የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)
Статистикаበዚህ የቴሌግራም ገጽ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቁ ስርዓተ አምልኮና ትምሕርቶች ይቀርብበታል። ክርስቲያናዊ የሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮችም ይነሱበታል። " ያየሁትን እናገራለሁ የሰማሁትን እመሰክራለሁ! "
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 263
- 1/48двое суток
- 1 447
- 1/72трое суток
- 1 561
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰው ሁሉ እንደ መቤታችን ንጹህ፣ልዩ፣ ጻድቅ፣ ክቡር፣ በልቡ ትሁት፤ ተዘክሮተ እግዚአብሔርን ገንዘብ ያደረገ ሊሆን ይገባዋል። የክርስትና ምሳሌአችን ለሆነችው ለእመቤታችን ጾም እንኳን አደረሳችሁ🙏
" ስለ እግዚአብሔር ብለህ ምን ተውክለት ??" +========++++++++++++++====+ ብዙ ለተወልህ ለእግዚአብሔር አንተ ስለ እርሱ ስትል ምን ተውክለት? ስለ እግዚአብሔር ብሎ መተው እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ህያው ምስክራችን የእምነት አባታችን አበ ብዙኃን አብርሃም ነው። አብርሃም ገና በጥላው ውስጥ በሕገ ልቦና ዘመን እየኖረ ስለ እግዚአብሔር ቤቱን፣ንብረቱን፣ዘመዶቹን፣ሀገሩን ጥሎ ወደ ማያውቀው ሀገር አምላኩን ብሎ የሄደ፤ ስለእግዚአብሔር ብሎ ሁሉን የተወ የእምነት ሰው ነው። አብርሃም ዘመኑ ካለፈ፤ሰውነቱ ከዛለ፤ ዓይኑ ከፈዘዘ፤ጉልበቱ ከደነዘዘ በሗላ በስተርጅና ያገኘውን፤ በስስት የሚያየውን ለልቡ ተስፋ፤ ለዓይኑም ማረፊያ የሆነ አንድ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር መስዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ ሲለው። እሺ ብሎ በመታዘዝ ልጁን መስዋት አድርጎ ያቀረበ፤ በእውነት የማይረባንን፣ የማይጠቅመንን፣የተጎዳንበት ነገር እንኳ ስለ እግዚአብሔር ብለን አንተውም ላልን ለእኛ ትልቅ ተግሳጽ የሆነ አባት ነው። እርሱ አንድ ልጁን እንኳን ስለእግዚአብሔር ብሎ ተወ። ስለ እውነት የማይጠቅመንን ዝሙት፣ሐሜት፣ምቀኝነት፣ ስካር፣ ዘረኝነት፣ክፋት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ያቃተን እኛን ጌታ ወደ እኛ መጥቶ " የሚጠቅመንን፣ የምንሳሳለትን፣የምንወደውን ነገር አብርሃምን እንዳለው ተዉ" ቢለን ምን ብለን እንመልስለት ይሆን? ስንት ጊዜስ መጥቶ አልታዘዝ ብለን፤እምቢ ብለን መልሰነው ይሆን? የተወደዳችሁ ሆይ የበዛ ኃጢአታችሁን ለተወላችሁ፤ ያየባችሁን ላላሳየባችሁ፣ ስለ ብዙ በደል ፈንታ በእልፍ ምሕረት ዛሬን ላሳያችሁ፤ " ስለ እኔ ብሎ ሁሉን ይተዋል ብሎ ዘጠና ዘጠኙን በጎች ትቶ ወደ እናንተ ለመጣ ጌታ ምን ተዋችሁለት? አምላካዊ ክብሩን ጥሎ በትሕትና በበረት ለተገለጠው ጌታ ምን ተዋችሁለት? የእሳት ቀሚሱን ትቶ እራፊ ጨርቅ ለብሶ በቤተልሔም ለታየው ጌታ ምን ተዋችሁለት? የዓለም ዓለሟ የሆነ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ኢየሩሳሌም ትቶ ወደ ግብጽ ለተሰደደ ጌታ ምን ተዋችሁለት? የእሳት መጎናጸፊያውን ትቶ ሄሮድስ ሊዘብትበት ቀይ መጎናጸፊያ ላለበሰው ጌታ ምን ተዋችሁለት? አምላካዊ ክብሩን ትቶ፣በደም ተለውሶ፤ምራቅ ተፍቶበት፣የእሾህ አክሊል ለብሶ ለተመለከታችሁት ጌታ እርሱ ይህን ሁሉ ለእኛ ከሆነ ስለ እርሱ ብላችሁ ምን ተዋችሁለት? ❤ ጌታዬ ሆይ እንደ አብርሃም የምወደውን፤የምሳሳለትን ነገር ስለ አንተ መተው ቢጠበቅብኝም፤ እኔ ግን ዛሬም የምጠላውን ኃጢአት እንኳን ስለ አንተ መተው አልቻልኩምና እኔ ኃጢአተኛውን እርዳኝ 🙏 ✍️ ኤፍሬም ሀብተ ማርያም አዳማ-ኢትዮጵያ 👉በቴግራም :- @ephrem_views ...
