tgindex
❤ ፈ ዳ ኢ ሉ

❤ ፈ ዳ ኢ ሉ

Статистика

۝﷽ﺍﻟﻠﻬُــــــﻢ صلی۩۞۩ ﻋﻠَﻰ ﺳَــﻴﺪﻧـﺎ ﻣُﺤـﻤَّـﺪْﷺ

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
арабский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
539
−2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
526
22 постов
Вовлечённость
97,6%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 22
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
53
1/48двое суток
60
1/72трое суток
65

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • 💖💖💖 "ረቢዕ ማለት ደግ ነው 💖💖💖 💖💖💖 የአህባቦቹ ሰርግ ነው" 💖💖💖 የመዲናዉ የሀዲስ አዋቂ ዶ/ር ሙሀመድ ኢብን አልዐለዊ በመካና በመዲና ለዘመናት የቆየዉንና እስከአሁንም በቤተሰባቸዉ የቀጠለዉን የታላቁን ነብይ የአሽረፈልኸልቅ የመዉሊድ ክብረበአል አፈጻጸምን ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ደስታና ብርታት በሚሰማን በየትኛዉም ቀንና አጋጣሚ የነብዩንﷺ መዉሊድ እናስባለን… በርሳቸዉ የመወለድ ጸጋ እንደሰታለን…ይህ መደሰታችን ሰኞ ቀንና በተወለዱበት በወርሀ ረቢዐል አወል መጠኑ ይጨምራል❤️… ጤነኛ አዕምሮ ያለዉ ሰዉ ‹በኢስራእና በሚዕራጅ ባለቤት ለምን ትደሰታላችሁ?›› ብሎ ሊጠይቀን አይችልም፡!!!!ይህ ጥያቄ በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በነብዩ ሙሀመድﷺመልዕክተኛነት ከመሰከረ ሙስሊም አንደበት ሊወጣ ይችላልን? እርባናቢስ ጥያቄ ስለሆነ መልስ አያሻዉም፡፡ ቢሆንም፡ ‹ሙእሚን ስለሆንኩ ነብዩንﷺ እወዳለሁ ፤ ስለወደድኳቸዉ በርሳቸዉ እደሰታለሁ፤ ደስታዬንም ዘወትር እገልጻለሁ›ካልኩ በቂ ነዉ፡፡›› ይላሉ🥰🥰❤️ የሀገራችንን የመዉሊድ ሂደት ስናጠና ከላይ ሸኽ አልዐለዊ ከሰጡት ገለጻ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የነብዩﷺ ልደት በሳምንታዊ፣በወርሀዊ ወይም በቀናት ዑደት ዓመቱን ሙሉ ይታሰባል፡፡ ሆኖም በረቢዐል አወል ይህ ደሰታ ይጨምራል፡፡ ከወሩ ዉስጥ ከ9-12 ባሉት ቀናት ደግሞ እርሳቸዉን የማሰቡና ገድላቸዉን በጋራ እያወሱ የመመሰጡ መጠን ይበልጥ ያይላል፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በየትኛዉም የዓመቱ ቀን ድሆችን ደግሶ የማብላቱ ክንዉን መዉሊድ ይባላል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሶደቃዎች ላይ ምንጊዜም የነብያችንﷺ ገድል ይነበባል፡፡ በርሳቸዉ ላይ በብዛት ሶለዋት ይወረዳል፡፡ እርሳቸዉን የሚያወድሱና የሚያሞግሱ መንዙማዎች ምንጊዜም ይደመጣሉ፡፡ በዋነኛነት በእዉቁ ዓሊም በአህመደ ዳኒ (ዳንዩል አወል) የተደራጀዉ ‹‹ራምሳ› እና ‹ተራ መንዙማ› የተሰኘ ሙሉ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ ይህ የመዉሊድ ሂደት በሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች የተለመደ ነዉ፡፡ ስለዚህ መዉሊድን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚከናወን ሂደት አድርጎ ማሰብ ስህተት ነዉ። እንኳን ለቆንጅየው ለምርጡ ለጣፋጩ ነብዬ አለይሂ ሰላት ወሰላም ዊላዳ ወር ረቢዑል አወል አደረሳችሁ❤️❤️❤️❤️❤️ #ትንሹ አሚር ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ https://youtu.be/b9vb_AOWKyU?si=NXxurRF733aUWocA

  • ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን የአብሬቶቹ የዘር ፍሬ ፣ የሸይኻችን ሠይዲ ሚቅባሰል ኑር(ቀ.ሢ) የልጅ ልጅ ፣ ተወዳጁ ወንድማችን ሱነን በድንገት ተለየን አላህ በረሕመቱ ይሸፍንልን ፣ ሩሁን በአባት አያቶቹ አካቢሮቹ ጥላ ስር ከነቢﷺ ጋር ያኑርልን🤲

  • 💖💖💖 " አ.ለ.ም  ነህ" 💖💖💖         የረቢዑ ንጉስ የኔ ዋና ርዕስ               ስለአንተ ሃያልነት ሊቃን መሰከሩ    የዋህነትህን በልዩ ህብረ ዜማ እርግቦች ዘመሩ ባንተ ፍልስፍና ጠቢባን ገርሟቸው ቆመው አጨበጨቡ ለተጠማ ውሃን ታዘንባለህና የከሰሙ አበቦች አካልህ             ነክቷቸዉ እንደ አዲስ አበቡ ነፋስ ተራራውም ሌት ስላንተ አለመ ካንተ ጋር ሲበላ ወጥ ያለ ጨው ጣመ ሲመሻሽ ጨረቃ አንድ ቀን አትቀርም አብሪነትህ ስቧት ብርሃንህ በልጧት    ያንተ ሱሰኛ ናት ጀንበር አዘቅዝቃ ታፈጥብሃለች ስለ አፈጣጠርህ ጌታን ታደንቃለች ምን አለ እሱን በሆንኩ ብላ ትመኛለች ክረምት አፍቃሪህ ነው በጋ ይወድሃል ረቢዕ ሲናፍቅህ በልግም ያስብሃል አንበሳ አጎንብሶ ይታዘዝልሃል ዝሆን በግዝፈትህ ሁሌ ይቀናብሃል ስትስቅ የሰማ የዓለም የሳቅ ንጉሥ መቼም ላልስቅ ብሎ ጥርስ ብሩሽ  ሰቅሏል ድምፅህን ያዳመጡ የዓለም ድንቅ ዘፉኞች ሙዚቃ አቆመዋል ለአይናችህ ነፀብራቅ ለአፍንጫህ መሰልከክ ለጉንጪህ ማሳሳት ለከናፍሮቺህ ለአንደበትህ ለዛ አቻ ታቶልሃል   .......... እናም ቃል ማጣቴ ቃል ተርፎ እንዳይመስልህ የምቀባዥረው መዝገብ ባገላብጥ የቱንም ብናገር አልገልፅ ቢለኝ ነው ለዚህ ቅንጣቱ ለዚህ ጨቅላው አሚር " አለሜ .. አለሜ ''ነህ በቃ አንተ አንደኛ እንዳልልህ ነህ ስላልኩኝ አለም ሁለተኛ ሚሆን ከአንደኛው ዝቅ የሚል ሌላ ዓለም የለም ለነገሩ ህያብ ህያው ከዚ የሚሻል ብቁ ቃል እስካገኝ ሰባቱን አህጉር ጠቅልሎ በሚገኝ ትልቅ በሚመስል ስም እጠራሃለው እንጂማ ከአንተ አንፃር ዓለም ኢምንት ነዉ አሚን መሰጠቴ ዘልአለም እልፍ አዕላፍ ሰርክ አፈቅሮታለሁ              ✍️...አሚር💡 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ https://youtu.be/UAg6gASShHI?si=cmk-0jGaP8XeeN07 💖subscribe , 🙏share and Like❤

