tgindex
AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴🇮

AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴🇮

Статистика

Spreading Ethnographic and Historical Truth.

Последний пост
30 янв.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
14 687
−14 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,01%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
3 482
20 постов
Вовлечённость
23,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10. ፊያሜታ ጊላይ= ፊዮሪላ (ይሁንና በእርሷ እና በጸጋዬ ሃይለማርያም መካከል የነበረው የፍቅር ግንኙነት ልብ ወለድ ነው)። * ስለኦሮማይ ይህንን ብያለሁ፡፡ ወደፊት አዲስ ነገር ከተገኘ መመለሴ አይቀርም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጽሑፍ አንብበው ብዙ ማስተካከያ የሰጡኝን ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስን አመሰግናቸዋለሁ (በዓሉ በኦሮማይ ምክንያት መሞቱን ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፉትም እርሳቸው ናቸው)። ሰላም! ---- አፈንዲ ሙተቂ ሸገር-አዲስ አበባ መጀመሪያ ጥቅምት 4/2006 ተጻፈ። እንደገና ታርሞ ጥቅምት 13/2013 ተጻፈ። ------ @Afendi Muteki, October 2020 ---- የቴሌግራም ቻናሌ የሚከተለው ነው። You may join my telegram channel here. https://t.me/afandishaHarar

  • ጋዜጠኛው በዚህ አባባል ተናዶ “ስብሰባው ላይ ምን ዘጋህ? ቅድም እንዲህ ብለህ አትናገርም ነበር፡፡ መድረኩ ለማንም ክፍት ነበር፡፡ማን ከለከለህ?” ሲለው መጽሐፈ ዳንኤል “ትቀልዳለህ ልበል?” በማለት በአጭሩ መልሶለታል፡፡ መጽሐፈ ልክ ነው፡፡ አንድ ሰው በሚፈልገው መንገድ ብቻ መደስኮር በሚፈቀድበት ስብሰባ ሐቁን እናገራለሁ ቢል የሚደርስበትን ቅጣት በደንብ ያውቀዋል፡፡ ለዚህም ነው በስብሰባና በጉባኤ ፊት እያስመሰሉ መለፍለፍ እና ለክፉ አሳልፎ የማይሰጥ ወዳጅ ሲገኝ ሐቁን መናገር የዘመኑ ወግ ሆኖ የቆየው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሰለሞን በትረ-ጊዮርጊስ የተባለው ገጸ-ባህሪ የያኔውን የፕሮፓጋንዳ አካሄድ እስኪበቃው ድረስ ሲወርፍ ይታያል፡፡ “እናንተ ጋዜጠኞች ጭንቀታችሁ ሁሉ ስታቲስቲክስ ነው፤ ይህን ያህል ሄክታር መሬት ታረሰ፤ ይህንን ያህል ህዝብ ተደራጀ፤ ይህን ያህል ሰዎች ከመሀይምነት ተላቀቁ፤ ነው የምትሉት፡፡ እንዲያው ወሬአችሁ ሁሉ ስታቲክቲክስ ነው፤ ዘገባችሁ ሰው ሰው አይሸትም፤ ሾለ አሐዝ ስትጨነቁ ሰው ትረሳላችሁ” ይላል (ኦሮማይ ገጽ፤ 67)፡፡ እነኝህን የመሳሰሉ የስርዓቱን ጉድፍ የሚያሳዩ በርካታ አንቀጾችን መልቀም ይቻላል፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ የመጨረሻ ግብ ናቅፋ የሚገኘውን የሻዕቢያ ዋና የዕዝ ማዕከል መቆጣጠር ተደርጎ ይታሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ናቅፋ በቀላሉ የምትደፈር ሆና አልተገኘችም፡፡ ሺዎች እንደ ቅጠል ረግፈዋል፡፡ ሺዎች ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል፡፡ ሁኔታውን በቅርበት የታዘበው ጋዜጠኛ ጸጋዬ ኃይለማሪያም ጦርነቱ ከኪሳራ ውጪ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ተገንዝቧል፡፡ ከናቅፋ ወደ አፍአበት ሲመለሾ “አይዞን! ገና ሺህ ናቅፋዎች ይጠብቁናል” ብሎ ለተናገረው ባለስልጣን “እኔ አንድ ናቅፋ ከወዲሁ በቅቶኛል፤ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ከአሁን በኋላ ላለማየት ቆርጫለሁ” በማለት ተቃውሞውን ገልጿል (በዓሉ ጦርነቱን ከተቃወመባቸው ዐረፍተ ነገሮች መካከል ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ይህኛው ነው)፡፡ * “ኦሮማይ” ፈርጀ ብዙ የዕውቀት ድርሳን ነው፡፡ ረጅምና ውስብስብ የሆኑ እውነተኛ ታሪኮችን እጥር ምጥን አድርጎ በቀላሉ ያስነብበናል፡፡ ለምሳሌ የኤርትራ ችግር መሰረታዊ ምንጭ ምን እንደሆነ መረዳት የሚፈልግ ሰው ከሰለሞን በትረጊዮርጊስ ታሪካዊ ትንተና ብዙ ቁምነገሮችን ይጨብጣል (ኦሮማይ፡ ገጽ 78-86)፡፡ እንግሊዝ በኤርትራ ምድር የቀበረችው ፈንጂ፤ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለመቀላቀል የተደረገው ጥረት፤ የጀብሃና ሻዕቢያ አነሳስና በመካከላቸው የተፈጠረው ፍጭት፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት ኤርትራን ከአማጺያን ለማጽዳት ያደረገው ዘመቻ ወዘተ… በሰለሞን አንደበት በሰፊው ተተንትነዋል (እርግጥ ትንተናው ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ለማለት አይቻልም፤ ግማሽ ያህሉ የደርግ መንግሥት በሚፈልገው መልክ የተቀናበረ ነው)፡፡ የጎሪላ እና መደበኛ የውጊያ ስልትን በተነጻጻሪ ማወቅ የሚፈልግ ሰው ከኦሮማዩ ኮሎኔል ታሪኩ ወልዳይ ትንታኔ ብዙ ነገሮችን ይማራል፡፡ ኮሎኔል በትሩ ተሰማ እና አጋዥ ቡድኑ (እነ ተክላይ ዘድንግል ያሉበት) የዘመኑ የኢንተሊጀንስ ጥበብና ስልት ምን ይመስል እንደነበር በቃልና በድርጊት ያሳዩናል፡፡ ጋዜጠኛው ጸጋዬ ኃይለማሪያም አስቸጋሪውን የናቅፋ ተራሮች የመሬት አቀማመጥ ለዓይናችን ወለል ብሎ እስኪታየን ድረስ በማይሰለቸው ብዕሩ እያጣፈጠ ይተርክልናል፡፡ ስዕላይ ባራኺ እና ጓዶቹ ደግሞ የሚያስገርሙ ጀብዶችን እየተገበሩ ሻዕቢያ በሰርጎ ገቦቹ አማካኝነት አስመራን እንዴት ያሸብራት እንደነበር ያሳዩናል፡፡ የአስመራ ነዋሪዎች የአኗኗር ወግና ማሕበራዊ ህይወት፣ የከተማዋ ታዋቂ ሰፈሮችና ሆቴሎች፤ የመንገዶቹ ውበትና አቀማመጥ ወዘተ… በመጽሐፉ ዘርዘር ብለው ተጽፈዋል፡፡ በኔ እይታ አንድ ሰው ልብ ወለድ ተብሎ የተጻፈውን “ኦሮማይ”ን ቢያነብ ከአምስት መጻሕፍት የሚያገኘውን ዕውቀት ሊገበይ ይችላል፡፡ * እንደዚያም ሆኖ ግን “ኦሮማይ” ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ አይደለም፡፡ ደራሲው የመጽሐፉን ተነባቢነት ለማጉላት ምናባዊ ገጸ-ባህሪዎችንና ታሪኮችን ጨማምሯል፡፡ ለምሳሌ ደራሲው የሁለት ሰዎችን ታሪክ አዳብሎ “ስዕላይ በራኺ” የተባለ ገጸ-ባህሪ ፈጥሮልናል፡፡ እንደዚሁ ደግሞ በመጽሐፉ ውስጥ የሻዕቢያ ሰዎች በዚሁ ስዕላይ በራኺ በተባለ ገጸ-ባህሪ መሪነት የሚያካሄዱት “ኦሮማይ” የተሰኘ ስውር ኦፕሬሽን የደራሲው ፈጠራ ነው (“ቢሮክራሲ” የተባለው የስለላ ኔትወርክ ግን ትክክለኛ ነው)፡፡ ከኦሮማይ ገጸ-ባህሪያት መካከል ኮሎኔል መንግሥቱ ሀይለማሪያምና ኢሳያስ አፈወርቂን የመሳሰሉት በእውነተኛ ስማቸው ተጠቅሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ስም የለሽ ሆነው በድርጊታቸው ብቻ ተገልጸዋል (ለምሳሌ “የቀይ ኮከብ ሁለገብ ዘመቻ ዋና ጸሐፊ” ተብለው በስራ መደባቸው ብቻ የተጠቀሱት ባለስልጣን አቶ አማኑኤል አምደሚካኤል ናቸው)፡፡ ከፊሎቹ ገጸ-ባህሪያት በእውነታው ዓለም የሚታወቁበት ስም በመጽሐፉ ውስጥ ተቀይሯል፡፡ ከነርሱ መካከል የጥቂቶቹ ትክክለኛ ስም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ 1. ኮሎኔል በትሩ ተሰማ= ኮሎኔል ግርማ ወልደማሪያም (የህዝብና ደህንነት ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር፣ አንዳንዶች "ኮሎኔል በትሩ ተብሎ የተሰየመው የደህንነት ሚኒስትሩ ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ" ነው ቢሉም እውነታው ይህ ነው)። 2. ኮሎኔል ታሪኩ ወልዳይ= ጄኔራል መስፍን ገብረቃል (በኤርትራ የተወለዱ የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ጄኔራል፣ በደርግ የመጨረሻ ዘመናት ም/ኤታማዦር ሹም የነበሩ። ይህንን መረጃ የሰጡን ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ናቸው። አንዳንዶች "ኮሎኔል ታሪኩ ማለት የአንበሳው ሶስተኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው ኮሎኔል ተሻገር ይማም ነው" ይላሉ)። 3. መጽሐፈ ዳንኤል= ዶ/ር ዳንኤል ክንዴ (ታዋቂ ኢኮኖሚስት፣ አሁን በአሜሪካ ሀገር የዩኒቨርሲቲ መምህር) 4. የሺጥላ ማስረሻ= አቶ ሽመልስ ማዘንጊያ (የኢሠፓ የፖሊት ቢሮ አባልና የርዕዮተ ዓለም ጉዳዮች ሃላፊ የነበሩ) 5. ጸጋዬ ሀይለማሪያም= የበዓሉ ግርማ ግርማ እና የቴሌቪዥን ጋዜጠኛው የጌታቸው ኃይለማሪያም ቅልቅል ይመስላል፡፡ 6. ተድላ ረጋሳ= ሻለቃ ፍሰሓ ገዳ (የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደርግ መንግሥት የፕሮቶኮል ሹም) 7. ሰለሞን በትረ ጊዮርጊስ= ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ (በቀይ ኮከብ ዘመን የኤርትራ ክፍለ ሀገር ኢሠፓአኮ ተጠሪ እና የክፍለ ሀገሩ የበላይ አስተዳዳሪ፣ በኋላም የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ በ1978 ከደርግ መንግሥት ተነጥለው ወደ ውጪ ሀገር የሄዱ) 8. ስዕላይ ባራኺ= የሁለት ሰዎችን ታሪክ በመቀላቀል የተፈጠረ ነው፡፡ አንደኛው ተስፋሚካኤል ጆርጆ ነው (አቶ ተስፋሚካኤል በሀይለስላሴ ዘመን የደቀምሐረ ወረዳ ገዥ ነበሩ)። ሁለተኛው ሰው ተክላይ ኣደን ይባላል (ተክላይ ኣደን "የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ" ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የድርጅቱ የጸጥታ ክፍል ሃላፊ ነበር፤ በኋላ ለደርግ መንግሥት እጁን ሰጥቶ በሀገር ውስጥ ሲኖር ከቆየ በኋላ ደርግ ሲወድቅ ወደ አውሮጳ ሄዷል)፡፡ 9. “ቢሮክራሲ”= አፈወርቂ ተወልደ መድሕን (ደሴ የተማረ የሻዕቢያ የውስጥ አርበኛና ሰላይ፣ “ቢሮክራሲ” በሚል ስም የሚታወቀውን የስለላ ኔትወርክ የሚመራው እርሱ ነው ይባላል)።