የእኛ የኦርቶዶክሳውያን ትልቁ ችግራችን ጀግና መጠበቅ አናውቅበትም። በኢኮኖሚ ፣በፖለቲካ፣በሚዲያ ወደ ፊት የመጡ ልጆቻችንን ከነ ሀሳብ ልዩነታችን በአንዲት ከኦርቶዶክሳዊት ሕብረት ውስጥ በመሆናችን ብቻ አብረናቸው እንዳለን እንዲሰማቸው ማድረግ አንችልበትም። በብዙ መመዘኛ እሸቱ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሁሉም ነገር ቅርብ ነው። እርሱን አይዞህ ማለት የሚጠቅመው ከእርሱ ባሻገር ለእኛም ነው። ሚዲያ በዚህ ዘመን አቅም ነው። ይህ አቅም በግልም በተቋም እንዲኖራቸው ብዙ ቤተእምነቶች በትጋት ይሰራሉ። ምክንያቱም ሃይማኖታዊ ባሕል፣እሴት ወዘተ ወደ ትውልዱ ሕሊና ዘልቆ የሚገባው በሚዲያ ተጽዕኖ ነውና ይፈልጉታል። እኛ ግን ይህ የገባን አይመስለኝም። አብዛኛው ድርጊታችን፣መጓተታችን፣ነገሮችን በኦርቶዶክሳዊት ሕብረት መረዳት ውስጥ ሆነን አለማየታችን ብዙ ነገር እያሳጣን ነው። እናም ምን ማድረግ ባንችል አይዞህ እንበለው! ወንድማችን አይዞህ 🙏ይህም ያልፋል! 📌 ቴሌግራም👉 @ephrem_views ✍️ የኤፍሬም ዕይታዎች
https://vt.tiktok.com/ZSXDRhVFN/
📌ወላጆች ለልጆች ! ወላጅ ለልጁ በዚህ ምድር ለሚኖረው ለነገ የተሻለ ሕይወት ጥሩ ት/ቤት፣ጥሩ እንክብካቤ ፣ጠንካራ ክትትል እያደረገ ያሳድገዋል።ነገር ግን ይኸው ወላጅ ልጁ ዘለዓለማዊ መኖሪያው ገነት መንግሥተ ሰማያት እንዲሆን በዛው ልክ ሲደክም፣ሲጥር አይታይም። በተለይም ከጥቂት ኦርቶዶክሳዊ ወላጆች በቀር አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ከልማድ በተሻገረ በቤቱ ውስጥ በጥንቃቄና በትኩረት ልጁን በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሕይወትና ትምህርት የራሱን ሕይወት አብነት አድርጎ በቃልና በተግባር ምሳሌ ሆኖ አያሳድግም። ይህ ትልቅ ችግር ገና ትኩረት አለመሰጠቱና አጀንዳ አለመሆኑ ደግሞ ነገን አስከፊና አደገኛ ያደርገዋል። ✍️ @ephrem_views 👈ቴሌግራም ...
የአምስት ዓመቱ ህጻን ባህታዊ ቅዱስ ዮሐንስ! ............................................................... የዓለም ሁሉ ደስታ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ተወለደ ......... ................ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ለወላጆቹ የዘገየ የሚመስል ግን ወደር የማይገኝለት ታላቅ ስጦታ ነው። ወላጆቹ ቅዱስ ዛካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥም በጸሎት የሚተጉ ዘወትር ከቤተ መቅደሱ የማይጠፉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው። ነገር ግን ልጅ ለምን አልተሰጠንም፣ ጥያቂችንም ለምን በፍጥነት መልስ አላገኝም ባንተ የማያምኑ በቤተ መቅደስህም ለጸሎት የማይቆሙ፣ እልፎች ልጅ ታቅፈው እኛን ለምን ከለከልከን ? ጸሎታችንንስ ለምን አልሰማህም ብለው በእግዚአብሔር ላይ አላጉረመረሙም። እንዲያውም ቅዱስ ሉቃስ እንደሚነግረን የዘጠና ዓመቷ ኤልሳቤጥና የመቶ ዓመቱ ካህኑ ዘካሪያስ "በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: ሉቃ 1÷6 እኛ ጠዋት ለምነን ማታ ካልሆነልን ብለን ስንት ዘመን አጉረምርመን ይሆን ? ሁለቱ ቅዱሳን ግን ቢዘገይም የሚቀድመው የሌለ አምላካቸውን ሙሉ ዘመናቸው ሲያመሰግኑ ኖሩ። እግዚአብሔርን ጠይቀነው፣ለምነነው ዝም ካለን እጅግ የተሻለ ውድ ነገር ሊሰጠን ነውና በትእግስት እንጠብቅ። እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ቅዱስ ዮሐንስ የመሰለ ድንቅ ልጅ ለዓለም ሁሉ ደስታ የሚሆን ድንቅ ስጦታ ለመቀበል ዕድሜ ሰጥቶን 1000 ዓመትስ ብንጠብቅ ስ ? በደስታ እንጂ። እስኪ ተመልከቱ ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ድንቅ ልጅ ሰጣቸው። ያውም አስቀድሞ በነቢያት ትንቢት የተነገረለት ኢሳ 40:3 ሚል 3:1ዐ በቅዱስ ገብርኤል ከመወለዱ አስቀድሞ የተመሰከረለት ሉቃ 1÷14 በሗላም ጌታ ክርስቶስ " እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም " ማቴ 11:11 ብሎ የመሰከረለት ታላቅ ነቢይ ልጅ ተሰጣቸው። ቅዱስ ዮሐንስ ገና በማህጸን ሳለ የአምላክ እናቱ የእመ ብርሃንን ድምጽ "ሰላምታ" በሰማ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ እናቱ ኤልሳቤጥ በምስጋና እርሱ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘሏል (ሰግዷል)። በቤተልሔም ህጻናት ላይ የሞት አዋጅ ሲታወጅ ቅዱስ ዮሐንስ 2 ዓመት ከ6 ወሩ ነበር። " የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው ?" ብለው ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ክፉው ሄሮድስ አስገደለ። እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ... " ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።" ማቴ 2:16 ። ነገር ግን ትንሽ ቆይተው ክፉዎች አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ስለ ዮሐንስ ነገሩት:: እንዲህ በማለት "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" ብለው። ይህንንም