Ethio Psychiatry
СтатистикаContact us today: ethiopsychiatry5@gmail.com Phone: +251925801544+251942863930 Buy ads: https://telega.io/c/ethiopsychiatry
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 39
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 448
- 1/48двое суток
- 513
- 1/72трое суток
- 553
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
🚀 በኢትዮጵያ የፋይናንስ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የሰው ሃይል ትራንስፎርሜሽን ፎረም - @FinHuman 2026! የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በዲጂታል ባንኪንግ፣ በካፒታል ማርኬት እና በአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ (AI) ፈጣን እድገት ውስጥ ይገኛል። ነገር ግን የዚህ ለውጥ እውነተኛ መሪዎች ዘመናዊ ሶፍትዌሮች ሳይሆኑ በእውቀት እና በክህሎት የበቁ መሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ናቸው! ሲናፕስ ኢትዮጵያ (Synapse Ethiopia) በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ፣ ኢንሹራንስ፣ ፊንቴክ እና የካፒታል ማርኬት ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚዎችን (CEOs, HR Directors, Regulators) በአንድ ጣሪያ ስር የሚያገናኘውን ታሪካዊ ፎረም ይዞላችሁ ቀርቧል። በመድረኩ የሚዳሰሱ አበይት ጉዳዮች፦ 🔹 በኒውሮሳይንስ የታገዘ የሰው ሃይል ልማት እና የአይ.ኤ (AI) አስተዳደር 🔹 ከፍተኛ ምርታማነት ያለው ድርጅታዊ ባህል መገንባት 🔹 የፋይናንስ ተቋማት አመራሮችን ለቀጣዩ ትውልድ ማዘጋጀት 🗓 ቀን፦ ነሀሴ 28 / 2018 ዓ.ም (September 03, 2026) 📍 ቦታ፦ ሃርመኒ ሆቴል፣ አዲስ አበባ 🔗 ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ፦ +251921733677 @EthioPsychiatry
ሂሩት እና "የማይታየው" ፈተና፡ መጠነኛ የአእምሮ እድገት ውስንነት (Mild IDD) ሂሩት የ9 ዓመት ታዳጊ ናት። መልኳ እና አካላዊ እድገቷ ከእኩዮቿ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ፣ በቤተሰቧም ሆነ በአካባቢዋ ዘንድ ችግር ያለባት አይመስልም። ነገር ግን ሂሩት በውስጧ መጠነኛ የአእምሮ እድገት ውስንነት (Mild IDD) ምልክቶች ይነበቡባታል። ሂሩት የሚከተሉት ክሊኒካል ምልክቶች ይታይባታል ። 1. የእውቀት (Cognitive) ውስንነት ሂሩት እንደ 9 ዓመት ልጅ ረቂቅ ነገሮችን መረዳት ይከብዳታል። ለምሳሌ ገንዘብን መመንዘር ፣ ሰዓት መቁጠር ወይም ውስብስብ መመሪያዎችን መከተል ትቸገራለች። 2. የትምህርት መዘግየት ሂሩት በክፍል ውስጥ የማንበብ፣ የመጻፍ እና የሂሳብ ስሌቶችን የመስራት አቅሟ ከእኩዮቿ በጣም ዝቅ ያለ ነው። 3. የማህበራዊ ግንኙነት ከሚጠበቀው በታች መሆን ሂሩት ከእኩዮቿ ጋር ስትጫወት የጨዋታ ህጎችን ቶሎ አትረዳም፣ ወይም በንግግር መሃል የሚሰነዘሩ ቀልዶችን እና ምሳሌያዊ አነጋገሮችን የመገንዘብ አቅሟ ዝቅተኛ ነው። 4. የዋህነት እና ለጥቃት መጋለጥ (Gullibility & Exploitation) የሂሩት ችግር ከትምህርት ቤት ውጤት በላይ ሲሆን ሂሩት ሰዎችን የመጠራጠር ተፈጥሮ የላትም። አንድ ሰው "ይህንን ካደረግሽ ከረሜላ እሰጥሻለሁ" ወይም "ይህ ምስጢራችን ነው" ቢላት፣ የሰውየውን መጥፎ ፍላጎት የመለየት (Social Judgment) አቅሟ ደካማ ነው። እንዲሁም ሂሩት ሌሎች የሚሉትን ነገር ሁሉ ያለምንም ማቅማማት ትቀበላለች። እምቢ ለማለት (Assertiveness) ትቸገራለች፤ ምክንያቱም ሰዎችን ማስቆጣት አትፈልግም። ማስጠንቀቂያ ለወላጆች ይህ የዋህነት ሂሩትን ለጾታዊ ጥቃት እና ለጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ ሊያደርጋት የሚችል ሲሆን አጥቂዎች እንዲህ አይነት ልጆችን በቀላሉ ማታለል እንደሚችሉ ያውቃሉ። ሂሩት