tgindex
ዘተዋሕዶ ZE TEWAHIDO

ዘተዋሕዶ ZE TEWAHIDO

Статистика
Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
505
−2 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,20%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
187
20 постов
Вовлечённость
37,0%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
22
1/48двое суток
25
1/72трое суток
27

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ​"የነቢያት እንባ የደረቀው የዓለም ሐዘን የተራገፈው ዛሬ ነሐሴ ሰባት ቀን በድንግል ጽንሰት ነው። እርሷ የለቅሶ ማቆሚያ የሰማይና የምድር ዕርቅ ናትና!" ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ፀሐይ ሳይወጣ ቀኑ ሳይመሽ በፊት ንጋት እንደሚቀድም የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ የንጋት ኮከብ ሆና የተገኘችው እመቤታችን በነሐሴ 7 ዕለት ተፀነሰች። እርሷ የጨለማውን ዓለም ያበራች የብርሃን ሠርጥ ናት። ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • መሬት በድርቅ ተይዛ ሳለ የበጋን ጽድቀት እንደሚጠብቅ ሁሉ የሰው ልጆችም በጥንተ ሰብእ ውድቀት ተይዘው ሳለ የነፃነት ዜና የተሰማው በዚች ዕለት ነው። የቅድስት ሐና ማኅፀን ለዓለም ሕይወት የበቀለችበት የመጀመሪያው የለምለም ቅጠል ናት። ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ይህቺን ዕለት ያልናፈቀ ትውልድ የለም ነሐሴ ሰባት ቀን የባሕርያችን መመኪያ የምትሆን ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነው። ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ለሆነባቸው ቅዱሳን አበውና ቅዱሳን አንስት ተስፋቸው የሚፈጸመው በዛሬው ዕለት በተጸነሰችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነውና፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ከእግዚአብሔር ቀጥሎ እንደ እመቤታችን ከፍ ከፍ የምታደርገው ፍጥረት የሌለው ስለዚሁ ነው፡፡ ሊቃውንቱ፡- «ሐና አንቺን የጸነሰችበት የደስታ ቀን ምን ያህል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን  ያፈራባት ቀን ምን ያህል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤» ብለው የሚዘምሩላትም ይህን ምሥጢር በልቡናቸው ቋጥረው ነው። እንኳን ለዓለም ሁሉ ደስታን ወዳመጣችው ዕለት አደረሰን አደረሳችሁ!! ነሐሴ 7 2018 ዓ.ም ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ሰው አለቀብኝ ​በሕይወት ጉዞ ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ሰው አለቀብኝ የምንልበት ደረቅ ወቅት ይመጣል። በዙሪያችን የነበሩ መከታና ደጋፊ ይመስሉን የነበሩ ሰዎች ሁሉ እንደ ጥዋት ጭጋግ ተነው ሲጠፉ ችግራችንን የምንነግረው ብቸኝነታችንን የምናካፍለውና አብሮን የሚቆም አንድም ሰው ስናጣ መንፈሳችን ይደክማል ተስፋችንም ይጨልማል። ​ነገር ግን በሕይወትህ ሰው አለቀብኝ ብለህ የምታስብበት ያ ቅጽበት እግዚአብሔር አዲስ ምዕራፍ ሊጀምርልህ ያዘጋጀው ድንቅ የጸጋ ጊዜ ነው። ​እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ከዙሪያችን የሚያርቀው እኛን ለመጉዳት ሳይሆን ​በሰዎች ላይ የጣልነውን ተስፋ እንድንመልስ እውነተኛ ረዳትና መከታ እሱ ብቻ እንደሆነ እንድናውቅ ነው። ​ድምፁን በጸጥታ እንድንሰማ የሰዎች ረብሻና ድምፅ ሲጠፋ የፈጣሪን ስስና ለስላሳ ድምፅ መስማት እንጀምራለን። በሰው ሳይሆን በጸጋው መቆም እንድንማርና መንፈሳዊ ጥንካሬ እንድናገኝ ነው። ​በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቤተሳይዳ መጠመቂያ አጠገብ ለ፴፰ ዓመታት ተኝቶ የነበረው ሽባው ሰው «ጌታ ሆይ ወደ መጠመቂያይቱ የሚያወርደኝ ሰው የለኝም» ብሎ ነበር። የሰው አለመኖር ታላቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ጥሎት ነበር። ነገር ግን ሰው የለኝም ባለበት በዚያው ቅጽበት የሰው ሁሉ ፈጣሪና የሕይወት ምንጭ የሆነው ጌታ በፊቱ ቆመ። የሰው ማጣት ወደ አምላክ መገኘት መራው በእግሩም ቆሞ እንዲሄድ አደረገው። ​ወዳጄ! ዛሬ በዙሪያህ ሰው ቢጠፋ ወዳጅ ቢርቅህ ወይም የሚረዳህ ሰው ባታገኝ አትዘን። ሰው ሲያልቅ እግዚአብሔር ይጀምራል። የሰው እጅ ሲያጥር የአምላክ እጅ ይረዝማል። ​ሰው ሲርቅህ እግዚአብሔር ወደ አንተ እየቀረበ እንደሆነ እወቅ። በሰው ላይ የተቀመጠ ተስፋ ይፈርሳል በእግዚአብሔር ላይ የተቀመጠ ተስፋ ግን በፍጹም አያፍርም። ሰው አለቀብኝ በሚለው እውነት ውስጥ ሆነህ እግዚአብሔር ግን ከእኔ ጋር ነው የሚለውን ታላቅ ተስፋ ጨብጥ። እሱ የሚበቃ የማይተውና የማይጥል ታማኝ ወዳጅ ነው። ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ

  • ​"በሰው ተስፋ ብትቆርጥ አትደንግጥ መድኃኔዓለም ተስፋህ የሚጀምርበት የማዕዘን ራስ ነውና። የሰው እጅ ተንሸራታች ሲሆን የእሱ እጅ ግን ለዘለዓለም የማትተውህ መጠጊያህ ናት።"

  • የተመረጠ ታማኝ አገልጋይ አረጋዊው  ቅዱስ ዮሴፍ ሐምሌ 26 ቀን መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ጠባቂ ሆኖ ሲያገለግላት የቆየው በተወለደ ጊዜም ቅዱሱ መልአክ መጥቶ ለወላጆቹ ይሆናል ተብሎ የተነገረለት አረጋዊው ጻድቁ ዮሴፍ  በክብር ያረፈበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ነው ። አረጋዊ ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከቤተ ዳዊት ሲሆን አባቱ ያዕቆብ ይባላል እግዚአብሔርን የሚፈራ ለሰው የሚራራ ደግ ሰው ነበር ድግር ጠርቦ ጥርብ አለዝቦ ሽጦ ይኖር የነበር ጻድቅ ሰው ነው ። አረጋዊ ዮሴፍ ያዕቆብ ዮሳ ስምዖን ይሁዳ የተባሉ አራት ወንዶችና ሶስት ሴት ልጆች ነበሩት ሚስቱ ከሞተችበት በኋላ አይሁድ በእመቤታችን ላይ በጠላትነት ተነስተው ከቤተ መቅደስ ትውጣልን ባሉ ጊዜ ልማ በሥሉስ ጥፋ በሥሉስ እንዲሉ በሶስት ነገር ተመስክሮለት እመቤታችንን ወስዶ ከቤቱ አስቀምጧታል። አረጋዊ ዮሴፍ ታማኝ አገልጋይ በመሆን ብዙ ዘመን ከእመቤታችንና ከጌታችን ጋር በረሃ ለበረሃ ሲንከራተት ኖሯል ይህም ጻድቅ አረጋዊ እመቤታችንና የተወደደ ልጇን መድኃኔዓለምን በእጆቹ ሥራ ይመግባቸው ነበር ። አረጋዊ ዮሴፍ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ከእመቤታችን ጋር ሆኖ በደስታዋም በኀዘኗም ጊዜ አልተለያትም ጌታን በወለደች ጊዜም ዳስ ሠርቶ ግርግም አዘጋጅቶ አገልግሏታል ። አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችን በስደቷ ወቅት ልጇን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማዳን ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ረሀቡን ጽሙን ሐሩረ መዓልቱን ቁረ ሌሊቱን ታግሣ በረሀ ለበረሀ በተንከራተተችበትም ወቅት አልተለያትም ነበር ፡፡ ከስደት ከተመለሱም በኋላ ጌታችንን እንደ አባት ሆኖ አሳድጎታል አይሁድ ጌታን «ወልደ ዮሴፍ » ማለታቸው ቅሉ ይህን ይዘው ነው ። አረጋዊ ዮሴፍ በመጨረሻ የእድሜ ዘመኑ ታሞ ሊያርፍ ሲል ጌታችን ተገልጦለት ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ ?  ቢለው በሞትኩ ጊዜ ሥጋዬን በምድር አታስቀርብኝ አለው ። ጌታችንም እሺ እንዳልክ ይሁንልህ ብሎት መላእክቱን አስከትሎ ደቀ መዛሙርቱን በደመና አምጥቶ ካለበት ሰብስቦ ክብርት ነፍሱን ከሥጋው ለይቶ በእጁ ዳሶ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ አድርጎ ሐምሌ 26 ቀን በክብር እንዲያርፍ አድርጎት ሥጋውን ብሔረ ብፁዓን አስገብቶለታል። የአረጋዊ የቅዱስ ዮሴፍ በረከቱ ከእኛ ከሁላችንም ጋር ለዘለዓለም ትሁን አሜን። ሐምሌ 26 2018 ዓ.ም ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • видео или голосовое, без подписи

