tgindex
E

EBC Ethics Department

Статистика
@ebcethicsанглийский

Integrity is our currency to fight corruption

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
ещё не заходили
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
409
0 за сутки
Сутки
 
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
623
20 постов
Вовлечённость
152,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
136
1/48двое суток
155
1/72трое суток
168

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP)፡- ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈጸሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እንዲሁ በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሰዎች ዝውውር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሲስተምን በማዛባት እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እንዲሁም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ 44 ደላሎች እና አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ሕገ-ወጥ ፈቃድ የነበራቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ ታሽገዋል። በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ፡- የግብር ውሳኔዎችን በመቀነስ፣ ሐሰተኛ ደረሰኞች በማወራረድ፣ እና በሲስተም መረጃ በማጥፋት የመንግሥት ገቢን ባሳጡ አካላት ላይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል። በራሳቸው፣ በዘመድ እና በሹፌሮቻቸው አካውንት በመጠቀም የጥቅም ትስስር የፈጠሩ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከእነዚህ መካከል 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት እንደማንኛውም ፈተና በጽናት እየተጋፈጣቸው መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል። መንግሥት ሌብነትን ለማጥፋት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በዲሲፕሊን የታነጸ አመራር ለመገንባት ቁርጠኛ ነው" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ሕዝቡ በስፋት የሚያነሣቸውን "ሌብነትን አስቁሙልን" ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረዉ ጠንካራ እርምጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ፣ ሕጋዊ መብቱን በመደለያ ባለመጠየቅ እና ከሕገወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገርን ከሕገወጥነትና ሙስና የመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

  • ይህንን የተደራጀ አሻጥር ለመግታት መንግሥት እና የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን አሻጥሩን ማክሸፍ መቻሉ ተገልጿል። በሌላ በኩል በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት ረገድ መንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ እናትዓለም በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ የፈጸሙ እና ተቋማዊ አሻጥር በሠሩ አመራሮች እና ሌሎች የጥቅም ትስስሮችና ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። በተለይም በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሰፍኗል ሲሉ ገልጸዋል። በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሙስና እና አሻጥር ወንጀሎችን ለማረም በተወሰዱት ሰፊ ኦፕሬሽኖች እና ሕግ የማስከበር እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ በማሰብ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ እንዲንር ሲያደርጉ የነበሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ባለቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል። በፋይናንስ ተቋማት እና የገንዘብ ዝውውር፡- በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓል። ለሕገ-ወጥ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ የነበሩ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ ታግደዋል፤ ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የህግ ተጠያቂነት ሰፍኗል። በቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች፡- የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ ታግዷል፡፡ በማዕድን ዘርፍ ሕገ-ወጥ ዝውውር፡- የወርቅ ምርትን ከገበያ ውጭ በኮንትሮባንድ በማስወጣት ወንጀል የተሳተፉ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን፣ አምራቾችን እና የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሕገ-ወጥ ወርቅ፣ የወርቅ ሚዛንና ማቅለጫ፣ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ አንጻር፡- በሕገ-ወጥ መንገድ የሽፋን ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት፣ ነዳጅ በመደበቅ እና አየር በአየር በመሸጥ ወንጀል የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከ650 በላይ ግለሰቦች፣ ማደያዎች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃ ተወስዷል። በአፈር ማዳበሪያ ግዢ አሻጥር፡- በተቋሙ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈጸም በማድረግ ሆን ብለው ችግር በፈጠሩ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃ ተወስዷል።

  • ሙስናና ሕገ-ወጥ አሠራር የተሳተፉ አካላት ላይ የሕግ እርምጃ ተወሰደ ************************ ( ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ። የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ሰፋፊና አስደናቂ ሀገራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሂደት ግን ይህ ውጤት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አመላክተዋል። ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሻገር፣ ሕገ-ወጥነት እና የሙስና ተግባራት የልማቱ ዋነኛ ፈተና ሆነው መቆየታቸውንም ክብርት ሚኒስትሯ አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የሕገ-ወጥነት ችግር በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸው፣ ከውስጥም ከውጪም ያሉ በርካታ ኃይሎች በተደራጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር። በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በልማት ድርጅቶች፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በግለሰቦች እና በተገልጋዮች ጭምር በተደራጀ መንገድ በስፋት የሚታይ ነው። እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዐቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጽሙ ቆይተዋል" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ድርጊቱ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ፣ የዋጋ ንረትና ኮንትሮባንድ እንዲባባስ እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አስታውቀዋል።

  • “ሌብነት ጠቃሚ አይደለም፤ ማስረጃ ማግኘት በህግም በአስተዳደርም ርምጃ ለመውሰድ ያግዛል፤ ሌብነት ክፉ መሆኑን አምነን መጀመሪያ ራስን መታገል አልፎ ሲሄድ ደግሞ በህግ የሚያስጠይቅ ማስረጃ መያዝ ጠቃሚ ይሆናል፡፡” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

