Hu sisters ministry
Статистика“ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።” ምሳሌ 31፥30 Leaders contact Wengel: 0996797989 Hawi: 0984980563 Eden :0956918445 Salem: 0966441194
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 10
- Всего постов
- 31
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 142
- 1/48двое суток
- 162
- 1/72трое суток
- 175
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ስለነበረን የፀሎት ጊዜ እግዚአብሄር ይባረክ። ሳምንትም በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥል ይሆናል። ተባረኩ🙌
Live stream finished (58 minutes)
Live stream started
እንዴት አደራችሁ የፌሎሺፓችን እህቶች? የማለዳ ፀሎታችንን ልንጀምር ትንሽ ደቂቃዎች ብቻ ነው የቀሩን join እንድታደርጉና አብረን እንድንፀልይ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን። ተባረኩ🙌
✨ሰላም ውድ የፌሎሺፓችን እህቶች እንደምን ቆያችሁ?✋ ከዚህ ቀደም እያደረግን እንደነበረው ቅዳሜ ጠዋት የነበረን የማለዳ ፀሎት ነገም ጠዋት 12:00 -1:00 "እውነተኛ ንስሀ" በሚል ርዕስ የሚቀጥል ይሆናል። አብረን በጌታ ፊት በፀሎት እድንሆን ጋብዘናችኋል። ተባረኩ🙌 #Husistersministry https://t.me/sistersmi
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ፀሎት:በእህት በረከት
ኑሃሚን 📌በመጽሐፈ ሩት ምዕራፍ 1 ላይ እንደምናየው ኑኃሚንና ቤተሰቧ በቤተልሔም ይሁዳ የእግዚአብሔር ኪዳን እና መገኘት በነበረበት ስፍራ ይኖሩ ነበር። 👉 ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ታላቅ ራብና ፈተና በደረሰ ጊዜ መፍትሔውን ከእግዚአብሔር በመጠበቅ ፈንታ ችግሩን በራሳቸው መንገድ ለመፍታት ወስነው ወደ ባዕድ አገር ወደ ሞአብ ኮበለሉ ይህ ከእግዚአብሔር ስፍራ የመውጣት ውሳኔ ለጊዜው መሸሸጊያ ቢመስልም በባዕድ ምድር ያጋጠማት ግን ታላቅ ባዶነት ነበር ኑኃሚን በዚያ ባሏን ሁለቱን ልጆቿን በሞት በማጣት (ሩት 1:21) በሙላት ወጣሁ፤ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ ብላ እስክትል ድረስ መሪር ሐዘን እንደገጠማት እንመለከታለን ። 📌ሆኖም እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጎበኘ በሰማች ጊዜ የእግዚአብሔር መገኘትና ፈቃድ ወደ ሚገኝበት ቦታ ቤተልሔም ተመለሰች እግዚአብሔርም በዚህ ስፍራ ባዶነቷን በምራቷ በሩት በኩል ሲሞላ እንዲህ ሆነ 👉የዳዊትና የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ ግንድ የሚሆን ተስፋን አገኘች! የት? ስንል🤔 የእግዚአብሔር መገኘት ባለበት ስፍራ ስትገኝ እንደሆነ እንመለከታለን 👉ታዲያ ከዚህ እኛ ምን ልንማር ይገባናል? እያንዳንዳችን በሕይወታችን ምንም ያህል ታላቅ ፈተና ቢገጥመን በፈተናው ውስጥ እግዚአብሔር ባስቀመጠን ረድኤቱ በሚገኝበት ስፍራ ላይ ጸንቶ መቆምን ነው! 👉ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሚገኝ ሙላት የለም ወደ ህልውናው ስንመለስ ግን አምላክ ያጣነውን ሁሉ የመተካትና የማደስ ኃይል አለው ነገር ግን አስቀድመን በማንኛውም ሁኔታ ስፍራችንን ልጠብቅ ጸንተንም በመቆም መታገስ እንጂ እግዚአብሔር በማይገኝበት ስፍራ ልንገኝ አይገባም::