ዜና በእድሜዋ ማብቂያ ውድ ስጦታ የተሰጣት እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ሰማች። ወዲያውም ይዛው ሸሸች። ቅዱስ ዘካርያስ ግን ካህን ነውና በቤተ መቅደስ መካከል አግኝተው ገድለውታል። ወንድሞቼ ሆይ መላ ዘመንን ለእግዚአብሔርና ለቤተ መቅደሱ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ እስከ ሞት ድረስ መታመን እንደምን መታደል ነው ? ጌታ ሆይ እኔ ኃጢያተኛውን ልጅህን ለቤተ መቅደስህ ታማኝ አገልጋይ ሆኜ እኖር ዘንድ ፈቃድህ ትሁን😭። ቅድስት ኤልሳቤጥም በበረሃ ገዳመ ዚፋታ በተባለ ስፍራ ሕጻኑን እያሳደገች ለ5 ዓመታት አብራው ቆየች። ነገር ግን ቅዱስ ዮሐንስ 5 ዓመት ሲሞላው እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች።ሰው የማኖርበት የሰውም ድምጽ በማይሰማበት አራዊት በሰለጠኑበት ዱር የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ግርማ በሚያስፈራበት በዚያ በስተርጅና የተሰጣትን ውድ ስጦታ ከሞት ለማትረፍ በዛለ ሰውነቷ በደከመ ጉልበቷ ተከራታ ከሰው ተለይታ በበረሃ የከተመችው እናቱ ገና በለጋነቱ እድሜ ህጻኑ ዮሐንስን እንደ ታቀፈች የሞት እንቅልፍ አሸለበች። 😭😭😭 ይህ የአምስት ዓመት ህጻን በበረሃ ይሰማ የነበረው ድምጽ የእናቱ ብቻ ነበረ። አሁን ግን እርሱም የለም በዚህ ጊዜ ሕጻኑ ዮሐንስ በበረሃ ውስጥ ምርር ብሎ አለቀሰ። የሚያስደንቀው ነገር እልም ባለው በረሃ በሀገረ እስራኤል በገዳመ ዚፋታ የተሰማው ለቅሶ... አንድ ልጇን ሄሮድስ እንዳይገልባት የግብጽን በረሃ አቆራርጣ የአሸዋውን ግለት፣ የውሃውን ጥማት ችላ ግብጽ የወረደች እመ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ የህጻኑን ለቅሶ ሰማችው። ያዘኑትን የምታረጋጊ የእኛ የልጆችሽ ለቅሶ ፈጥነሽ የምትሰሚ እመቤቴ ሆይ ዛሬም የኢትዮጵያ እናቶችን ለቅሶ ሰምተሽ መከራውን በቃ በይን። ከዚያም እርሷም አንድ ልጇን ታቅፋ ስደት ላይ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ጋር በደመና ፈጥና ከዮሐንስ ዘንድ ደረሰች። አቅፋም አጽናናችው፣ ከዓይኖቹ የሚወርደውን እንባም አበሰችለት። ልጇንም ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ "እንውሰደው ይሆን?" አለችው። ጌታችንም እናቴ ሆይ "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት። እመብርሃንም አጽናንታው፣ባርካው ተለያዩ። ተመልከቱ ይህ አስደናቂ የአምስት ዓመት ህጻን ገና በህጻንነቱ የብህትውናን ህይወት ጀመረ። ❤️የመጀመሪያው የአምስት ዓመት ህጻን ባህታዊ ሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዚያው በበረሃ የግመል ጠጉር ለብሶ፤ ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ለ25 ዓመታት በዚያው ቀጠለ። የብህትውናን ሕይወት በህጻንነት ዕድሜው በበረሃ የጀመረው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሰው በቆይታው በንጽሕና በቅድስና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም። ምን ይደንቅ ምን ይረቅ። 30 ዓመት ሆኖት እግዚአብሔር ከሰማይ ተናግሮ "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" እስካለበት ድረስ በዚያ ኖረ። የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በረከቱ ይደርብን ! ✍️የኤፍሬም እይታዎች (ኤፍሬም ሀ.) 👉ቴሌግራም @ephrem_views ...........
መልኩ እንደ ማለዳ ፀሐይ የሚያበራ፣ ግርማ ሞገሱም ፍጥረታትን ሁሉ የሚያስደንቅ፣ ከክብሩ የተነሳ ምድር የምታበራለት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ በተሰጠው ክብርና ባለማዋልነት በሰማይ ካሉ መናብርትና ሥልጣናት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለ። ለሰው ልጆች ሁሉ የሚራራ፣ የእንባችንን ነጠብጣብ ወደ ሰማያዊው መንበር የሚያደርስ ፣ የሰማይና የምድርን መጋረጃ የሚከፍት፣ የጸሎታችንን መዓዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚያሳርግ፣በሕይወት ማዕበል ለሚናወጡ የማረፊያ ወደብ የሆነ፣ በመከራና በጭንቅ ቀን ለሚጠሩት ፈጥኖ ደራሽ፣ ለደካሞችና ለተገፉት የሚራራ፣ በጠላት ለተከበቡ የብርሃን ክንፎቹን ዘርግቶ የሚያሻግር፣ በክንፎቹ ጥላ ሥር የሚጠለሉትን ሁሉ ከክፉ ነገር ሁሉ የሚጠብቅ፣ የምሕረት፣ የይቅርታ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው። ቅዱስ ሚካኤል የሞት ደብዳቤአችንን የቀየረልን የዚህ ዘመን ባሕራን እኛ ነን። ዙሪያችንን ከቦ እንደሚያገሳ አንበሳ ሊወጠን ከተዘጋጀው ከዲያብሎስ ክፋት የጠበቅ የዚህ ዘመን አፎምያ እኛ ነን። ቅዱስ ሚካኤል የረዳችሁ፣በፍቅሩ ጥላ ያረፋችሁ የመልአኩ ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ 👏 ✍️የኤፍሬም ዕይታዎች @ephrem_views ...
እኛ ሁላችንም ወደዚህች ምድር ለአጭር ጊዜ የመጣን እንግዶች ነን። ግን ቆም ብለን ራሳችንን ብናይ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሰው ልባችን በክፋት የጠቆረ፣ዓይናችን በቅናት የቀላ፣አንደበታችን የሚሰብር ነው። ✍️ @ephrem_views ..
