- Последний пост
- 6 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 584
- 1/48двое суток
- 669
- 1/72трое суток
- 721
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሞቱን የናፈቀው ከያኒ በአንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሃይሌ ሩት ስለ ኤሊያስ መልካ የመጨረሻዎቹ ጊዚያት ተጠይቆ ሲመልስ ፤ ያሳለፈውን ስቃይ እንዲህ ብሎ ነበር የገለፀው " ህክምናውን ካላደረገ መተንፈስ ስለሚቸግረው ሰውነቱ ይነፉፉ ነበር። ጠዋት እስቲዲዮ ስንሄድ በጭንቀት ውስጥ ሆኖ እየሰራ ነበር የምናገኘው፤ በልመና - - - በለቅሶ ካልሆነ በቀር እሺ ብሎን ሀኪም ቤት ሄዶ አያውቅም" ኤልያስ ለአጭር ጊዜ ተልዕኮ ኖሮት እሱን ለመፈፀም የመጣ ሰው ነበር የሚመስለው። በፍፅም ጊዜ አልነበረም። በፀሀይ መውጣትና መግባት እርግጠኛ ቢሆን እንኳን ቀንና ለሊትን ለይቶ አያውቅም ነበር። ኤሊያስ ለትውልዱ መልዕክት በዘሪቱ ፤ በቴዲ ፤ በኃይሌ ፤ በእዮብ ና በሚኪያ በኩል አስተላልፎ መሄድ አለበት። ለዚህ ደግሞ ጊዜ እንደሌለው ስለሚያውቅ ከስቲዲዮው ግድ ካልሆነበት በቀር አይወጣም። ለኤልያስ ሞት ምክንያት ሆኖ የምትነገረውን በሽታ እንኳን የመጣችበት ከስቲዲዮ ባለመውጣቱ ምክንያት ነው።ርሃብ ሲሰማው ጣፉጭ ጁስና ብስኩት እየቀመሰ ስራውን ይቀጥላል። የበዛችው ጣፉጭ ስኳር ሆናበት ፤ ስኳሩ ኩላሊቱን ከጥቅም ውጪ አደረገበት። አብዛኛው ሰው ኤልያስን የሚያውቀው "እንዳይገለኝ" የሚለው የዘሪቱ ከበደ ዘፈን ቪዲዮ ላይ ጆሮ ጌጥ አድርጎ ፊቱ ላይ "ዘራፍ" የሚል ወጣትነት እየተነበበት ጊታሩን ሲጫወት ነው። በቅርብ ደግሞ አንድ የቲቪ ፕሮግራም ላይ ኤልያስ የዘፈን ተወደዳሪዎችን ሲዳኝ አይተነው ነበር። እዛ ላይ የኤልያስ ገፅታ ልብ የሚሰብር ነበር። ፈገግታው ቅስፈታዊ ሆና ብልጭ ብላ ድርግም ትላለች። በሽታው ሆዱን አተለቆበት መልኩን አጥቁሮታል። ያን ባለ ሎቲ ጊታሪስት ወጣት በዚህ መልኩ ማየት ልብ ይሰብራል። ኤልያስ በርግጥ ታሞ ነበር። በመጨረሻም ህዝብ ኤልያስ እንደታመመ እንዳወቀ ሁሉ ኤሊያስ ደግሞ እንደማይድን ያውቀው ነበር። ተልዕኮውን እንደሆነ ጨርሷል። አሁን ወንበሩ ላይ ደገፍ ብሎ የሚናፍቀውን ፤ ከስቃዩ ሁሉ መቶ የሚገላግለውን ተናፉቂውን በመጠበቅ ላይ ነው። ተናፉቂው ዘግይቶ ስቃዩ ሲበረታበት ፤ ኤልያስ ውብ ድምፅ ባላት መሰሉ ፉንታሁን በኩል እንዲህ ብሎ ጠራው ሀገሩ ደጁ ሩቅ እየመሰለኝ እንደ ወፍ እንግዳ እየተብሰለሰልኩኝ ዘመድ እንደሌለው እንደ በዕድ ሀገር ሰው እንደ ቀልድ ባይተዋር ሆዴን እየባሰው (ኤልያስ እዚህ ጋር የቤቱ ደጅ ባቡር ተሰፍሮ እንደሚሄድበት ሀገር ርቆበት አቅም አቶ ቁጭ ብሏል። እንዲህ በመሆኑ ደግሞ ብቻ አርጎት ሆድ አስብሷታል።) ወይ ምጣ ወይ ልምጣ ከሆንክ የኔ ዕጣ በምን ጥፉቴነው ልቤ እ'ዲ የሚቀጣ (ልብ አርጉ እዚህ ጋር ኤልያስ እንማትመጣ ከሆነ እኔ ልምጣ ከዚህ በላይ አልሰቃይ እያለ ነው) እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር የውሃ ሽታ ሆኖ ሄዶ ባይቀር በል በርታ በል በርታ ልቤ ጨከን በል ሲመጣ ይመጣል እውነቱን ተቀበል ( እዚህ ጋር ደግሞ ኤልያስ ቢመጣ እጆቹን ዘርግቶ እንደሚቀበለው ይናገርና ፤ ከላይ "እማትመጣ ከሆነ ልምጣ" ማለቱ ልክ አለመሆኑንን አምኖ ልብን አይዞህ ሲመጣ ይመጣል ጨከን በል ብሎ ያፅናናዋል) እህ ወየው ጉድ ስንት አለ በሆዴ አምቄው ነው እንጂ ንሮዬን በዘዴ አለ ጋደም ጋደም ሰው ሁሉ ሊተኛ እኔ ቁጭ ብያለሁ ያንተ በሽተኛ (የከፉ በሽታ ሳይዛቸው እንዲሁ በድንገት በጊዜ ጋደም ጋደም ካሉ ወጣቶች መካከል ኤልያስ ጋር የሰሩት እዮብ መኮነን ፤ ሚኪያና ደረጀ ዱባለ የሚጠበሱ ናቸው ኤልያስ ግን ታሞ በስቃይ ውስጥ ሆኖ ቁጭ ብሎ ቢጠበቀውም አልመጣ ብሎታል) አብዛኛው የኤልያስ ስራዎች ፊት ለፊት ከሚናገረው በላይ ናቸው!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በክርስቶስ አምናለሁ የሚል ብሄርተኛ ቢያጋጥመኝ የክርስቶስ ሰው እንዳልሆነ አውቃለሁ። ረቂቅ ምርመራም አያስፈልግም እሱን ለማወቅ ቀኖና ትውፊት መመርመር ግድ አይደለም። ሺህ ግዜ እንጥልህ በመዝሙርና በቅዳሴ ቢነድ ብሄርተኛ(ጎሰኛ) ነህ?በቃ ክርስቲያን አይደለህም። [ አዳም ረታ ]
አዋላጅና አዋቂ ሰው ያየውን ሁሉ አይናገርም። ያወቁትን ሁሉ መናገር እውቀት አይደለም የእውቀት ማነስ ምልክት ቢሆን እንጂ… አንዳድ እውቀቶች ለአንተ አዲስ ሲሆን ለምትነግረው ሰው ያረጀ ሊሆን ይችላል። አእምሮህ የመዘገበውን ሁሉ አፍህ አይናገር አንዳዱን እራስህ ጋር አብስለህ ለራስህ ተጠቀምበት።
видео или голосовое, без подписи
★ ሁሌም አስታውስ.... ★ ምንም ነውር የሌለበት ጓደኛ የፈለገ ሰው ብቻውን ይኖራል፣ ★ ምንም አይነት ችግር የሌለበት ትዳር የፈለገ ላጤ ሆኖ ይኖራል፣ ★ ሙሉ የሆነ ዘመድ የፈለገ ሰው ዝምድናውን ቆራጭ ይሆናል። (ፊዮዶር ዶስቶዬቭስኪ)
"ከዚህ በኋላ ክርስቶስን በገንዘብ የሸጠው ሰው ላይ አልፈርድም።በደካሞችና በሰካራሞች ልብ ውስጥ ምን እንዳለ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው።" ከአንድ ሰዓት በኋላ ወደ ሆቴሉ ስመለስ ጨቅላ ህጻን ያቀፈች ወጣት አየሁ። ሕፃኑ ስድስት ሳምንት ቢሆነው ነው። በዚያ ቅፅፈት ነበር ህፃኑ ለመጀመርያ ጊዜ ፈገግ ሲል እናቱ ያየችው። እናትየዋ በጥልቅ ስሜት ደጋግማ ስታማትብ አየኋትና ጠየቅኋት። "የእኔ ውድ ምን እያደረግሽ ነው?" "ፈጣሪ ከሰማይ ሆኖ ከልቡ የሚፀልይን አንድ ሃጢያተኛ የሚሰማውን ደስታ የሚያክል ሌላ ደስታ ቢኖር የህፃን ልጇን ፈገግታ ለመጀመርያ ጊዜ የምታይ እናት ልብ ውስጥ ያለ ደስታ ነው"አለቺኝ። የወጣቷ ሴት ንግግር ጥልቅ ነበር። በውስጥ መላውን የክርስትና አስተምህሮ ብቻ ሳይሆን በፈጣሪ እና በሰው ልጅ መካከል ያለውን የአባትና ልጅ የፍቅር ትስስር የሚገልፅ ነበር። በንግግሯ የክርስቶስን መሠረታዊ ሃሳብ መግለጿ ልቤን ነካው። 📖ነሆለሉ ገፅ 187
