Useful Talks 🇪🇹
СтатистикаDaily motivation | Success mindset | Life-changing wisdom https://telega.io/c/UsefulExpression
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 540
- 1/48двое суток
- 618
- 1/72трое суток
- 667
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
አንድ አባት በግ አረደና ልጁን እንዲህ አላት። "ወጥተሽ ጓደኞቼንና ጎረቤቶቼን ጥሪልኝ መጥተው አብረውን ይደሰቱ ማዕድ እንካፈል!" ልጅቱም ወጣች ነገር ግን ወደ ሰፈሩ ስትደርስ "እባካችሁ እርዱኝ! አባቴ በጠና ታሟል ወደ ሕክምና ልንወስደው ነው፤ ድረሱልን!" ብዙ ሳይቆይ ጥቂት ሰዎች በድንጋጤና በጭንቀት እየሮጡ ወደ ቤቱ ደረሱ። አባትየው የመጡትን ሰዎች ሲመለከት ግራ ተጋብቶ ልጁን ጠየቃት "ለመሆኑ እነዚህ የመጡት ሰዎች የማን ናቸው? የት አሉ። ጎረቤቶቼ? የት አሉ። ጓደኞቼ?" ልጅቱም "አባቴ እውነተኛ ወዳጆቻችንና አብረናቸው ማዕድ ልንጋራ የሚገቡን ሰዎች እነዚህ ናቸው! በደስታህ ጊዜ የሚሰበሰቡት ሳይሆኑ በችግርህ ጊዜ ከጎንህ የሚቆሙት እውነተኛ ወዳጆችህ ናቸው!" አለች። በደስታህና በግብዣህ ጊዜ ከጎንህ የሚሰበሰቡት ሁሉ እውነተኛ ወዳጆችህ አይደሉም። እውነተኛ ወዳጅ ማለት አብሮህ የሚስቅ ሳይሆን፣ በጭንቅህ ቀን ከጎንህ የሚቆም ነው... 🙏🙏🙏🙏🙏
..🤔
በደረሰብህ መገፋት አትዘን፤ ይልቁንም ሁሌም እንዴት ውደፊት መራመድ እንደምትችል አሰላስል። ግለሰቡ እህያውን ለዘመናት ተገልግሎበታል። አሁን ግን እህያው በዕድሜ በመግፋቱ ሁለት ችግሮች ተፈጠሩ። በመጀመሪያ አቅሙ ስለደከመ ዱሮ የሚሸከመውን ያህል መጫን እልተቻለም። በዚያ ላይ ፍጥነቱ እጅግ ቀስስተኛ በመሆኑ ብዙ ሰዓት አየፈጀ ነው። ስለዚህ ግለሰቡ ሌላ አህያ ለመግዛት ማሰቡ ግድ ነበር። ያዘገየው በቂ ገንዘብ እጁ ላይ አለመኖሩ ብቻ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ አንድ ቀን አህያው ከነሸክሙ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀ። ባለቤቱም ያሸከመውን ዕቃ ለይቶ ከጉድጓዱ ካወጣ በኋላ አህያውን ለመጎተት ሞከረ። ግን ጥቂት እንደጣረ አንድ አሳብ መጣለት። አህያው ያረጀ እንደመሆኑና ሌላ ሊገዛ እንደማሰቡ መጠን አሁን እሱን ለመጎተት በ መሞከር አቅሙን መጨረሱ አስፈላጊ አይደለም። ስለዚህ እዚያው ትቶት ሊሄድ ወሰነ። ግን ደግሞ ብዙ ዓመት አገልግሎታልና የእውሬ እራት ከሚሆን