tgindex
ጥበብ ፍልስፍና

ጥበብ ፍልስፍና

Статистика

ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ ፫፮፱ ፤ ሰዉም ትሆናለህ!!

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 699
+2 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 189
30 постов
Вовлечённость
44,1%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 30
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
220
1/48двое суток
252
1/72трое суток
271

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "Would you die for me?"                  "Yes"   "No.. no.. no! that's too easy. Would you live for me¿" #Agape & #Eros በዓለም ላይ ፍቅርን የወከሉ ሁለት መሠረታዊ ዋልታዎች ናቸው። አጋፔ መለኮታዊ ወይንም ለፈጣሪ ያለን ፍቅር ሲሆን seeketh not it's own የእኔነት ምንምነት የሚገልጽ እንኳን ሌላን ይቅርና እራስን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፍቅር መስጠት  ማለት ነው። #The_Greek_god_of_erotic ኤሮስ ወይንም የግሪክ የፍትወት አምላክ በመባል ይታወቃል። በስጋ አምሳል አስቀምጠው ከሞት በኋላ የማይዘልቅና ህይወት የሌለው 'ፍቅር' ቢያደርጉትም፤ በዘመናችን ኤሮስ የፈጠረው የሁለት ፆታ ግንኙነት ሞት ችሎ የማይበጥሰው ጠንካራ ትስስሮሽ እንደሆነ ተመልክተናል። #Suicide_squad የተሰኘ ፊልም ላይ፤ 'ሃርሊ ኩዊን' የምትባል ሴት ጆከር እስር ቤት በነበረት ጊዜ ካለበት Psychopath/የእብደት ዓለም ለማስጠወጣት ስነ-ልቦናዊ እገዛ  የምታደርግለት ዶክተር ነበረች፤ ኋላ ኋላ ግን በእርሱ ፍቅር ኩፍኛ ተይዛ የለየላት እብድ ሲወጣት ያሳያል። በፍቅሯ ውስጥ የጆከር ግዴለሽነት ተጨምሮ ለ Trauma/መቃወስ ይዳርጋታል። ይህ ምናባዊነቷ በዝቶ ሙሉ በሙሉ በመስጠም እብድ ወንጀለኛ ትሆናለች። የያዛት ፍቅርም #ኤሮሳዊነትን ጋርዶ የጆከርን ግዴለሽነት ውሃ ለበስ ያደርግበታል። ይህ ውትወታ ሲታክተው አንድ ጥያቄ ይጠይቃታል - ለኔ ብለሽ ትሞቻለሽ? ‘አዎ!’ -አይ..አይ ቆይ ይህ ቀላል ነው፤ ለእኔ ብለሽ ትኖሪያለሽ !¿| ይህ dialogue ተራ ቢመስልም እጅግ ጥልቀት ይታይበታል። በአጋፔ ውስጥ አንድ ሰው ለፍቅር ብሎ ነፍሱን ለመስዋት ያቀርባል፤ ለዛ መለኮታዊ ፍቅርም ይሞታል። በተቃራኒው በፆታዊነት የተከበበው ኤሮስ ውስጥ አንድ ግለሰብ ለሚያቀረው ሰው እስከ ሞት ድረስ ይሄዳል። ነገር ግን በኤሮስ ውስጥ አፍቃሪው ለአንድ ሰው ሲል መስዋትነትን ቢመርጥም፤ አብሮ በመኖር ውስጥ ብዙ እንከንና መሠለቻቸት ምን አልባትም አንድ ሺህ አንድ ግዜም የመለያየት ሀሳቦች ተነስተው ይሆናል። ያ እንኳን ቀርቶ አንድ ሰው ከመኖር ህላዌነት አልፎ ለሚያፈቅረው ሰው እንዲሞት ግድ ሲሆንበት ክህደት ሲፈጽም ይታያል። ይህን ታላቅና ጥልቅ በሚባለው አጋፔ ውስጥ ይሁዳ እና ጴጥሮስ በመጨረሻ ለክርስቶስ ያላቸውን መለኮታዊ ፍቅር ሲፈተን ማየት በቂ መገለጫ ነው። በአጋፔ ውስጥ ሰው ለፈጣሪው ፍቅር ሊሞት ሰማዕትም ሊሆን ይችላል ይህ ቀላል ነው። ነገር ግን ለእግዜሩ ብሎም ለሃይማኖቱ ሲል በመሰቃየት እንግልትንም በማየት ባጭሩ በመኖር አገልግሎት ውስጥ እስከመች ይዘልቃል?። ለዚህ መልስ ሊሆን የሚችለው በእኛ ሀገር ተፈጥረው ለነበሩ #Religion_paradox ስሜት አዘል መልሶች ናቸው። ሃይማኖታቸው ወይንም አምላካቸው የሚገፋ ተግባር ሲፈጸም ይህን ግፍ ለመቃወም እስከሞት ድረስ የሚደርሱት ሃይማኖታቸው ላይ ብዙም ጠንካራ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች በህይወታቸው ውስጥ አገልግሎታቸውን ለፈጣሪ ያልሰጡ ሆነው ሳለ ለፈጣሪ ለመሞት ግን ከእነርሱ በላይ የሚፈጥን የለም። በዚህ መስዋት ወይንም 'ሰማዕት' መሆን የበፊት እድፋቸውን በጠቅላላ የሚጸዳ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ይህ አቋራጭ መንገድ ይበል የሚያሰኝ ተመራጭ መንገድ ሆኖ ተቀምጧል። በመጨረሻም ለፍቅር ወይንም ለምንወደው ነገር ብለን የሞት ሰይፍ ውስጥ አንገታችንን ለማስገባት ከመሮጣችን በፊት፤ እራሳችንን እንጠይቅ። ለዛ ነገር ለመኖር ዝግጁ ነበርን ወይ..¿