  • ኦሮማይ እና በዓሉ ግርማ ------ ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ ------ ይህንን ጽሑፍ ከዚህ በፊት ለጥፌው ነበር። ዛሬም ወቅታዊ ሆኖ በመገኘቱ በድጋሚ ለጥፌዋለሁ። ------ ኦሮማይ ከልቡ መጽሐፍ ነው፡፡ በአማርኛ ልብ-ወለድ መጻሕፍት (Novel) ታሪክ በጣም አነጋጋሪውና አከራካሪው መጽሐፍ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ፍቅር ካልተነፈጋቸው ጥቂት መጻሕፍት አንዱም ነው፡፡ በህይወቴ ብዙ ጊዜ እየደጋገምኩ ካነበብኳቸው መጻሕፍት መካከልም በመጀመሪያው ረድፍ ይሰለፋል፡፡ ይሁንና ሰዎች ለዚህ መጽሐፍ ያላቸው አድናቆት እንደየ አመለካከታቸው ይለያያል፡፡ መጽሐፉ የብዙዎቹን አትኩሮት የሳበው ታሪኩ እውነት ነው ስለተባለ እና በመጽሐፉ ሳቢያም የደራሲው ህይወት ለአደጋ በመጋለጡ ይመስለኛል፡፡ ከመጽሐፉ ዐቢይ ገጸ-ባህሪያት አንዱ የሆኑት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ “የደም እምባ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ተመሳሳይ እይታ አንጸባርቀዋል፤ እንደ ሻለቃ ዳዊት አባባል ኦሮማይ ባይታገድ ኖሮ ተወዳጅነቱ ይሄን ያህል አይገዝፍ ነበር፡፡ ሆኖም እኔ በዚህ አባባል አልስማማም፡፡ ደራሲው ባይሞት እና ታሪኩ እውነተኛ ባይሆን እንኳ “ኦሮማይ” ተደናቂ የመሆንን እድል አያጣም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህም በርካታ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ “ኦሮማይ” በቅድሚያ ቀልብን የሚስበው በአጻጻፍ ብሂሉ ነው፡፡ ደራሲው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አጫጭር ዐረፍተ ነገሮችን ይጠቀማል፡፡ ይህም አንባቢው የመጽሐፉን የትረካ ቅደም ተከተል ሳይስት ድርሰቱን ያለድካም እንዲያጣጥም ያግዘዋል፡፡ ደራሲው ጠጣር ሃሳቦችን በቀላሉ ይዘረዝራል፡፡ የዘመኑ መንግሥት አሰራርን ለተደራሲው በሚገባው ቋንቋ ቀለል አድርጎ ያስረዳዋል፡፡ በሌላ በኩል መጽሐፉ ኪናዊ ውበቱን እንዳይስት ደራሲው በእጅጉ ተጠቧል፡፡ ዘይቤአዊ አባባሎችን ከዘመኑ የአነጋገር ፋሽን ጋር እየቀላቀለ አንባቢውን ያዝናናዋል፡፡ በተለይም “ኦሮማይ” ፈጠራ እየነጠፈ በዘመቻ ግርግር እና በንድፈ-ሓሳብ ዝብዘባ የሚፈበረኩ ቃላት የድርሰቱን ጎራ እያጠለሹ በመጡበት ዘመን አንባቢው በማይሰለቸው የቋንቋ ጥበብ የተጻፈ በመሆኑ የደራሲውን ልዩ ተሰጥኦ በጉልህ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ኦሮማይ የዚያ ዘመን ድርሰት ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመንም እንኳ ተደግመው ሊጻፉ ከማይችሉ ድርሰቶች መካከል ሊመደብ ይችላል፡፡ ይበልጥ አስደናቂው ነገር ደግሞ ወዲህ ነው፡፡ ደራሲው ያንን ውብ መጽሐፍ የጻፈው በጥቂት ወራት ውስጥ ነው፡፡ ይገርማል! ሰውዬው በወቅቱ ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትር ነበር (በደንበኛ ስሙ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ ይባል ነበረ)፡፡ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሆኖም ይሰራ ነበር፡፡ በአዲስ ዘመን እና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጦች ዝግጅትም ይሳተፋል፤ ዝግጅታቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡ ቱባ ባለስልጣን በመሆኑ የብዙ ኮሚቴዎች አባል መሆኑም ይታመናል፡፡ በርካታ የቢሮክራሲ ስራዎችም ነበሩት፡፡ እና ከነዚህ ሁሉ የስራ ጋጋታዎች ጋር የሚታገል ሰው ያንን የመሰለ ውብ መጽሐፍ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዴት ብሎ ነው የጻፈው? ይህንን በቀላሉ ማመን ይቻላል? በትርፍ ጊዜው መጻፉ ይቅርና የሙሉ ጊዜ ደራሲ ቢሆን እንኳ አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርለትም፡፡ ሰውዬው ግን በዓሉ ነውና ቻለው! የስራ መደራረብ “ሳይበግረው” ኦሮማይን ከዘጠኝ ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲያ ከሽኖ አቀረበው (የቀይ ኮከብ ዘመቻ ያበቃው በየካቲት ወር 1974 ነው፤ ኦሮማይ የታተመው በታህሳስ ወር 1975 ነው)፡፡ ችሎታ ማለት እንዲህ ነው!! ለኦሮማይ ዘመን አይሽሬነት ሁለተኛ አብነት ሆኖ የሚጠቀሰው ደግሞ የመጽሐፉ ጭብጥ ነው፡፡ በዚህ ላይ በርካታ ሰዎች የተለያየ አስተያየት ነው ያላቸው፡፡ አንዳንዶች በዓሉ ኦሮማይን የጻፈው የቀይ ኮከብ ዘመቻ ውጥረትና ውድቀትን ለመግለጽ ስለፈለገ ነው ይላሉ፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለሾ ዜናዊ “የመጽሐፉ ጭብጥ በርዕሱና በመጨረሻው ዐረፍተ ነገር ላይ ነው የሚገኘው” ብለው ነገር፡፡ አቶ መለሾ ንግግራቸውን ሲያሰፉም “በዓሉ በመጽሐፉ “እናንተ ደርጎች በኤርትራ ላይ ሙዝዝ ካላችሁ በአዲስ አበባ ያላችሁንም ስልጣን ታጣላችሁ” የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፈው” ብለዋል፡፡ አቶ መለሾ ይህንን ትንተና የሰጡት ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የአልጀርሱን ስምምነት ፈርማ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ በምትጠባበቅበት ወቅት “የስምምነቱ አካሄድ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነው” የሚል ሃሳብ ለሰነዘሩ ተቃዋሚዎች መልስ በሚሰጡበት ጊዜ ነው (ባልሳሳት ጊዜው የካቲት 1994 ይመስለኛል)፡፡ ሆኖም የኦሮማይ ጭብጥ በእንዲህ ዓይነቱ የፖለቲካ ዘውግ ብቻ የታጠረ አይደለም፡፡ ኦሮማይ በዘመኑ “አይነኬ” (taboo) የነበሩ በርካታ ጉዳዮችን ይነካካል፡፡ ለማስረዳት ይፈቀድልኝ፡፡ የደርግ መንግሥት በወቅቱ የሀገሪቱን ህዝብ ከአቅሙ በላይ እያሯሯጠው ነበር፡፡ ህዝቡ በየዓመቱ ከሚመጣበት የዘመቻ መአት ሳያገግም በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቀው ግዙፉ የቀይ ኮከብ ሁለገብ ዘመቻ በጫንቃው ላይ ወረደ (ዘመቻው የጠየቀው የሰው ሀይልና ማቴሪያል ሳይደመር ሁለት ቢሊዮን ብር ወጥቶበታል፤ ይህም በወቅቱ ከሀገሪቷ በጀት ግማሽ ያህሉን ይሸፍናል)፡፡ ሆኖም በዘመኑ ወታደራዊው መንግሥት ያሻውን ቢያቅድና ቢፈጽም አይደፈሬ ነውና ማንም ሰው አፍ አውጥቶ አልተቃወመውም፡፡ በዓሉ ግርማ ግን ለመጪውም ዘመን ትምህርት በሚሆን መልኩ የቀይ ኮከብ ዘመቻን በግልጽ ቋንቋ ሄሶታል፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፉ ውስጥ የጋዜጠኛ ጸጋዬ ኃይለማሪያም እጮኛ እንዲህ ትላለች፡፡ “ኤጭ እቴ! ለሁሉም ነገር ቸኩሎ መሞት! ነጋ ጠባ ዘመቻ! እድገት በህብረት ብሎ ዘመቻ! ለጦርነት ዘመቻ፡፡ የኢኮኖሚ ግንባታ ዘመቻ፡፡ ማይምነትን ለማጥፋት ዘመቻ፡፡ የቁጥጥር ዘመቻ፡፡ አሁን ደግሞ የኤርትራን ችግር ለመፍታት ዘመቻ፡፡ የዘመቻ ባህል ፈጥረናል፡፡ ያለዘመቻ ኖረን የምንሞትበት ቀን መቼ ይሆን?” (ኦሮማይ ፤ ገጽ 9) ጋዜጠኛው የመንግሥት ባለስልጣን ሆኖ ለእጮኛው ንግግር የሰጠው ምላሽ ይበልጥ የሚደንቅ ነው፡፡ “ጊዜ ያጥረናል፤ እብዶች ነን፤ ችኩል ትውልድ፤ ያበደ ትውልድ…” ወዘተ.. ይላታል (ኦሮማይ፤ ገጽ 10) በአንድ በኩል ጸሓፊው የዘመኑ ባለስልጣናት ለቀይ ኮከብ ዘመቻ መሳካት አኩሪ ገድል ሲፈጽሙ ያሳየናል፡፡ ወዲያው ዞር ይልና ደግሞ የመንግሥቱ የቀን ቅዠትና ሀገር አጥፊ ፖሊሲ ያስከተለውን ቀውስ በራሳቸው በባለስልጣናቱ አንደበት ይገልጽልናል፡፡ ለምሳሌ ከመጽሐፉ ዐቢይ ገጸ-ባህሪያት አንዱ የሆነው ኢኮኖሚስቱ መጽሐፈ ዳንኤል ዘመቻው በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ጫና በማስረዳት የዘመኑን አመራር እንዲህ ይሸረድደዋል፡፡ “ይህንን የቆየ ችግር በዘመቻ እንፈታለን ብለን ስንረባረብ ከአሁኑ ሌላ ችግር እየፈጠርን ነው፤ 450 ከባድ የጭነት መኪናዎች፤ 250 ሼልቶ፣ 200 ከነተሳቢያቸው ወደ ሰሜን ማዞር ምን ማለት ነው? ባጭሩ ኢኮኖሚው ተናግቷል ማለት ነው፤ ደሞ አሁን የመኸር ጊዜ መሆኑን አትርሳ” (ኦሮማይ፤ ገጽ 75)

  • ገለምሶ ትነሳ- 2018 ---- (ሁሉም እንዲያነበው ይመከራል) ----- ገለምሶ በቀድሞው ዘመን ዝናዋ የተነገረላት ከተማ ነበረች። የአውራጃ ዋና ከተማ ስለነበረች ከሌሎች አካባቢዎች እየመጣ የሚያያት ሰው ብዙ ነበር። በስራ ዝውውርም ከተራ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ እስከ ባንክ ማኔጀር እና የአውራጃ ኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ ድረስ ተቀይረው ወደ እርሷ መጥተዋል። ከተማዋ ከሰላሳ አምስት ዓመት በፊት ያላት ሕዝብ ብዛት ከ15,000 አይበልጥም ነበር። እንደዚያም ሆና ስሟ ከፍ ብሎ ይሰማል። የዝነኝነቷ ምክንያት ብዙ ቢሆንም በምርት በሽበሽ መሆኗ፣ የቡናዋ እና የሀረር ሰንጋ ምንጭ መሆኗ፣ የህዝቧ እንግዳ ተቀባይነትና ንቁ መሆን፣ የሆቴሎቿና ሬስቶራንቶቿ ልዩ መስተንግዶ፣ የአየሯ ተስማሚነት ወዘተ ይጠቀሳሉ። የገለምሶ ዝነኝነት በተለይ በዘፈኖች በጣም ይንጸባረቅ ነበር። በሀረርጌ ውስጥ ከድሬ ዳዋ እና ሀረር ቀጥላ በዘፈን ውስጥ ተደጋግማ የተጠራችው እርሷ ናት። ለምሳሌ ከታች የተጠቀሱት አርቲስቶች ከዛሬ ሰላሳ ዓመት በፊት ባወጧቸው ካሴቶች ውስጥ ገለምሶን አውስተዋል (ዓመቶቹ የተጠቀሱት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ነው)። 1. የAfaan Oromoo ዘፈኖች a. ጋዲሳ ዐብዱላሂ- 1976 (Koo naaf hin nayu) b. ዓሊ ሸቦ- 1978 (Qalbii to Naseente) c. አደም ሃሩን- 1979- (Galamsoo fi Habroo) d. ዘሪሁን ወዳጆ- 1982- (Ya Shagge Ya Tiru) e. ቀመር ዩሱፍ- 1984- (Yaa Shirri Shirri) f. ዳግም መኮንን- 1986- (Shamarran Harargee) 2. የአማርኛ ዘፈኖች 1. ንግሥት አበበ (ልይህ እንደገና) 2. ወጋየሁ ደግነቱ (የሀረር ልጅ ናት) 3. ኤልሳቤት ተሾመ (የሀረር ሸጋ) ----- እኔ እነዚህን አስታውሻለሁ። እናንተም የምታስታውሱትን ልትጨምሩበት ትችላላችሁ። ----- ገለምሶ ተቆርቁራ "ከተማ" መሆኗ እውቅና የተሰጠው በ1901 ነው። ይህም የዛሬ 117 ዓመት መሆኑ ነው። ዕድገቷ ግን ከዕድሜዋ ጋር የሚሄድ አይደለም። ከተማችን እንደ ስሟ ሆና ያልተገኘችው በተለያዩ ምክንያቶች ነው። ምክንያቶቹን በተለያዩ ጊዜዎች ገልጬአለሁ። አሁን እያወያየ ያለው ጥያቄ "ገለምሶን ከያዛት የዱካክ አባዜ አላቅቀን በፍጥነት እንድታድግና ስሟን በሚመጥን ደረጃ ላይ እንድትገኝ ለማድረግ ምን እናድርግ?" የሚል ሆኗል። የጥያቄው መልስ አንድና አንድ ብቻ ነው። እርሱም "ነዋሪዎቿ፣ ተወላጆቿ እና ወዳጆቿ ተያይዘው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ" የሚል ነው። ----- ይህ ጥያቄ የቆረቆራቸውና "የገለምሶን ፈጣን የዕድገት ጉዞ ጅማሮ ማብሰር አለብን" በማለት በጣም የተቆጩ የከተማዋ ነዋሪዎች ኮሚቴ አዋቅረው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጀምረዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት በከተማዋ የተጀመረውን የአስፋልት መንገድ ሼል ለማገዝ ቀላል የማይባል ገንዘብ አሰባስበዋል። አሁን ደግሞ ለሌሎች የከተማዋ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ ታላቅ ቴሌቶን አዘጋጅተዋል። ይህ ቴሌቶን የሚካሄደው የካቲት 1/2018 ነው። እኛም በዚህ ታላቅ ቴሌቶን በመሳተፍና የምንችለውን ድጋፍ በመለገስ የከተማችን ዕድገት አጋር መሆናችንን ማሳየት አለብን። የቴሌቶኑን ዝርዝር መርሐ-ግብር እንደደረሰኝ የምለጥፍላችሁ ይሆናል። ይህ ፖለቲካ አይደለም። ሁላችንንም የሚመለከት የሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ጥሪ ነው። በመሆኑም የትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ያለው፣ በማንኛውም የስራ ዘርፍ የተሰማራ እና በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚኖር ሰው ሊሳተፍበት ይገባል። ----- ሁላችንም ለገለምሶ ዕድገት ተያይዘን ወደፊት!! ድር ቢያብር አንበሳ ያስር! Tokko taanee Galamso haa kaafnu.

  • ማሕቡባ- ቢሊሌ- የጨረፍታ እይታ ------- ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ ------ ሰዎች በባርነት እየተፈነገሉ ይሸጡ በነበረበት ዘመን በኢትዮጵያ ምድር የተወለዱ በርካታ ጉብሎች እና ኮረዳዎች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ፣ አውሮጳ እና ሌሎች አህጉሮች መወሰዳቸው ይታወቃል። ከኢትዮጵያ እየተወሰዱ በባርነት ከተሸጡት ኮረዳዎች መካከል በጣም ዝነኛ ለመሆን የበቃችው ደግሞ "ቢሊሌ" (ማሕቡባ) ናት። ማህቡባ እውቅና ያተረፈችው በውበቷ እና ከአውሮጳ ባህልና ቋንቋ ጋር በፍጥነት ለመላመድ በመቻሏ ነው። ይህቺ ወጣት በአውሮጳ ምድር ከሶስት ዓመት በላይ አልቆየችም። ነገር ግን በዚያ አጭር ጊዜ የብዙዎችን ቀልብ ከመሳቧ በላይ ለትውልድ እና ለታሪክ የሚጠቅም ቁም ነገር ሰርታለች። እነሆ በዚህ ምሽት ማህቡባን በአጭሩ እንዘክራት ዘንድ ወደድኩ። ------ "ማህቡባ" በቤተሰቦቿ የተሰጣት ስም "ቢሊሌ" መሆኑ ይነገራል። በአፋን ኦሮሞ "ቢሊሌ" ሲባል "የምታምር፣ ብዙዎችን የምትስብ፣ በውበቷ ከሌሎች የምትበልጥ" እንደማለት ነው። "ማሕቡባ" ደግሞ የዐረብኛ ቃል ሲሆን ይህም "በጣም የምትወደድ" እንደማለት ነው። ይህ ስም የወጣላት በባርነት ከተሸጠች በኋላ መሆኑ ይታመናል። "ማሕቡባ" ልደቷ የተበሰረው በግምት በ1820 ገደማ ነው። የተወለደችው ደግሞ በዛሬው ደቡብ-ምዕራብ ኢትዮጵያ አብበው ከነበሩት አምስቱ የጊቤ ሱልጣኔቶች አንዱ በነበረው የ"ጉማ" ሱልጣኔት ነው። የማሕቡባ የልጅነት ሕይወት ብዙም አይታወቅም። በዚህም የተነሳ ታሪኳ ለፈጠራ ትርክቶች የተጋለጠ ሆኗል። ፈጠራውን መጻፍ ለኛ አይጠቅመንም። በዚህ ጽሑፍ በሰነድ ከሚታወቀው ታሪኳ ውጪ ሌላውን ትርክት አንቀላቅልም። ----- እ.ኤ.አ. በ1835 ገደማ ነው! ቢሊሌ (ማሕቡባ) የተወለደችበት የጉማ ሱልጣኔት በሌላ የአካባቢ መንግሥት ተወረረ። ወራሪው ሃይል በጦርነቱ በለስ ቀንቶት ወደ ጉማ ከተሞችና መንደሮች ገባ። ብዙዎች አለቁ። የሕዝቡ ሀብትና ንብረት ተዘረፈ። ወራሪዎቹ ቢሊሌ የተወለደችበትን መንደር በእሳት አቃጠሉት። ህዝቡንም ፈጁት። የቢሊሌ አባት እና ስድስት ወንድሞቿ ተገደሉ። እርሷ፣ እናቷ እና አንድ እህቷ በባርነት ተወሰዱ። ------ ቢሊሌን ባሪያ ያደረጉት ሃይሎች የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑትን ሰዎች ለባሪያ ነጋዴዎች ሸጧቸው። ባሪያ ነጋዴዎቹ ቢሌሌንና ሁለቱን ሴቶች እየተቀባበሉ በወለጋ-ጎጃም መሾመር አሳልፈው ጎንደር አስገቧት። ከጎንደር ደግሞ በቅድሚያ ወደ ካርቱም ተወሰዱ። ካርቱም ላይ እህቷ ከእርሷ እና ከእናቷ ተለየች። ቢሊሌ ደግሞ ከእናቷ ጋር ወደ ካይሮ ተወሰደች። ቢሊሌ ካይሮ እንደገባች ከእናቷ ጋር ተለያየች። ስሟም "ማሕቡባ" ሆነ። ባሪያ ነጋዴዎቹ ማሕቡባን ገበያ ላይ ሲያቆሟት ብዙ ሰዎች በውበቷ ተማርከው ሊገዟት መጡ። ነጋዴዎቹ ግን "ይህቺ የንጉሥ ልጅ ናት! በርካሽ ዋጋ አትሸጥም" እያሉ ዋጋዋን ከፍ አደረጉባቸው። በዚህ መሃል ለሽርሽር ወደ ካይሮ የመጣ አንድ ሀገር ጎብኝ ማሕቡባን ገበያ መሃል እንደሸቀጥ ቆማ አያት። ሰውዬው በመልኳ እና በቁመናዋ በጣም ተማረከ። ወደ ነጋዴዎቹ መጥቶም ሊገዛት መሻቱን ነገራቸው። ነጋዴዎቹ በጊዜው ውድ የተባለ ዋጋ ቢነግሩትም ሰውዬው የተጠየቀውን ሁሉ ከፈለ። ማሕቡባም ከዚያ ቀን ጀምሮ የእርሱ ሆነች። ------ ማህቡባን የገዛት ሰው "Prince Hermann Ludwig Heinrich von PĂźckler-Muskau" ይባላል። ይህ ሰው ጀርመናዊ ልዑል ሲሆን አባቱ በዘመኑ የጀርመን-ሳክሶኒ ንጉሣዊ መንግሥት አልጋ ወራሽ ነበር። ልዑል ሉድዊግ ሄንሪክ በወቅቱ ሽርሽር ላይ ነበር። በመሆኑም በሄደበት ቦታ ሁሉ ማህቡባን ይዞአት ሄዷል። ማሕቡባን የያዛት ደግሞ እንደ ባሪያው ሳይሆን እንደ ፍቅረኛዋ ነበር (እንግሊዝኛው Mistress ይላል። ከፍቅረኛ በቀር አቻ የአማርኛ ቃል አላገኘሁለትም)። ልዑሉ የአፍሪቃ፣ የእስያ፣ የቱርክና የሩሲያ ጉብኝቱን ሲያበቃ ከማሕቡባ እና ከሌሎች አገልጋዮቹ ጋር ወደ ጀርመን ተመልሷል። ------ የሳክሶኒው ልዑል ማሕቡባን በቤተ መንግሥቱ ነው ያኖራት። ከአውሮጷ ሕይወትም ጋር በቶሎ ነው ያላመዳት። ይሁንና የማሕቡባ ውበትና ትህትና በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ መሆኑ አስፈራው። በመሆኑም ከሳክሶኒ በሚርቀው የቪየና ከተማ በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት አስገባት። ታዲያ ማሕቡባ ቪየና ስትገባ ውበት መነጋገሪያ መሆኑ ባሰበት እንጂ አልቀነሰም። ያዩዋት ሁሉ "ያቺ ከአፍሪቃ የመጣችው ጉብል እንዴት ነው የምታምረው?" እያሉ ይጠያየቁ ነበር። ከዚህ አልፎ የማሕቡባ ውበት፣ ቁመና እና ትህትና በቪየና ከተማ በሚገኙ ጋዜጦች ላይ ጭምር ይጻፍ ጀመር። ማሕቡባ በበኩሏ የኢጣሊያ እና የጀርመን ቋንቋዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተምራ የበለጠ ተደናቂ ሆነች። ልዑል ሉድዊግ ሄንሪ በክስተቱ ተሸበረ። ማሕቡባንም በሌሎች የሚነጠቅ መሰለው። በመሆኑም "እዚህ መልሼአት የግል አስተማሪ ቀጥሬ ባስተምራት ይሻላል" በማለት ከቪየና ወደ ቤተ-መንግሥቱ ወሰዳት። ይህ የልዑሉ ውሳኔ እንደ መነሻ ሆኖ ነው ማሕቡባ ለታሪክ የሚጠቅም ቁም ነገር የሰራችው። ------- ማሕቡባ ወደ ሳክሶኒ ቤተ መንግሥት ስትመለስ በአስተማሪነት የተቀጠረላት ሰው Karl Tutschek ይባላል። ይህ ሰው በዘመኑ ካርኩለም ይሰጡ የነበሩ ትምህርቶችን በደንብ አጥንቶአል። በመሆኑም ማሕቡባን ስድስት ያህል የትምህርት ዓይነቶችን ያስተምራታል። ታዲያ ካርል ቱሼክ በአስተማሪነት የተመደበው ለማሕቡባ ብቻ አይደለም። ከእርሷ ጋር በባርነት ተሽጠው ወደ አውሮጳ የመጡ ሁለት የኦሮሞ ተወላጆችም ነበሩ። እነዚያ ልጆች "አካፌዴ ዳሌ" እና "ኦሹ አጋ" ይባላሉ። ካርል ቱሼክ ከዚያ ቀደም ብሎ የኦሮምኛ-ጀርመንኛ-እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ማዘጋጀት ጀምሮ ነበር። ነገር ግን ብዙ ቃላት ባለማሰባሰቡ ስራውን አቋርጧል። ሶስቱ ልጆች (ማሕቡባ፣ አካፌዴ ዳሌ እና ኦሹ አጋ) በተማሪነት ሲመደቡለት በአጋጣሚው ለመጠቀም ወሰነ። በመሆኑም ከሶስቱ ልጆች በርከት ያሉ ቃላትን ሰብስቦ በመዝገበ ቃላቱ ውስጥ አካተታቸው። ኦሮምኛንም ከእነርሱ በደንብ ተማረው። ማሕቡባ ለቱሼክ ከሰጠቻቸው ቃላት በተጨማሪ 208 የሚሆኑ የኦሮምኛ ባህላዊ የዘፈን ግጥሞችን ሰጥታዋለች። ቱሼክ ግጥሞቹን በመዝገበ ቃላቱ አካትቶ ለማሳተም እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ። ነገር ግን ሞት ቀደመውና በ1842 አረፈ። መዝገበ ቃላቱ እርሱ ሞቶ በሁለት ዓመቱ (1844) ታተመ። ማሕቡባ ለቱሼክ የሰጠቻቸው የዘፈን ግጥሞች በጀርመንኛ ሳይተረጎሙ በነበሩበት ሁኔታ ከቆዩ በኋላ በታዋቂው ኢትኖግፈር "ፊሊፕ ፖሊሽኪ" አማካኝነት በ1890 በመጽሐፍ ታተሙ። ------- እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ በሉ። የቱሼክ መዝገበ ቃላት በታተመበት ወቅት ማሕቡባ ልሡ በሕይወት አልነበረችም። ይህቺ በውበቷ መነጋገሪያ የሆነችና በፈጣን ተማሪነቷ የተደነቀች ኮረዳ በሳምባ ነቀርሳ በሽታ ተለክፋ በ1840 አርፋለች። ------ ማሕቡባ ጥንት አርፋለች። ነገር ግን ዛሬም ድረስ በብዙዎች እየተዘከረች ነው። ሪቻርድ ፓንክረስት፣ አሌሳንድሮ ትሪሉዊዚ፣ ፖል ባክስተር፣ ሙሐመድ ሐሰን፣ ገመቹ መገርሳ፣ ሪቻርድ ካውክ ሾለ እርሷ ጽፈዋል። ፕሮፌሰር ክላውድ ሳምነር እርሷ የሰበሰበቻቸውን የዘፈን ግጥሞች በአንድ መጽሐፍ ጠርዘው የግጥሞቹን ውበት እና እማሬያዊ መልእክት ከሚዳስስ ትንተና ጋር አሳትመዋል። ብዙዎች ደግሞ "ቢሊሌ-ማሕቡባ" እያሉ ዘፍነውላታል። በዚህም የተነሳ የቤተሰባችን አባል እንደሆነች ነው የሚሰማን።