ይልቅ ጉድጓዱን በአፈር ሞልቶ በቁሙ ሊቀብረው ፈለገ። ስለዚህ ጥቂት ግለሰቦችን ለምኖ አፈር በአካፋ እየዛቁ ወደ ጉድጓዱ መወርወር ጀመሩ። አህያው ለዘመናት አገልግሎቱ የተሰጠው ምላሽ ከነሕይወቱ መቀበር መሆኑን ሲያይ በጣም አዘነ። ግን አዝኖ አልቀረም። በበኩሉ አንድ መላ መታ። ይኸውም አቧራውን ማራገፍ የሚል ነበር። አናም አንድ አካፋ በተወረወረበት መጠን እርሱም እላዩ ላይ የሚያርፈውን ማራገፍ ጀመረ። ያ ደግሞ አስደናቂ ውጤት አመጣ። ጉድጓዱ በሞላ መጠን እህያውም ከፍ ማለት ጀመረ። በመጨረሻም ጉድጓዱ በእፈር ሲሞላ አህያው ተራምዶ መውጣት ቻለ። 🙏🙏🙏🙏🙏
..🤔
...😀
1. ‹‹ደስተኛ ለመሆን መርሁ፡- የምትሠራው ሥራ፣ የምታፈቅረው ሠው፤ ተስፋ የምታደርገው ነገር ሲኖርህና እነዚህን መመሪያዎች ስትተገብር ነው፡፡›› 2. ‹‹ደስታ ከምክንያታዊነት ጋር የሚስማማ ሳይሆን ከምናብ ጋር የሚዋሃድ ነው፡፡›› 3. ‹‹ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡ ምክንያቱም ትክክል ስለሆነ፡፡›› 4. ‹‹ሳይንስ ዕውቀትን፤ ጥበብ ደግሞ ሕይወትን ያደረጃል፡፡›› 5. ‹‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡›› 6. ‹‹ልምድ ንድፈሃሳብ ከሌለው እውር ነው፡፡ ነገር ግን ንድፈሃሣብ ራሱ ልምድ ከጎደለው እንደው ዝምብሎ የምሁር ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡›› 7. ‹‹የሠው ልጅ በሠውነቱ ያገኘውን ክብርና ማዕረግ በውሸት ድምጥማጡን ያጠፋዋል፡፡›› 8. ‹‹ሁሉም ዕውቀቶቻችን ከስሜቶቻችን ጀምረው በመረዳት ቀጥለው በምክንያት ያበቃሉ፡፡ ከምክንያት በላይ ምንም የለምና፡፡›› 9. ‹‹ዘላቂ ሠላም የሚገኘው መካነ መቃብር ውስጥ ብቻ ነው፡፡›› 10. ‹‹ለማሠብ ድፈር! የራስህን አዕምሮ ለመጠቀም ብርታት ይኑርህ፡፡›› 11. ‹‹ነፃነት ማለት የሠው ልጅ በመወለድ ያገኘው ተፈጥሯዊ መብቱና በሰብዓዊ ሃይሉ የሚጎናፀፈው የግል ሐብቱ ነው፡፡›› 12. ‹‹ብልሕነት ልትማረውም ሆነ ልታስተምረው የማትችለው ተሠጥኦ ነው፡፡›› 13. ‹‹የፍርድ ጉድለት ሌላ ስሙ ድድብና ነው፡፡ በዚህ ፍርድ ጉድለት ምክንያት የሚመጣ ውድቀት ምንም መፍትሄ እንደሌለው እናውቃለን፡፡››