  • видео или голосовое, без подписи

  • #Ego #ንቁ_አእምሮ ታዋቂው የስነ-ልቦና ጠበብት #Carl_Gustav_Jung የሰው አእምሮ (psyche) እጅግ ውስብስብ የስነ-ልቦና ስርዓት (Analytical Psychology) አለው ይለናል።በተለያዩ የማንነት ክፍሎችም የተዋቀረ መሆኑንም ይገልፃል። ከነዚህም ክፍሎች ውስጥ አንዱ ኢጎ  ነው። "#Ego" (#ኢጎ ) በትክክል ምንድነው? እንደ ዩንግ እይታ፣ ኢጎ የንቁ አእምሯችን #Consciousness…

  • መላእክትና ጻድቃን ያለ ጉቦ በማይሠሩበት ሀገር የትራፊክ ፖሊሶችና ገቢዎች ላይ ማካበድ አግባብ አይደለም!፡፡ ስእለት, ነዝር ይባላል እንጂ ያው ጉቦ ነው የምድሩን ጨርሰህ ሰማዩንም ብራይብ ታደርጋለህ። ሼኪው ያለ ጉቦ (የበርጫ ¡ ካልተሰጠው ዱአ የማያደርግበት ፣ ፓስተሩ ያለ ጉቦ ጸሎት የማይጸልይበት ፣ ቄሱ ያለ ጉቦ የማይፈታበት ኑሮ ውስጥ እየኖርክ ዓለማውያን በምን ዕዳቸው ነው በነጻ የሚሠሩት!? ባይሆን ባያበዙት። መንግሥትም ጉቦን ለማጥፋት ባይደክም ጥሩ ነው። ጻድቃን ሙስና እየላፉ ፤ ኃጥኣን ጻድቃን ይሁኑ ማለት በቀላሉ አይሳካም።