  • без подписи

  • ይሁን እንጂ፣ የፀረ-ሙስና ትግል የመንግስት ወይም አስፈጻሚው አካል ብቻውን የሚከላከለው ተደርጎ አጥብቦ የመረዳት ሁኔታዎች ይስተዋላሉ። በባለድርሻነት የተዘረዘሩት ተቋማት፣ በቅድሚያ የራሳቸውን ተቋማዊ አሰራር ሥርዓት የግልጽነትና ተጠያቂነት ባህል ማላበስ ይጠበቅባቸዋል። በጋራ ተቀናጅተው የአገር ህልውና ሥጋት የሆነውን ሙስና ያለማመንታት በባለቤትነት መታገልና መግታት ይገባቸዋል። በሌላ በኩል፣ የሙስና ወንጀል ከላይ በተዘረዘሩት ተቋማት ውስጥ በተሰገሰጉ ግለሰቦች ቢፈጸም የሕግ እና አስተዳደራዊ ተጠያቂነትን በግልጽነት እና ያለአድሎ ማረጋገጥ የግድ ያስፈልጋል። የሙስና ወንጀል ውስብስብነት፣ ሚስጢራዊነት እና ጣልቃ ገብነት የመከላከል እና ሕግ የማስከበር ሚና በተቀላጠፈ እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማከናወን ነጻና ገለልተኛ የሆነ አገራዊ ጥርስ ያለው የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መፍጠር ዘመኑ የሚመጥን የብልህ እርምጃ ይሆናል። ለኢትዮጵያ የሚበጀው፣ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር፣ የሕግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ፣ በየትኛውም የሥልጣን እርከን ያለ ግለሰብ እና የጥቅም ትስስር ቡድን ሙስና ወንጀል መፈጸሙ ቢጠረጠር እውነተኛ ማስረጃ በማመንጨት መርምሮ፣ ከሶና አስቀጥቶ፣ በሙስና የተመዘበረ ሀብት ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር መዳረሻዎች በውጤታማነት የሚያስመልስ ጥርስ ያለው የሕዝብ ቅቡልነትና ታማኝነት የሚያረጋግጥ ተቋማዊ ብቃት ለመፍጠር አገራዊ የጋራ መግባባት የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። የፀረ-ሙስና ትግል የሁሉም ባለድርሻዎች የጋራ እና አገራዊ ኃላፊነት በመሆኑ፣ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች በሕገ-መንግስቱ ጭምር በማመላከትና የፀረ-ሙስና ተለዋዋጭ ሁኔታን የሚያስተናግድ የመደበኛ ህጎች ተፈጻሚነት ማላቅ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ አንገብጋቢ ሆኖ ይታያል። የኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ትግል ለመምራት ወሳኝ የሆኑ ዓለምአቀፍ ስታንዳርድ የሚያሟሉ እና አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ያማከሉ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ያሉ ቢሆንም የማስፈጸም ውስንነት ይታይባቸዋል። ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

  • ግንዛቤ ያሳድጉ፣ አስተያየት ይስጡበት! **************** የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር የፀረ-ሙስና ሥርዓት ግንባታ እንደአንድ የምክክር አጀንዳ ለይቶ በማቅረቡ፣ ተመካካሪዎች እየመከሩበት መሆኑ ይታወቃል። ይህ በአገራችን የተቋማት የሙስና ችግር የመቋቋም እና የትውልድ ሥነምግባር ብልሽት የማስተካከል ምክረ-ሐሳብ የሚገኝበት እና መግባባት የሚፈጠርበት ታላቅ ምዕራፍ ነው። የፀረ-ሙስና ትግል ባለድርሻዎች በቀዳሚነት ዜጎች ናቸው። ዜጎች፣ ሥነምግባራዊነት የመላበስ እና ሙስናን በጽናት የመታገል አገራዊ ግዴታ አለባቸው። ይህን በተግባር ማረጋገጥ የሚቻለው ብቁ የፀረ-ሙስና ትግል ሥርዓት በመዘርጋት ብቻ ነው። አልያም፣ መፈክር ብቻ ሆኖ ይቀራል።  በተቋማት ደረጃ፣ ሁሉም የመንግሥት አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የትምህርትና ማህበራዊ ተቋማት፣ ሚዲያ፣ ሲቪክ ማህበራት፣ እንዲሁም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀቶች እና የቢዝነስ ድርጅቶች መሆናቸውን መመልከት ይቻላል። የፀረ-ሙስና ትግል የሀገር ህልውና የማስጠበቅ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ከዚህ በታች አሳንሶ ማየት፣ ምናልባትም አገር ያለመችውን የብልጽግና ጉዞ አሳንሶ ከማየት ባሻገር፣ የአገር ሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታን የሚያስተጓጉል ይሆናል። ሙስና አደገኛ ካንሰር ነው። ተቋማትን እንደነቀዝና ካንሰር ከሥር ቦርቡሮ ባዶ የሚያደርግ ጨካኝ ጉዳይ ነው። ተቋማት የዜጎች እና የሕዝብ የጋራ ሀብት እስከሆኑ፣ በጋራ ከሙስና የመታደግ ግዴታ ማበጀት ያስፈልጋል። ማንም ችግሩን ከዳር ቆሞ መመልከት አይገባም፤ ይልቁን ተባብሮ በመታገል አሽቀንጥሮ መጣል ያስፈልጋል። ከሥሩ መንቀል ግድ ይላል።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ሌብነት ጽዩፍ ቆሻሻ ነገር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ************************************** (ሰኔ 30/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በሚመለከትከህዝብ ተወካዮች አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ፤ ሌብነት ጥዩፍ ቆሻሻ ነገር ነው፤ ደግሜ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው መግስታዊ ሌብነት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ለመንግሥት የሰጠው ድጋፍ ለዕቅዶች ስኬት እና ለሥርዓታዊ ሌብነት መጥፋት ያለውን ተስፋ እንደሚያመላክት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠን የተጀመሩ የኢኮኖሚና የፀረ-ሙስና ጥረቶችን በማጠናከር፣ የአገልግሎት አሰጣጥን አሻሽለን ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ሀገር እንድናስረክብ የጣለብንን አደራ ለመወጣት ነው ሲሉምአጽንኦትሰጥተዋል። በዚህም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሻሻል፣ ሌብነትንና ሙስናን ለማጥፋት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።

