በክርስቶስ ( in christ)
Статистикаበክርስቶስ ቴሌግራም ቻናል ውስጥ ክርስቶስ ማዕከል ያደረጉ መልዕክቶች ይተላለፋሉ ። @cgfsd
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 49
- 1/48двое суток
- 56
- 1/72трое суток
- 60
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰሞኑን በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ የቲኔጀር ፕሮግራም ነበር ። እየተማሩ የነበረው ትምህርት ኢየሱስ ማን ነው? የሚል ነበር ። አንድ ጥያቄ ጠየቅናቸው " ኢየሱስን እንዴት ማወቅ ይቻላል? አንድ ልጅ እንደዚህ በማለት መለሰ " ኢየሱስን ክርስቶስን ለማወቅ ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ደቀመዝሙር መሆን ነው የሚያስፈልገው " ። @cgfsd
በክርስቶስ ( in christ) pinned «ሰኞ ሰኞ ከአንድ ሳምንት በኋላ live ፕሮግራም እንጀምራል ። በምን ጉዳዮች ላይ ብናጠና ፣ ብንማር ፣ ሰው ጋብዘን ብንነጋገር የምትፈልጓቸውን ጉዳዮች mention አርጉልን comment ላይ ወይም inbox @filicross ትችላላችሁ ።»
ሰኞ ሰኞ ከአንድ ሳምንት በኋላ live ፕሮግራም እንጀምራል ። በምን ጉዳዮች ላይ ብናጠና ፣ ብንማር ፣ ሰው ጋብዘን ብንነጋገር የምትፈልጓቸውን ጉዳዮች mention አርጉልን comment ላይ ወይም inbox @filicross ትችላላችሁ ።
በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ጠዋት ለ30 ደቂቃ ስብከት በመስማት እውነተኛ ደቀመዝሙር መሆን አይቻልም ። እሁድን አርዝምልን !! @cgfsd
https://youtu.be/FwtuuUlx3uA?si=zEADuEZ_OFCXZ-Zj
እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። መዝሙር 145:18
ምስባክ(ፑልፒት) የእግዚአብሔር ቃል ዙፋን ነው ። እስራኤል ቴዎድሮስ @cgfsd
https://youtu.be/d79p2emwuxU?si=FqyqkGF-cDH6J2zT
https://youtu.be/d79p2emwuxU?si=FqyqkGF-cDH6J2zT
ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣ ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል። 2 ሳሙኤል 22:51 አንዳንድ ጥቅስ ግን እያስተዋሉ ማንበብ እንዴት ያለ ነገር መሰላችሁ !
ከቤተክርስቲያን አባት መካከል የሆነው ባስልዮስ በቤተክርስቲያን ስለሚያገለግሏቸው ሰዎች ሲናገር በተለይ በድሆች አገልግሎት ዙሪያ " እያንዳንዱ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ክርስቶስ በድንኳን ነው " @cgfsd
የርስቱን ትሩፍ፣ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል። ተመልሰህ ትራራልናለህ፤ ኀጢአታችንን በእግርህ ትረግጣለህ፤ በደላችንንም ሁሉ ወደ ጥልቁ ባሕር ትጥላለህ። ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል እንደ ገባህላቸው፣ ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም ምሕረትን ታደርጋለህ። ሚክያስ 7:18-20 - መማር ያስደስተዋል ለምን ? * ከርህራሄው የተነሳ * ታማኝ ስለሆነ * ምህረት ስላለው @cgfsd
መፅሃፍ ቅዱስን በዝግታ ፣ በቀስታ፣ ደጋግሞና መላልሶ ማንበብን የመሰለ ነገር የለም 🙅♂️
ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች ጒረኖ ውስጥ ወሰደው፤ ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣ የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው። እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው። መዝሙር 78:70-72