  • 20 июл.1 301132

    ፍቅረኛዬ እግሮቿ ውብ ናቸው። በየትኛውም አምሳለ ፍጡር ያልተሳሉ፣ ያልተቀረጹ። በራስ ቤት ነው ያደገቸው፣ የራስ ልጅ፡፡ ጠቢባን እሑድን ማኅሌት አድርሰው ሲመለሱ ቁርስ አፋቸው አድርገው ጌቶች ለስብሰባ እስኪጠሩዋቸው የልዕልቲቷን እግር እንዲስሉና እንዲቀረፁ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ በቀደሙት ሳምንታት የምትወደው ክፍለ ጊዜ ነበር በቆይታ መሰላቸትን አመጣች በዛ ላይ አንጀት አርስ ሰዓሊ ልብ የሚሞላ ቀረፂ አለመገኘቱ ያዝላት ተያያዘ፡፡ ከፊቷ ተጎልተው እኒያ ጠቢባን እግሮቿ ላይ ተተክለው ሲያፈጡ እርሷም ደፋ አለች የዓይኖቿ ብርሃን ከእግሮቿ ሳይደርሱ መከፋትና ፅንስ ያረገዘው ሆዴ መንገዷን ገታት፡፡ ዐይኗ እንባ አቀረረ ፊቷ ፍም መሰለ በራስ ቤት አንዲት ዘለላ እንባ እንኳ ማውረድ የተከለከለ ነው ያን ያደረገች እንደሆነ በተለይ እንግዶች ፊት፣ እንደ አሽከር መታጠቂዋ ተፈቶ ጀርባዋን ትገረፋለች፡፡ ያን ለመቀበል አልፈለገችም ጭኗን በእጇ ዳመጠችውና ከእንባዋ ቀድማ ፈንደድ ብላ ተነሳች። እኔም የራስ ልጅ ነበርኹ አዪ ''ነበር ለካ እንዲ ቅርብ ነው'' አሉ የብጡል ልጅ እቴጌ ጣይቱ እውነትም ነበር ለካ እንዲ ቅርብ ኑሯል በዛን ሰንበት እነርሱ ግዛት ለአባቷ ከአባቴ የተላከ ሥጦታን ለማስረከብ ስጋልብ አርፍጄ በጊዜ ደረስኩ የልዕልቲቱ አባት ከመኝታ ቤታቸው ነበሩና ከሰፊው ክፍል እንድንጠብቅ በአክብሮት ተጋበዝን አንድ ፈርጣማ ወጣት እየመራን አስገባን ያኔ ነው ከልዕልቲቱ እንባ ያቀረሩ ዐይኖች ጋር የተላተምነው። እምታምር እንቡጥ ደም ግባታም ሴት ነች ለአፍታ ዐይኗን ሰርስሬ ዐየሁት ጠቢባኑ የተተከሉበት እግሮቿን በዓይኔ ሰረሰርኩት፣ ፍም እሣት ነው ለበለበኝ፣ ጉልበቴ ሊረድ ዳዳው። እጅ ነሳኋት፥ እጅ ነሳችኝ ። የአግርሽ ውበት ፈጀኝ አልዃት 'ውሰደኝ' አለችኝ። ሻሞላዬን ከሰገባው መዘዝኩ መልካም የተቀበለን አገልጋይዋ ጦሩን ቀሰረ:: ጠባቂዎቼና ጠባቂዎቻቸው መሳሪያ ተለካካን ተጎዳዳን በግርግር እንደ አዲስ ሙሽራ አቅፌት ወጣሁ። እየጋለብን ጠፋን ተሰደድን፡፡ አሁን እርቀን እንኖራለን ዛሬም እሑድ ነው እረፋዱ ላይ። ከመስኮቱ ጎን የሙላቱ አስጣጥቄን ጃዝ እንሰማለን የቡና ጭስ በስሱ ወደ ሰርናችን ይገባል ፤ ቀሚሷን እስከ ጉልበቷ ሰበሰበችው ሔድኹ እግሯን ሳምኩት በወይራ ዘይት ውብ እግሮቿን ታፋዬን አስረግጬ ከባቷ እስከ ጣቶቿ ጫፍ..... ፤  ያን ዕለት ሰንበት ስለሆኑት ነገሮች እያወጋኋት እየተረኩላት፣ አሻታለሁ። የአባቷን ስም ስጠራ ቅርም ንድድም ይላታል ናፍቃለችም፡፡ በግዛቴ ሳለሁ አንዲት የራስ ልጅ ከአባቷ እንዳረገዘች ይነገር ነበር፡፡ አንስቼባት አላውቅም። እንባዋን አልሻም፡፡ ባባቷ ግዛት መሳል መቀረፅ አልፈለገችም በራሷ ግዛት መዳበስ መፃፍ ነበር የፈለገቸው። ቸሩ መድኀንያለም የልቧን መሻት ፈፀመ ፡፡