የሚደረግባትን ነገር "ጥቃት" መሆኑን ላታውቅ ትችላለች፤ ወይም አጥቂው በሚሰጣት አነስተኛ ስጦታ ተታልላ ድርጊቱን እንደ ፍቅር ልታየው ትችላለች። ቤተሰቦች እንዴት ልጃቸውን ሊረዱ ይችላሉ? ምልክቶቹን ቀድሞ መለየት፦ ልጅዎ ከእድሜዋ በታች የሆነ የዋህነት ካሳየች፣ ሰዎችን ከመጠን በላይ የምታምን ከሆነ እና በትምህርት ደካማ ከሆነች "ሰነፍ ናት" ብለው ችላ አይበሉ። የደህንነት ትምህርት (Body Safety)፦ የትኛው የሰውነት ክፍል የግል እንደሆነ እና ማንም ሰው ሊነካው እንደማይገባ በተደጋጋሚ (በቀላል ቋንቋ) ያስረዱዋቸው። ለአጠራጣሪ ሁኔታዎች ንቁ መሆን፦ ልጃችሁ ከማን ጋር እንደምትውል፣ ከአዋቂዎች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እና ያልተለመደ የባህሪ ለውጥ ካሳየች በቅርብ ተከታተሉ። ሙያዊ ምርመራ፦ ልጅዎ መጠነኛ የአዕምሮ እድገት ውስጥነት (Mild Intellectual Developmental Disorder እንዳለባት በስነ-ልቦና ባለሙያ ከተረጋገጠ፣ ልዩ ድጋፍ እና ጥበቃ በማድረግ የጥቃት ሰለባ እንዳትሆን መታደግ ይቻላል። ማሳሰቢያ! ይህ ታሪክ በዕውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ሂሩት የሚለው ስም እውነተኛ ስሟ አይደለም። ካሉት የአዕምሮ እድገት ውስነት አይነቶች ውስጥ 85% የሚሆኑት ከላይ የተጠቀሰው አይነት ሲሆን ወላጆች ተገቢውን ክትትል እና ድጋፍ እያደረጋችሁ በትምህርት እና በየዕለት አኗኗራቸው ልጆቻችሁ ላይ የታዘባችሁት ቅር የሚያሰኝ ነገር ከታዘባችሁ ባለሙያ ማማከር በልጆ ላይ መጥፎ ነገር ማሰብ አይደለም። ከ EthioPsychiatry ለሰው የማይታየው የውስጥ ህመምዎ ይሰማናል! ከተለያዩ ስነ ልቡናዊ ችግሮች የማገገም ጉዞዎን ዛሬ ከኢትዮ ሳይካትሪ ጋር ይጀምሩ! ✅ ቀጠሮ ለማስያዝ ወይም ለተጨማሪ ጥያቄዎች በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ለመደወል ምንም አያመንቱ ! +251949114685 +251942863930 +251964192737 +251925801544 📧 ኢሜይል: ethiopsychiatry5@gmail.com
COUNSELLING – Talk Therapy for a Healthier Mind Sometimes, all you need is a safe space to talk. Counselling, also known as Talk Therapy, helps individuals understand their emotions, manage stress, and develop healthier coping strategies. Whether you’re struggling with anxiety, stress, relationship conflicts, sleep problems, emotional exhaustion, loss, or major life changes, professional counselling provides a confidential and supportive environment to help you heal and grow. At Ethio Psychiatry, we believe mental health is as important as physical health. Our experienced Mental Health Professionals and Psychologists use evidence-based approaches to help you gain clarity, emotional balance, and confidence in everyday life. Why Counselling Helps ✅ Provides a non-judgmental, safe space to express thoughts ✅ Teaches coping skills and emotional regulation ✅ Strengthens relationships and communication ✅ Improves focus, confidence, and overall wellbeing ✅ Encourages personal growth and resilience To book your counseling session with Ethio Psychiatry 📲 Call Us today: 0786677667 +251949114685 +251942863930 +251925801544 📧 Email: ethiopsychiatry5@gmail.com ETHIO PSYCHIATRY – We feel the invisible pains!
