tgindex
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️

❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️

Статистика

« ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበ ትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ » •••• « ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ •••• ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው‼️ -------------------------------------------

Последний пост
6 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 135
−3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 145
25 постов
Вовлечённость
68,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 6 апр.1 42664

    ✝ ሰሞነ ሕማማት •• ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት ፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። •• በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም •• 👉 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት እንዲሁም •• 👉 ከምሽቱ 1ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት ናቸው:: •• በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ:: •• 👉 #አለመሳሳም አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። •• 👉 #መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም። •• በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። •• የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። •• ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው። •• 📌 የጌታችን ሕማማት የምናስብበት ሳምንት ይሁንልን •• 👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️ •• 👉🏻 https://t.me/Terbinos 👉🏻 https://www.facebook.com/terbinos

  • 6 апр.1 1251

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 апр.1 19612

    ✅ #ሆሳዕና - የዐብይ ጾም #8ኛ ሳምንት። ✅ መጋቢ ሃይማኖት ዶ/ር ዘበነ ለማ ✅ ይህንን ትምህርት ለሌሎችም ያካፍሉ። -- ⭕️ ከታች ያለውን ሊንኩን በመጫን ትምህርቶችና መረጃዎች እንዲሁም ዝማሬዎች በቴሌግራም ሆነ በፌስቡክ መከታተል ይችላሉ ‼️ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ⭕️ Telegram chanal:- https://t.me/Terbinos .. ⭕️ Facebook page :- https://www.facebook.com/terbinos/?modal=admin_todo_tour

  • 9 мар.1 55223

    ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ••• ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን ፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን ፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታች ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡ ••••‌ የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinosy

  • 9 мар.1 25622

    👉 #መጻጉዕ •••• በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው "ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም" አለው። "ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ" ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ "የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ" እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ "በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና "በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ" እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡

  • 23 февр.1 36154

    የልብን ሲያዋዩሽ ሰምተሽ ዝም አትይም(፪) ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም ከአይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሽለታለሽ(፪) ከህዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ(፪) •• ኪዳነ ምህረት እመቤት እመቤት(፪) ነይልን ነይልን ካለንበት (፪) •••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinosy

  • 19 февр.1 403102

    እንደ እድል ሆኖ ያደግኹት በመልአኩ ቤት ነው። ስለ እርሱ በቃል የማይገለጽ ልዩ ፍቅር አለኝ። በሄድኩበት ሁሉ ስሙ ሲጠራ ከሰማኹ አንዳች የደስታ ስሜት ሰውነቴን ውርር ያደርገዋል። "ሚካኤል" ብዬ ያልቀለለ ሸክም፣ ያልተመለሰ ጸሎት የለኝም። አንዳንዴ መልአኩ በጣም ቅርቤ ይመስለኛል። ደግሞ ስለ እርሱ ሳስብ ያሳዝነኛል። ለምን? እንጃ ግን ለእኔ ስለሚያዝንልኝ ይሆናል። ስለ እኔ የሚጨነቅ፣ የሚሳሳልኝ ይመስለኛል። ስለዚህ ያሳዝነኛል። ሚካኤል የዋህ፣ ትሑት፣ ሰውን ወዳጅ መልአክ ነው። ሁልጊዜ ሲዘመር ደስ የሚለኝ መዝሙር አለ •‎• 👉 ነዋ ሚካኤል መልአከክሙ       ይስአል ለክሙ በእንተ ምሕረት ትርጉም:- " እነሆ ሚካኤል መልአካችሁ ምሕረትን ይለምንላችሁ " •‎• 👉 ሚካኤል መልአኬ ፣ ሚካኤል መልአካችን! •‎• ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው! •‎• መልካም የጾም !