  • ጥበብ ፍልስፍና pinned «የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ፣ ልብህ አድርገህ ተመልከት:: ኢትዮዽያ የተባላቸው አንደኛ እናትህ ናት:: ሁለተኛ ክብርህ ናት:: ሶስትኛ ሚስትህ ናት ። አራተኛ ልጅህ ናት :: አምስተኛም መቃብርህ ናት:: እንግዲህ የ እናት ፍቅር ፣ የዘውድ ክብር ፣ የሚስት ደግነት ፣ የልጅ ደስታ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀ ተነሳ :: አፄ ዩሐንስ ፬ኛ ሐምሌ 5/1829 - መጋቢት 2/1881…»

  • 11 июл.1 531168

    видео или голосовое, без подписи

  • 8 июл.1 567139

    #Identity_Fragility የማንነት መሰባበር / የማንነት ደካማነት አንድ ሰው ስለራሱ ማንነት፣ እሴቶች፣ እምነቶች እና ቦታ ያለውን ግንዛቤ ምን ያህል ደካማ፣ ያልተረጋጋ እና በቀላሉ ሊናወጥ እንደሚችል የሚገልጽ የስነ-ልቦና ሁኔታ ነው። ፤ ይህ ሁኔታ ያለባቸው ሰዎች የራሳቸውን ማንነት በግልጽና በፅናት ከመግለጽ ይልቅ፣ በውጫዊ ሁኔታዎች፣ በሌሎች ሰዎች አስተያየት ወይም በሚያጋጥሟቸው ክስተቶች በቀላሉ…

  • 7 июл.1 188111

    ኩስሚ መብላት አማረኝ አንቺ ማነሽ! መሰረት! መሰረት! ይሔ ልጅ አልተነሳም ፡ ትላለች አትዬ እማድ ቤት ሆና፡፡ እኔን አይሰማኝም እኮ ነይና ቀስቅሽው ትላላች የቤታችን የበኩር ልጅ መሲ (ስወዳት) እኔን አያርገኝ ከመጣው ትላላች እትዬ እዛው እማድ ቤት ሆና። እኔ እቴ አልጋ ልብሴን ይበልጥ እላዬ ላይ ጠቅልዬ የሚሉትን እየሰማው እንዳልሰማው አይኔን ጨፍኜ ፀጥ ምናባቱ ይሔ ት/ቤት ረፈደበት እኮ ተኝቶ ሊውል…