Let us help you! Begin our Healing and Recovery journey with Ethio Psychiatry! Call or WhatsApp us on +251942863930 +251925801544 to book your session 📧 Email: ethiopsychiatry5@gmail.com
без подписи
About Us: Ethio Psychiatry Mental Health Services offers personalized support for individuals facing biological, psychological, and social-related mental health conditions. Creating a conducive and non-judgmental environment is crucial for promoting healing and well-being. Our Mental health services typically involve a range of therapeutic interventions, such as counseling, psychotherapy, medication management, and holistic approaches. These services aim to address the unique needs of each individual and help them manage their condition effectively. We feel your invisible pains! If you have any specific questions or if there's anything else we can assist you with regarding mental health services, please feel free to ask! 0786677667 /+251942863930/+251925801544 Email: ethiopsychiatry5@gmail.com
Ethio Psychiatry Mental Health Service We provide professional and quality mental health services. We are motivated by passion and we try to bridge the gap in mental health service delivery by bringing help to our communities. We offer home and online based mental health services including; √ Mental health assessment √ Counselling √ Home based mental health Nursing care √ Home based management and reviews √ Drug and alcohol comprehensive treatment package √ Mental Health consultations(online & physical) √ Psychotherapy √ Support group linkages √ Quality Rehabilitation services. √ We provide Sensitization and education programs about mental health in our communities. We feel your invisible pains! EthioPsychiatry For more information contact 0786677667/ +251925801544/+251942863930 E-mail:ethiopsychiatry5@gmail.com
Did you know? One of the benefit of booking online therapy sessions is the privacy and comfort it offers. Many people find it easier to open up about their thoughts and emotions when they’re in a familiar and safe environment, such as their own home This sense of comfort helps reduce anxiety and allows for more honest conversations, making therapy more effective. Online sessions also protect your privacy since you don’t have to worry about being seen visiting a clinic or waiting in a public space, helping you focus fully on your healing journey. Begin our Healing and Recovery journey with Ethio Psychiatry! Call or WhatsApp us on +251942863930 +251925801544 to book your session 📧 Email: ethiopsychiatry5@gmail.com