  • 16 февр.1 56481

    እግዚአብሔር በዚህ ጾም አልወጣ ፤ አልላቀቅ ያለልን አመላችንን ይንቀልልኔ •‎• ክብር ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሰይጣንን ወግቶ ድል የነሣው በቆሮንቶስ በረሃ ነበር። እንደ አይሁድ ትውፊት ከሆነ ሰይጣንና የክፋት መናፍስቱ ከእጽዋት የተራቆተ በረሃማን ስፍራ ለማደሪያነት ይመርጣሉ። በርግጥም ሕያዋን የሆኑ ጻድቃንን፣ ከውኃ ዳር እንደ ተተከለ ዛፍ የለመለሙ እና ፍሬያማ የሆኑ ቅዱሳንን የማይወድ ሰይጣን፣ ለማደሪያነት የውኃ ምንጭ እና ልምላሜ የሌለበትን በረሃ ይመርጣል ቢባል የሚደንቅ ነገር አይደለም። ይህም በመሆኑ መድኃኒታችን ሰይጣንን አጎሳቁሎ እና አዋርዶ ያሸሸው ሰልጥኖ ከሚኖርበት በረሃ ገብቶ ነው። ዛሬም የቅድስና ምንጭ የደረቀበት፣ ከበጎ ምግባር ተራቁቶ ገላጣ መሬት በመሆን ለሰይጣን ምቹ ማደሪያ የሆነ ሌላ በረሃ በዚህ አለ። ይህም በረሃ ሃይማኖት የሰለለበት፣ የመልካምነት ፍሬም ደርቆ የረገፈበት የእኛ ሰውነት ነው። በቆሮንቶስ በረሃ የነበረውን ፈታኝ ድል የነሣ ጌታ፣ በእያንዳንዳችን ሰውነት መሽገው የተቀመጡትን መናፍስት "ከኋላቸው ሂዱ" ብሎ ገስጾ ከእኛ ያርቅልን። •‎• መልካም የጾም ጊዜ ይሁንልን! •‎• ዲያቆን አቤል ካሳሁን ዘወረደ 2018 ዓ.ም. ••‌•• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinosy

  • 29 дек.2 04014

    እግዚአብሔር ይመሰገን

  • አቤቱ በፍጥረት ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ #ለመድኃኔዓለም_ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ። •• አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ ይምትሆናቸው ለአንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ። •• አቤቱ ነፍስና ሥጋን አዋህደህ በምግባር በሐይማኖት አጽንተህ የምታከብራቸው ለአንተ #ለመድኃኔዓለም_ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ። አቤቱ በመንግሥትህ ሽረት በሕልውናህ ሕልፈት የሌለብህ ለአንተ ለንጉሥ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ። •• አቤቱ የቅዱስ አብ አካላዊ ቃል የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን። / መልክዓ መድኃኔዓለም / ••••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤️ ድንግልን ይዞ ያፈረ የለም ‼️ ••• “ #ድንግል ሆይ ፣ ቅድስት ሆይ ፣ ንጽሕት ሆይ ፣ የተመሰገንሽ ቡርክት ሆይ የድግልናሽ ምስጋና በኹሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዙሪያ ሰፈረ ••• የውቅያኖስ ባሕር በምልአቱ ውሱን ነው የሐኖስም ባሕር በመጠኑ ልክ አለው ፤ ••• ለአንቺ ምስጋና ግን ልክና መጠን ወሰንና መስፈርት ፣ ማለቂያም የለውም አእምሮም አይወስነውም አንደበትም ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም  “  (  አርጋኖን ዘሰኑይ ፰ ÷ ፲ - ፳፰ ) ••••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

  • 👉 ሰንበትን ሊያጸናልን •• የአይሁድ ሰንበት ፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናት ። በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት ፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ) ፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች። ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች። ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት። እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም። እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ •• 👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት •• ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል። በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። " ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ " ( ዮሐ20:29 ) •• የተሣተውን ፤ የተረሳው ፤ የተገደፈውን ፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት •• ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ ! ••••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

  • 👉🏼 እንኳን ለዳግም ትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ‼️ •• ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት ( ሁለተኛ መነሳት ) •• ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ " ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? •• 👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን •• የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። •• ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል። ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ። ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች ( የዳሰሰች ) እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች። እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።

  • ባንች ጠገቡ የቀደሙት ሁሉ በቀን በለሊት ቅድስት ሆይ እያሉ የእንጀራ ቤት ነሽ ሀገረ ሰላም ቤዛዊት ኩሉ ድንግል ቅድስት ማርያም ••• 👉 እናታችን #ቤዛዊት_ማርያም የልባችንን መሻት ትሙላልን ምልጃዋ አይለየን ፤ •••••• ምልጃሽ አይለየን •••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