  • “ሰው የተመኘውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው” የሚሉት ታላቁን የቤተክርስቲያን አባት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም ዐረፉ፡፡ በረከታቸው ይደርብን። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ስምከ ሕያው ዘኢይመውት ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ሐምሌ 15 ቀን ኅሊናው በእመቤታችን ፍቅር የተማረከ አንደበቱ የምስጋና ጅረት የሆነለት የታላቁ ሊቅ የቅዱስ ኤፍሬም በዓለ ዕረፍት ነው ቅድስት በረከቱ ትደርብን። ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ​መጋቤ ብሉይ ​ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከመምራትና ከመመገብ ባለፈ የእግዚአብሔርን ሕግና ሥርዓት ለነቢያት በማድረስና ቅዱሳኑን ከክፉ ነገር በመጠበቅ ቀዳሚው መልአክ ነበር። በዚህም ምክንያት መጋቤ ብሉይ ይባላል። ​ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ላይ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ታቦተ ጽዮንን በተቀበለ ጊዜ የእግዚአብሔርን ክብር ተሸክሞ በመካከላቸው የነበረውና ሙሴን ያነጋግረው የነበረው የቃል ኪዳኑ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው። ​ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ጭንቅ ውስጥ በነበረበት ወቅት የፋርስ መንግሥት አለቃ (ክፉው መንፈስ) በወጋው ጊዜ ብርታትን ሊሰጠው የመጣውና «ከዋናቶቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ» ዳን. 10:13 የተባለው እርሱ ነው። ​ሙሴ በሞተ ጊዜ ዲያብሎስ «ሙሴ ሰዎችን ግብፅ ውስጥ በደምና በስም ማጥፋት የገደለ ነፍሰ ገዳይ ነው ሥጋው የኔ ነው» ብሎ በተከራከረ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ግን በሥልጣኑ ተከራክሮ የሙሴን ሥጋ ሰውሮታል። ይሁዳ 1፡9። ​መጽሐፍ የሥልጣኑን ታላቅነት ሲመሰክር​«በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል።» ዳንኤል 12:1 ​ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን እስራኤል ዘሥጋን እንደመራና እንደጠበቀ ሁሉ ዛሬም በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በክርስቶስ ደም የተዋጀችውን ቤተ ክርስቲያንን (እስራኤል ዘነፍስን) ይጠብቃታል። ​ፈጣሪ በሰጠው ባለሟልነትና ርኅራኄ ምክንያት አማላጅነቱ ፈጣንና ኃያል ነው። በሕይወታችን የሚገጥሙንን ልዩ ልዩ የፈተና ማዕበላት የሕማምና የችግር ደመናዎች እንዲገለሉልን የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ እኛ ያመጣል። ክንፎቹን ዘርግቶ በመጋረድ ከሚታየውና ከማይታየው የጠላት ውጋት ከከለላ በላይ ከለላ ይሆነናል።​የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና አማላጅነት አይለየን። ​​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሐምሌ 5 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያቱን የቅዱስ ጴጥሮስንና የቅዱስ ጳውሎስን ሰማዕትነት በየዓመቱ በታላቅ ሥነ ሥርዐት ትዘክርዋለች። ሁለቱ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዕማድ ናቸው ብላ በመሠረትነት ባፀኗት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ክብር ታላቅ ስለሆነ በየዓመቱ በታላቅ ሥርዐት ትዘክርዋለች። ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር ‹‹ ኢየሱስ ጴጥሮስን አለው በዚች ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆች አይችሏትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ ። ›› ሲል ከፈጣሪው የሰማይና የምድር ሥልጣን እንደተሰጠው መስክሯል ። እንዲሁም « የዮና ልጅ ጴጥሮስ ሆይ ደምህ በመስቀል ጽዋ ተቀዳ ፤ የጳውሎስ ደም ደግሞ ወደ ሰማያት ጮህ » በማለት ገልጦታል። ቅዱስ ጴጥሮስ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ የሚሰቀልበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ እጁን በሰንሠለት አስረው ፍርዱ ወደ ሚፈጸምበት ቦታ ሲወስዱት እንዲህ ብሎ ለመናቸው  « ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እኩል እንዳልሆን ራሴን ወደታች ዘቅዝቃቹ ስቀሉኝ » ብሎ ለመናቸው እነሱም እንደለመነው ራሱን ወደ ታች እግሩን ወደ ላይ አድርገው ዘቅዝቀው ሰማዕትነት እንዲቀበል አድርገውታል ። ቅዱስ ጳውሎስም ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ታስሮ ከቆየ በኋላ በኔሮን ቄሳር ፊት ቀርቦ በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ሳይፈራ የክርስቶስን ነገር መሰከረ ኔሮን ቄሳርም በቁጣ ቃል በሠይፍ ይገድሉት ዘንድ ፍርድ ፈረደበት። ቅዱስ ጳውሎስን ወደ መሰዊያው ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩ በአስተያየቱ ምንም ፍርኀት አልነበረበትም እንዲያውም በጦርነት ላይ ድል አድርጎ ማርኮ እየፎከረ በደስታ ወደ ቤቱ የሚመለስ ወታደር ይመስል ነበር። በመጨረሻም በ 74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱ ተሰይፎ በ 67 ዓ.ም ሐምሌ አምስት ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ። ጭሮ / አሰበ ሐምሌ  4/2018 ዓ.ም ​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • видео или голосовое, без подписи