🧐 የህልውና ቀውስ (Existential Crisis) እና ራስን የማጥፋት ሐሳቦች "ሞት ሁሉንም ነገር የሚያቆም ከሆነ፣ ታዲያ ጊዜዬን ለማሳለፍ እየታገልኩ ያለሁት ምንድን ነው?" "ሁሉንም ነገር አሳክቻለሁ፣ ግን በውስጤ ትልቅ ባዶነት ይሰማኛል። በየቀኑ ከዚህ ባዶ ስሜት ጋር መኖር ህመም ሆኖብኛል፤ ከዚህ መውጫ መንገድ የማላገኝ ከሆነ መሞት ይሻላል ብዬ አስባለሁ።" የህልውና ጥያቄዎች (Existential Questions) የሰው ልጅ ስለ ሕይወት ትርጉም፣ ዓላማ፣ ነጻነት፣ ብቸኝነት እና ሞት ከሚጠይቃቸው ጥልቅና መሠረታዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ ወደ ህልውና ቀውስ ሊያመሩ ይችላሉ። በ ህልውናዊ ፍልስፍና አውድ፣ እነዚህ ጥያቄዎች የሚነሱት ግለሰቡ ለራሱ ሕይወት ትርጉም የመፍጠር ከባድ ሃላፊነት ሲሰማው እና የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ (ለምሳሌ የሞት አይቀሬነት) ሲገጥመው ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በራሳቸው ጤናማ ቢሆኑም፣ መልስ የማያገኙ ሲመስሉ ከባድ ጭንቀት ፈጥረው የድብርት ወይም ራስን የማጥፋት ሐሳብ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። በመግቢያ ላይ የተጠቀሱትን የህልውና ጥያቄዎች ጨምሮ ዋና ዋና የሰው ልጆች የህልውና ጥያቄ ጭብጦች ተጠቅሰዋል። ሀ. የሕይወት ትርጉም አልባነት (Meaninglessness) ይህ ጭብጥ አንድ ሰው የድርጊቱን ዋጋ (Value) ወይም ዓላማ (Purpose) ሲጠራጠር ይመጣል። ለምሳሌ: - "ይህ ሁሉ ጥረት( ለምሳሌ : ስራ፣ ትምህርት ቤተሰብ መመሰረት ወይም የቢዝነስ ስራ ) መጨረሻው ሞት ከሆነ፣ ታዲያ አሁን የምሰራው ሥራ ወይም የምገነባው ሕይወት ምን ፋይዳ አለው?" "በዓለም ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ብቀይር እንኳን፣ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የሚሰጠው ትርጉም ምንድን ነው?" ለ. የነፃነት ሸክም እና ሃላፊነት (Burden of Freedom and Responsibility) ይህ ጭብጥ የሚመጣው አንድ ሰው የራሱን እጣ ፈንታ የመወሰን ፍጹም ነፃነት እንዳለው ሲገነዘብ ነው። ይህ ነፃነት ደግሞ ለእያንዳንዱ ምርጫ ሙሉ ሃላፊነት የመውሰድን ከባድ ሸክም አብሮ ያመጣል። ለምሳሌ: - "ምንም አይነት ቅድመ-ውሳኔ የተደረገበት እውነት ከሌለ፣ የትኛውን መንገድ መከተል እንዳለብኝ እንዴት አውቃለሁ?" ሐ. ጥልቅ ህልውናዊ መገለል (Existential Isolation) ይህ ጭብጥ የሚያመለክተው ምንም ያህል ጠንካራ ግንኙነት ቢኖረንም፣ በመጨረሻ በአስተሳሰባችንና በተሞክሯችን ውስጠኛ ክፍል ብቻችንን መሆናችንን ስንገነዘብ የሚመጣ ነው። ለምሳሌ: - "ሰዎች ቢወዱኝም እንኳ፣ በእርግጥ ማን እንደሆንኩ ወይም በውስጤ ያለውን ስሜት ማንም ሊረዳው ይችላል?" "ከሌሎች ጋር ጥልቅ ትስስር ለመፍጠር መሞከሬ ከንቱ ጥረት ነው? ሁላችንም እርስ በርስ ተለያይተን ብቻችንን መሞታችን አይቀር !?" "የራሴን የህልውና ባዶነት ራሴ ብቻ የምቋቋመው ከሆነ፣ ለምን ከሌሎች ጋር ለመገናኘት እደክማለሁ?" መ. የሞት አይቀሬነት (Inevitability of Death) ይህ ጭብጥ ሕይወት ጊዜያዊ መሆኗን እና የሁሉም ነገር መጨረሻ ሞት መሆኑን ጥልቅ መገንዘብ ይመጣል። ለምሳሌ: - "ሞት ሁሉንም ነገር የሚያቆም