  • ዓሊ ቢራ እና የድሬ ዳዋ ጭልፊት --- ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ --- በፌስቡክ የሚዘዋወረው የጩልሌ እና የጭልፊት አተካራ የአጭር ጊዜ ግርግር ከመፍጠር ባሻገር የትም የሚደርስ አይደለም። እኛም በሀገሪቱ መሪ አንደበት ባይነገር ኖሮ ትኩረት ባልሰጠነው ነበር (ሰውዬውም በምርጫው እሸነፋለሁ ብሉ ስለሰጋ ነው ከመሪ በማይጠበቅ ሁኔታ መዘላበድ የጀመረው)። በዚህ ፖስት የምናጋራችሁ አጭር ዘመን ተሻጋሪ ጨዋታ ነው። አዎን! ስለተወዳጁ ድምፃዊ ድምጻዊ ዓሊ ቢራ ብናወራ ይሻላል። እንደሚታወቀው ሁሉ ዓሊ ቢራ በዘፈኖቹ የተወለደባትን የድሬ ዳዋ ከተማን እየደጋገመ ያነሳታል። ከታዋቂ ግጥሞቹ መካከል ደግሞ የሚከተለው ተወዳጅ ግጥም ይገኝበታል። Alattiin Dirree Dhawaa foon malee lafee hinnyaatina jetti Magaalleen Dirree Dhawa namalee hindubbisina jetti በዚህ ግጥም ነው እንግዲህ ዓሊ ቢራ ድሬ ዳዋን በጥበብ ስራዎቹ መዘከር የጀመረው፡፡ ዓሊ በዚህ ባህላዊ ግጥም ሁለት ተቃራኒ ባህሪያትን ነው እንደ አንድ አምሳያ አድርጎ ለመግለጽ የፈለገው፡፡ የድሬ ዳዋ ጭልፊት እና የድሬ ዳዋ ጉብል፡፡ የያንዳንዳቸው ፍላጎት ምን እንደሆነ ለማወቅ የግጥሙን መልዕክት ወደ አማርኛ መልሰን እንየው፡፡ የድሬ ዳዋ ጭልፊት “ስጋ እንጂ አጥንት አትብሉ” እንዳለች የድሬዋ ጉብልም “ከኔ በቀር ሌላዋን አታናግሩ” ትላለች፡፡ --- ጭልፊቷ አጥንት አትብሉ ያለችው ለውንብድና ተግባሯ እንደሚያመቻት በማሰብ ነው፡፡ ሰዎች ስጋውን ትተው ወደ አጥንቱ ጎራ ካሉ እርሷ ጦሟን ማደሯ ነው፡፡ ከሰዎች እጅ እየሞጨለፈች ከርሷን የምትሞላበት ስጋ ብርቅ ሊሆንባት ነው፡፡ ስለዚህ ያ እንዳይሆን ለድሬ ነዋሪዎች “የምን አጥንት ማሳደድ ነው? ስጋውን ጠንከር አድርጋችሁ ያዙ እንጂ” እያለች “የብልጠት” ምክር ትሰጣለች፡፡ ታዲያ ዓሊ ቢራ “አጥንት አትብሉ ትላለች” ያለው ነገር ጨዋታ ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ የድሬ ዳዋ ነዋሪዎች ልክ እንደ ሀረሪዎቹ አጥንትን በሁልበት መረኽ (የአብሽ ወጥ) ውስጥ መጨመርን እንደ ባህል ከያዙት በጣም ቆይቷል፡፡ እናቶች ወደ ሱጉያ ቤት (ልኳንዳ) ሄደው በስጋው ፈንታ አጥንት ሸምተው የሚመለሱበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ይህ ነገር ቀጣይ ሆኖ ከዘለቀ የጩልሌዋ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ ነው፡፡ ይህንን አደጋ ለመከላከል ነው አጅሪት “ምክር እንካችሁ” በሚል አኳኋን “ስጋውን ተመገቡ” እያለች የምትለፍፈው፡፡ የድሬ ቆንጆ “ከኔ በቀር አታናግሩ” የማለቷ ሚስጢር ግን ከጭልፊቷ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ብሂል ይለያል፡፡ በዓሊ አንደበት ሊነገረን የተፈለገው “የድሬ ጉብል ከሁመካከል ትልጣለች” የሚል መልዕክት ነው እንጂ “የድሬ ጉብል ልሾ ወዳድ ናት” ለማለት አይደለም፡፡ የድሬ ልጅ በራስ ወዳድነት በጭራሽ አትታማምና፡፡ --- ("ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬ ዳዋ" ከተሰኘው መጽሓፋችን የተቀነጨበ ነው)።

  • "ምንዱባን" ---- በዚህ ስም የሚጠራውን መጽሐፍ ታስታውሳላችሁ አይደለምን? አዎን! የፈረንሳዊው ደራሲ ውብ ሾል የሆነው Les Miserables በአማርኛ ቋንቋ ከተተረጎመባቸው ሁለት መጻሕፍት አንዱ ነው። የምንዱባን ተርጓሚ ከኔ ጋር በዚህ ፎቶ የሚታዩት ናቸው። "ዮሐንስ ገብረጻድቅ" ይባላሉ። በቅርቡ አንድ ትልቅ ሾል ተርጉመው ለአንባቢያን እንደሚያቀርቡ ገልጸውልኛል። ርእሱንና ኦሪጅናሌውን ደራሲ መጽሐፉ ለህትመት በበቃበት ጊዜ ብታዩት ይመረጣል። (ርእሱን እንድናገር አልተፈቀደልኝም)።

  • The countdown starts --- = This book is in the final phase. 97% of the works are completed now. We are going to order its printing soon. And I guess that it will be available in the first week of the month of April/2026. We will notify you the way you would order your copy then. Insha Allah. = Note that the subtitle of the book isn't similar to the one I was posting before now. That one was the title I set out when I started writing the book. And it was changed in the last year due to the phenomena I encountered throughout my works. So the full title of the book will be this "Hundee:- Maatii Keenya, Harargee fi Qabsoo Ummata Oromoo". ----- = Most of the fund to publish the book is secured now. Thanks to the Almighty Allah! And thanks to my friends, relatives, supporters, families of the pioneers of the Oromo people struggle in Galamso and the whole region of Hararge, and especially the Diaspora of Galamso.