  • 👉 የምህረት እናት 👉 ኪዳነ ምህረት •• የእውነት እና የህይወት ባለቤት የሆነንን አምላክ ያየንብሽ ሠላምን የወለድሽ የሠላም እናት ኪዳነምህረት የአምላክ እናት የምህረት ቃልኪዳን የድህነታች ምልክት ኪዳነ ምህረት። •• ምልጃሽ አይለየን ••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

  • ‹‹ ቤዛ ›› ማለት ምን ማለት ነው? እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም  ቤዛ ትባላለችን ? ብዙ ጊዜ ድንግል ማርያም እንዴት  ቤዛ ትባላለች ? ይላሉ ፤ በእርግጥ ግን እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናት ።‹‹ ቤዛ ›› በቁሙ ሲተረጐም ዋጋ አለው ወይም ጥቅም አለው ማለት ነው ። እንዲሁም ቤዛ የሚለው ቃል "ቤዘወ"፦ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ቤዛ በቁሙ ሲተነተን እንዲህ ማለት ነው ። ዋጋ ፣ ካሳ ፣ ለውጥ ፣ ምእትክ ፣ ሀላፊ ፣ ዋቢ ፣ ዋሥ ፣ መድኅን ፣ ተያዥ ፣ ጥላ ፣ ጋሻ ... ማለትነው ።ቤዛ በደቂቅ አገባብ ሲፈታ ደግሞ ሥለ ፣ ፋንታ፣ ምክንያት የሚሆንተብሎም ይተረጐማል ። ••• አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መፅሐፍ ሠዋሠው ውግሥ በመዝገበ ቃላት ሐዲሥ 1948 ዓ ም ገፅ 266፡፡ ወይምደግሞ በሌላ መንገድ ከሣቴ ብርሐን ተሠማ መፅሐፋቸው ቤዛ ሲተረጉሙ እንዲህ ብለው አሥቀምጠውልናል ለውጥ ፣ ካሣ ፣ ወይም ደግሞ በአንድ ሠው ላይ መከራና ሞት ተላልፎ መሞትማለት ነው ወይም ታደገኝ ወይም ምትክ ሆነኝ ማለት ነው ወይም ደግሞ ለመከራ ለሞት ለወጠኝ ማለት ነው ወይም ቤዛ ሆነኝ ማለትነው ። የበለጠ ለመረዳት አልያም ቤዛ ሥለሚለው ቃል በደንብ ለማወቅ እነዚህን መፅሐፍቶች መመልከት ይቻላል ። ••• እንደዚሁም ቤዛ የሚለው ቃል ፦ ካሣ ፣ የደም ቤዛ ፣ አንዱ ሠው የሠውንደም ሥለሚያፈሠው ለውጥ ወይም ዋጋን ፣ ገንዘብን ፣ ካሣን መሥጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው ።ከሣቴ ብርሐን 1951 ዓ.ምገፅ 532 ድንግል ማርያምን ስለምን የአለም ቤዛ እንላታለን? የእመቤታችን ቤዛነትም ከላይ በተረዳነው መሠረት ቤዛ ከሚሉት የትርጓሜ ቃላት መካከል ምትክ ፣ ዋሥ ፣ ምክንያት ... ከሚሉት መካከል ምትክ የሚለውን ስንወስድ ድንግል ማርያም የህይዋን (ሔዋን) ምትክ በመሆኗ ነው ፤ ‹ምክንያት› የሚለውን ስንወስድ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው። እግዚአብሔር ለአለም መዳን በድንግል ማርያም ታላቅ ስራን አድርጉአልና ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። የድንግል ማርያም በእምነት መታዘዝ ለዓለም መዳን ምክንያት ሆናለች። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ስለተቤዤ ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። ••• ቤዛ የሚለው ቃል ለሙሴም ተሰጦት እናነባለን። ( የሐዋ ሥራ 7:35) በመልአክ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።እንግዲህ ይህ የፍጡር ቤዛነት የእግዚአብሔርን ቤዛነትይሽራልን? አይደለም፡፡ እንዲያውም ቸር እግዚአብሔርለወዳጆቹ የሚሰጠውን የባለሟልነት ስጦታ ብዛት ይገልፃልእንጂ፡፡ ሙሴ ወገኖቹን ከመጥፋት እንደምን አዳናቸው ( ተቤዣቸው  )( ታደጋቸው )? እንደክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነውን? አይደለም በእግዚአብሔር ዘንድ ‹ይህን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው ፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍኽ እባክኽ ደምሰሰኝ› በማለትየተወደደፀሎቱን በማቅረብእንጂ ( ዘጸ.32፤32 )፡፡ ••• ዳዊትም ‹ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ ›› ሲል የገለፀው ይሄንኑ ነው፡፡ስለዚህም መጽሐፍ የፃድቅ ሰው ፀሎት በስራዋ እጅግ ሃይልን ታደርጋለች ይላል፡፡የእመቤታችንና የድንግል ማርያም ቤዛነት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርሥቶስ ቤዛነት ጋር ያለው ልዩነትእጅግ የሚራራቅ ነው ።ጌታችን በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው ። እንዲሁም በደሙ ዋጅቶ በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው። ቤዛ ማለትእራሥን ሥለሌሎች አሣልፎ መስጠት ማለት ሥለሆነ ጌታችንም ሥለበጐቹ እራሱን አሣልፎ ሠጥቷል ሆኖም የአለም ቤዛ ነው ። ታዲያ የአለምቤዛ ክርስቶስ ከሆነ ድንግል ማርያምስ ቤዛዊት አለም መባሏ ስለምን ነው ቢሉ፦ ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከሞት ወደህይወት ያሻገረበት፣ ሃጢአታችንን ሁሉ የደመሰሰበት ፣ የሚደመስስበትም ክቡር ደሙ ፣ ቅዱስ ስጋው ከእመቤታችን ስለነሳው ነው ፤ በዚህም ክርስቶስ ከመወለዱ አንስቶ በቤተልሄም የከብት ግርግም ተጀምሮ፡ በግብፅ ስደቱ በቀራኒዮ ስቃዩና ሞቱ ሁሉ አብራው አለችና በክርስቶስ የድህነት ስራ ውስጥ የእመቤታችን ስራ ጉልህ ሆኖ ይታያልና ነው፡፡ለማጠቃል ያክል፡- ሙሴ ምክንያት ሆኖ ነጻ ያወጣቸው ለጥቂት ነገዶች ወይም ‹ለእስራኤላውያን› ብቻ በመሆኑ ‹‹ቤዛ›› ብቻ ተብሏል፡፡ •• ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ግን ምክንያተ ድኅነት ሆና ነጻ ያወጣችው ‹ዓለም ሙሉ›ስለሆነ (ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ተሰቅሏልና) ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› ትባላለች፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን ለቅዱሳንም በጸጋ ተሰጥቷል፤ በመጸሐፍየጸጋ አምላክነት ለቅዱሳን ተሰጥቶ እናያለን ‹እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦እይ፥እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌኻለኹ›፤ ክርስቶስየዓለም ብርሃን እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ቅዱሳንንም ‹እናንተየዓለም ብርሃን ናችኹ› በማለት በጸጋ የዓለም ብርሃን እንደሚባሉ መጽሐፍ ምስክርነው ( ዘጸ7፤1 ማቴ 5፤14) የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ነዉ ፤ ክብርና ምሥጋና ለቤዛዊት አለም ለእመቤታችን ለቅድሥት ድንግልማርያም ይሁን አሜን። ••••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