ከሆነ፣ ታዲያ ጊዜዬን ለማሳለፍ እየታገልኩ ያለው ምንድን ነው?" "ሞቴ ቅርብ ከሆነ፣ ይህን ሥቃይ ቶሎ መጨረስ አይሻልም?" "በመጨረሻው ውጤት ላይ ቁጥጥር ከሌለኝ፣ ሕይወቴን በራሴ መንገድ ዛሬ ብጨርሰው ምን ችግር አለው?" እነዚህ የህልውና ጥያቄዎች ግለሰቡን ከባድ ጭንቀት ውስጥ ሲከቱና ወደ ራስን የማጥፋት ሐሳብ ሲመሩ ፤ ችግሩ የፍልስፍና ብቻ ሳይሆን ክሊኒካዊ ይሆናል። ስለዚህ እርስም ወይም የሚያውቁ ት ሰው ከላይ በተጠቀሱት የህልውና ጥያቄዎች የሕይወት ትርጉም የለሽነት የሚሰማዎ ከሆነ እና ራስን የማጥፋት ሐሳብ እየተፈታተነዎ ከሆነ የህልውና ቀውስ ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ ወዲያውኑ የአዕምሮ ህክምና ባለሙያዎችን ያማክሩ። @EthioPsychiatry We feel your invisible pains!! Begin your Healing and Recovery journey with Ethio Psychiatry! ✅For any Inquiries & Bookings please reach out: +251942863930 +251925801544 to book your session 📧 Email: ethiopsychiatry5@gmail.com
The wait is finally over. ✍️✨ One of Ethiopia's first international youth writing competitions. The moment we’ve all been waiting for is here! Beyond the Page is proud to announce the launch of our very first Writing Competition, an opportunity for writers, dreamers, thinkers, and storytellers to share their voices and make an impact through the power of words. Whether you’ve been writing for years or you’re simply looking for the courage to tell your story, this competition is for you. Every great writer starts with a single page—this could be yours. 📝 Here’s what you need to know: • Four unique writing prompts will be provided, giving you the freedom to choose the one that inspires you most. • Word Limit: 650–850 words • Registration Fee: 100 ETB (All proceeds will be donated to Abel.) • Registration is now open through the Google Form linked below. • Submission deadline: August 20 We’re incredibly grateful to be organizing this event alongside our amazing collaborators: 🤝 Tselem Youth 🤝 Ethio Psychiatry 🤝 Project EDSA 🤝 Social Service Club of SSC 📌 Register now using the Google Form below, read through the prompts, and start writing! https://docs.google.com/forms/d/1yVmIbQQL-E7KU4LSSMwPBmChNwNshW26Gl6qgtj3EMw/edit?usp=drivesdk We can’t wait to read your work. Good luck to everyone participating! 💙 #BeyondThePage #WritingCompetition #YoungWriters #CreativeWriting #WritersCommunity #StudentWriters #EthiopianYouth #WriteToInspire #Storytelling #WritingChallenge #VoicesThatMatter #WritersOfInstagram #YouthEmpowerment #Education #Creativity #AmWriting@ethiopsychiatry