  • "ሪፖርተር" ድርብ ታሪክ ሰል! አፈንዲ ሙተቂ ---- 1ኛ- በኢትዮጵያ ምድር የሚታተሙ የግል ጋዜጦች ረጅም ዕድሜ የላቸውም። ብዙዎቹ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ተቋቁመው ህትመታቸውን መቀጠል ይሳናቸዋል። ድሮ የምናውቃቸውና ወጣቱን ንባብ ያለማመዱት ብዙ ጋዜጦችና መጽሔቶች ተራ በተራ ከስመዋል። ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ መዘጋት ነው። ይሁንና ለችግሮች ሳይበገር ለሰላሳ ዓመታት መቆየት የቻለ አንድ ጋዜጣ አለ። እርሱም "ሪፖርተር" ይሰኛል። በ1987 ተጀምሮ ዛሬም በገበያው ውስጥ አለ። ይህ የቆይታ ጊዜ በራሱ ሪከርድ ሲሆን ለወደፊቱም በቀላሉ የሚሰበር አይመስልም። 2- ሪፖርተር ለረጅም ጊዜ የግለሰብ ፎቆችን እየተከራየ ነው ስራውን ሲሰል የኖረው። አሁን ደግሞ የራሱን ውብ ህንጻ አሰርቷል። ከበፊት ጀምሮ ደካማ የንባብ ባህል ባለበት ሀገር ውስጥ ነው የምንኖረው። ኢንተርኔቱ በጣም ከተስፋፋ ወዲህ ደግሞ የመጽሐፍና የጋዜጣ አንባቢ ቁጥር በ 2/3 ቀንሷል። "ሪፖርተር" በዚህ አውድ ውስጥ ነው ተነባቢ ሆኖ ለሰላሳ ዓመታት የዘለቀው። ታዲያ ተነባቢ መሆኑ ብቻ አይደለም ጥንካሬው። በየሳምንቱ አንድ ኩባኒያ የሚሰራውን ያህል ቢዝነስ እየሰራ ነው ለሕዝቡ መረጃ የሚያቀርበው። የጋዜጣው ገጾች በጣም ብዙ ናቸው። ከገጾቹ መካከል ከ65 የሚልቁት ቢዝነስ ለመስራት የሚታተሙ ቢጫ ገጾች ናቸው። በተለይም መሃል ላይ የቅጥር ማስታወቂያ ብቻ የሚወጣባቸው "Ethio-Jobs" የሚባሉ ገጾች አሉ። ሪፖርተር በነዚህና በሌሎች ገጾች ነው ቢዝነስ የሚሰራው። ሪፖርተር አካሄዱ የጠነከረ በመሆኑ ከህትመት ውጪ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። ከእርሱ ቀጥሎ Addis Fortune እና Capital የተሰኙት የእንግሊዝኛ ጋዜጦች በጣም ጠንካሮች ናቸው።

  • ዓሊ ቢራ እና የድሬ ዳዋ ጭልፊት ---- ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ ------ ዛሬም ስለተወዳጁ ድምፃዊ ድምጻዊ ዓሊ ቢራ ልናወጋ ነው። እንደሚታወቀው ሁሉ ዓሊ ቢራ በዘፈኖቹ የተወለደባትን የድሬ ዳዋ ከተማን እየደጋገመ ያነሳታል። ከታዋቂ ግጥሞቹ መካከል ደግሞ የሚከተለው ተወዳጅ ግጥም ይገኝበታል። Alattiin Dirree Dhawaa foon malee lafee hinnyaatina jetti Magaalleen Dirree Dhawa namalee hindubbisina jetti በዚህ ግጥም ነው እንግዲህ ዓሊ ቢራ ድሬ ዳዋን በጥበብ ስራዎቹ መዘከር የጀመረው፡፡ ዓሊ በዚህ ባህላዊ ግጥም ሁለት ተቃራኒ ባህሪያትን ነው እንደ አንድ አምሳያ አድርጎ ለመግለጽ የፈለገው፡፡ የድሬ ዳዋ ጭልፊት እና የድሬ ዳዋ ጉብል፡፡ የያንዳንዳቸው ፍላጎት ምን እንደሆነ ለማወቅ የግጥሙን መልዕክት ወደ አማርኛ መልሰን እንየው፡፡ የድሬ ዳዋ ጭልፊት “ስጋ እንጂ አጥንት አትብሉ” እንዳለች የድሬዋ ጉብልም “ከኔ በቀር ሌላዋን አታናግሩ” ትላለች፡፡ --- ጭልፊቷ አጥንት አትብሉ ያለችው ለውንብድና ተግባሯ እንደሚያመቻት በማሰብ ነው፡፡ ሰዎች ስጋውን ትተው ወደ አጥንቱ ጎራ ካሉ እርሷ ጦሟን ማደሯ ነው፡፡ ከሰዎች እጅ እየሞጨለፈች ከርሷን የምትሞላበት ስጋ ብርቅ ሊሆንባት ነው፡፡ ስለዚህ ያ እንዳይሆን ለድሬ ነዋሪዎች “የምን አጥንት ማሳደድ ነው? ስጋውን ጠንከር አድርጋችሁ ያዙ እንጂ” እያለች “የብልጠት” ምክር ትሰጣለች፡፡ ታዲያ ዓሊ ቢራ “አጥንት አትብሉ ትላለች” ያለው ነገር ጨዋታ ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ የድሬ ዳዋ ነዋሪዎች ልክ እንደ ሀረሪዎቹ አጥንትን በሁልበት መረኽ (የአብሽ ወጥ) ውስጥ መጨመርን እንደ ባህል ከያዙት በጣም ቆይቷል፡፡ እናቶች ወደ ሱጉያ ቤት (ልኳንዳ) ሄደው በስጋው ፈንታ አጥንት ሸምተው የሚመለሱበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ይህ ነገር ቀጣይ ሆኖ ከዘለቀ የጩልሌዋ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ ነው፡፡ ይህንን አደጋ ለመከላከል ነው አጅሪት “ምክር እንካችሁ” በሚል አኳኋን “ስጋውን ተመገቡ” እያለች የምትለፍፈው፡፡ የድሬ ቆንጆ “ከኔ በቀር አታናግሩ” የማለቷ ሚስጢር ግን ከጭልፊቷ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ብሂል ይለያል፡፡ በዓሊ አንደበት ሊነገረን የተፈለገው “የድሬ ጉብል ከሁመካከል ትልጣለች” የሚል መልዕክት ነው እንጂ “የድሬ ጉብል ልሾ ወዳድ ናት” ለማለት አይደለም፡፡ የድሬ ልጅ በራስ ወዳድነት በጭራሽ አትታማምና፡፡ --- ("ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬ ዳዋ" ከተሰኘው መጽሓፋችን የተቀነጨበ ነው)።

  • ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ -------- "ከቤ አባ መርዙ"- ያልተዘመረለት ጀግና (ቁጥር አምስት) ----- አፈንዲ ሙተቂ ----- በዚህ ጽሑፋችን ለኢትዮጵያ ነፃነትም ሆነ ለኦሮሞ ሕዝብ መብት መከበር በከፍተኛ ደረጃ የተዋደቀውን የሜታ ሮቢ እና የአድአ በርጋ አንበሳ ነው የምንዘክረው። በእርግጥ "ከበደ ብዙነሽ" በአንጻራዊነት ከሌሎች በተሻለ ሁኔታ ተዘክሮአል። "ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ" በሚል ርእስ ተስፋዬ ገብረአብ አርታኢ ሆኖ ባሳተማቸው መጻሕፍት ውስጥም ገድሉ በአርባ ገጾች ተጽፎአል። ይሁንና ከሰውዬው ስብዕና አንጻር በቂ አይደለም። ወጣቱ ትውልድም ይህንን ታላቅ ጀግና እንዲያውቀው እየተደረገም አይደለም። ስለሆነም ጀግናውንና ሀገር አስተዳዳሪውን "ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ"ን በአጭሩ እንዲህ እናስታውሰዋለን። ----- የጀግናችን ትክክለኛ ስም "ከበደ በቸሬ ደበላ" ነው። ይሁንና ከበደ በቸሬ በተወለደበት ቤት አላደገም። ገና እንደተወለደ ነው ልጆች ያልነበራት "ብዙነሽ በቸሬ ደበላ" የተባለች አክስቱ ወስዳው ልክ እንደወለደችው ልጅ አቀማጥላ ያሳደገችው። ከበደ በቸሬም የአሳዳጊ አክስቱን ውለታ ላለመርሳት ሲል መጠሪያ ስሙን ከ"ከበደ በቸሬ" ወደ "ከበደ ብዙነሽ" ቀይሮታል። ---- ከበደ ብዙነሽ በኢጣሊያ ወረራ ዋዜማ በአድአ በርጋ ወረዳ የአንድ አጥቢያ አስተዳዳሪ ነበር። ጣሊያኖች ሀገራችንን ሲወርሩ ግን "እምቢ ለሀገሬ! እምቢ ለነፃነቴ!" በማለት ወደ ዱር ገባ። በርካታ ወጣት ታጣቂዎችን እየመራ ወራሪዎችን በተለያዩ ግንባሮች አስጨነቀ። ጀግንነቱን ያየው የሜታ ሮቢ ወረዳ ሕዝብም "ከቤ የሚተኩሰው መርዝ እንጂ ጥይት አይደለም" እያለ አደነቀው። "እሱ የሚወረውረው ቦምብም መርዝ ነው" ተባለ። በዚህም የተነሳ "ከቤ አባ መርዙ" የተሰኘ የፉከራና የቅሰቀሳ ስም ወጣለት። በረገዳ ግጥም የተካኑት የአድአ በርጋ ወጣቶች ደግሞ የፉከራ ስሙን ከአሳዳጊ አክስቱ ስም ጋር በማያያዝ እንዲህ ብለው ገጠሙለት። ilma Addee Bizuu (ይህ ልጅ ነው የወይዘሮ ብዙ) Kabbee Abbaa Marzuu (ከቤ አባ መርዙ) ------ ከቤ አባ መርዙ በሜታ ሮቢ እና በአድአ በርጋ ወረዳዎች ጣሊያንን በጣም ነበር ያስጨነቀው። በእነዚህ ወረዳዎች ከጣሊያን ወራሪዎች ጋር ባደረጋቸው ውጊያዎች ተሸንፎ አያውቅም። በተለይም በአንድ ወቅት በአዲስ አለም ባለው የጣሊያን የመሳሪያ ዲፖ ላይ ባደረሰው ጥቃት ብዙ መሳሪያዎችን ማርኮ ለአርበኞቻችን ጥቅም አውሎታል። ኢጣሊያኖች ሲባረሩ ወደ ፊንፊኔ ከተመሙት ጦሮች አንዱ በእርሱ ይመራ ነበር። ከኢጣሊያ ወረራ መልስ ከቤ አባ መርዙ ለሀገሩ ያደረገው ተጋድሎ በጣም ደምቆ እየተወራ ቤተ መንግሥት ድረስ ተሰምቷል። በገድሉ የተመሰጡት አጼ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግሥት ድረስ አስጠርተው ከፍተኛ ሽልማት ሸልመውታል። ብዙ ጋሻ መሬትም ሰጥተውታል። የደጃዝማች ማዕረግ ያገኙትም ያኔ ነው። ከቤ አባ መርዙ ከኢጣሊያ ወረራ ወዲህ ባለው ዘመናቸው የተለያዩ አውራጃዎች ገዥ በመሆን ሀገራቸውን አገልግለዋል። በአስተዳደራቸው ፍትሐዊ እንደነበሩም ተነግሮላቸዋል። ------ "ከቤ አባ መርዙ" ከመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር መስራቾች አንዱ ነበሩ። ለማህበሩ ከፍተኛ መዋጮ ከሚከፍሉትም አንዱ እሳቸው ነበሩ። በወቅቱ ካላቸው መሬት ግማሹን ለማህበሩ ሰጥተዋል። ከተቀረው መሬት ደግሞ የሚበዛውን እጅ ለኦሮሞ ገበሬዎች በማከፋፈል ብዙ ጭሰኞችን ባለመሬት አድርገዋል። ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ ያስቀሩት መሬት ከሁለት ገበሬ ቤተሰቦች መሬት የበለጠ አልነበረም። የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር በመንግሥት ሲታገድ ግን አባላቱ "መንግሥትን ሊገለብጡ ሲያሴሩ በቁጥጥር ሾር ውለዋል" በሚል የሐሰት ምክንያት በሞትና በእስር ሲቀጡ ከእመቃው የተረፉት ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ አፋቸውን ዘግተው አልተቀመጡም። በቀጥታ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘንድ በመሄድ የተወሰደው እርምጃ ህግን ያልጠበቀ እና በዜጎች መካከል እኩልነት እንደሌለ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል። አጼው "በታሰሩት ላይ ፍትሓዊ ፍርድ ይሰጣል" በማለት ቃል ገብተውላቸው ነበር። ይሁንና ቃላቸውን በተግባር ላይ አላዋሉትም። ------- የደርግ መንግሥት ወደ ስልጣን ሲመጣ ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ በጡረታ ላይ ነበሩ። ደጃዝማች ጡረታ እንደወጡ ወደ አዲስ ዓለም ሄደው ላይ በሰላም በመኖር ላይ ነበሩ። የደርግ መንግሥት ስልጣን ሲይዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ለዘመናት ሲካሄድ የነበረው ጭቆና እና በደል ያበቃል የሚል ተስፋ ነበራቸው። ይሁን እንጂ ወታደራዊው ቡድን ህዳር 12/1967 ቀን ስድሳ ያህል የቀድሞው መንግሥት ሚኒስትሮችና ባለስልጣኖችን ፍርድ ቤት ሳያቀርባቸው ከህግ አግባብ ውጪ ሲረሽናቸው በጣም ነው የደነገጡት። "የባለስልጣኖችን ጉዳይ በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን አጣርቼ ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጣቸው አደርጋለሁ" ሲል የነበረው ደርግ ዓለም በሙሉ የሚከታተለውን ጉዳይ በዚያ መንገድ ሲያጠናቅቀው በዚያ ዘመን በዓለም ሚዲያ ብዙም የማይታወቀው የኦሮሞ ሕዝብ የነፃነት ጥያቄ ከዚያ በባሰ የጭካኔ መንገድ ሊደመሰስ እንደሚችል መረዳት አላዳገታቸውም። ይሁንና ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ እንደ ሌሎች በፍርሃት ተሸብበው ዝም አላሉም። ያንን አሰቃቂ እርምጃ የሚያጋልጥ ደብዳቤ በመጻፍ ለደርግ መንግሥት መሪዎች ልከዋል። ደርጎች በዚህ አድራጎታቸው ተናደው ሊይዟቸው ሲሞክሩም በ74 አመታቸው መሳሪያ አንግተው ከሜታ ሮቢና ከአድዋ ገርባ ገበሬዎች ጋር ጫካ ገብተዋል። ከቤ አባ መርዙ የአማጺ ቡድኑን እየመሩ በሸዋ ከፍተኛ ተራሮች ላይ ሲታገሉ ከቆዩ በኋላ በግንቦት 1967 በተደረገ አንዱ ፈታኝ ውጊያ ላይ የራሳቸውን ህይወት አጥፍተዋል። ----- ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ በመጨረሻ ዘመናቸው ድምጻቸውን ሳያሰሙ በቤታቸው በሰላም መኖር ይችሉ ነበር። ይሁን እንጂ ውርደትን እምቢ ብለው በሰባ አራት ዓመታቸው በማመጽ ወደ ጫካ ገብተዋል። በዚያ ትልቅ ዕድሜአቸው ያካሄዱት አመጽ ለነፃነት ያላቸውን ጥማትና ጉጉት የሚያሳይ ነው። ------- "ኢልማ አዴ ብዙ ከቤ አባ መርዙ" ------ አፈንዲ ሙተቂ ህዳር 22/2017 ----- የቴሌግራም ቻናሌ የሚከተለው ነው። You may join my telegram channel here https://t.me/afandishaHarar ----- ተማም። እናመሰግናለን። Galatoomaa