  • እንኳን አደረሳችሁ !!!

  • የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ሥራ አመራር ተመራቂ ደቀመዛሙርት ከቅዱስነታቸው ቡራኬን ተቀበሉ

  • ​"የጰራቅሊጦስ እሳት በወረደ ጊዜ ምድር አዲስ ማኅፀን አገኘች ቤተክርስቲያንም ለዓለም ተወለደች። ያ እሳት የኃጢአትን እሾህ አቃጠለ የልብንም ቅዝቃዜ አስወገደ። ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ፍርሃት ወደ ድፍረት ድንቁርና ወደ ጥበብ ተለወጠ ዓለምም የክርስቶስን መዓዛ አሸተተች።" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ​"በጎልጎታ ሙሽራው ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ሕይወቱን ሰጠ፤ በጴራቅሊጦስ ዕለት ግን መንፈስ ቅዱስ በእሳት ዘውድ አክሊል አቀዳጃት። ያ የእሳት ነበልባል የቤተክርስቲያን የልደት ጩኸት ነበረ ድምፁም ወደ ዓለም ሁሉ ደረሰ። ለአለም የታወጀችው በደም ተዋጅታ በእሳት ተኳኩላና በመንፈስ ቅዱስ ከብራ ነው።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

  • ​"እስከ ጰንጠቆስጤ ዕለት ድረስ ቤተክርስቲያን በጽዮን ሰገነት ውስጥ የተሸሸገች የሰማይ ምስጢር ነበረች። የጴራቅሊጦስ እሳት ግን መጋረጃውን ቀደደው ምሥጢሩንም ለዓለም አገለጠው። እሳቱ ሐዋርያትን እንደ ፍላጻ አፈነጠራቸው እነርሱም የአለምን ጨለማ እየቀደዱ ቤተክርስቲያንን በሁሉም ሕዝብ ልብ ውስጥ ተከሏት።" ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ ​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

  • ዓለም በውጥረትና በጦርነት ወሬ ሲናወጥ ሥጋውያን ወዳጆቻችን አብረውን ይጨነቃሉ እንጂ በልባችን ውስጥ ሰላምን ሊያሰፍኑ አይችሉም ቅዱስ ገብርኤል የጭንቀትን እሳት አብርዶ የጌታ ሰላም ለእናንተ ይሁን የሚል የብስራት ድምፅ ይዞልን ይመጣል የሰላምና የብስራት መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለሀገራችንም ሰላምን ያምጣልን የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!! ​➤ Share በማድረግ ለሌሎች ማድረስን አትርሱ 💚 https://t.me/yimesze 💚 💛 https://t.me/yimesze 💛 ❤️ https://t.me/yimesze ❤️

ዘተዋሕዶ ZE TEWAHIDO — tgindex