ሰላም👋 ውድ የ HU fellowship እህቶች የጌታ ፀጋ እና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን 🙌 ✨መልካም ሳምንት እንዳሳለፋችሁ ተስፋ እናደርጋለን። 👉በዚህ ሳምንት ደግሞ በ Hu sisters ministry telegram channel "ኑሀሚን"በሚል ርዕስ እንቆያለን እግዚአብሔር በብዙ ያስተምረናል።አብራችሁን እንድትቆዪ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን፡፡ 💫 እንዲሁም hu sisters ministry telegram channel join ያላደረጋቹ እህቶች ከታች ባለው link join እንድታደርጉ እየጋበዝን ሌሎች join ያላደረጉ እህቶችም ካሉ join እንዲያደርጉ ጋብዙዋቸው፡፡ ተባረኩ!🙌 👇👇👇 Telegram channel:https://t.me/sistersm
ለዳሳንች ሕዝብ እንፀልይ ያዕቆብ 5:16 ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል። ጌታ ሆይ ዛሬ በፊትህ ይሄንን ሕዝብ ይዘን እንፀልያለን የወንጌልህ ብርሃን ለዚ ሕዝብ እንዲበራ የመዳንን መንገድ ማስተዋል እንድችሉ አይኖቻቸው እንዲበሩ የመኸሩን ሰራተኞች ወደዚህ ሕዝብ እንዲፈጥኑ በጌታ በኢየሱስ ስም ፀለይን አሜን
ስለነበረን የፀሎት ጊዜ እግዚብሄር ይባረክ ሳምንት ቅዳሜ በሌላ ርዕስ የማለዳ ፀሎት ፕሮግራማችን ይቀጥላል። ተባረኩ🙌 #hu_sistersministry
Live stream finished (57 minutes)
Live stream started
ሰላም የተወደዳቹህ እህቶቻችን live ፀሎት ልንጀምር ትንሽ ደቂቃ ስለቀረን ሁላችሁም join እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን ። ተባረኩ🙌
ወደ ሮሜ ሰዎች ፩:፲፮ --- ፲፮፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
ወደ ሮሜ ሰዎች ፲፫:፲፩ -------------------------------- ፲፩፤ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ✨ሰላም ውድ የፌሎሺፓችን እህቶች እንደምን ቆያችሁ?✋ መልካም ጊዜን እያሳለፋችሁ እንደሆነ እምነታችን ነዉ ። ከፊታችን ያለው ቅዳሜ ማለትም ነገ ጠዋት 12:00 - 1:00 በ Hu sisters ministry channel ላይ "መንፈሳዊ ንቃት" በሚል ርዕስ live የማለዳ ፀሎት ይኖረናል። ስለዚህም እህቶች በፀሎት አንድ ላይ በእግዚአብሄር ፊት እንሆን ዘንድ በጌታ ፍቅር ሁላችሁንም ጋብዘናችዃል:: ተባረኩ🙌 #Husistersministry https://t.me/sistersmi
видео или голосовое, без подписи
የእግዚአብሄር ቃል፡ በእህት ረድኤት
ወንጌልና የዘመኑ ክፍተቶች 👉በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ወንጌል ማለት፣ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ ሞት፣ ትንሣኤ እና ክቡር መንግሥቱ አማካኝነት ለሰው ልጆች ያደረገውን የማዳን ሥራ የሚያበስር መልእክት ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፲፭:፫-፬ ---------------------------------------------- ፫፤ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ ፬፤ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ 👉ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መቅረቡን፣ ሰዎች ንስሐ ገብተው በእርሱ እንዲያምኑ፣ ደቀ መዛሙርት ሆነው አዲስ ሕይወት እንዲኖሩ የሚጠራ የእግዚአብሔር መልእክት ነው። 