  • 💖💖💖 ለይለቱል ጁመዕ_💖💖💖 ❤ " ና ፍቀውኛል ኧረ እንደው ምን ይሻለኛል የማደርገው መላቅጡ ጠፍቶብኛል ያሞኘኛል በማያልቀው ነገ ዛሬ " 🔥 ሰይዲ ዩውሱፍ አነብሃኒይ    ከሸይኹል አክበር  ማድ ዘግነው  ምን አሉ አትለኝም ወይ?.....አሽከር ላሽከር መዛመዱ ሠይዳችን  ያለምንም ጋላቢ  ቡራቅ  በይተል መቅዲስ  በርቀው መድረስ ይችሉ ነበር....አውሊያኦች በአይን ጭርፍታ  ዱንያን አሰስ አርገው እንደሚመለሷት!... ከራማው ሁላ  ከርሳቸው ነዋ!                  ታዲያ  ቡራቅ  የተላከው   አንድም ሰበብያን ለማስተማር     አንድም  ከበረቱ ሥር  በናፍቆት ከስቶ  የከረመን ሚስኪን  የሙስጦፋ  ናፋቂ   •አብሽር ደረስንልህ • ለማለት በይተል መቅዲስ ደርሰው  ከቡራቅ ከወረዱ በኋላ   ቡራቅን  አስረው  አላቆሙትም ወይ?       አንተዬ ቡራቅኮ  ወግድ ቢሉትም መርሃባ አይል...አንድም  ሰበብያን ሊያስተምሩን    አንድም  በማሰሪያው አሳብበው  የቡራቅን አንገት ሊኮረኮሩት...ተሻሽተው ናፍቆቱን ሊያወጡለት!.....           በናፍቆት የከሳ ሙሂብ በቡራቅ ይመሰላል፡ይቅረብም ይራቅ   በሐቢቡ መዳበሱ  አይቀሬ ነው.....ቡራቅ ቂያም  ደርሶለት  ጀነት አብሮ እስኪኸትም ድረስ  ምን ይሰራ ይሆን?   መንዙማ ይከትባል?   ለሌሎች ቡራቆች ስለ ሠይዳችን ሃርማ  እጆች ልስላሴ ይሰብካል?      ወይስ   የኢስራእ ትንግርት  የቁም ቅዠት መስሎት  ዳግም  የሸውቅ  ኺያም ቀልሶ    በነዳፊ ሃዘኑ ይንደፋደፋል?.......ሁሉም እንደዘውቁ!                #اللهم_صل_على_سيدنا_محمد_وعلى_آله_وصحبه_ وسلم اَللهم صَلِّ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ اَلْفَاتِحِ لِمَا اُغْلِقَ وَالْخَاتِمِ لِمَا سَبَقَ نَاصِرِ الْحَقِّ بِالْحَقِّ وَالْهَادِي اِلَى صِرَاطِكَ الْمُسْتَقِيمِ وَعَلَى آلِهِ حَقَّ قَدْرِهِ وَمِقْدَارِهِ الْعَظِيمِ #አሚር💊 ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ https://youtu.be/RmvDvcsgUow?si=cq6Ga5CB80f_O5BF

  • 💖💖💖💖መገን ገበያ 💖💖💖💖        በአላህ ይሁንብኝ የነብዩ ﷺ ዋጋ ልብህ(ሽ) ላይ ከቀነሰ በፍፁም ወደ ሱና አትመራም ፣ በውስጣዊም ሆነ በውጫዊ እሳቸውን አትከተላቸውም ፤ ሰሓቦች ነብዩን ﷺ ተምሳሌት የማድረጋቸው ዕጣ ነብዩን ﷺ በማላቃቸው ድርሻ ልክ ነበር »                         صلوا عليه وسلموا تسليما   اللهم_صل_على_سيدنا_محمد_وعلى_آله_وصحبه_وسلم https://youtu.be/_HnXKfwLTkc?si=2P0lR-iqYdTfLR9u #አሚር🤌 በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793 https://t.me/Tenshu6793