  • በመጸሐፍ ቅዱስ ቤዛ ማነው? ቃሉ የዋለው ለኢየሱስ ብቻ ነው ? ወይስ እንደ አገባብ ይተረጎማል? ••• 1ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ብር ቤዛ ነው “አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።”ዘጸአት 30፥12 ••• 2ኛ- በመጽሐፍ ቅዱስ ሀብት ቤዛ ነው “ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።” ምሳሌ 13፥8 ••• 3ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ኅጥእ እና በደለኛ ሰው ቤዛ ተብሏል “ ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው ፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።” ምሳሌ 21፥18 ••• 4ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ አገር ቤዛ ተብሏል “ እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።” ኢሳይያስ 43፥3 ••• 5ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ መሪ ቤዛ ተብሏል “ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን ፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው። ” ሐዋርያት 7፥35 ••• 6ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ቀን ቤዛ ተብሏል “ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ”  ኤፌሶን 4፥30 •••

  • 👉 እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️ 👉 Baga ayyaana Du'aa Ka'u Kiristosin nagaan gessan!‼️ 👉 እንኳዕ ንበዓል ትንሳኤ ኣብፀሓኩም‼️ •• ዛሬ .... " ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ " 1ኛ  ቆሮ 15፣54 •• 👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️ ••••••• የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️ — tgindex