ዘሌ ተፈቷል❗️ ውድ ወንድሜ Zelalem Taye እንኳን ለቤት አበቃህ። 👉 @ephrem_views ..
“የከበረ ፍሬ ለመቅጠፍ፣ የከበረ ዛፍ መሆን ይቀድማል” +=================+ ዛሬ የዓለም ሁሉ ደስታ፣የከበረች አማናዊት መቅደስ የድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው።በአዳም ገላ የምታበራ የከበረች ነጭ እንቁ የሐናና የኢያቄም ፍሬ ልደት። የእመቤታችንን ልደት ስናስብ ይህን ማሰብ ተገቢ ነው። ሁለንተናዋ ውብ፣ ንጽሕትና ቅድስት የሆነች ልጅ በምኞት ብቻ እንዳልተገኘች።ይልቁንም ጌታን ባከበረ በተቀደሰ የትዳር ሕይወት፤በንጹህና በከበረ ልብ፣በፍቅርና በትሕትና በተዋበ የጸሎትና የቅድስና ሕይወት እንጂ። እግዚአብሔር በሕጉ ጥላ ላረፉ፣በፍቅሩ መዓዛ ለሰከሩ፤ የትዳር እልፍኛቸውን የምናኔ ዋሻቸው ላደረጉ ሰዎች በምድር ላይ ከሚሰጣቸው ታላላቅ ጸጋዎች ሁሉ የሚበልጠው ቅዱስ የሆነ ልጅ ከአብራካቸው የሚሰጣቸው ስጦታ ነው። የዚህ ህያው ምስክር ማሳያ የሚሆነን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደትና የወላጆቿ የቅዱሳን ኢያቄምና ሐና የተቀደሰ ትዳር ሕይወት ታሪክ ነው። የከበሩ ኢያቄምና ሐና በትዳራቸው የኖሩት ሕይወት ለሁላችንም ይህን ያስተምረናል:- 1.በትዳር ውስጥ ፍጹም የሆነ አንድነትና መተሳሰብ ሊኖር እንደሚገባ። ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ በሰዎች ዘንድ "አምላክ የተዋቸው፣ጌታም የረሳቸው" አንድም የእግዚአብሔር በረከት የራቃቸው እንደሆኑ ተቆጥረው ይናቁ በነበረበት ወቅት ያንን ሁሉ የመከራ ዘመን ያሳለፉት እርስ በርስ በመወቃቀስ ሳይሆን በፍቅርና በአንድ ልብ በመጸለይ ነበር። ሰጪም ነሺም እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ አምነው በእምነት ጸንተው ጌታን ጠበቁት። የልጅ መገኛ ቅዱስ መሠረት የወላጆች የአንድነት ፍቅር ነውና። 2.በንጽሕናና በሕገ እግዚአብሔር ተጠብቆ መኖር። ሐናና ኢያቄም "ላላመኑብህ ያልነሳኸው፣ላላከበሩህ ያልከለከልከው፣ሕግን ላልጠበቁ የሰጠኸውን የልጅ በረከት ለእኛ ለምን ነሳኸን?" ብለው አንድም ቀን አላጉረመረሙም። ይልቁንም ሕይወታቸው ከምቀኝነት፣ ከትዕቢትና ከርኩሰት የራቀ ነበር። ሀብታቸውንም ለነዳያንና ለቤተ መቅደስ በመክፈል፣ በጸሎትና በጾም ተወስነው ይኖሩ ነበር። 3.በፍጹም ጽናት ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገዛትን ልጅን ለማግኘት የፈለጉት ለክብራቸው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ፍሬ ለመቅደስ ለመስጠት ነበር። “ልጅን ብናገኝ ብላቴናውን ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ አድርገን እንሰጣለን” ብለው ነበር ስዕለት የተሳሉት። ሐናና ኢያቄም ስጦታውን መልሰው ለሰጪው ለመስጠት ነበር የለመኑት። ይህ ደግሞ ተቀባዩ ቅዱስ ስለሆነ የተቀደሰ ነገር ይፈልጋልና ፈቃዱን እንጂ ፈቃዳቸውን አልጠየቁም። እኛስ ብንሆን? የቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ትዳር በእንባ፣ በጸሎትና በቅድስና የተዋበ ስለነበር እግዚአብሔር በስተርጅናቸው የወለዷትን ያችን ብላቴና “ከፍጥረት ሁሉ በላይ ውብና ንጽሕት” አድርጎ ሰጣቸው። ድንግል ማርያም ከአዳም ባሕርይ የተገኘች ብትሆንም፣ በወላጆቿ ጽኑ ጸሎትና ቅድስና ምክንያት ለሰማያዊው ንጉሥ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ተለይታ የተሰጠች የንጽሕና ማኅደር ሆነች። ዛሬ ቅዱሳን ልጆችን ለመውለድ ምን ያስፈልጋል? እንደ እመቤታችን ዓይነት ሁለንተናዋ ያማረች፣ ለቤተሰብና ለሀገር የምትተርፍ የከበረች ልጅ ለመውለድ ዛሬ ካሉ ወላጆች ሊኖሩት የሚገባ የትዳር ሕይወት ይህንን ሊመስል ይገባል:- 1.በትዳር ውስጥ የጸሎት ሕይወት ያስፈልጋል ጽንሱ በማኅፀን ውስጥ ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሚወለደው ልጅ ቅዱስና የተባረከ እንዲሆን ወላጆች ቅድሚያ በጸሎትና በንስሐ ሕይወት ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው። ልጁ የሚመጣው ከተቀደሰ መንፈሳዊ ተራክቦ እንጂ ከሥጋዊ ፍላጎት ብቻ መሆን የለበትም። 