  • <<" ትመር እንደሆነ ምረር እንደ ቅል   አልመርር ብሎ ነው ዱባ ሚቀቀል" >> ለምረኛ ሰው ነገሮች ሁሉ ምር ይሆኑለታል፡፡ በቁም ነገር የሚቀልድ ሰው ከችግር አይወጣም ! ቁርኣንም አውግዞታል የመሃይምነት መገለጫ አድርጎታል ፡፡ ድመት ስትጠግብ አይጥን ያዝ ለቀቅ ያዝ ለቀቅ ታረጋታለች ለድመቷ ቀልድ ነው ለአይጧ ደግሞ የነፍስ ጉዳይ ነው ፣ዲን ቀልድ አይደለም የህይወት ጉዳይ ነው አንድ ሰው ሁልግዜ ያሸንፋል የብዙ ጊዜ የማሸነፍ ሚስጥርህ ምንድን ነው ተብሎ ሲጠየቅ ፣ ጋዜጠኛውን ጣትህን አፌ ውስጥ የኔንም ጣት አፍህ ውስጥ ከተን እንነካከስ አለው ፣ ከዛ ትንሽም ሳይቆይ ጣ ቴ ን ብሎ ጮኸ ፣ ለዚህ ነው ማሸንፈው ህመምን ሰለምቋቋም ነው ብሎ መለሰላቸው፡፡ Pain and gain አንዳንድ ሰው ካልተጨነቀ ሚሰራ አይመስለውም  ከተጨነክ ችግር አረከው በተጨነቀ ልብ መፍትሄ የለም ፣ ከተሳካ እንኳን ያንኑ ሙጭጭ ብሎ ይቀራል ከፍ ያለ ስራ አያስብም ፡፡ ውዴታን የሚያህል ትልቅ ሃይል የለም  ያሁን ሰው ፍቅርን እየረሳው ነው፣ ከሚወደዱ ሁሉ በጣም ሚወድድ አሏህ ነው አሏህን ያለልክ መውደድ አለብን  አሏህን ካልወደድን ግን  በጣም ነውረኛ ነን። ✨ራብየቱል አደውያ  የፍቅር መጨረሻ ምንድን ነው ብለው ጠየቁዋት፡፡ ፍቅር መጨረሻ የለውም ምክንያቱም የምንወደው ጌታ ዘላለማዊ ስለሆነ ፍቅራችንም ዘላለማዊ ነው የፈጣሪዬ ውዴታ ከፍጡሮቹ ውዴታ ፊቴን አዙሮታል ትላለች ፡፡ ሸይጣንን _ትጠይዋለሽ?_ አዎ! _ እሱን _ በመጥላት ታዝዣለሁ፡፡ግን ጊዜዬ በሙሉ ለፈጣሪ ውዴታ ሞልቼዋለሁ ስለዚህ እሱን ምጠላበት ጊዜ አልሰጠሁትም ማለቷ ነው፡፡ ፈጣሪን ከመውደድ የበለጠ ደረጃ የለም ሰጪውን ትተህ ስጦታውን መውደድ መታለል ትልቅ ስህተት ነው። በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793

  • ♥♥♥♥ዛሬ እሁድ ነው♥♥♥♥ ሰይዳችን ሰለላ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ=> እሁድ ቀን አይሁዶች በኔ ላይ እርግማን ያበዛሉ። እናንተ ደሞ ሰለዋት አብዙብኝ።                  ♥ተንቢሁል አናም♥ #اللهم_صل_على_سيدنا_محمد_وعلى_آله_وصحبه_ وسلم اَللهم صَلِّ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ اَلْفَاتِحِ لِمَا اُغْلِقَ وَالْخَاتِمِ لِمَا سَبَقَ نَاصِرِ الْحَقِّ بِالْحَقِّ وَالْهَادِي اِلَى صِرَاطِكَ الْمُسْتَقِيمِ وَعَلَى آلِهِ حَقَّ قَدْرِهِ وَمِقْدَارِهِ الْعَظِيمِ # አሚር💡 ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ https://youtu.be/EEG-2gyR6cs?si=2jHHoZ13kmSW2c6w

  • ❤❤❤ለይለቱል ሀሚስ❤❤❤ ❝ አንዳንዶች የረሱልን (ﷺ) ሲራ ለመረጃ ያጠናሉ፣ ከፊሎቹ እውነትን ለመፈለግ ያጠናሉ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ለፍቅር ያጠናሉ። ፍቅር ግን ሁሉንም ዓላማዎች ከፍ ያደርገዋል።   ❤️❞ -- ሠይድ ሐቢብ ዐልይ አል-ጂፍሪይ #ምርጥ መንዙማ በሼኽ ሰአዱ ተጋበዙልን 👇💖👇💖👇💖👇💖👇💖👇💖 https://youtu.be/y183PS8ejZE https://youtu.be/y183PS8ejZE ☝️💖☝️💖☝️💖☝️💖☝️💖☝️💖 #Hadra#አሚር#መንዙማ #newmenzuma #Hadretukejentuna ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793 https://t.me/Tenshu6793