  • “ከቢር” እና “አርዳ ዊጅ" በሀረር ከተማ ----- አፈንዲ ሙተቂ ------ “ለዕድለኛ ሰው የህይወት ጥሪ ይደርሰዋል” ይባላል፡፡ እኔ ድሮ በዚህ አላምንም ነበር፡፡ ተኣምረኛዋ ከተማ ግን ተስፈንጣሪ አቋሜን ትቼ ከብዙሀኑ እምነት ጋር እንድታረቅ አስገድዳኛለች፡፡1 “እንዴት?” የምትሉኝ ከሆነ ነገሩን በጥቂቱ ላጫውታችሁ፡፡ የዚህችን ከተማ ሾመ-ገናናነት ቀድሞውንም ቢሆን እመሰክራለሁ። በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪቃ በጥንታዊነታቸው ከሚጠቀሱ ጥቂት ማዕከላት መካከል እንደምትመደብም ተጠራጥሬ አላውቅም፡፡ እርሷን በአካል ካወቅኳት በኋላ ግን በመጠነ ሰፊ ተአምራት የተሞላች ባለትንግርት (mystique) መዲና መሆኗ አነቃቃኝና በትንግርቶቿ ላይ አሰሳ ማድረግ ጀመርኩ፡፡ በዚሁ መሰረት በንባብ (reading)፣ በምልከታ (observation)፣ በመጠይቅ (interrogation)፣ በፍተሻ (survey) እና በውይይት (discussion/ dialogue) የማገኘውን ሁሉ ከማስታወሻ ደብተሬ ላይ ማስፈሩን ተያያዝኩት፡፡ አንዳንድ መረጃዎችን ደግሞ እንደኔው ለከተማዋ አዲስ ለሆኑ ወገኖች ማስተላለፍ ጀመርኩ። ይህንን ሁሉ ሳደርግ ታዲያ “ራሴን ላረጋጋበት” 2 ከማለት ያለፈ ሐሳብ መጥቶብኝ አያውቅም፡፡ ጥቂት እንደሰነባበትኩ ግን ከአስገራሚ እውነታዎች ጋር መናበብ ግድ ሆነብኝ፡፡ ለምሳሌም ከተማዋ “የምስራቅ አፍሪቃ ቲምቡክቱ” 3 የተሰኘችበትን ወርቃማ ዘመን ማሳለፏ፣ ከ1750ዎቹ መጨረሻ እስከ 1850ዎቹ መጀመሪያ በዘለቀው ዘመን እርሷን ለማየት ከፍተኛ ጉጉት የነበራቸው የአውሮጳ ምሁራን ከተማዋ ያለበችን ቦታ ማወቅ ተስኗቸው መላውን የአፍሪቃ ምድር ሲያስሱት መክረማቸው ወዘተ... ድሮ የማላውቃቸው እውነታዎች ናቸው፡፡ በዚህን ጊዜም ነበር “እኔ ተራ ሚኒባስ እየጋለብኩ የገባሁባት ከተማ ዓለምን እንዲህ ጉድ አሰኝታ ነበርን? እንደዚያ ከሆነ ምክንያቱ ምንድነው?” የሚል ሙግት በአዕምሮዬ የተከሰተው፡፡ የዚህን ጥያቄ ምላሸ ሳፈላልግም ዕድለኛ መሆኔ ታወቀኝና “ራሴን ላረጋጋ” ማለቱን ከነአካቴው ትቼ ይህንን ድርሳን ለመቀመር “ኒያ” (ልባዊ ውሳኔ) አደረግኩኝ፡፡ * * *** አዎን! ከታላቋ ከተማ ጋር የተዋወቅኩበት አጋጣሚ የህይወት ጥሪ ከደረሳቸው እድለኞች ጎራ አሰልፎኛል። በዕድለኛነቴም ሾለርሡ ላወጋችሁ ነው:: ሾለ ትንግርተኛዋ የጥበብ መንደር! ሀረር! የዕውቀት ሰፈር!....... ሀረር የተወለድኩባትን ከተማ ገለምሶን ትመስላለች፤ አዲስ አበባን ትመስላለች፤ ድሬ ዳዋን ትመስላለች፡፡ ጅማንና ደሴንም ትመስላለች፡፡ በስነ-ጽሁፍ ብቻ የማውቃቸውን ቃሂራን (ካይሮን)፣ ዲመሽቅን (ደማስቆን)፣ ሎንዶንን፣ሮማን፣ አቴናን፣ ፓሪስን፣ ኒውዮርክን ወዘተ…ትመስላለች። ከአሰላም ሆነ ከነቀምቴ፣ ከጎንደርም ሆነ ከመቀሌ የተገኘ ሰው በሀረር ላይ ሲከትም ተመችቶት የሚኖረው ከተማዋ እንዲህ ሁሉንም መምሰል የምትችልበት በመሆኑ ነው። መምሰልና መሆን ግን ለየቅል ናቸው። ሀረር ሌሎችን ብትመስልም ራሷን ብቻ ነች፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የምታውቋቸውን ነገሮች በሙሉ በሀረርም ለማየት አይቸግራችሁም፡፡ በሀረር የሚገጥማችሁን ተአምር ግን ወዴትም ብትሄዱ ላታገኙት ትችላላችሁ፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ሀረርን የረገጠ ሰው ሁለመናው ወደ አዲስ ሰውነት የሚቀየረው፡፡ * * *** “ሁሉንም እየመሰሉ ራሳቸውን ብቻ ሆነው መገኘት የሚችሉ ከተሞችን ጥሩ!” ብትባሉ በቶሎ የሚታወሷችሁ እነማን ናቸው? የናንተን ምላሽ አላውቅም፡፡ እኔ ግን ሁለት ከተሞችን ልጠራላችሁ እችላለሁ፡፡ አንደኛዋ በጽሁፍ ብቻ የማውቃት በጝዳድ ናት፡፡ ሌላኛዋ ከተማ አሁን የምኖርባት ሀረር ናት፡፡ የሁለቱ መመሳሰል ደግሞ በእጅጉ ይደንቃል፡፡ አዎን! በጝዳድና ሀረር በጣም ይመሳሰላሉ፡፡ በዚህም የተነሳ እህትማማች ከተሞች መሆናቸው በሰፊው ይነገርላቸዋል።5 ይህንንም በጥቂት አብነቶች ላስረዳ፡፡ በጝዳድ የኸሊፋዎች መንበር ነበረች - ሃሩን አል-ረሺድን ያስታውሱ፡፡ ሀረር ደግሞ የአሚሮች መንደር ነበረች - አሚር ኑርን ያስታውሱ። በሌላ በኩል ሁለቱም ከተሞች “የአባዲር ከተማ” በመባል ይታወቃሉ። የሼኽ አባዲር ስም በሁለቱም ከተሞች የተከበረ ነው። ሶስተኛው አብነት ደግሞ (ከተሞቹን የሚያመሳስላቸው) ከዓለም አቀፉ አሳሽና ደራሲ ከሰር ሪቻርድ በርተን ጋር ይያያዛል። በርተን በአፍላ የወጣትነት ዘመኑ ላይ ጀብድ የመስራት ስሜት ቢወጥረው ለ“አጭቤነት” ተዳረገና ከርሱ በፊት ያልተሞከሩ አደገኛ የ“ማጭበርበር” ድርጊቶችን ለመዳፈር ቆረጠ። በቅድሚያም “አፍጋናዊ ሼኽ ነኝ” የሚል ካባ ደርቦ ወደ መካና መዲና በመግባት 8 እዚያ ያየውን ነገር ሁሉ ለዓለም ህዝብ አስነበበ፡፡ በዚያው እግሩ ወደ አፍሪቃ ምድርም ተሻገረ፡፡ “የመናዊ ሼኽ ነኝ” በሚል የማጭበርበሪያ ስልት ወደ ሀረርም ገባና ጓዳዋን መረመረ፡፡ የምርመራውንም ውጤት “First Footsteps in East Africa፡ or the Exploration of Harar” በሚል ርዕስ ሾር ለአንባቢያን ላከ። ሪቻርድ በርተን በሕይወቱ መጨረሻ ላይ በጝዳድንም ጎበኛትና ዝነኛውን “The Book of Thousand Nights and a Night” (ወይንም ደግሞ The Arabian Nights) ለዓለም ህዝብ አበረከተ፡፡ 9 ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለቱን መጽሀፍት የሚያነብ ሰው ሀረርና በጝዳድን በደንብ ያውቃቸዋል። * * *** ሀረር በነዚህና በሌሎችም ትንግርቶች የተመላች ናት፡፡ እኔም ላለፉት ሶስት ዓመታት “ዚሸርቂ ኢፍሪቂያ ታዕሊም መርከዝ” 10 ከምትባለው ከዚህች የታሪክና የስልጣኔ አምባ ጋር የ“ከቢር” እና የ“አርዳ ዊጅ” ጥምረት መስርቼ አስገራሚ “ዒልሚ” ስሸምት ከርሜአለሁ፡፡ ሀረር የምታስተምረውን “ማድዲ” ሙሉ በሙሉ ከማጠናቅቅበት ደረጃ ላይ ገና ላይ አልደረስኩም። ስለዚህ “አርዳ ዊጅ” ሆኜ መሰንበት ግድ ይለኛል። ለአሁኑ “ጢት ከቢር” እንድሆን በተፈቀደልኝ መሰረት “ከቢር” ካስተማረችኝ “ዒልሚ” በጥቂቱ እየቆነጠርኩ ላቀብላችሁ ተዘጋጅቻለሁ፡፡ “ቀለም መስበር” ደረጃ ላይ ስደርስ የሚሆነውን ደግሞ በጊዜው አጫውታችኋለሁ። ዕድሜና ጤና ይስጠንና! ---- አፈንዲ ሙተቂ ሀረር ጌይ ጥር 2004 ----- የቴሌግራም ቻናሌ የሚከተለው ነው። You may join my telegram channel here https://t.me/afandishaHarar ----- ተማም። እናመሰግናለን። Galatoomaa

