋጋ ያደርጋል
ዝም ብለህ በመጠበቅ ብቻ የምታገኘው ምንም ነገር የለም። ነቢ ሙሳ (ዐ.ሰ) ወደ መድየን በደረሰ ጊዜ፣ ዝም ብሎ ዕድል እስኪመጣ አልተቀመጠም ነበር። እርሱ በወቅቱ ተሰዶና ደክሞት የነበረ ቢሆንም፣ እርዳታ የሚፈልጉ ሁለት ሴቶችን ባየ ጊዜ ግን ፈጥኖ በመቅረብ አገዛቸው። 'የተጻፈልኝማ አይቀርም' ብሎ እጁን አጣጥፎ አልጠበቀም፤ ይልቁንም ተንቀሳቀሰ። ያኔም ፈጽሞ ካልገመተው አቅጣጫ በረከት መጣለት። ሁሌም አትርሳ ዕድሎች የሚሰጡት ለሚጠባበቁ ሳይሆን ለሚንቀሳቀሱ ነው። ታዲያ አንተ በዝምታ ከሚጠብቁት ወገን ነህ? ወይስ አሁኑኑ ሥራ ከሚጀምሩት?
ሽሮ ለመግዛት ወተህ ሽቶ አትግዛ አላማህን ትስታለህና
የሰው ልጅ ከሚያሳልፍቸው ከባድ ስሜቶች በውስጡ ያለውን ስሜት ማስረዳት አለመቻሉ ነው !
«የምእመናን መሪ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፦ "እውነተኛ ወዳጆችን(የአላህ መንገድ ወንድሞችን) አጥብቀህ ያዝ፤ በጥላቸውም ስር ተጠለል። በምቾትና በደስታ ጊዜ ጌጥ፣ በችግርና በፈተና ጊዜ ደግሞ ጋሻ/መሳሪያ ይሆኑሃልና።" ኢማም አሽ-ሻፊዒይም እንዲህ ይሉ ነበር፦ "አላህ አንዳንዶቻችንን ለሌሎቻችን እንደ እዝነት ይልካል። አንዳንዴም የአላህ እዝነት በወዳጆች መልክ ይመጣል። ★በደል በደረሰብህ ጊዜ ከጎንህ የሚቆም ሠራዊት ይሆኑልሃል፤ ★ዕዳ በወደቀብህ ጊዜ ደጋፊ/ካዝና ይሆኑልሃል፤ ★ጭንቀት በከበበህ ጊዜ ደግሞ አጋዥና ረዳት ይሆኑልሃል።" : ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) በስደት (በሂጅራ) ቀን ከመንገዱ በፊት ወዳጅን (አቡ በክርን) መምረጣቸውን አላስተዋልክምን?… የመንገዱ ርዝመት ለብቻ አይገፋም ከአላህ የሆነ ወንድም ይፈልጋል።» [በሰለዋት የደመቀ በመልካም ስራ የታጀበ ጁምዓ ይሁንልህ ወዳጄ💖]
ትርፍ መሆን እንኳን በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ይቅርና በታክሲ ውስጥ እንኳን ዋጋ ያስከፍላል
ሀዘንህን የማይጋራህ ሰው ደስታህን እንዲቀማህ አትፍቀድ
ሁሉም ነገር ያለ ቦታው ሲሆን ዋጋ የለውምና ቦታችሁን ፈልጉ
የእውነት ልንገራቹህ አቅፎ የሳማቹህ ሁሉ ወዳጅ አይደለም
"ጌታህም ስለፈለገ እድሜቸው ደርሶ ሀብታቸውን እንዲያወጡ አደረገ ይህም የጌታህ እዝነት ነው " በአላህ ላይ እርግጠኛ ሁን የስጧታወች መዘግየት ጥበብ ነው ካንተ ቢደበቅም አንዳንድ ነገራቶች ቀድመን ብናገኛቸው እናጣቸዋለን ነበር ። ጊዜውን መጠበቁ ከመልስ ማገኘት ነው ነገር ግን የሰው ልጅ ችኩል ነው በመከልከል ውስጥ እዝነት አለ እኛ ባናቀውም የፈለግናቸው ነገራቶች ስላልተሳኩ ብዙ ጊዜ አለቀስን ከጊዜ ብኋላ ግን ያልተሰጡን ነገራቶች እነሱን ማጣታችን ለኛ የሚሻለው እሱ እንደነበር ተመለከትን ። በጊዜ ሒደት የአላህን ጥበብ በሁሉም ነገር ላይ ትመለከታለህ አላህ ላንተ የመረጠልህ ነገር አንተ ለራስህ ከመረጥከው የተሻለ እንደሆነ ታያለህ !