👉ስለዚህ ወንጌል ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የመጣው የድነት፣ የእርቅ፣ የተስፋ እና የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ነው። 👉በዚህ ዘመን ያሉ ክፍተቶችን ስናይ ከሁሉ የሚበልጠው ክፍተት የወንጌልን የመመስከር ቴክኒክ ማጣት አይደለም። ዋነኛው ክፍተት ወንጌልን በማወቅና በሕይወት በመኖር መካከል ያለው፣ ወንጌልን በማመንና ስለ እርሱ መሥዋዕት ለመሆን ፈቃደኛ በመሆን መካከል ያለው፣ እንዲሁም ድነትን በመረዳትና የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልዕኮ በመቀበል መካከል ያለው ክፍተት ነው። 📌ዛሬ በዋነኝነት እንደ ክፍተት የሚታዩት ትንሽ እንጥቀስና በሚቀጥሉት ቀናቶች ደግሞ የቀሩትን እንመለከታለን። 👉 የተሳሳተ አመለካከት ወንጌል የድነት መልእክት ብቻ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መልእክት፣ የሕይወት ለውጥ ጥሪ እና የደቀ መዝሙርነት ጥሪ ነው። ስለዚህ በምድር ላይ የመቆየታችን ዋና ተልዕኮ መሆኑን መረዳት አለብን። ትክክለኛውን ወንጌልና የክርስቶስ ሞት የተረዳ ክርስቲያን አጠገቡ ያለው ወንድሙ መጥፋት የሚያሳዝነውና ግድ እንዲለው የሚያደርግ ነው።አሁን ላይ አብዛኞቻችን ትኩረት የምንሰጠው ለራሳችን መንፈሳዊ ዕድገት በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለን ቆይታ ነው ይህ በጣም ጥሩ ነገር ቢሆንም በዚሁ ልክ ስለሌሎችም በጨለማ ስላሉት ልናስብላቸው ያስፈልጋል። እኛ ከእግዚአብሄር ጋር ስላለን ህብረት እንደምንጨነቅ ሌሎች እንዲኖራቸው ደግሞ ልንፀልይላቸው ና ወንጌልን ልንነግራቸው ያስፈልጋል። 👉ምቾትና ቁሳዊ አስተሳሰብ (Materialism) 📌በዘመናችን ወንጌልን ለመመስከር ካሉት ትልልቅ ክፍተቶች አንዱ ምቾትንና ቁሳዊ ነገሮችን ከክርስቶስ ተልዕኮ በላይ ማስቀደም ነው። ብዙ ክርስቲያኖች የሕይወታቸው ዋና ግብ ምቹ ኑሮ፣ የገንዘብ ብዛት፣ የሥራ ስኬት፣ የማኅበራዊ ክብር ወይም የግል ደህንነት እንዲሆን ይፈልጋሉ። እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ኃጢአት ባይሆኑም፣ የክርስቶስን ጥሪ ሲተኩ መንፈሳዊ አደጋ ይሆናሉ። 📌የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ለወንጌል ሲል ሀብትን፣ ምቾትን፣ ነፃነትን እንኳን ለመተው ዝግጁ ነበረች። ሐዋርያት መከራን፣ እስራትን፣ ረሃብን እና ሞትን ቢገጥማቸውም ወንጌልን አልተዉም። ለእነርሱ የክርስቶስ መንግሥት ከዓለማዊ ምቾት እጅግ የላቀ ዋጋ ነበረው። ዛሬ ግን በአንዳንድ ጊዜ ወንጌልን በመመስከር ምክንያት ሥራችንን፣ ዝናችንን ወይም ምቾታችንን እንዳናጣ እንፈራለን። ይህ ፍርሃት በጸጥታ እንድንኖር እንጂ ስለ ክርስቶስ በድፍረት እንዳንናገር ያደርገናል። መፅሀፍም እንዲህ ይለናል፦ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ፩:፳፯ --------------------------------------- ፳፯፤ ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ። ወንጌል ከማንኛውም ቁሳዊ ሀብት፣ ስኬት ወይም ምቾት የበለጠ ዋጋ እንዳለው በሕይወታችን ልናሳይ ይገባል። ተባረኩ🙌