  • ቁጥር ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴንያጠናቀቅኩት በቁጥር ሁለት ት/ቤት ነው፡፡ የትምህርት ቤታችን ዋነኛ ህንጻ በስዕሉ ላይ የምትመለከቱት ነው፡፡ ይህንን ህንጻ የኢጣሊያወራሪዎች ናቸው የሰሩት፡፡በከተማችን ውስጥ ለረጅም ዘመናት በቁመቱ ከርሱ ጋር የሚስተካከል ሰው ሰልሽ ግንባታ አልነበረም፡፡ በዚህም የተነሳ በኦሮምኛ ስሙ “Mana Dheeraa” (ረጅሙ ህንጻ) በማለት ነው የምንጠራው፡፡ የትምህርት ቤቱ የኦፊሴል ስም ነው “ገለምሶ ቁጥር ሁለት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት” ነው፡፡ በተለምዶ ህንጻውን የምንጠራበት “ቁጥር ሁለት” የተሰኘው የአማርኛ ስሙ የተገኘው ከዚሁ ነው፡፡ “ቁጥር ሁለት” (“መነ ዴራ”) በኢጣሊያ ወራሪዎች ዘመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነበር፡፡ ጣሊያኖቹ ሲወጡ የወረዳ ጽ/ቤት ሆኖ ማገልገል ጀመረ፡፡ ከዚያም ወደ አዳሪ ት/ቤት ተቀየረ፡፡ በ1962ገለምሶ የአውራጃ ዋና ከተማ ስትሆን ደግሞ ህንጻው ወደ እስር ቤት ተቀየረ፡፡ በርሱ ምትክም ሌላ ትምህርት ቤት በከተማው የምስራቁ ክፍል ተሰራ፡፡ “ቁጥር ሁለት” እስከ ዘመነ ቀይ ሽብር ድረስ እንደ እስር ቤት ካገለገለ በኋላ በ1972 ገደማ እንደገና ወደ ትምህርት ቤት ተቀየረ፡፡ ሁለቱን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በስም ለመለየት በሚልም “ቁጥርሁለት” የሚለው ስያሜ ተሰጠው፡ እያደገ የመጣውን የተማሪ ብዛት ለማስተናገድ እንዲችልም በርካታ ክፍሎች በግቢው ውስጥ ተሰሩለት፡፡በማስከተልም ሌሎች በርካታየአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በከተማው ውስጥ ተከፈቱ፡፡

  • የትራምፕ የሰላም ቦርድ አባላት እነማን ናቸው? ------- አፈንዲ ሙተቂ ------ የአሜሪካውን ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የጋዛን መልሶ ግንባታ ስራዎች ይመራል፣ ይቆጣጠራል" ብለው በሰየሙት "የሰላም ቦርድ" ውስጥ እነዚህ መሪዎችና ዲፕሎማቶች ተካተዋል። 1. ኢሳ ቢን ሳልማን ቢን ሃማድ (የባህሬን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ሃላፊ ሚኒስትር) 2. ናሲር ቡሪታ፣ የሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 3. ሃቪየር ሚሊ፣ የአርጀንቲና ፕሬዚዳንት 4. ኒኮል ፓሺኒያን፣ የአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር 5. ኢልሃም አሊየቭ፣ የአዘርባይጃን ፕሬዚዳንት 6. ሮሰን ዜክላያዞፍ፣ የቡልጋሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ 7. ቪክቶር ኡርባን፣ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር 8. ፓራቦዎ ሱቢያንቶ፣ የኢንዶኔዥያ ፕሬዚዳንት 9. አይመን አል-ሰፈዲ፣ የዮርዳኖስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 10. ቃሲም ዮማርት ቶካዬቭ፣ የካዛኽስታን ፕሬዚዳንት 11. ቪጆሳ ኡስማኒ ሳዱሩ፣ የኮሶቮ ፕሬዚዳንት 12. ሚያን ሙሐመድ ሺህባዝ ሸሪፍ፣ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር 15. ሳንቲያጎ ፔና፣ የፓራጓይ ፕሬዚዳንት 16. ሙሐመድ ቢን ዐብዱራሕማን አል-ሣኒ፣ የቀጠር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ 17. ፈይሳል ቢን ፈርሃን አል-ሱዑድ፣ የሳዑዲ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር 18. ሀካን ፊዳን፣ የቱርክ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር 19. ኻልዱን ኸሊፋ አልሙባረክ፣ በአሜሪካ የተባበሩት የዐረብ ኢሜሬቶች ልዩ ወኪል 20. ሸቭከት ሚርዚዮዬቭ፣ የኡዝቤኪስታን ፕሬዚዳንት 21. ጋምቦጃቪን ዘንደንሸተር፣ የሞንጎሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ------ ከላይ የተጠቀሱት ልዑካን ትራምፕ ያደረጉላቸውን ጥሪ ተቀብለው በዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ በመገኘት የቦርዱ አባል መሆናቸውን በፊርማቸው አጽድቀዋል። የትራምፕን ጥሪ ውድቅ ያደረጉ የብዙ ሀገራት መሪዎችና ዲፕሎማቶች (እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ኖርዌይ፣ ስዊዲን ወዘተ) አሉ። አንዳንድ ሀገራት ደግሞ (ሩሲያ፣ ስፔን፣ ቤልጅየም፣ ግብጽ ወዘተ) ጥሪ ተደርጎላቸው ጉዳዩን እያጠኑት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የብሪክስ ሀገራት የሆኑት ታላላቆቹ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል አልተጋበዙም። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ፍልስጥኤማዊያን በቦርዱ ውስጥ የሉበትም። አንዳንድ አባላት ደግሞ በግልጽ ጸረ-ፍልስጥኤማዊ ድንፋታ (rhetoric) ሲያሰሙ የነበሩ ናቸው። ለምሳሌ የአርጀንቲናው ፕሬዚዳንት በግልጽ በፍልስጥኤማዊያን ላይ ብዙ ድንፋታና ዘለፋ ሲያሰማ የነበረ ሰው ነው። ትራምፕ ጸረ-አፍሪቃ መሆኑ የታወቀ ነው። ይህንንም በዚህ ዝርዝር ላይ አሳይቷል። በዝርዝሩ ውስጥ ሞሮኮ ያለችበት ስትሆን እርሷም በዐረባዊቷ ነው የተካተተችው። ትራምፕ ሐቀኛ ቢሆን ኖሮ ከታላላቅ የአፍሪቃ ሀገሮች (ደቡብ አፍሪቃ፣ ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ጋና) እና በሚዲያ ተደጋግመው ከሚነሱት ሀገሮች (ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሴኔጋል፣ ካሜሩን) መካከል ጥቂቱን ያካትት ነበር። ትራምፕ ይህንን ማድረግ ይቅርና በቅርቡ በሰላም ጉዳይ ላይ በዋይት ሀውስ ያፈራረማቸውን ሩዋንዳን እና ኮንጎን እንኳ አላስታወሳቸውም። ከሁሉ በላይ የፖለቲካ ተንታኞች በአስቂኝነቱ የወሰዱት ነጥብ ግን በቦርዱ ውስጥ የተወከሉት አንዳንድ መሪዎች ስለፍልስጥኤም እና እስራኤል እዚህ ግባ የሚባል እውቀት የሌላቸው እና ሀገራቸውም በዓለም ፖለቲካ መድረክ ድምጻቸው የማይሰማ መሆናቸውን ነው። ለምሳሌ ፓራጓይ፣ ሞንጎሊያ እና ቡልጋሪያ በዚህ ጎራ ይመደባሉ። --------- ትራምፕ የጋዛን ፕላን አሳምሮ ሰርቶ በስክሪን አሳይቷል። የዓለም ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ ግን ፍልስጥኤም ከአፓርታይድ ኮሎኒ ነፃ ወጥታ ሰላማዊና ሉዓላዊነቷ የተከበረ መንግሥት ሆና ማየት ይፈልጋል። አፈንዲ ሙተቂ ጥር 15/2018 ----- ተማም!

  • The GERD Dam ----- => It belongs to the Ethiopian people. => It is financed by Ethiopian people, not USA => There was no war between Ethiopia and Egypt because of the dam, it was just a dispute => The dispute can be solved through dialogue without interference by USA => The water of the Nile isn't hold because of the dam, the Nile is still flowing to Sudan and Egypt ----- Conclusion: Trump is a bombastic, dump, infuriating, paranoid, delusional leader who doesn't care about any African nations.

  • The best place where one can see the Mirriga in its natural beauty is a clan assembly. This clan assembly is usually lead by the leader of the clan called “abba gosaa” or more commonly “damiina”. The “damiina” is assisted by councilors called “hayyuu”. The “qondaala”, who are known for their Mirriga skills, also act as assistants of the “damiina”. It is the presence of such skilled people in the assembly that would be the source of the beauty of Mirriga song. It must be noted that the clan assembly wouldn’t be gathered for a mere purpose of singing Mirriga. There should be other reasons for hayyus (clan leaders, elders and other elites) to meet at certain place and deal at a clan level. For example, the hayyus may assemble to find solutions for a dispute between two people or to collect finance to be paid as a blood money of a killed person. This act is usually called “gosa bulchuu” (letting the clan to pass the night at certain place or house). The event is sponsored by the person who summoned the clan leaders to resolve his issue; and the clan assembly holds its meeting until it finds out the best way of resolving the problem. It is after the accomplishment of this task that the clan assembly opens the way for Mirriga. And wherever an act of “gosa bulchuu” took place, it is common to see a performance of Mirriga. Thus the Ittu Oromos say Bakka guuzni oole darasiidhaan beekhani Bakka gosti bulte ammo mirrigaadhaan beekhani It can be translated approximately as follows A place where guuzaa passed the day is known by the voice of “Darasii” A place where the clan passed the night is known by the performance of Mirriga --- The Mirriga poems are some of the best preserved examples of the ancient Oromo folk literatures. They are still being transmitted by oral narrations. However, as they are the stores of Oromo tradition and history, they should be documented and made ready for further ethnographic studies. Afendi Muteki September 20/2015 Harar

  • Qallu are usually the religious leaders of the people). “The five who passed the night at Darrabba” refers to the five clans consisting the “Khura” branch of Ittu Oromo. They are called Addayyo, Waayye, Gaamo, Arroojjii and Baaye. These five clans discuss new laws under “Garbii Darrabbaa”- a big acacia tree found two kilo meters north of Oda Bultum. The law drafted at the two places will be brought together at Oda Bultum for the ratification by the tribal assembly. It was only after this process was accomplished that the new laws would be proclaimed at Oda Bultum in the last night of the event. The other verses of the poem refer to the items (Khilla, Khorma, Haqaara) and materials (okholee, okkotee, waraana, siinqee, goojjoo etc) needed to undertake certain ritual ceremonies at Oda Bultum. These rituals were undertaken side by side with the drafting of new laws. The poem says “the eight” because only eight clans undertake these rituals and two clans of Ittu Oromo were exempted from conducting the rituals. One of the two clans exempted from the rituals was the Waayyee who had a responsibility of monitoring the security during the celebration of the congress of Oda Bultum. The second clan was the Qallu who are regarded the people of blessing and healing. * The non-traditional Mirriga poems are those which are composed on specific events or those which an individual poet-singer called “qondaala” composes on his own will. Most of these poems are short lived; they have little chance of spreading in the society and establishing themselves at equal level with the traditional poems. However, they are the determinants in examining the wisdom and eloquence of the “qondaala”. They are also some of the denominators that determine the status the “qondaala” will have in the society and the future prospects he may assume. If the “qondaala” is an incumbent leader of an Ittu clan, then the fame he would get because of his poems may bring him more respects; moreover, his role as a clan leader may increase. If the “qondaala” that composes the new exciting poems is of young age, then it is very likely for him to be the future leader of his clan and to get a place in the leadership of Oda Bultum. The following is a type of non-traditional Mirriga poem that was composed during Haile Silasie era. Bakkan baanu nindhaqe waanin baanu nindhabe Adilee mooraa ciistu diimtuu biraahin dhabe Sagadi sagadi malee, gabbari gabbari malee Yaa Gubbaa Qorichaa waani naaf hiiqun dhabe The poem can be translated as follows I went to the place I said, but I couldn’t find what I wanted I saw “the white cow” in the compound but I couldn’t see the red one Except saying bow down and except saying pay the “gibir” Oh Gubba Qoricha! I couldn’t see any change in my life Although it heavily relies on the poetry skills of “qondaala”, Mirriga is not a solo song; it is performed by a group. Its performance requires usually the elites (hayyuu) of a clan or certain group gathered in a house or under a shade of a tree. When the singing starts, the qondaala (poet-singer) of the clan stands within the crowd by holding his “halangee” (a whip made from skin) and howls the rhythmic Mirriga poems. He starts his singing by the famous two verses. Dhagayi Dhageeffadhu (Hear me, and Listen to me) Guurii gurraa guuradhu (Take way the dust from your ears) Then after, he starts his singing. Whenever he utters one verse of the poem, the crowd will accompany him by replaying with the famous Oromo word “hayyee” (meaning “let it be”). And when the “qondaala” show his ability by composing an extra ordinary poem, the members of the crowd will express their excitement by words like “buli” (long live), “kormoomi” (be strong as a roaring bull), “irra aani” (be able to defeat your enemy) etc…..