без подписи
የፕሩስት ኤፌክት (Proust Effect) - የሽቶና የትዝታ ምስጢር አንድ ሰው ሲያልፍ ባሸተታችሁት የሽቶ ጠረን ብቻ ድሮ የምታውቀት ሰው ወዲያው ወደ አእምሯችሁ መጥቶ ያውቃል? ወይም የልጅነት ጊዜያችሁን የሚያስታውስ ምግብ ሽታ ሲሸታችሁ፣ በቅጽበት ወደዚያ ጊዜና ቦታ የተመለሳችሁ ያህል ተሰምቷችሁ ያውቃል? ይህ ነገር በሳይንሱ "Proust Effect" (የፕሩስት ኤፌክት) በመባል ይታወቃል። ማርሴል ፕሩስት (Marcel Proust) የተባለ ፈረንሳያዊ ደራሲ "In Search of Lost Time" በተሰኘው መጽሐፉ ላይ፣ በማዴሊን ኬክ እና በሻይ ጠረን ምክንያት በቅጽበት የልጅነት ትዝታዎቹ በግልጽ እንደታወሱት ጽፎ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሽቶ ወይም በጠረን ምክንያት የሚቀሰቀሱ ጥልቅ ትዝታዎች የፕሩስት ኤፌክት ተብለው መጠራት ጀመሩ። በአእምሯችን ውስጥ የማሽተት ስሜታችንን የሚያስተናግደው ክፍል (Olfactory bulb)፣ ከስሜትና ከትዝታ ጋር በቀጥታ ከተያያዙት የጭንቅላታችን ክፍሎች (Amygdala እና Hippocampus) ጋር በቅርብ የተሳሰረ ነው። የማየት ወይም የመስማት ስሜት መረጃዎች ወደ አእምሮ ከመድረሳቸው በፊት በሌሎች የአእምሮ ክፍሎች process ሆነው ሲያልፉ የማሽተት ስሜት ግን ምንም አይነት ማጣራት በማድረግ በቀጥታ ወደ ስሜትና ትዝታ ማዕከላችን ይሄዳል (Bypass ) በማድረግ የድሮ ትዝታዎችን ይቀስቅሳል። ለዚህ ነው አንድ ሽቶ ሲሸተን እንዲሁ ትዝታ ብቻ ሳይሆን፣ ያን ጊዜ የተሰማን ስሜት (ደስታ፣ ፍቅር፣ ወይም ናፍቆት) ጭምር በግልጽ የሚመለስልን ። እናንተስ? በብዛት ወደኋላ የሚመልሳችሁ እና አንድን ሰው ወይም ቦታ የሚያስታውሳችሁ ልዩ ሽቶ ወይም ጠረን አለ? አስተ አስተያየታችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን! 👇 © Ethiopsychiatry Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ
Schizophrenia is more than a dopamine disorder. New research highlights the role of muscarinic M1 receptors in cognition, memory, and attention, offering fresh insights into the biology of schizophrenia and the potential for more personalised treatments. Read the research to discover how targeting the brain's cholinergic system could shape the future of schizophrenia care. https://www.psychologs.com/muscarinic-m1-receptor-deficits-in-schizophrenia-a-new-path-to-better-treatments/ #Schizophrenia #MentalHealth #Neuroscience #Psychology #BrainHealth #CognitiveHealth #MuscarinicReceptors #M1Receptors #Neurobiology #Psychiatry #MentalHealthResearch #BrainResearch@ethiopsychiatry
Say No to War. Choose Peace. Every conflict leaves more than physical destruction, it leaves invisible wounds that linger for generations. War brings trauma, anxiety, depression, grief, displacement, and long-lasting psychological distress to individuals, families, and entire communities. The toll is staggering: 💔 Children lose their sense of safety and stability. 👨👩👧👦 Families are displaced and separated. 