  • ❤ ፈ ዳ ኢ ሉ pinned a photo

  • без подписи

  • 9 июл.39135из Tenshu6793

    💚💛❤  ለይለተል 💚💛❤ 💚💛❤   ጁመአ   💚💛❤ 💚💛❤  ሙባረክ  💚💛❤ «.. የፍቅር መጀመሪያ ተወዳጁ ውስጥ ባለች አንዲት ነገር ምክንያት እሱን መውደድ ነው.. መጨረሻው ደግሞ ተወዳጁ በውስጣቸው ያለበት ነገራቶችን ሁሉ መውደድ ነው.. » በሰይዳችን ﷺ ፍቅር የተነካም እሳቸው አሉበት የተባለን ነገር ሁሉ አሕለ በይታቸውን ፣ ሰሓባዎቻቸውን ፣ ታቢዒዮቹን ፣ ወዳጆቻቸውን ሱናቸውን ፣ ስራቸውን ፣ አኽላቃቸውን ፣ ሁሉ ነገራቸውን ያፈቅራሉ .. ኢማም ማሊክ( የማሊኪያ መዝሀብ ሊቅ ) አላህ ይዘንላቸውና  ኪታብ እያስቀሩ እያለ ጊንጥ ነደፋቸው  ከዛም ደርሳቸውን ማስቀራት ቀጠሉ  ከዛም ለምን የዛኔ ኪታብ ማስቀራቱን አላቆሙም ሲባሉ እንዴት ለነብስያዬ ብዬ የነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀዲስ አቋርጣለሁ አሉ........🤲 አላህ እውነተኛ መሐባቸውን የሁለቱም ሀገር ስንቃችን ያድርግልን #ትንሹ አሚር https://youtu.be/G01vGnd3br8?si=X3O59CfvmwFNEy6X ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ ❤ ኡስታዝ - ፈድሉ ቀ.ሲ ጀማሉል አለም ተጋበዙልን ❤ 🙏ሰብስክራይብና ሼር እያደረግን ያጀማ🙏 ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️

  • 🌙 የዓሹራእ ጾም – ታላቅ የአላህ ጸጋ 🌙 የዓሹራእ ቀን የሙሃረም ወር 10ኛው ቀን ነው። ነቢዩ ﷺ አላህ ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) እና ሕዝባቸውን ከፈርዖን በማዳኑ ምክንያት አላህን ለማመስገን በዚህ ቀን ጾመዋል። 📖 የዓሹራእ ጾም ያለፈውን አንድ ዓመት ኃጢአት እንዲሰረዝ ተስፋ የተሰጠበት የተወደደ ሱና ነው። 🤲 ነቢዩ ﷺ አይሁዶችን ለመቃረን 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን አብሮ መጾምን አበረታተዋል። ✨ አላህ ከጾሚዎች ያድርገን፣ ጾማችንንም ይቀበለን። አሚን! #ዓሹራእ #Ashura እስልምና_ምክር #ሙሃረም #ጾም #ዚክር #ኢስላም #Alhamdulillah 🤍🌙 # ትንሹ አሚር ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793 https://t.me/Tenshu6793

  • 6 мар.7046из Tenshu6793

    ❤ ❤ ❤ አህለል በድርይ ❤ ❤ ❤ ረመዷን 17ኛዋ ለሊት በንጋታዋ ሰይዳችን ﷺ እነዛን በዳዕዋቸው ዘመን ብዙ ችግሮችንና አዛን ያደረሱባቸውን የዲኑም የሳቸውም ጠላቶችን ገጥመው ድል ያደረጉበት በድር ዘመቻ በመባል የሚታወቀው የመጀመርያው ዘመቻ የተከሰተበት ቀን ነው ። ለሊቱን በሙሉ " ያሐዩ ያቀዩም " እያሉ አላህን እየተማፀኑ ነበር ያደሩት ። አላህም በ3000 መላይካ እርዳታውን ልኮ የሰይዳችንን ﷺ የበላይነት ያሳየበት ድንቅ ድል ነበር ። በዛች ለሊት አላህ ሰይዳችንን ﷺ በረዳበት እገዛና በሱና በሳቸው መሀከል ባለው ፍቅር ይሁንበት እኛም በነፍሳችን፣በሸይጣን፣ከአላህ በምታርቀን ዱንያ፣ ከሐቁ በሚያሰናክለን ስሜትና በአጠቃላይ ከሰውም ከጂንም በሆኑ ጠላቶቻችን ላይ ድልን የምንጎናፀፍበትን መደድና እርዳታ ይስጠን አሚን አሚን ያረቢ 🤲🤲🤲 🌹اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا وقدوتنا وشفيعنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين #አሚር ትንሹ በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793 https://t.me/Tenshu6793