  • Mirriga- An Elite Song of the Oromo People ---- Written by : Afendi Muteki ---- Mirriga (also called “Mirriysa) is an epic song very popular among the Eastern Oromos. It is commonly known in the traditions of the tribes of Ittu, Karrayyu and Afran Qalloo. However, from these three groups, Mirriga highly deepens its root among the Ittu Oromos of Carcar (West Harerghe). The reason is that “Ittu” is the Oromo group to whom the foundation and preservation of the famous Oda Bultum is ascribed, and Mirriga is the main genre of song that dominates the events commemorating the ancient caffee assembly of Oda Bultum. “Mirriga” is considered the power house of knowledge and wisdom. The Ittu Oromo say that their tradition, customs, history and ethics are highly enshrined in the Mirriga song. Furthermore, many of the Ittu Oromo tribal laws can be learned easily from the Mirriga poems. Thus the Ittu Oromo say Fooni nyaatti malee adurree ilkaan meetaa Namaatu hinbeyne malee mirrigaa kheessi heera. Meaning The cat eats a meat yet her teeth are “silver” Mirriga is a law internally, yet many people don’t understand. Mirriga is a highly elicitic song that can’t be sung by everybody except those who have a knowledge. It isn’t sung also at everywhere. It is usually performed on two occasions. One is when a senior leaders of a clan and the men at their service come together to discuss an issue that needs consideration at a clan level, or when the leaders and deputies of all clans of Ittu Oromo discuss a tribal issue. The other occasion is the one I said above. That is the celebration of special events like the congress of Oda Bultum. * The Mirriga poems are of two types, the existing (traditional) poems and the non-traditional ones. The traditional poems are those which have been transmitted orally from one generation to the next. The themes of these poems are the Oromo history, culture, tradition and law. These traditional poems are known by most of the clan leaders of Ittu Oromo although there may be variations on the usages of the words of the poems. For a person to be elected as a leader of a clan, the other posts in the leadership of the clan, to be the member of the congress of Oda Bultum or to be elected in the tribal office of Ittu Oromo, he must have a good knowledge of the traditional Mirriga poems. The best example of the traditional Mirriga poem is the following one which the Ittu Oromos regard as “The golden Constitution of Oda Bultum” Afuriin Odaa bule shaniin “Darrabbaa” bule Darraabbaa halkan heeraa gaariin maal hasaasaa bule Okholee saddeetin heeree, okkotee saddeetin heeree Khorma saddeet heeree, khilla saddeet heeree Ciicoo saddeet heeree, haqaaraa saddeet heeree Siinqee saddeet heeree, Dhibaayyuu saddeet heere Waraana saddeetiin heere, fal’aana saddeetin heeree Eela saddeet heere, goojjoo saddeet heeree Daadhii Bookhaa nannaqee, deyma wal-kheessa tufe Mee akka galaana kufee siitu garaa nadhufe. ----- The poem can be translated as follows. The four have passed the night at Odaa, the five passed the night at Darrabaa What did the “wise” whispered in the law-making night of Darrabbaa? He Decreed eight “Okholee”, and eight pots He decreed eight bulls and eight “Khilla” He decreed eight “Ciicoo” and eight “Haqaaraa” He decreed eight Siinqee and eight “Dhibaayyuu” He decreed eight spears and he decreed eight spoons He decreed eight wells and eight huts He prepared a drunk from pure honey, and he breath the same Oh my blood! You have come to my mind as a traveling flood. In the poem, the verse “the four have passed the night at Odaa” refers to the four clans comprising the “Galaan” moiety of Ittu Oromo. They are called Baabbo, Alga, Gaadulla and Elelle. According to the tradition of Oda Bultum, these four clans discuss and draft new laws under the oda tree (Qallu is the fifth clan grouped under this moiety but it is prohibited by the tradition to participate in political affairs; thus the Qallu clan don't take part in the formulation of new laws and the assumption of political power.

  • Americans are under a "Hitler" type leadership.. ------ How did Hitler started the second world war? It was because of his "Lebensraum" rhetoric and policy of greed. While he was running for the 1933 election, Hitler was propagating "Germany deserves additional living space" day and night. When he assumed power, he believed that he would take any land in Europe by force or through negotiations. At first he took many smaller lands by force while UK, USA and France were watching. Next he took Bohemia. In the third step he invaded Poland which was a strong ally of UK, France and USA. That became the start of WWII Trump was propagating a similar thing during his election campaign. First he was frightening Panama. Then he was saying he would make Canada the 51 US state. He was scaring Cuba, Iran, Venezuela, Greenland repeatedly. Two weeks he started his illegal imperialist aggression by attacking Venezuela. He clearly stated that his target is taking that country's oil. Now Trump is frightening Greenland day and night. He says he would impose Tariff on the whole continent of Europe. His rhetoric is an exact copy of Hitler's propaganda. Will he really invade Greenland and torch the WW-3? Time will solve that. But the American society is amazing. They elect this murderer mugal and theft-addicted old man of 80 years who is impeached twice. And when he is shaking the world with his greed and invasion threat, both the Senate and the Congress are watching him as if nothing is happening. Imperialism is exposing itself with its true marks.

  • Sa eedaan qalbiin tuni wahayyuma beyti (ለካስ ይህቺ ቀልቤ የፊቱን ትገምታለች) Baddeeysa ol kunnaan khate gammachutti (በዴሳን ሳልፈው በደስታ ተብከነከነች) Jaalalleen tiyya tun intala Habrootii (ፍቅረኛዬ ለካንስ የሀብሮ ልጅ ነች) አዎን! ዋናው ተስፋ አለመቁረጥ ነው፡፡ ችግር መከራውን ከታገሱት ያሰቡትን ያሳካሉ፡፡ ተስፋን ይዞ ሲባዝን የከረመው ዓሊ ሸቦም ድካሙን ሁሉ ቻለው፡፡ እናም ከውስጡ የተስፋ እንጥፍጣፊ ሳያልቅ የደስታ መዓዛ አወደው፡፡ ከጭሮ ታጥፎ በዴሳን እልፍ እንዳለ ፍቅረኛው ከሩቅ ሸተተችው፡፡ ለካስ ውቃቢው ነው ዝም ብሎ ፈልግ ያሰኘው እንጂ ልጅቱ ቀድሞውንም ቢሆን አልጠፋችበትም? እንደተፈጠረች እትብቷ ከተቀበረባት ቦታ ሆና ትጠብቀው ነበር፡፡ “የት?” ብትሉ “ሀብሮ” ነው መልሱ! የዓሊ ሸቦ ፍቅረኛ የሀብሮ ልጅ ሆና ተገኘች፡፡ ታዲያ “ሀብሮ” ሰፊ አውራጃ ነው እንጂ አንድ ከተማ ወይንም መንደር አይደለም፡፡ ከቁኒ እስከ ባሌ ጠረፍ ድረስ ያለው ተራራማ ምድር ሁሉ የሚካተትበት ክልል ነው፡፡ ስለዚህ የልጅቱ ትክክለኛ አድራሻ መታወቅ አለበት፡፡ ዓሊ ሸቦ የመጨረሻውን ውጤት እንዲህ በማለት ያበስረናል፡፡ Jaalallen gar meeqaan barbaadaan of rakkee (ስንት ሀገር በፍለጋ ያዳረስኩላት ፍቅረኛዬን) Tanin deemee dhabe baakkan itti shakkee (ከሁሉም ቦታዎች ያጣኋት ጉብልዬን) Walakkaa magaalaa Galamsottiin arke (ገለምሶ መሀል ላይ አገኘኋት ወዳጄን) እንዲህ ነው ዓሊ ሸቦ! ብራቮ ዓሊ ሸቦ! እርሱ ከቆላ ደጋ የተንከራተተላት ጉብል የገለምሶ ልጅ ሆና ተገኘች! የወንዜ ልጅ! ግዳዩም በድል ተጠናቀቀ! ዓሊ ሸቦ በሐሴት ባህር ዋኘ፡፡ ነፍሲያውም በደስታ ረካች! በመጨረሻም ዓሊ እንዲህ አለና አጠቃለለ፡፡ Arkadhe qal’o too diimtuu tiyya dheertuu (አገኘሁ የኔን አለንጋ ያላት የደስ ደስ) Isii barnootarra kharaa gala deemtu (ከትምህርት ቤት ወደ ቤቷ ስትመለስ) Gammadeen bahaa mee ree dheebuu tootuu (ዛሬ ጥማቴን ልወጣው የልቤ እንዲደርስ) ----- ዘፈኑን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ፡፡ በቪዲዮው ላይ ካሉት አምስት ዘፈኖች የመጀመሪያው እርሱ ነው፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=How9bBrPeo4 * አንድ የሚነደኝ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? በሸዋ ከተሞች (አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ ወዘተ..) “የገለምሶ ልጅ ነኝ” ከተባለ በሳቅ የሚያውካኩ ሰዎች አሉ፡፡ ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል? አንዳንድ “ውሪ ውሪ” ነጋዴዎች የከተማዬን ስም ከዚያ “ቅጠል” ጋር በማያያዛቸው ነው፡፡ በመሆኑም ገለምሶ ሲባል ብዙዎቹ የሚታያቸው ያ ጫት የሚባለው ቅጠል ብቻ ነው፡፡ ደግሞ እኮ የሚያሳዝነው ቅጠሉ ከዚያ አይደለም የሚጫነው፡፡ አብዛኛው “ከራ ዱለቻ”፤ “ዴፎ”፣ “ቢዮ”፤ “ሚሊሎ” እና “ዳሎ” ከሚባሉ ትንንሽ የገጠር ከተሞች ነው የሚጫነው፡፡ ነጋዴዎቹ ጫቱ “ዳሎ” ወይንም “ሚሊሎ” ቢባል የማይታወቅ ሰለመሰላቸው ነው በከተማዬ ስም የጠሩት፡፡ እነዚህ ከይሲዎች! ጂንኒ ጀቡቲ ሁላ! እርግጥ ጫት በገለምሶም አለ፡፡ ግን ብዙዎች እንደሚያስቡት ገለምሶ በጫት የናወዘች ከተማ አይደለችም፡፡ የዛሬን አያድርገውና ዓሊ ሸቦን እንዲህ በፍለጋ ያንከራተተች “ቀሽቲ” ከተማ ነበረች፡፡ በሀረርጌ ምድር ከሀረርና ከጉርሱም (ፉኛን ቢራ) በስተቀር በእድሜ የሚቀድማት ከተማ የለም፡፡ የወያኔ “በዘበዛ” መጥቶ አደከሟት እንጂ፡፡ ግድ የለም! አንድ ቀን ትነሳለች፡፡ አንድ ቀን ገለምሶም፣ ሀረርም፤ ድሬዳዋም፣ አዳማም፣ ሸገርም፣ ኦሮሚያም፣ አማራም፣ ትግራይም፣ ኢትዮጵያም ሁሉም ይነሳሉ፡፡ ዋናው ተስፋ አለመቁረጥ ነው ጓዶች፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ ----- አፈንዲ ሙተቂ ነሐሴ 2005 በሀረር ከተማ ተጻፈ፡፡ ----- ትክክለኛዎቹ የሶሻል ሚዲያ አድራሻዎቼ የሚከተሉት ናቸው። = የፌስቡክ ፔጅ (My New Facebook Page) https://www.facebook.com/AfendiEthno2018 => የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel) https://t.me/afandishaHarar ----- Thank you..