  • 5 июл.1 704124

    ዴዚዴራታ በዚህ ዓለም ጥድፊያና ውካታ ሳትበገር በርጋታ ኑር። ከጸጥታ ሰላም ሊገኝ የሚችል መሆኑንም አትዘንጋ ያለ አግባብም ሳትበለጥ የተቻለህን ያህል ከሰዎች ሁሉ ጋር ስምምነት ይኑርህ። እውነት ነው ብለህ የያዝከውን ነገር በጥሞና እና በግልጽ ከመናገር ወደ ኋላ አትበል። ሌሎች የሚናገሩትን ከመስማትም አትቦዝን። ሆነ ብሎ ለሚያዳምጣቸው ከዳተኞችም ሆነ ከደደቦች ቁም ነገር አይታጣም ከጯሂዎች እና ከእኔ አለሁ ባዮች ራቅ፤ እንዲህ ያሉ ሰዎች መንፈስን ያውካሉና። ራስህን ከሌሎች ሰዎች ማመዛዘን ከያዝክ እብሪተኛና መንፈሰ መራራ ልትሆን ትችላለህ። ምክንያቱም ከሰዎች መካከል ካንተ የሚበልጡም የሚያንሱም አይታጡም። በምትሠራው ሥራ መሳካትም ሆን በወደፊት ውጥንህ ተደሰት ፤ የምትሠራው ሥራ ዝቅተኛም ቢሆን የእኔ ነው ብለህ ያዘው። በዚህ ወረቱ ተለዋዋጭ በሆነ ዘመን የሚያዋጣው የአንድ ሙያ ባለቤት ሆኖ መገኘቱ ነው። ዓለም በሸፍጥ የተሞላ በመሆኑ ገንዘብን በሚመለከት ነገር ጥንቃቄ አይጉደልህ። ይህ ሲባል ሰው ሁሉ ክፉ ነው ብለህ በደፈናው አትገምት። ከፍተኛ ቁም ነገር ያለው ተግባር ለመፈጸም የሚጣጣሩ ብዙ ሰዎች መኖራቸውን እና ሕይወትም ብዙ ጀብዱ የሞላበት መሆኑን አትሳት። በራስህ ተማመን!። በተለይም ፍቅር ማስመሰልን የሚጠላ መሆኑን እወቅ። እንዲያውም ፍቅር በዘፈቀደ የሚታለፍ ነገር አይደለም። በዚህ የመንፈስ ድርቀትና መሰልቸት በሚያጠቃው ዓለም እንደ ሜዳ ሳር ጠውልጎ የሚለመልም ፍቅር ብቻ ነውና የወጣትነት ወራት ፍላጎትህ ብዙ ዘመን ለተጠራቀመ የሽምግልና ምክር በለዘብታ ይገዛ። ሳታስበው ለሚያጋጥምህ መከራና ችግር ድጋፍ እንዲሆንህ የመንፈስ ጽናት ይኑርህ። ሆናም እንዲህ ያለ ነገር ሳይደርስብኝ አይቀርም እያልክ በከንቱ ልብህ አይታወክ፡ ብዙውን ጊዜ ፍርሃት የሚመነጨው ከመዳከምና ከብቸኝነት ነው። ወግ ባለው ሁኔታ ኑሮህን መቁጣጠር አስፈላጊ ቢሆንም እንኳን፣ ራስህን መንከባከብ ቸል አትበል ከዕፅዋትና ከከዋክብት የማታንስ የዚህ ታላቅ ፍጥረተ ዓለም ዝርያ ስለሆንክ፣ በዚች ዓለም ላይ የመኖር መብት አለህ። ሁኔታው ላንተ ግልጽ ሆኖ ባይታይም፤ ይህ ታላቅ ፍጥረተ ዓለም ያለ ጥርጥር ምስጢሩ እያደር እየተገለጠ በመሄድ ላይ ይገኛል? ስለዚህ ሕሊናህ አውጥቶ አውርዶ ከተቀበለው አምላክ ጋር ግንኙነትህ የሠመረ ይሁን ከትግልህና ከወደፊት ምኞትህ ጋር በዚህ ትርምስ በበዛበት ዓለም ስለምትኖር ለነፍስህ ሰላም አትንፈጋት ከክፋቱም፣ ከልፋቱም ሆነ ከውጣ ውረዱ ጋር ይህ ዓለም ግሩም ስፍራ ነው። እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት። ደስተኛ ለመሆንም ተጣጣር። @ethiosecret