  • 20 дек.806104из Tenshu6793

    🔰ለዘመናችን ታላቁ ዓሊም አልሐቢብ ዑመር ቢን ሐፊዝ የረጀብን ወር ቱሩፋት እንዴት እንጠቀምበት? ምንስ ነው መስራቱ የሚገባው? ተብለው ተጠየቁ። 🟢እንዲህ በማለት መለሱ ሰይድና ዐልይ ቢን አቢ ጣሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ከረጀብ ወር የመጀመሪያው ለሊት ላይ እራሳቸውን ለዒባዳ ፍሪ ያደርጉ ነበር። እርሷ (የረጀብ የመጀመሪያዋ ለሊት) በላጭ ለሊት ነች። ዱዓ በእሷ ሙስተጃብ ይሆንባታል ከተባሉት አንዷ ነች። ረሱሉላህ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከረጀብ ወር ይፆሙ ነበረ የሚል መጥቶዋል። ያከብሩት፣ ያልቁት፣ ያከብዱት፣ ያልቁት ነበረ። አቡ አልሐሰን ዐሊይ ብኑ ሙሐመድ አርሪብዒይ ሪጃሎቹ ሲቃት በሆነ ሰነድ እንደዘገቡት ዑርዋህ ለሰይድና ዐብደላህ ብነ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ ረሱሉላህ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ረጀብን ይፆሙ ነበር ወይ? ብሎ ጠየቃቸው። አዎ ያከብሩት ነበር። በረጀብ ወር ይፆሙ ነበር። ይህን የተከበረ ወርን ያከብሩት ነበር። ከተከበሩ ወራቶች ሁሉ ነጥለው አልፈድር ብለው ሰየሙት። በሐዲስ (በረጀብ ከእስቲግፋር አብዙ። ለአላህ በየሰዓቱ ከእሳት ነፃ ወጪዎች አሉት።) اللهم اجعلنا مِن خواص أهله، اللهم بارك لنا في رجب وشعبان وبلِّغنا رمضان، وأعِنَّا على الصيام والقيام. በረጀብ ወር ተውበትን ማረጋገጥና እስቲግፋር ማብዛት ተገቢ ነው። ረጀብ የመዝሪያ ወር ነው። ሻዕባት የማጠጫ ወር ነው። ረመዷን የማጨድ ወር ነው። ያልዘራ ሰው ምንን ያጠጣል? ያልዘራ ያላጠጣ ምን ያጭዳል? ይህ የመዝሪያ ወር ረጀብ ነው፦ 🔰እስቲግፋርና ወደ አላህ መመለስ (ተውበት) 🔰ወደ አላህ በመቅጣጨት እውነተኛ ቆራጥነት 🔰ዘመድንና ጎረቤትን ማየት 🔰በረጀብ ከሰደቃ የድርሻን መወጣት 🔰ከረጀብ ወር የሆነ ያህል መፆም። ማብዛቱ ካልተቻለ ሶስትም ቀናት ቢሆን 🔰አቅም ያለው ለአላሁ ተባረከ ወተዓለ አንድ በግ ማረድ። የረጀብ ወር እርድ (ዐቲረቱን) ይባላል። ዒድ ላይ (ኡዱሒያህ) እንደሚባለው።  በአንድ ቤተሰብ እንደ አቅማቸው እንደ ገራላቸው በግ ማረዳቸው ተገቢ ነው። የረጀብ የመጀመሪያው ለሊት ፈድል ነው። እንደዚሁም የኢስራና የሚዕራጅ ትውስታ ይመጣል። በውስጧ ያሉ ትምህቶችና ግሳፄዎች። አብዛኛዎቹ በረጀብ ወር በ27ተኛ ለሊት መሆንዋ ነው። 📗አልዐላመቱ አሽሸይኽ አልሐቢብ ዑመር ሐፊዘሁላሁ ተዓላ # አሚር ትንሹ በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793 https://t.me/Tenshu6793