ታዋቂው የምጣኔ ሀብት (Economics) አባት በመባል የሚታወቀው አዳም እስሚዝ እንዲህ ይላል፦ "አንድን ሀገር ከከፋ ድህነት ወደ ላቀ ብልፅግና ለማሸጋገር ሰላም፣ ዝቅተኛ ግብር እና ፍትሃዊ የሕግ አስተዳደር ብቻ በቂ ናቸው፤ ሌላው ሁሉ በተፈጥሯዊ የነገሮች ሂደት የሚከናወን ነው።" ይህ አባባል በጥቂት ቃላት ውስጥ ትልቅ የኢኮኖሚ ፍልስፍናን ይዟል። አዳም እስሚዝ እንደሚያስረዳው፣ አንድ ሀገር እንዲያድግ በመጀመሪያ የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ሁኔታዎች ሰላም፣ የሰዎችን የሥራና ንግድ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ግብር፣ እንዲሁም ለሁሉም እኩል የሚተገበር ፍትሃዊ የሕግ አስተዳደር ናቸው። እነዚህ ሦስት መሠረቶች ከተሟሉ በኋላ ሰዎች በነፃነት ይሰራሉ፣ ያመርታሉ፣ ይነግዳሉ፣ ኢንቨስት ያደርጋሉ፣ ሀብት ይፈጥራሉ፤ ኢኮኖሚውም በተፈጥሯዊ ሂደት ያድጋል። በሌላ አነጋገር፣ መንግሥት ከእነዚህ መሠረታዊ ሁኔታዎች በላይ የሕዝቡን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ መቆጣጠር ሳያስፈልገው፣ ሕዝቡ ራሱ የኢኮኖሚ እድገት አንቀሳቃሽ ኃይል ይሆናል የሚል እምነት ነው። ይህ ሀሳብ ከተነገረ መቶዎች ዓመታት ቢያልፉም፣ እስካሁን ድረስ በዓለም የኢኮኖሚ ውይይቶች ውስጥ ተጠቃሽ ሆኖ ይቀጥላል። 🙏🙏🙏🙏🙏
ወይ ጥረትህን ጨምር ወይ ፍላጎትህን ቀንስ በዚ ኑሮ ..🤔
#ለሷ ብለህ_ማድረግ የሌለብህ 6 ነገሮች🤝 1,#ራስን መቀየር፡ ፍቅርን ለማግኘት ብለህ ማንነትህን አትቀይር። 2,#ክብርን ማጣት፡ እሷን ለማስደሰት ብለህ ራስህን ዝቅ አታድርግ። 3,#ጓደኛና ቤተሰብን መተው፡ ከሚወዱህ ሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት አታቋርጥ ከፈለገች እሷ ትቅር😎 4,#የገንዘብ ጫና ውስጥ መግባት፡ ለማስመሰል ብለህ እዳ ውስጥ አትግባ። 5,#ዓላማህን መረሳት፡ ህልሞችህን ትተህ ትኩረትህን በእሷ ላይ ብቻ አታድርግ! ካንተ የተሻለ ስታገኝ ትታህ መሄዷ አይቀርም so አትሸወድ። 6,#ሁልጊዜ ይቅርታ መጠየቅ አቁም ጥፋተኛ ሳትሆን ይቅርታ አትጠይቅ እንደ አማራጭ ነዉ ምትታየዉ።
"ዋንጫውን የሸጥኩት ቁምሳጥኔ ጠቦኝ ነው" — ቤንጃሚን ሜንዲ 🏆😲 የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ቤንጃሚን ሜንዲ በ2018 ያሸነፈውን የዓለም ዋንጫ ምስለኔ (replica) በ54,000 ዩሮ ገደማ በጨረታ መሸጡ አነጋጋሪ ሆኗል። ድርጊቱ በደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ያስከተለበት ሲሆን፣ ሜንዲ ግን ለተሰነዘሩበት ትችቶች በቀልድ የታጀበ ምላሽ ሰጥቷል፡ "ለመሆኑ ዋንጫው የእኔ ነው ወይስ የእናንተ? የራሴ በመሆኑ በፈለግኩት መንገድ የማድረግ መብት አለኝ፤ ደግሞም በቁምሳጥኔ ውስጥ አላስፈላጊ ቦታ አጥቦብኝ ነበር!"