ዱንያ ምን ያህል ብጠብብህ አላህ በሮችን ያለ ቁልፍ እንዳልፈጠራቸው አትርሳ ባሪያወቹ በሩን እንዲያንኮኩ ሲፈልግ ይፈትናቸዋል አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላም በባሪያው ልብ ውስጥ ከሱ የሚተልቅ ምንም ነገር እንደሌለ ሲመለከት ፈረጃውን ይፈቅድለታል ። ልብህን በአላህ ላይ አንጠልጥል..❤
"ቀናቶችን በሰወች ዘንድ እንገለባብጣቸዋለን" ማን ያሰበ ነበር ነብዩላህ ሙሳ ለአመታት እረኝነት ሰርቶ ከአመታት ብኋላ የአላህ አናጋሪ ይሆናል ያለ... ነብዩ ሙሀመድም ﷺ ለቁረይሽ ከበርቴወችና ባለስልጣናት በትንሽ ገንዘብ እረኝነት ሰርተው በመጨረሻም የመልዕክተኞችና የነብያት መደምደሚያ ነብይ ይሆናሉ ብሎ ያሰበ አልነበረም ። የእድሜህ ቆንጆው ክፍል ምናልባት አልደረሰ ይሆናል ጥቂት ልፍት ብዙ አላህ ላይ መልካም የሆነን ተስፍ ማድረግ . ታያለህ መጪው ጊዜ የተሻለ ይሆናል
እናታችን ሀጀር በሶፍና በመርዋ መሀል ስትወጣና ስትወርድ የነበረው ተስፍዋ ትንሽየ ጥሞን የምታስታግስበት ውሀ ፈልጋ አላህ ግን የዘምዘም ውሃን እስከዛሬ ድረስ ያላለቀ ምንጭ ወፈቃት የአላህ ብስራት ፈረጃም ሲመጣ እንደዚሁ ነው ።
ነብዩላህ ዩሱፍ አለይሂ ሰላም ጋር በእስር ቤት ውስጥ አብረውት ሁለት ወጣቶች ነበሩ ዩሱፍ ከሁለቱም በልብ ጥራት ይበልጥ ነበር ቢሆንም ግን አላህ እነሱን ቀድሞ ከእስር አወጣቸው ። አንደኛው የወጣው ሰራተኛ ለመሆን ሲሆን ሁለተኛው ለመገደል ነበር ከእስር አላህ ነፃ ያደረገው ። ነብዩላህ ዩሱፍም ከአመታት ብኋላ የንጉሱ አማካሪ ለመሆን ከእስር ቤት ነፃ ተባለ እናልህ ወዳጄ ምኞታችን ሊዘገይ ይችላል ስጧታው ሊበዛ ሲል....❤
ህይወት በውጣ ውረድ ስትሞላ፣ ቀናቶቿም አሰልቺ በሆነ የድካም ስሜት ሲደነዝዙ... ነፍስ ጥቂት የራስዋን የጸጥታ ስፍራ ትሻለች። አሻግረን ለማየትና የነገን ብሩህ ተስፋ ለመሰነቅ፣ ለራሳችን የምንሰጣት ጥቂት ክፍተት ያስፈልገናል። ሁልጊዜ በአንድ አይነት አሰልቺ መንገድ እየተጓዙ፣ የተለየና አዲስ መዳረሻን መመኘት በፍፁም አይቻልም። እስኪ ቆም በልና አስተውል... ባለፍከውና ዛሬም በምትሮጠው የህይወት ትንቅንቅ ውስጥ "የኔ" የምትላቸው ትርጉም ያላቸው ነገሮች እየራቁህ ይሆን? ችግሩ በተፈጠረበት በዚያው በጠበበው አስተሳሰብ ውስጥ ሆኖ መፍትሄን ማለም ዘበት ነው።ስለዚህ... አንድ አፍታ ወስደህ ለራስህ ጥቂት ጊዜ ስጥ… መልካም ጁመዓ!