  • 2 июл.1 260138

    ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ ፫፮፱ ሙሉ በሙሉ ውስጥህን ባዶ አድርግ እርጋታ ይኑርህ። ምንም እንኳን ሁሉም ነገር አንድ ለይ ቢነሳም፤ ሲመለስም ተመልከት። ሁሉም ነገር ያብባል፣ ግን ውሎ አድሮ ወደ ስሩ ይመለሳል። በእርጋታ እያንዳንዱ እጣ ፋንታውን ያሟላል ወደ መሰረቱ ሲመለስ እርጋታ ይባላል፣ እርጋታው ደግሞ ወደ ተፈጥሮ ይመልሳል፣ ወደ ተፈጥሮ መመለስ ደግሞ…

  • 1 июл.1 385131

    ጠቅላላ ዕዉቀት! የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ህብረት (USSR) ብሔራዊ መዝሙር (1977-1991) በታዋቂው የሩሲያ አቀናባሪ አሌክሳንደር ቫሲሊየቪች አሌክሳንድሮቭ (1883-1946) በ 1938 ዓ.ም.  አካባቢ ተቀናብሯል።  መጀመሪያ ላይ ለቦልሼቪክ ፓርቲ መዝሙር እንዲሆን የተሰራ ነበር። ግን  በ 1944 ዓ.ም.  (በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት) ይፋዊ ብሔራዊ መዝሙር ሆነ።  የመጀመሪያው ግጥም በሰርጌይ ሚክሃልኮቭ እና ጋብሪዬል ኤል-ሬጊስታን የተፃፈ ሲሆን የጆሴፍ ስታሊንን ስም በግልጽ ያካተተ ነበር።  ከስታሊን ሞት (1953) በኋላ፣ በ1956 ዓ.ም.  በተጀመረው ዲ-ስታሊናይዜሽን (ከስታሊን አምባገነናዊነት የመላቀቅ) ምክንያት፣ መዝሙሩ ለ20 ዓመታት ያህል ያለ ግጥም መሳሪያ ቅንብር ብቻ ይቀርብ ነበር።  በ1977 ዓ.ም.  የጥቅምት አብዮት 60ኛ ዓመት እና አዲሱ የሶቪየት ህገ-መንግሥት ክብረ-በዓል በማስመልከት ሰርጌይ ሚክሃልኮቭ የቀድሞውን ግጥም በማሻሻል አዲስ መዝሙር አዘጋጀ።  ስታሊንን የሚያወድሱ ክፍሎች ተወግደው የጦርነት አውዶች ተለውጠው እና በኮሙኒዝም ድልና የህዝቦች አንድነት ተተክተዋል።  ይህ መዝሙር እስከ 1991 ዓ.ም.  የሶቪየት ህብረት መፍረስ ድረስ አገልግሏል።  ዛሬም ይህ ዜማ በተለያዩ ግጥሞች በሩሲያ ብሔራዊ መዝሙር ሆኖ ቀጥሏል።  ሙዚቃዊው ባህሪያቱ የአሌክሳንድሮቭ ዜማው ጀግነትና፣ ድፍረት እና ሐያልነት የያዘ እና በጣም ማራኪ ዜማ ያለው ነው። በሩሲያ ባሕላዊ ዘፈኖች፣ የቤተ-ክርስቲያን ዝማሬዎች እና የወታደራዊ ሰልፍ ሙዚቃ ተጽዕኖ ያደረበት ዜማ ነው።  ዜማው አንድነትን ታላቅነትን፣ ኩራትን እና የብሩህ የወደፊት ተስፋን ያስተጋባል። በትላልቅ ስታዲየሞች፣ በወታደራዊ ሰልፎች ወይም በታሪካዊ ፊልሞች ሲደመጥ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አስደናቂ ነው።  ብዙ ሰዎች ይህን ዜማ ከዓለም ምርጥ ብሔራዊ መዝሙሮች ጋር ያወዳድሩታል። የግጥሙ ትርጉም የህዝቦች አንድነትን፣ የሌኒን ፓርቲን፣ የኮሙኒዝምን ድል እና ለቀይ ባንዲራ ያለውን ታማኝነት ያወድሳል። ግጥሙ ባጭሩ ...  አልል በይ፣ ነጻዋ የአባት ምድር፣ የህዝቦች ወዳጅነት የጸናው ምሽግሽ! የሌኒን ፓርቲ የህዝቡ ብርታት፣ ወደ ኮሙኒዝም ድል ይመራናል! ማይሞተው የኮሙኒዝም ዕሳቤ ድል ውስጥ፣ የሀገራችንን ብሩህ ተስፋ እናያለን። ለክብርት እናት ሀገርና ለቀይ ሰንደቅ ዓላማዋ፣ ሁልጊዜም በታማኝነት እንቆማለን! ይህ መዝሙር የሶቪየት ርዕዮተ-ዓለምን  የአንድነት፣ የጥንካሬ እና የተስፋ በጥሩ ሁኔታ የሚገልፅ ሲሆን  ታሪካዊ ጠቀሜታው እጅግ ትልቅ ነው። ☭ ✊☭