  • 4 дек.72635из abellramuzjente

    ሰይዱል ዓሪፊን ሰይዱና ኑር ሁሰይን ባሌ ረ.ዐ ====== 💚 💕====== * ብርሀናማ ጨረቃ በጀማዱልሳኒ አጋማሽ ላይ ስትዘልቅ ከወደ ባሌ አናጂና ደማቅ የአሺቆች መዐድ  ይኖራል ገልገለ ጎበና መውሊድ * ሰባት ክፍለ ዘመናትን የኋሊት መለስ ብለን ስንቃኝ ከታሪክ ብራና ላይ ይሄንን በወርቃማ ቀለም ተከትቦ እናገኛለን.. ከገውሱል አዕዞም ..💚ሰይድ ዐብዱልቃዲር አል-ጀይላኒ መድረሳ ምሩቅ የሆኑ 405 ተማሪዎች💚 በሸይኽ አባዲር እየተመሩ ወደ ጥንታዊቷ ሀረር ከተማ ይዘልቃሉ በዚህ እንቁ ስብስብ ውስጥ ሸይኽ ኢብራሂም የተባሉ ፈርጥ ነበሩበት * 💚 💕 ሸይኽ ኢብራሂም ቁረይሺይ ናቸው፣ የዘር ሀረጋቸው ከአቂል ቢን አቡጧሊብ ይመዘዛል.. ይህም አህለልበይት ያደርጋቸዋል የኋላ ኋላ ከወደ ባሌ አናጂና ቀበሌ ዘልቀው እመት ማኪዳ ጋር በትዳር ይጣመራሉ መልካም ፍሬዎችንም ያፈራሉ የሀበሻውን የብርሃነ ቀንዲል  ተወዳጁ ልዑልም ከፍሬዎቻቸው መካከል ናቸው። * 💚ሸይኹ ሰቀለይን ቁጥቡል ሀበሻ ሰይዱል ዓሪፊን ሰይዱና ኑር ሁሰይን ባሌ … አቢዮ በመባል ይታወቃሉ..ከ400 አመታት በላይ በህይወት እንደኖሩ ተዘግቧል ሀበሻን በማቅናት ወደርየለሽ ገድል ፈፀመዋል..ሰለእርሳቸው የህይወት ታሪክ አያሌ ምሁራን ጥልቅ ጥናት አድርገዋል..ግለ ታሪካቸው "ረቢዐል ቁሉብ"ደግሞ ከመሻኢኾቻችን ዘንድ እጅግ ውዱ ንብረት፣ የተከበረው ካዝናቸው ነው። አንድ ውብ ንግግራቸውን ለናሙና *       «ድር ፤ ለሸረሪት ብቸኛ መንገዷ ብቻ ሳይሆን ሌላን የማያስጉዝ ጭምርም ነው ቦይም ዉሃን'ንጂ ሌላን አያሳልፍም ውሃውም ያለ ቦይ ሲፈስ  አጥፊ ነው ልክ እንዲሁ የአዋቂዎች መንገድም አዋቂዎችን ብቻ የሚያስጉዝ ነዉ»           ❤️ሰይዱና ኑር ሁሰይን ባሌ ረ.ዐ  ✍ትንሹ አሚር በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! 👇👇👇 https://t.me/Tenshu6793

  • 20 нояб.66671из Shabdlwehab

    ሶሉ ዓለል ሀቢብ አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወንድምና እህቶች ሰሞኑን እጄን ወደናንተ መዘርጋቴ አይቀርም ያልኳቹህ ጉዳይ የኚህ ሸይኽ ጉዳይ ነበረ። በውስጥ በተወሰኑ ወንድሞች ቢቻ ለማሳካት ባለመቻሌ ወደናንተ መጣሁ አላህ እንዲህ ካለው ሙሲባ እናንተንም የናንተ የሆነን ሁላ አላህ ይጠብቅላቹ የተቻላቹን ሁላ አድርጉ ሼር ሼር አድርጉልኝ 1000596776993 Shmiftah musa ቴሌግራም 👇 @Shabdlwehab اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين في كل لمحة الف الف مرة አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወዚድ ወባሪክ ዓላ ሰዪዲና ሙሀመዲን ወዓላ አሊሂ ወሷህቢሂ አጅመዒን ፊኩሊ ለምሀቲን አልፈ አልፊ