🏥 Healthcare systems are disrupted when they are needed most. 🩺 Mental health professionals witness the psychological aftermath long after the physical fighting ends. As healthcare professionals and mental health advocates, we must use our platforms to raise our voices for peace, compassion, and humanity. Every life matters, and every person deserves to live free from fear and violence. Let us stand together and say: ❌ No to War. 🤝 Yes to Peace. 🕊️ Yes to Dialogue. 🧠 Yes to Protecting Mental Health. #SayNoToWar #Peace #MentalHealth #TraumaInformedCare #MentalHealthMatters #Humanity #PublicHealth #EthioPsychiatry@ethiopsychiatry Join us👇 @ethiopsychiatry
በሥነ-ልቦና እና አእምሮ ጤና ውስጥ የሶሻል ወርከሮች (Social Workers) የማይተካ ሚና! ስለ አእምሮ ጤና ሕክምና ሲታሰብ አብዛኛውን ጊዜ ወደ አእምሮአችን የሚመጡት የሥነ-አእምሮ ባለሙያዎች ወይም የሥነ-ልቦና ባለሙያዎች ናቸው። ነገር ግን አጠቃላይ እና ዘላቂ የሆነ የአእምሮ ጤና ድጋፍን ሙሉ የሚያደርጉት የሶሻል ወርከሮች ናቸው። የሶሻል ወርከሮች አቀራረብ ጎልቶ የሚወጣው አጠቃላይ ባዮ-ሳይኮ-ሶሻል (Biopsychosocial) እይታ በመከተላቸው ነው። የአእምሮ ጤና ሕክምናን ከሆስፒታል በማሻገር፣ ከታካሚው እውነተኛ የሕይወት ተሞክሮ፣ የቤተሰብ ሁኔታ እና የማህበረሰብ ደጋፊ መዋቅሮች ጋር አስተስስረው ይመሩታል። የሶሻል ወርከሮች ዋና ዋና ሚናዎች👇 ቀጥተኛ የክሊኒካል እና የችግር ጊዜ (Crisis) ድጋፍ፡ 1. ተገቢውን የሥነ-ልቦና ምክር (Counseling/Psychotherapy) ከመስጠት ባለፈ፣ አስቸኳይ የአእምሮ ጤና ቀውስ በሚያጋጥምበት ጊዜ የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ እና እርዳታ ያደርጋሉ። 2.የህክምና እና የህይወት ትስስር መፍጠር (System Navigation): አንድ ታካሚ ከህክምና በኋላ ወደ ተረጋጋ ህይወት እንዲመለስ የቤት፣ የኢኮኖሚ፣ የህግ እና የማህበረሰብ ድጋፎችን በማመቻቸት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። 3.የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ድጋፍ፡ የአእምሮ ሕመም የታካሚውን ብቻ ሳይሆን የቤተሰብንም ህይወት ይነካል። ሶሻል ወርከሮች ለቤተሰብ አስፈላጊውን ግንዛቤ (Psychoeducation) በመስጠትና በማዘጋጀት የህክምናውን ስኬታማነት ያረጋግጣሉ። 4.የመብት ተሟጋችነት እና ማገለልን (Stigma) መቀነስ፡ ለተገለሉ እና ድምፅ ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በመቆም፣ በአእምሮ ጤና ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማስወገድ በግንባር ቀደምትነት ይሰራሉ። በአጭሩ፡ የሥነ-አእምሮ ሐኪም መድኃኒት ሊያዝ፣ የሥነ-ልቦና ባለሙያ ደግሞ ሕክምና ሊሰጥ ይችላል፤ ሶሻል ወርከር ግን ታካሚው ያገኘውን ጤና ጠብቆ የሚኖርበትን አስተማማኝ አከባቢ ያመቻቻል። በየሆስፒታሉ፣ በየማህበረሰብ ክፍሉ፣ በሰብአዊ እርዳታ አገልግሎቶች (Humanitarian services) እና በየተቋማቱ ለሰው ልጅ አእምሯዊና ማህበራዊ ደህንነት የሚተጉ ሶሻል ወርከሮችን እናመሰግናለን! © Ethiopsychiatry Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ
በሥነ-ልቦና እና አእምሮ ጤና ውስጥ የሶሻል ወርከሮች (Social Workers) የማይተካ ሚና!