2.የቃላትና የግብር ንጽሕናን ገንዘብ ማድረግ ትዳር ውስጥ እርስ በርስ መከባበር፣ ከክፉ ንግግር መራቅና ሰላምን ማስፈን ያስፈልጋል። በእናትና በአባት መካከል ያለው ፍቅርና ሰላም በማኅፀን ላለው ጽንስ ቀጥተኛ ሰላምና ቅድስናን ያላብሰዋል። ገና ከማኅጸን ጀምሮ በጎ ቃላት፣ዝማሬዎችን እየሰማ ጽንሱ ማደግ አለበት። ጸሎት፣ከምስጢራት ማሳተፍም እንዲሁ ጽንሱ የተባረከ እንዲሆን ያደርገዋል። ልጅ የሚባረከው ከተወለደ በሗላ ሳይሆን ከማኅጸን ጀምሮ ነው። 3.ልጅን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት ቅዱስ ሐና እና ኢያቄም እመቤታችን ስትወለድ “ይህች ልጅ የአምላክ ስጦታ ናት፣ የእርሱንም ክብር እንድታሳይ አድርገን እናሳድጋታለን” የሚል የልብ ስዕለትና ቁርጠኝነት ነበራቸው። ያደረጉትም እንዲሁ ነው። በእስተርጅና ያገኟትን፤ሲያዩአት የምታሳሳ ገና የሥሦት ዓመት ብላቴና ለራሳቸው ደስታ ሳይሳሱ ወደ ቤተመቅደስ ወስደው ነው በዚያ ትኖር ዘንድ የሰጧት። እኛስ ልጆቻችንን በየት ነው እያሳደግን ያለነው? ወላጆች ልጃቸው በሰው ፊት ንጽሕት የሆነች፣ በእግዚአብሔር ፊትም የከበረች እንቁ ልጅ እንድትሆን ከተመኙ በመጀመሪያ የትዳር ሕይወታቸው በፍቅር፣ በጸሎትና በንጽሕና ያጌጠ መሆን አለበት። ልክ እንደ ቅዱስ ኢያቄምና ሐና በትዳር ውስጥ እግዚአብሔርን ካነገሡ፣ እርሱም ማኅፀንን ይባርካል፤ የሆድ ፍሬአቸውም በምድር ላይ የተመሰገነና የከበረ ይሆናል። ትዳር መዳናችን የሚፈጸምበት፣ የከበሩ ቅዱሳን ልጆች ልናፈራበት የሚገባ፤ በፈቃደ እግዚአብሔር የምንኖርበት የከበረ የንጽና ደሴት መሆኑን አውቀን በክብር እንኑረው። ✍️ ኤፍሬም ሀብተ ማርያም (የኤፍሬም እይታዎች ) 👉 @ephrem_views ሰኞ- ሰኔ 1/2018 ዓ.ም - ከስዕሏ ፊት ....📌Share ያድርጉ ይማሩበት ዘንድ❗️ .
ቅዱሳት መጻሕፍትን በጾመ ሐዋርያት እናንብብ! +======== =======+ ጾመ ሐዋርያት የመንፈሳዊ ሕይወት ተጋድሎ መጀመሪያ፣ የጸሎትና የሱባኤ ወቅት ነው። ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ጨለማውን ዓለም በወንጌል ብርሃን ለመቀየር ከመነሳታቸው በፊት በጾምና በጸሎት ተዘጋጅተዋል። እኛስ ፈተናና መከራ በጸናበት፣በበዛበት ዓለም ለሕይወታችን ጉዞ ራሳችንን እንዴት እያዘጋጀን ነው? ወጣትነት በብዙ ጥያቄዎች፣ ምርጫዎችና ፈተናዎች የተሞላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ “ወጣት መንገዱን በምን ያቀናል? ቃልህን በመጠበቅ ነው” (መዝ. 119፥9) ይለናል። ሕይወታችንን የሚመራ እውነተኛ አቅጣጫ ጠቋሚ ቅዱስ ቃሉ ነው። ሐዋርያት ዓለምን የለወጡት በዕውቀት ጥበብ ብቻ ሳይሆን በቃሉ ኃይል ነው። እኛም የነሱ ተከታዮች እንድንሆን የኖሩበትን፣ ያስተማሩትንና የተጋደሉለትን እውነት ማወቅ ይኖርብናል። በዚህ በቴክኖሎጂና ጫጫታ በበዛበት ዘመን፣ አእምሯችንና ልባችን እረፍት የሚያገኘው በቃሉ ውስጥ ካለው ዘላለማዊ እውነት ጋር ሲገናኝ ብቻ ነው። በዚህ ጾም ረጅም ሰዓት በሶሻል ሚዲያ ላይ ከምናጠፋው ጊዜ ላይ ጥቂት ደቂቃዎችን ቀንሰን፣ በቀን አንድ ምዕራፍ እንኳ በማንበብ የንባብ ልምምድ እንጀምር። በተለይ የሐዋርያት ሥራን እና የሐዋርያትን መልእክታት በማንበብ የቤተክርስቲያንን ታሪክና የሐዋርያትን የሕይወት ተጋድሎ እንመርምር። ወጣትነቱን በቃሉ የማያድስ ትውልድ ነገን በጽኑ መሠረት ላይ መገንባት አይችልም። ይህ የጾም ወቅት በፌስቡክና በቲክቶክ የምናሳልፈውን ጊዜ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ገጾች የምናዞርበት የለውጥ ጊዜ ሊሆን ይገባል! 📌አምና በዚህ ገጽ ሙሉ የሐዋርያት ጾምን "የሐዋርያት ሥራ" መጽሐፍን አጥንተን ነበር። ዘንድሮም ጊታ ቢፈቅድ አንድ መጽሐፍ እናጠናለን። መጽሐፍ ያላችሁ እንዲያነቡ ለጓደኞቻችሁ አውሱ፣የተዋሳችሁ መልሱ፣ያነባብችሁትን አጋሩ።መልካም ጾም👏 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም…” (ዕብ. 4፥12) ✍️ @ephrem_views 👈ይቀላቀሉ❗️ ......📌Forward ያድርጉ...........