  • без подписи

  • ♥♥♥♥ዛሬ እሁድ ነው♥♥♥♥ ሰይዳችን ሰለላ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ=> እሁድ ቀን አይሁዶች በኔ ላይ እርግማን ያበዛሉ። እናንተ ደሞ ሰለዋት አብዙብኝ።                  ♥ተንቢሁል አናም♥ #اللهم_صل_على_سيدنا_محمد_وعلى_آله_وصحبه_ وسلم اَللهم صَلِّ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ اَلْفَاتِحِ لِمَا اُغْلِقَ وَالْخَاتِمِ لِمَا سَبَقَ نَاصِرِ الْحَقِّ بِالْحَقِّ وَالْهَادِي اِلَى صِرَاطِكَ الْمُسْتَقِيمِ وَعَلَى آلِهِ حَقَّ قَدْرِهِ وَمِقْدَارِهِ الْعَظِيمِ #ትንሹ አሚር ❀በቴሌግራም ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢🍀🍀🍀 👇👇👇 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️ 💚💛❤️@Tenshu6793  💚💛❤️

  • ረመዳን 29 ኢላሂ!… የስህተቴን ብዛት፣ ሀፍረተ—ቢስነቴን ላንተ እነግራለሁ!… ምላሴ "ላኢላሃ ኢለላህ" ቢልም ልቤ በእልፍ ጣዖታት ተሞልቷል! በድርብርብ ቆሻሻዎች አድፏል! ኢላሂ!… የልቤን ዐይን በደማቁ ብርሃንህ ግለጠው! የልቤን ዝገት ጥረግልኝና ስውሩን ምስጢርህን አሳየኝ! ልቤ የእውነትህን ፀሀይ በእርግጠኝነት እንዲመሰክር በረከትህን አድለው! ኢላሂ!… ወራዳነቴ ትዝ ቢለኝ ኖሮ ተንበርክኬ አለቅስ ነበር! ውለታህ ትዝ ቢለኝ ኖሮ መናፈቄ አያባራም ነበር! ቸርነትህ ቢታየኝ ኃጢኣቴ ትዝ ቢለኝ ኖሮ መኝታዬም ሆነ ሚሕራቤ በእንባ ጎርፍ ይጥለቀለቅ ነበር! ኢላሂ!… ማንነቴን አስታውሰኝና ወዳንተ አዙረኝ! ከኔነቴ ነቅለህ ወዳንተነትህ አቅርበኝ! ድክመቴን አሳውቀኝና በልቅናህ ብርታት ባዶነቴን ሙላው! ኢላሂ!… የማይምነቴ ብዛት ኃጢኣት ውስጥ ዘፈቀኝ! የማወቄ አለማወቅ በመልካም ሥራዎቼ ውስጥ ኃጢኣት እንድቀላቅል አደረገኝ! በማወቄና ባለማወቄ መሀልም ስህተቶቼ ንፅህና አሳጡኝ! ነፍሴና ሰይጣኔ ነገሱብኝ! የፍጥረትህ ውበት አታሎኝ ጥበበኛው እጅህን አስረሳኝ! ኢላሂ!… በፍትሃዊው ብዕርህ የከተብከውን የኃጢኣት መዝገብ ሰርዝልኝ! በችሮታህም መልካሙን ሁሉ ፃፍልኝ! ኢላሂ!… ላመሰግንህ ስፈልግ ችሮታህ ዝም ያሰኘኛል! ውለታህን መቁጠር ሳስብ መለኪያው ይጠፋኛል! ኢላሂ!… ካፈቀርኩህ እንዳፈቅርህ ያደረግከኝ አንተው ነህ! ከተንቀሳቀስኩም ያንቀሳቀስከኝ አንተው ነህ! ከረጋሁም ያረጋኸኝ አንተው ነህ! ከዘከርኩህም እንድዘክርህ ያደረከኝ አንተው ነህ! ኢላሂ! በፍቅሬ ውስጥ ‘አንተ’ እንጂ ‘እኔ’ን አስወግድልኝ! እንቅስቃሴዬን ወዳንተ መቅረብ ብቻ አድርግልኝ! መርጋቴን ባንተ መርካት አድርግልኝ! አንተን ማስታወሴን ከመርሳት በኋላ አታድርግብኝ! ❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን 👇👇 https://t.me/Tenshu6793