✅
ከምእራብ በሪሊን ምስራቅ በርሊን ኮንትሮባንድ እያመላለሰ የሚሸጥ ነጋዴ ነበር፡፡ ለንግድ ሲመላለስ በሳይክል እየጋለበ ጀርባዉ ላይ ቦርሳ አዝሎ ነበር ቦርሳዉ ዉስጥ ደግሞ አሸዋ ሁል ጊዜ ይይዛል፡፡ ልክ ኬላዉ ጋር ሲደርስ ፖሊሶች ያስቆሙትና ቦርሳዉን ከፍተዉ ሲያዩ አሸዋ ብቻ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ፈታሽ፡ ስማ አንተ ሁልጊዜ ቁንጥር አሸዋ ይዘህ የምትዞረዉ ለምንድነዉ? ነጋዴዉ፡ አይ የአሸዋ ምርምር ስራ ስለምሰራ ለዛ ነዉ አሸዋ የምይዘዉ ፈታሽ፡ ያንተ ምርምር ደግሞ ኤጭ! ሃሳብህ አሸዋን ወደወርቅ ለመለወጥ ይመስላል፡፡ በል እለፍ! እሱም ሁልጊዜ ኬላዉን እንዳለፈ አንድ ቀን እንኳን የያዘዉ አልነበረም፡፡ ፖሊሶቹ ያላወቁት ነገር ሰዉየዉ 'ተመራማሪ ሳይሆን ሳይክል ነጋዴ' ነበር፡፡ ሁልጊዜ አዳዲስ ሳይክል ይዞ እየነዳ ያልፍ ነበር፡፡ ሰዎች የሚመለከቱት ማየት የሚፈልጉትን ወይም የሚጠረጠሩትን ነገር ብቻ ነዉ፡፡ ከዛ ዉጪ ስላለዉ ነገር ማሰብ አይፈልጉም፡፡ ስለዚህ የሰዎች የልብ ትርታ በሚያርፍበት ነገር ላይ ማንነትህን አትገላልጥ..🤔
ያስታመመ ሲቀብር ብዙ አያለቅስም...🤔
በገንዘብ ምክንያት ያላጣችሁት ነገር ...🤔
#የጀግንነት_መገለጫዎች 1. ድፍረትና ፍርሃትን ማሸነፍ ለእውነትና ለፍትሕ መቆም፡ ምንም እንኳን ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም፣ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ከመንቀሳቀስ አለመመለስ። ፍርሃትን ተጋፍጦ መስራት፡ ጀግንነት ማለት ጨርሶ አለመፍራት ሳይሆን፣ ፍርሃትን ተቆጣጥሮ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት ነው። 2. ሰዋዊነትና መስዋዕትነት ራሱን ለሌሎች አሳልፎ መስጠት፡ የራሱን ምቾት፣ ጥቅም ወይም ሕይወት ለወገን፣ ለሀገር ወይም ለደካሞች ደህንነት ሲል አደጋ ላይ መጣል። ርኅራኄና ደግነት፡ ጉልበትንና ጥበብን ደካሞችን ለመጠበቅና ለመርዳት እንጂ በደካሞች ላይ ለመጨከን አለመጠቀም። 3. ፅናትና እልህ (Resilience) በፈተና አለመሸነፍ፡ ታላላቅ ውድቀቶች፣ መሰናክሎች ወይም መከራዎች ሲገጥሙ ተስፋ ሳይቆርጡ እንደገና ተነስቶ መታገል፤ እስከ መጨረሻው መፅናት። ጽኑ ዓላማ ያለው መሆን፡ በግልጽ የተቀመጠ መልካም ግብ እና ራዕይ ኖሮት ለዚያ ስኬት በቁርጠኝነት መስራት። 4. ታማኝነትና የሞራል ጥንካሬ ለእምነትና ለቃሉ ታማኝ መሆን፡ ጥቅም ወይም ማስፈራሪያ ሲመጣ መبادኦቹን (Principles) አለመሸጥ። ኃላፊነትን መቀበል፡ ለስህተትና ለውሳኔዎች ሙሉ ኃላፊነት የመውሰድ ድፍረት ማሳየት። 5. ጥበብና አስተዋይነት ትክክለኛ ውሳኔ በወሳኝ ጊዜ፡ በውጥረትና በጭነቶች ውስጥ ሆኖ የተረጋጋና አቅጣጫ አመላካች የሆነ ውሳኔ መስጠት። አርቆ አስተዋይነት፡ ከጊዜያዊ ስሜት ወጥቶ የረጅም ጊዜ በጎ ተፅዕኖ የሚያመጡ ነገሮችን ማከናወን። ✅ጀግንነት በጦር ሜዳ በሚደረግ ተጋድሎ ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፤ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ለእውነት በመቆም፣ ሰዎችን በመርዳት፣ በሚገጥሙ ፈተናዎች ባለመሸነፍና ለበጎ ዓላማ በመፅናት የሚታይ ታላቅ የሰብዕና ከፍታ ነው።
ክረምት vs ኑሮ እንዴት ይዟችኋል..?