በምስራቅ አርሲ እየሆነ ስላለውም፣ስለሆነውም፣ ለማሰብም፣ ለመናገርም እጅግ የሚከብድ ነው። እልቂቱ የማያቋርጥ ሆኗል። ይህን በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ምትና እንግልት ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሃይማኖት ፣ዘርና የፖለቲካ አመለካከት ሳይለይ በአንድነት ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር ነበር። ብዙዎች ዝምታን መርጠዋል። የሰሜን አፍሪካዋ ቱኒዚያ የክርስትና ማዕከል ነበረች፣የመን የኦርቶዶክሳውያን መኖሪያ ነበረች፣ ቱርክ ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤን የምታዘጋጅ ኦርቶዶክሳዊት ሀገር ነበረች እነዚህ ሀገራት ዛሬ ላሉበት የደረሱት በዚህ መንገድ ነው። ቤተክህነቱ እንደ መንፈሳዊ አባት፣የልጆቹ ሞትና ሕመማቸው ተሰምቶት ስቃያቸውን ሊያስቆም ይገባል። ግን ይህ አልሆነም ሬሳ እየቆጠርን ዓመታት ተቆጠሩ። ፍትሕ ልጇንም ባሏንም በአንድ መቃብር ለቀበረች እናት፣ፍትሕ ወላጅ አልባ ሆነው ለቀሩ ሕጻናት፣ፍትሕ በዘመድ ተከቦ ኖሮ በአንድ ጀንበር ዘመድ አልባ ለሆነው ወጣት😭😭😭 ፍትሕ ፍትሕ😭 ✍️ @ephrem_views ..
የሰኔ (የሐዋርያት ) ጾም ነገ ግንቦት 24 ይጀምራል። ጾመ ድኅነት(ረቡዕና አርብ) ደግሞ ግንቦት 26። መልእክቱን ለጓደኞቻችሁ አድርሱ! መልካም ጾም ✍️ @ephrem_views ....
видео или голосовое, без подписи
. #ሦስቱ_እንግዶች_ከደጅ_ቆመዋል +====================+ እንደምን አመሻችሁ ። የተከበሩ ሦስት እንግዶችን እስኪ ላስተዋውቃችሁ። እነዚህ እንግዶች ብዙ ጊዜ ወደ ባለ ትዳሮች በመሄድ ይጠይቃሉ። ዛሬም እንደተለመደው በአንዲት መንደር ወደ ሚኖሩ ባልና ሚስት ቤት በመሄድ ከመሸ በራቸውን ያንኳኳሉ። የበራቸውን መንኳኳት የሰማች ሚስት በሩን ለመክፈት ትሄዳለች ከዛም ባየችው ነገር በጣም ትገረማለች ። ከደጅ ቆመው የጠበቋት ሦስት ነጫጭ ሽበት ያለባቸው የሚያማምሩ ባለግርማ ሞገስ ሽማግሌዎች ነበሩ ። አቤት ግቡ ምን ፈልጋቹ ነው? አለቻቸው ፈራ ተባ ባለ የአነጋገር ድምፀት ። እንግዶቹም " ኸ... ሥስታችንም አንገባም አንዳችን ነን የምንገባው ነገር ግን ግልጽ እንዲሆንልሽ እራሳችን እናስተዋውቅሽ " አሉና እንግዶቹ ራሳቸውን ማስተዋወቅ ጀመሩ። 1ኛው እንግዳ " ስኬት " እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ አሳብሽ ሁሉ ይሳካል አላት። 2ኛው ደግሞ እኔ "ገንዘብ " እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ ችግር የሚባል ነገር ፈጽሞ አይኖርም አላት ቀብረር እያለ። 3ተኛው እንግዳ በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ ሆኖ " ፍቅር " እባላለው ፍቅር ማብራሪያ የለውም አላት ። ከዛ ሚስት ባለቤቴን ላማክር ብላ ወደ ውስጥ ገባችና ልክ ለባለቤቷ ስትነግረው በነገሩ ተደንቆ እንዲህ አለ ። በእውነቱ ይሄ እድል ሊያመልጠን አይገባም ገንዘብን የሚያክል ነገር ደጅ ቆሞ መወያየት ግፍ ነው ሰርቼ ከሰው በታች የሆንኩት ገንዘብ ሰለሌለኝ ነው እና ፈጠን በይ ገንዘብን ወደቤታችን እንዲገባ ንገሪው አላት። ሚስትየውም በሀሳቡ ተስማምታ ገንዘብን ልትጠራው ስትል ልጇ እንዲ አላት " እማዬ ገንዘብ ገብቶ አባዬ እንደለመደው ማታ ማታ ከሚደበድብሽ ፍቅር ገብቶ ሰላምሽን ብታገኚ አይሻልም ? " አላት ። እሷም በልጇ ሀሳብ በጣም ተደነቀች በፊት ሰርተው ያገኙት ጥቂት ገንዘብ ነበራቸው ነገር ግን በመካከላቸው ሁልጊዜ ጸብ፣ጥል፣ክርክር በመኖሩ ባል በመጠጥ ጨረሰው።ይህ ብቻ አይደለም ሰክሮ አምሽቶ እየመጣ ይረብሻቸው ነበር።ይኼን ትዝ አላትና ተደስታ በሀሳቡ ባልየውን ፍቅር ካልገባ ብላ ሞገተችው በመጨረሻም ፍቅር እንዲገባ ወስነው ወደ ሽማግሌዎች ሄዱና ፍቅር የተባልከው ሰው ወደቤታችን ግባ ይሉታል ። እሱም ተከትሏቸው ይገባል ባልና ሚስቱም።ዞር ብለው ሲያዩ 3ቱም ሰዎች ቤት ገብተው ቆመዋል ባልየው ደንግጦ እኛ በቤታችን እንዲገባ ያልነው ፍቅርን እኮ ነው አለ ከሽማግሌዎቹም አንዱ ዞር አለና ልክ ብለሀል ። ነገር ግን ፍቅር ካለ ስኬት አለ ፍቅር ካለ ገንዘብ አለ ። በማለት 3ቱም ወደቤታቸው ገቡ ፍቅር የሆነው ፈጣሪ ወደቤታችን ሲገባ መልካም የሆኑ በሙሉ አብረው ይገባሉ ። ........... ክርስቶስ የሞተለት ዓላማ ፍቅር ነው። ፍቅር የህይወታችን ህልውና ነው። ፍቅር ከሁሉም ይበልጣል። " ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። " 1ኛ ዮሐ 4: 8 እንዲል መጽሐፍ። በገንዘብ፣በእውቀት፣በዝና በሥልጣን በምንም ነገር ፍቅርንም መግዛት አይቻልም። #ነገር_ግን_በፍቅር_ዓለምን መግዛት ይቻላል። #አርብ_ፍቅር_በቀራንዮ_የተገለጠባት_ዕለት_ናት ፍቅር በፍቅር ሁኑ ።ሰላም_እደሩ 👉ቴሌግራም ይቀላቀሉ👇👇👇 @ephrem_views ግንቦት 2014 ዓ.ም በድጋሜ! ✍️ የኤፍሬም ዕይታዎች ....