የዕብራውያን መፀሃፍ ውስጥ በተለይ (ዕብ 9:15-22) ላይ "ኪዳን" (covenant) የሚለውን ቃል " ኑዛዜ" ወይም " የአደራ ሰነድ " (will/ Testament) ከሚለው ሕጋዊ ትርጉም ጋር ያዛምደዋል ። የኑዛዜው ሰነድ የሚሰራው ተናዛዡ ሲሞት ብቻ ነው ፤ የአዲሱ ኪዳን በረከቶችም ተፈፃሚ ሊሆኑ የቻሉት በክርስቶስ ሞት ነው ። ለዚህ ነው አዲሱ ኪዳን በደም የተመረቀ ነው የሚባለው ። የክርስቶስ ደም የክርስቶስን ሞትና ራሱን አሳልፎ መስጠት የሚወክል ስለሆነ ። @cgfsd
ዛሬ ምሽት(2:30) የጀመርነውን Pneumatology Class የመጨረሻ ክፍል እንማማራለን። ባለፈው የአብንና የወልድን Eternal relations of origins አይተናል። ዛሬ የመንፈስ ቅዱስን relation of origin to the Father and the Son እናያለን። * መንፈስ ቅዱስ የሚሠርጸው(የሚወጣው) በምዕራቧ ቤተክርስቲያን(በካቶሊኮች እና በብዙ ፕሮቴስታንቶች) እንደሚታመነው Hypostetically…
ዛሬ ምሽት(2:30) የጀመርነውን Pneumatology Class የመጨረሻ ክፍል እንማማራለን። ባለፈው የአብንና የወልድን Eternal relations of origins አይተናል። ዛሬ የመንፈስ ቅዱስን relation of origin to the Father and the Son እናያለን። * መንፈስ ቅዱስ የሚሠርጸው(የሚወጣው) በምዕራቧ ቤተክርስቲያን(በካቶሊኮች እና በብዙ ፕሮቴስታንቶች) እንደሚታመነው Hypostetically ከአብ እና ከወልድ ነው ወይስ በምስራቋ ቤተክርስቲያን እና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን እንደሚታመነው ከአብ ብቻ? (እና ከወልድ Hypostetically ሳይሆን Economically) * መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? Should we affirm the Filioque("..And the Son")? *ሁለቱም የላቲን እና የግሪክ አባቶች(Augustine, Cyril, Basil the great, Gregory Of Nyssa, Athanasius ) ምን አስተማሩ? Hypostetical(Personal)processionን ወይስ Just Economic procession? ይኼ ከነበሩት ቤተክርስቲያንን በ 1054 ዓ.ም ለሁለት ከከፈሉት ጉዳዮች አንዱ ነበር። ሁለቱም አብያተክርስቲያናት ተወጋግዘዋል(ካቶሊኮች በ Lyon ጉባኤ Filioqueን ዶግማ አድርገዋል። የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ደግሞ በበኩሏ ይሄንን ትምህርት Soul damning የሆነ አደገኛ ምንፍቅና ነው ብለው ያምናሉ። ውግዘቱ እኛንም የሚመለከት ነው ምክንያቱም ሁሉም የፕሮቴስታንት ሪፎርመሮች የ Filioqueን Clause affirm ስላደረጉ።) በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የራሳችሁን Research ሰርታችሁ ኑ። እንወያይበታለን። ኦርቶዶክሳዊያን ቢኖሩ ደግሞ የእነርሱንም Perspective ከራሳቸው ለመስማት More በጣም አሪፍ ይሆናል።
@cgfsd
ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤ 1 ጴጥሮስ 3:15
አስር ልጆቿንና ባሏን በጦርነት ያጣች የትግራይ እናት በአንድ ቪዲዮ ተመለከትኩ ፤ ሀዘኗን መቋቋም አቅቷት መናገር ስትቸገር። ምን ያህል ጦርነት አስከፊ እንደሆነ ፀያፍ ተግባር እንደሆነ ግልፅ ነው ። አሁንም የጦርነት ቅስቀሳ አለ እያሉ እናቶች ሲያለቅሱ ልጆቻቸውን ስደት ሲልኩ ማየት እጅግ ያማል። ትግራይ የመሄድ እድል ባይገጥመኝም እዛም ዘመድ ባይኖረኝም እንኳን ከጓደኞቻችን ፣ ከማህበራዊ ሚዲያ፣ በእየ ከተማው ተሰደው የሚመጡን ወጣቶችና አዛውንቶች ሳይ ምን ያህል ጉዳዩ አስከፊ እንደሆነ መረዳት እችላለሁ። ግን ለምን ? ከትናንት ስሕተቶች የማንማረው ይህን ህዝብ ልናፅናናው ከጎን ልንቆም ይገባል ። መፅናናት ያስፈልጋቸዋል! ስለ ሰው ለማዘን ለመጨነቅ የግድ ከእኛ ዘር ሀረግ መሆን የለበትም ለክርስቲያን ባልንጀራው ያገኘው የሰው ልጅ በጠቅላላ እንጂ የዘር ሀረጉ ብቻ አይደለም ።ጦርነት እንዲቆም ፣ እናቶችና አባቶች እንዲፅናኑ ፣ ልጆች በሰላም እንዲኖሩ የመፀለይ ግዴታ አለብን ። እግዚአብሔር ሆይ በቃ በለን 😭 ህዝብን አስብ ። እንፀልይ !😭😭