  • ሴቶች ትውልድን የመቅረጽና ሙስናን የመከላከል ሚናቸው ላቅ ያለ ነው! ****** ​ ሙስና የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መሰረት የሚናድ ትልቅ ወረርሽኝ ነው። ይህንን እኩይ ተግባር ለመዋጋት በሚደረገው ጉዞ ደግሞ የሴቶች ሚና የላቀ ነው። ሴቶች በትውልድ ቀራጭነታቸው፣ በስራ ታማኝነታቸው እና ለፍትህ ባላቸው ቀናኢነት የፀረ-ሙስና ትግሉ ግንባር ቀደም መሪዎች እና የለውጥ ሐዋርያት ናቸው። ​ሴቶች በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ ያላቸውን ልዩ ጥንካሬ እና ሚና የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተጠቃሾች ናቸው። ​👉 የማህበራዊ እሴት ታማኝነት፦ ሴቶች በአብዛኛው በማህበረሰቡ ውስጥ ካላቸው የእናትነት እና የቤተሰብ መሪነት ሚና አኳያ፣ ለታማኝነት እና ለቅንነት ቅርብ ናቸው። ራስ ወዳድነትን አሸንፎ ለሌሎች የመኖር፣ የማስተማር እና የማረቅ ባህሪያቸው በስራ ቦታዎች ላይ ሲንጸባረቅ ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር በር የሚዘጉ ይሆናሉ። ​👉 የትውልድ ቀራጭነት ሚና (ከቤት እስከ ማህበረሰብ)፦ ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ሥነ-ምግባር ያለው ትውልድ መፍጠር ቀዳሚው ተግባር ነው። ሴቶች ልጆችን በቅንነት፣ በሃቀኝነት እና በሌሎች መብት አለመጋፋት እሴቶች ኮትኩተው በማሳደግ ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው። የሙስናን አስከፊነት ከቤተሰብ ጀምረው የሚሰብኩ እናቶች፣ ነገ ሀገርን የሚረከቡ ንጹሃን ዜጎችን ያፈራሉ። ​👉 በአመራር ቦታዎች ላይ የሚያሳዩት ጥንካሬ፦ ሴቶች ውሳኔ ሰጪ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲቀመጡ፣ ህግን የማክበር እና የመተግበር ዝንባሌያቸው ከፍተኛ ነው። የግል ጥቅምን ከማሳደድ ይልቅ የጋራ እድገትን እና ፍትሃዊነትን ስለሚያስቀድሙ፣ የመንግስት እና የህዝብ ሃብት ለታለመለት አላማ ብቻ እንዲውል በማድረግ ረገድ የላቀ ጥንካሬ ያሳያሉ።

  • #ሌብነት ክፉ ሥር ነው! ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

  • አሰራርን ከግል ፍላጎት ማጽዳት ለሙስና መከላከል ዋነኛው መፍትሔ ነው! ************************************************ አሠራርን ከግል ፍላጎት ለማጽዳት ውሳኔዎችን በግለሰቦች ፍላጎት ሳይሆን ግልጽ በሆኑ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ደረጃዎች ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል። ሙስና የሚመነጨው በአብዛኛው ግለሰቦች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተጠቅመው የራሳቸውን ወይም የዘመዶቻቸውን ፍላጎት ለማስቀደም ሰፊ ክፍተት ሲያገኙ ነው። አንድ አመራር ወይም ባለሙያ የሕዝብን/የተቋምን ኃላፊነት ከግል ወይም ከቤተሰብ የንግድ ጥቅም ጋር የሚያጋጭበትን ዕድል ሙሉ በሙሉ መዝጋት ይኖርበታል። አሠራር ከግል ተጽዕኖ ሲጸዳ ተቋማዊ ሥርዓቱ ግልጽና ሊተነበይ የሚችል ይሆናል።

  • без подписи

  • 9 апр.1 9122

    без подписи

  • без подписи

  • 27 янв.3 264111

    без подписи

  • 7 янв.1 14211

    без подписи

  • 29 дек.1 2351

    без подписи