" ለብ ያለ ሕይወት " ይህ የትውልዱ ፈተና ነው። በአንድ ጊዜ ዘማሪም፣ ዘፋኝም መሆን። በአንድ ጊዜ መንፈሳዊም ዓለማዊም መሆን፣ በአንድ ጊዜ አስቀዳሽም፣ደናሽም መሆን መፈለግ። በራድ ወይም ተኩስ አለመሆን። @ephrem_views ...
ሰማዕት በክርስቶስ የፍቅሩ መዓዛ ሰክሮ እውነት ክርስቶስን ከሕይወቱ በላይ የሚናፍቅ ነው።ሰማዕት በክርስቶስ የፍቅር መዓዛ ስለሰከረ ዓለምን እንደ ትቢያ ይቆጥራታል። ምክንያቱም የእሱ እውነት፣ የእሱ ተስፋና የእሱ ዘላለማዊ ናፍቆት በሰማያዊው ሙሽራ በክርስቶስ ዘንድ ብቻ ነውና።ለሰማዕታት ሥቃዩ የማይታወቃቸው ስለማያማቸው ሳይሆን፣ ከሕመሙ በላይ የክርስቶስ የፍቅሩ ጣዕም ስለበረታባቸው ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ያን ሁሉ መከራ እንደ መሉ ደስታ ቆጥሮ በፀጋ የተቀበለው በክርስቶስ የፍቅር መዐዛ ሰክሮ ለሂድ ከእርሱም ጋር ሊኖር ስለናፈቀ ነው። በክርስቶስ የፍቅሩ መዓዛ ሰክረን ይህችን ዓለም እንነቃት ዘንድ ኑ በሥጋ ወደሙ እንክበር። ከክርስቶስ ጋርም እንኡር። ።። @ephrem_views ✍️። የኤፍሬም ዕይታዎች ...
የሰው ባሕርይ የከበረባት፣ የፍጥረት ሁሉ መመኪያ፤ ንጽሕናዋ እንደ ሰማይ የጠራ፣ ቅድስናዋም እንደ መላእክት ያበራ፤ በጭንቅ ቀን የምትደርስ፣ በሐዘንም ጊዜ የምታጽናና እመብርሃን👏 @ephrem_views ......
በጌታ ቤት የምታገኘው ሰላም በዓለም ካለ ከማንኛውም እረፍት ይበልጣል። ነገ ሰንበት ነው።ስለዚህ ዓለም በ6ቱ ቀናት የጫነችብህን ሸክም ታስወግድ ዘንድ፤ ደስታ፣ ሰላምና እረፍትም ታገኝ ዘንድ ከመቅደሱ ተገኝ። ✍️ @ephrem_views
📌 ዝሙት ለምን ከባድ ኃጢአት ሆነ? (ክፍል ፪) 1.በገዛ ሥጋ ላይ" የሚደረግ በደል በመሆኑ:- ሌሎች ኃጢአቶች ነፍስን ይጎዳሉ።ዝሙት ግን ነፍስንም ሥጋንም በእኩል የሚያቆሽሽ፣ የሥጋን ክብር የሚገፍ በመሆኑ "በገዛ ሥጋ ላይ" የሚደረግ ኃጢአት ይባላል። የተወደደ ሃዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ "ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል" (1ኛ ቆሮ 6፡18) ይላል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ሌሎች ኃጢአቶች ለምሳሌ:- ስርቆት ወይም ሐሜት መነሻቸው ልብ ቢሆንም ውጤታቸው ከሰውየው አካል ውጭ ነው። ዝሙት ግን የሰውን ማንነትና አካል መሣሪያ አድርጎ ራሱን ሰውየውን ስለሚበክል "የውስጥ ኃጢአት" ይባላል። 2.የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነ መቅደስ ሰውነትን ማርከስ ስለሆነ:- ቤተመቅደስ ምን ማለት ነው? ምንድን ነው? በአጭሩ ቤተመቅደስ ማለት:- ጌታ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚገልጥበት፣ ሰውም ቅድስናንና ጸጋን የሚቀበልበት፤ መንፈሳዊ ሰላምና እረፍት የሚገኝበት፤ሰውና መላእክት ፤ተጋዳዮችና ድል ነሺዎች ሕብረት የሚያደርጉበት፤ የምስጋና መስዋዕት የሚሰዋበት፣የቃልኪዳኑ ታቦት ማንበሪያ፣ ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሃደው የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት፤ይቅርታ የምናገኝበት፤ የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር በቃል ኪዳን የሚተሳሰርበት ክቡር ስፍራ ነው። ሰውም ሰውነቱ መስዋዕት፣ልቡም የመንፈስ ቅዱስ ታቦት ነው። በመቅደስ የተዘጋጀው አማናዊ ቁርባን መኖሪያው የሰው ሰውነት ነው። ስለዚህ ቅዱስ መጽሐፍም የሰው ልጅ ይህ ታላቅ ክብር የታደለ አማናዊ ቤተመቅደስ እንደሆነ ሲገልጥ “ሥጋችሁም በእናንተ ውስጥ የሚኖረው ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበላችሁት የእርሱ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?” ፩ኛ ቆሮንቶስ 6:19 አለን። የክርስቲያን ልብ፤የክርስቲያን ሰውነት የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነውና። ኦርቶዶክሳዊው