Extroverts and Mental Health
Extroverts and Mental Health
semicolon ( ; ) እና ኮማ ( , ) ከሰዋስው ምልክትነት ባሻገር… ጓደኞቻችሁ ወይም በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች እጃቸው ላይ የሰሚኮሎን ( ; ) ወይም የኮማ ( , ) ምልክት ተነቅሰው (Tattoo አድርገው) አይታችሁ ታውቃላችሁ? እነዚህ ምልክቶች ከጽሑፍና ከሰዋስው ስርአት በላይ የሆኑ እጅግ ጥልቅ የሆኑ የመንፈስ ጥንካሬ መግለጫዎች ናቸው። እነዚህ ምልክቶች የሰው ልጅ ከአእምሮ ጤና ትግል ጋር ያለውን ተጋድሎ ያሳያሉ። እንዴት? 1. ታሪክን ላለማቆም የመምረጥ ምልክት (The Semicolon Project) በአእምሮ ጤና ዙሪያ «ሴሚኮሎን» በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ንቅናቄ ነው። አንድ ደራሲ ሴሚኮሎን ( ; ) የሚጠቀመው ዓረፍተ ነገሩን እዚያ ላይ በአራት ነጥብ ማብቃት እየቻለ፣ ነገር ግን ታሪኩን ለመቀጠል ሲመርጥ ነው። የሰው ልጆች ስሜታቸውን ሲምቦሊክ በሆነ መንገድ ይገልፃሉ እና ይህን ምልክት ከባድ ጭንቀትን (Depression)፣ ራሳቸውን የማጥፋት ሃሳብን ወይም ከባድ የአእምሮ ስብራትን የታገሉ እና ያሸነፉ ሰዎች ሲጠቀሙት ይታያል። ምልክቱ፦ "ደራሲው አንተ ነህ፣ ሕይወትህ ደግሞ መጽሐፍህ ነው፤ ታሪኩን እዚያ ላይ ልታበቃው ትችል ነበር፣ ነገር ግን ላለማቆም መረጥክ" የሚል የጽናት ነፀብራቅ ነው። 2. "ኮማ" ( , ) - ለአፍታ ማረፍ እንጂ ማቆም አለመሆን ሰዎች በከፍተኛ ውጥረት ምክንያት ሙሉ በሙሉ የመዛል ስሜት ሊሰማን ይችላል። ብዙዎቻችን ሕይወት ሲከብደን ወይም አእምሯችን ሲጨነቅ ነገሩን ሙሉ በሙሉ "አራት ነጥብ" (.) አድርገን የመተው ፍላጎት ሊሰማን ይችላል ፤ ነገር ግን ምን ኮማን ምልክት የሚያደው ሰዎች ሌላ ነገር ያስተምሩናል ''ቆም በል፣ ተንፍስ፣ እረፍት አድርግ… ከዚያ ግን ቀጥል!"። የሚል የህይወት ፍልስፍና ። 3. ስብራትን ወደ ጥንካሬ መቀየር እነዚህን ምልክቶች በሰውነታቸው ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ጠባሳቸውን ደብቀው አይኖሩም፤ ይልቁንም ጠባሳቸውን ወደ ጥንካሬ ምልክትነት ይቀይሩታል። "አዎ፣ ተሰባብሬ ነበር፣ አዎ፣ ለአፍታ ቆሜ ነበር፤ አሁን ግን እየኖርኩ ነው" የሚል የፅኑ ማንነት ማረጋገጫ ነው። 💡 አሁን ያላችሁበት የጭንቀት፣ የብቸኝነት ወይም የድካም ስሜት የሕይወትታችሁ ማብቂያ "አራት ነጥብ" አይደለም። ይህ ወቅት ለአፍታ የምታርፉበት፣ የምትተነፍሱበት እና ራሳችሁን የምታድሱበት እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ የምትፈልጉበት "ኮማ" ችሁ ነው። 📌 በአእምሮ ጤና ዙሪያ ለሚታገሉ እና ለምትወዷቸው ወዳጆቻችሁ Share በማድረግ ተስፋን ስጡዋቸው! © Ethiopsychiatry Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ #Psychology #HumanBehavior #MentalHealth #Peace@ethiopsychiatry