  • [መፍረስ አለመፍረስ] ስላቮይክ ሲናገረው የሰማሁት 'ቁምነገር አዘል ቀልድ ' ነበር እንዲህ የሚል። የጥንቷ ታላቋ ሶቬት ህብረት ላይ ነው : አንድ በዛች ግዛት ውስጥ |አገርም አሃጉርም ለመባል የምታስቸግር ግዛት ናት| የነበረ አንድ ምስኪን የኮሙኒዝም ምልክት ከሆነችው አገር ሊጠፋ ሲሞክር ድንበር በሚጠብቅ ሰው ይያዝና ለምን ለመጥፋት እንደተነሳ ይጠየቃል። ሰዎዬውም በርግጥ ሁለት ምክንያቶች አሉኝ…

  • 29 июн.1 9622012

    አንዳንዴ ስንኖር የምንሞት አይመስለንም አስታውሱ!         ትሞታለህ!! MEMENTO MORI!!       መልካም አዲስ አመት🙌

  • 27 июн.1 266174

    ⁶“#Love_is_a_serious_mental_disease” ሲንደሬላ አንድ ጫማ አውልቃ ፍጹም ፍቅር አገኘች። አንቺ ግን ሙሉ ልብስሽን አውልቀሽ  ፍቅረኛ አጣሽ..🤓

  • 26 июн.2 735239

    የተገናኘን ቀን ነው አልጋ ላይ ራሳችንን ያገኘነው ፤ ወሲባችን ፍቅር አልነበረውም ፤ ሰክረን ነበር ፤ ከአንድ ዙር   መፋተግ በኋላ ፤ አንድ ዙር  ፍቅር  አልባ ወሲብ እንዳለቀ ፊቴን አዞርኩ ሲጋራዬን ለኮስኩ ፤ ፊቷን አዙራ ስልኳን መነካካት ጀመረች ። ሁለታችንም ጀብረር ብለን ነበር። ምንም ያላወራው ይመስለኛል ፤ እርግጠኛ ነኝ ከዚህ በኋላ አንገናኝም ፤ በአንድ ቀን የምትጋደም ፣ ከሴተኛ አዳሪ…

  • 19 июн.1 487135

    ከህልሜ ፍቅር ያዘኝ በጣም በተደጋጋሚ ፈፅሞ አግኝቻት በማላቃት ልጅ ሃሳብ ፈገግ እያልኩ እተክዛለሁ ጸጥታ በሰፈነባቸው የምናቤ ጥጋጥግ ውስጥ የተወሸቀች አንዲት ሴት። ሃሳቤ ወደዛ ምናብ ውስጥ በገባ ቁጥር እራሴን በሷ ፍቅር ደጋግሞ እየወደቀ አገኘዋለሁ። በተጋራነው ጊዜ፣ ባሳለፍናቸው ሰዓታት፣ ባወጋናቸው ቃለት፣ በመገናኘት የተጸነሰ ፍቅር አይደለም። በብቸኝነት ሃሳቤ ውስጥ የሚያድግ ፍቅር ነው፣ እኔ ውድ…