የክርስትና ትምህርት ክርስቲያን የሆነ የሰው አካል "የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ" እንደሆነ ያስተምራል። ዝሙት ደግሞ ይህንን የተቀደሰ መቅደስ ለርኩሰት አሳልፎ መስጠት ነው። ለዛነው “ሰውነቱ ቤተ መቅደስ እንደሆነ የሚያውቅ ሰው የኃጢአትን እድፍ ይፈራል።” በማለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የተናገረው። ምክንያቱም ሰውነቱ(ሥጋው) የከበረ የክርስቶስ ብልት እንደሆነ ያውቃልና ያሳድፈው ዘንድ አይደፍርም። ታላቁ ገዳማዊ መነኮስ አባ መቃርዮስም “ነፍሱም ሆነ ሥጋው የእግዚአብሔር ቅዱስ ማደሪያ እንደሆኑ ሳያውቅ ማንም እግዚአብሔርን ማወቅ አይችልም።” ያለን ለዚህ ነው። 3. የነፍስና የሥጋ አንድነትን ያናጋል! ሥጋ የነፍስ ማደሪያ እንደመሆኑ መጠን፣ ያ ማደሪያ ያለ ፍቅርና ያለ ክብር ለጊዜያዊ ስሜት ሲጋለጥ ነፍስ ታዝናለች። ይህም ዝሙት በሚፈጽመው ሰው ሕሊና ውስጥ "የባዶነት ስሜት" ይፈጠራል። ሥጋው ደስታን ቢፈልግም፣ ነፍሱ ግን በክብር ማጣት ምክንያት ትሳቀቃለች፤ትጎሳቆላለች በዚህም የሥጋና የነፍስ ስምምነት ይናጋል። ምክንያቱም " መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ነው" (ዕብ 13:4) የሚለው የነፍስ ዘለዓለማዊ ቃልኪዳን የሚያፈርስ ስለሆነ ዝሙት። በባለትዳሮች (በኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ) ውስጥ የሚደረግ የሩካቤ ሥጋ ሥርዓት የከበረና ንጹህ ነው። አንድ አካል፣አንድ ሥጋ ናቸውና። ከዚህ ውጪ ሲፈጸም ግን ነፍስ ታዝናለች። 4. ሰውን ከፈጣሪ ጸጋ የመለየት አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ ዝሙት ሰውን ለጸሎትና ለመንፈሳዊ ሕይወት ዳተኛ ያደርገዋል። የዝሙት ሐሳብ ልቡን የተቆጣጠረው ሰው የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ይሳነዋል። ቅዱሳን አባቶች ዝሙትን "የነፍስ መጋረጃ" ነው ይሉታል። መጋረጃው ብርሃኑን እንደሚጋርድ ሁሉ፣ ዝሙትም የእግዚአብሔርን ብርሃን ለሰውየው እንዳይታይ ይጋርደዋል። አንድ ሰው ለዝሙት ተላልፎ ራሱን ሲሰጥ ሀሳቡ፣ፍቃዱ፣ስሜቱ ሁሉ በዛ ይያዛል። መጾም፣ መጸለይ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ፣ስብከት መስማት አይችልም። በምዕናቡ ክፉ ምስሎችን እየፈጠረ ይሰቃያል። በዚህም ከፈጣሪ ጸጋ ይለያል። 6. በዋጋ የተገዛ ሰውነት ስለሆነ (የክርስቲያን ሰውነት) " ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን# በዋጋ_ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ 6÷19 ተወዳጆች ሆይ የክርስቲያን ሰውነት ( ሥጋ) ዋጋው የክርስቶስ ደም ነው። ይህ ሥጋችንን የተገዛው በወርቅ፣በብር፣በእንቁ አይደለም በከበረ የክርስቶስ ደም፣በአምላክ ደም ነው የተገዛው። ይህ ሥጋችን ፈርሶ በስብሶ የሚቀር አይደለም ህያው ይሆን ዘንድ አዲስ ፍጥረት ሆነ የሚነሳ ሥጋ ነው። ስዚህ ዝሙት ከባድ ኃጢአት የሆነው በዋጋ በተገዛ በከበረ ሥጋችን የሚፈጸም ኃጢአት ስለሆነ ነው። በንጽህና እንጠብቀው። ንጽሕና እንደ ነጭ ልብስ ነው። በነጭ ልብስ ላይ የወደቀ የጭቃ ነቁጥ ከሩቅ ይታያል። ዝሙትም እንዲሁ በነፍስ ቅድስና ላይ የሚወድቅ ጥቁር እድፍ ነው።ሌሎች ኃጢአቶች እንደ ቁስል ናቸው፤ ዝሙት ግን እንደ ነቀርሳ (ካንሰር) ነው። ውስጥ ውስጡን እየበላ መላውን ሰውነት ስለሚያጠፋ። ዝሙት ከባድ ኃጢአት የሆነው ሰውን ከአምላኩ፣ ከራሱ ማንነትና ከቅድስናው ስለሚለየው ነው። ሆኖም ግን፣ የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን "በእግዚአብሔር ዘንድ የማይሠረይ ኃጢአት የለም" ንስሐ ከማንኛውም ከባድ ኃጢአት በላይ ኃይል አለውና ንስሓ እንግባ። 📌 በማወቅም ሆነ ባለማወቅ መቅደስ የሆነ ሰውነታችንን ያቆሸሽን በንጽህና እንጠብቀው ዘንድ 👉 #ንስሓ እንግባ! 👉 @ephrem_view 👈ይቀላቀሉ ✍️ (part 3) ይቀጥላል❗️ ✍️ የኤፍሬም እይታዎች ..........