አእምሯችን በየቀኑ ሳናውቀው የሚሸውደን 7 የስነ-ልቦና እውነታዎች! ብዙዎቻችን የምንወስዳቸው ውሳኔዎች በሙሉ በበሰለ እሳቤና በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረቱ ይመስሉናል። ነገር ግን አእምሯችን ጉልበትና ኤነርጂ ለመቆጠብ ሲል በየቀኑ ሳናስበው በሚከተሉት 7 ዘዴዎች ይመራናል፦ 1. የመጀመሪያ እይታ ተፅዕኖ፦ ሰዎችን ባየን በሰከንዶች ውስጥ አእምሯችን ስለነሱ ታሪክ ይፈጥራል። ከዚያም ያላንን የመጀመሪያ ግምት ትክክል ለማስመሰል የሚደግፉ መረጃዎችን ብቻ መፈለግ ይጀምራል። 2. የምናምነውን ብቻ ማስተዋል፦ አዲስ መኪና ስትገዙ ተመሳሳይ መኪኖችን በመንገድ ላይ በብዛት ማየት ትጀምራላችሁ? መኪኖቹ ቀደም ብለውም ነበሩ፤ ነገር ግን አእምሯችሁ ትኩረት መስጠት የጀመረው አሁን ነው። 3. በፍርሃት መመራት፦ አእምሯችን ለደህንነታችንና ለህልውናችን ቅድሚያ ስለሚሰጥ፣ 10 ሰዎችን ቢያመሰግኑንና 1 ሰው ቢነቅፈን፣ ትኩረታችን ሙሉ በሙሉ የሚያርፈው በተነቀፍንበት ነገር ላይ ነው። 4. ትዝታ የተቀረፀ ቪዲዮ አይደለም፦ የማስታወስ ችሎታችን እንደተቀረፀ ቪዲዮ አይሰራም። አንድን ነገር በስታወስን ቁጥር አእምሯችን ታሪኩን እንደገና የሚገነባው ሲሆን፣ በሂደትም ትንሹ መረጃ ሊቀየር ይችላል። 5. አለመረጋጋትንና እርግጠኛ አለመሆንን መጥላት፦ አእምሯችን እርግጠኛ ያልሆነ ነገርን ስለሚጠላ፣ ሙሉ በሙሉ መልስ ከማጣት ይልቅ የተሳሳተም ቢሆን መልስ መያዝን ይመርጣል። 6. ውሳኔዎችን በስሜት መወሰን፦ አብዛኞቹን ውሳኔዎቻችንን በቅድሚያ የምንወስነው በስሜት ነው፤ ከዚያ በኋላ ነው ምክንያታዊ ለመሰል አእምሯችን ማብራሪያ የሚፈልገው። 7. ለራሳችን የምንነግረው ታሪክ ማንነታችን ይሆናል፦ "እኔ ጎበዝ አይደለሁም" ወይም "እድል የለኝም" እያላችሁ ለራሳችሁ በደጋጋማችሁ ቁጥር አእምሯችሁ እንደ እውነት አድርጎ ይቀበለዋል። እነዚህን የስነ-ልቦና ህጎች መረዳታችን የተሻለ ውሳኔ እንድንወስድና ህይወታችንን በተሻለ መልኩ እንድንመራ ይረዳናል። ከእነዚህ ውስጥ የእርስዎን አእምሮ በብዛት የሚያታልለው የትኛው ነው? አስተያየትዎን በኮመንት ያጋሩን! ምንጭ፦ አሜሊ ጃፍሰን
...🤔