  • 17 июн.1 398135

    እማ ዘንድ ይደር?! ቴዎድሮስ ገብሬ በ'በይነ-ዲሲፕሊናዊ የሥነ ጽሁፋዊ ንባብ፣ ሚካኤል ሽፈራው በ'ማስጠንቀቂያው ደውል፣ ሀብታሙ አለባቸው በ'ታላቁ ተቃርኖ፤ ስለ 'Myth' ወይንም ትርክት አፈጣጠር፣ አስተዳደግና በአገረ መንግስት እና የብሄር ግንባታ ላይ ያለውን አውንታዊ ተፅዕኖና የአንድ ማህበረሰብን ስብዕና እንዴት እንደሚቀርፅ አትተዋል። እማ ዘንድ ይደር እነዚህን የጥናት መስኮች የሚነካ ሙዚቃ ነው። ሀብታሙ አለባቸው እንደሚሉት 'ኢትዮጵያ አሁንም አሁንም state formation ወይም ሀገረ- መንግስት ግንባታ ላይ ነች እንጂ Nation build አድርጋ አልጨረሰችም።' ይህም ማለት ህዝቧን ለአንድ አላማ አስተባብሮ የሚያኖር የወል ማንነት ወይም Collective Consciousness እስካሁን አልፈጠረችም። ይሄ ሙዚቃ ይህንን ይደግፋል.. ቁጭት የወለደው መጠይቅ ያነሳል፣ በትዝታ ቅኝት ይቃትታል። ሙዚቃው በጭብጥ ረገድ ታሪክ ጠቃሽ፣ Folklore (ሀገረሰባዊ)'ና rhetoric ነው። በዚህ ሙዚቃ የወል ማንነት (National myth) ሊመሰርት ነው የፈለገው። ለ' Great Britain- King Arthur ለ'Japan- Emperor Jimu እንደሆነ ሁሉ እዚህ ላይ ንግስት ማክዳን¹ መርጧታል። ብሄር ግንባታ ላይ ያተኮረ በአዲስ ማንነት የተዋቀረ ሌላ አገር የመስራት ተልዕኮ። ለዚህም አንድ ጀግ'ና ያስፈልጋል። ምን የሚያደርግ? "ማ ዘንግ ይዞ ገብቶ ገዳም ቢያገናኘው ፍቅርን ካ'ዳም ማ ፆም ይዞ ቆጥሮ ጠጠር ባሳከለው ፍቅርን ሀገር" ራቁቱን ለሆነ ገላ የምንጥለት ነው! "ስለት አለብኝ ከርቤ እና እጣን ለመተያየት እንዲያበቃን፡፡ የጠቢቡ ሰው የሊቁን ቅኔ ህልሜ አይፈታም ሳላይሽ ባይኔ፡፡ እማ ዘንድ ይደር ሄዶ ጎኔ ሰው አልሆንም ካላንቺ እኔ፡፡ ማዘብ ኖሮ ለኔ ገላ ደግሞ አያለሁ ካንቺ ሌላ፡፡" ¹በቅዱስ በመፅሃፉ የተጠቀሰች ብቸኛ በራሷ የነገሰች ሴት። እውቀትን ፍለጋ ባህር የተሻገረች እና የሁለት ሺ አመታት ስርወ' መንግስት መመስረት ምክንያት የሆነች ንግስት።

  • 17 июн.1 0452

    видео или голосовое, без подписи

  • 17 июн.1 07574

    видео или голосовое, без подписи

ጥበብ ፍልስፍና — tgindex