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
«አንድ ሰው ይህ ያጋጥመዋል፤ ከእንቅልፉ ሲነሳ በጥልቅ ድንጋጤ ራሱን ይጠይቃል፦ እውነት ሃያ ሞላኝ? ሰላሳ፣ አርባ? እናስ ህይወት እንዴት አለፈች?!» ―ኢቫን ቶርጌኔቭ
በትዝታችን ስሜት አለን፤ በልምዳችንም እውቀት አለን፤ ስሜት ኢ-ምክኒያታዊው ጎናችን ነው። የስሜታችን እኛ፥ በስሜት የምንኖረው የህይወት ጉዞ፤ ከሰዎች ጋ ስንሆን የሚሰማን መደሰት መከፋት፤ ማፍቀር መፈቀር ጥላቻ ክብር ወዘተ የምንለው አይነት ስሜት አለን። ደስታን በምክኒያት አንመዝነውም። ጥላቻንም ሁሌ ሳናውቀው ሊጣባን ይችላል። ሌላም ሌላም ስናፈቅር በምክኒያት አይሆንም። ስንናፍቅም ምክኒያት የለንም። ግን የኖርናቸውም የምንኖራቸውም የእኛው አካሎች ናቸው፥ የምንወደውን ሰው በማጣት ከባድ የሀዘን ትዝታ ይኖረን ይሆናል። እጅግ ተደስተን ያለፍንበትም ገጠመኝ ይኖረናል። የምናስታውሳቸው ሲሆኑ በትውስታችንም ጊዜ የሚሰማን የደስታ ወይም የማዘን ስሜት አሁናችንን ይዳኛል። የምንሆነው ላይ አሻራ ያሳርፋል። ያሳለፍነው ትናንት ውጤቶች ነን። የምናስታውሰው ስሜትን የሚሰቀዝ ክስተት አለን፤ ያዳበርነው የእውቀት ልምድ የሆነን መረዳትም አለን። በእውቀታችን ዛሬን ለመኖር ስንጠቀም፤ በትዝታችን ደግሞ በጎውንም ክፉውንም አስበን በስሜት እንነካለን። ወደ ትናንት የመመለስ ኃይል በዚህም መስክ አይለቀንም። ሁሌም አብሮን አለ፤ አሁንም አለ፤ መለስ ብለን ለማስታወስ ስንሞክር የምንችለው ብዙ ማስታወስ ይኖረናል። ስንፈልግ የምናስታውሰው ምንም ነው፤ እንዲሁ ሳንፈልግ ትዝ እያለ የሚረብሸን ብዙ ትናንት ግን ዛሬን ይጎዳብናል። በሁላችንም ዘንድ መጠኑ ቢለያይም የትናንት ጉልበት ተጽዕኖ አለብን። የምንመዝንበት ኃይል ያስፈልገናል። ትዝታዎቻችን የጉድኝት ስሜቶቻችን ናቸው። የኖርንበት ቤተሰብ አብሮነት የሚወልዳቸው ትውስታዎች። የበዓላት፥ የጨዋታ፥ የጸሎት፤ ወዘተ አይነት ጠባያት። የመንደራችን ሰዎች የተለያየ ገጠመኝ፥ የእኛ ግንኙነትና የተለየ ስሜት የፈጠሩብን ትውስታዎች ወዘተ ከፍ ስንል ደግሞ የወደድናቸው የፍቅር አጣማጆችና የኛ ሁኔታ፥ በትምህርት ቤት የማንረሳው መምህርና ድርጊት ወዘተ ብዙ ብዙ ነገሮችን በማስታወስ ውስጥ ስሜታችን ይነካል። እንደኃይማኖተኛም ከእምነታችን ግብር የተቆራኙ ድርጊቶች፥ ኃይማኖታዊ ጉዞዎች፤የስብከት ስርዓቶችና ትዝታዎች ወዘተ አስታውሰን የሚሰማን ስሜት አለ አሁን ላይ። የኖርነው ሁሉ በመጠን ይለያያል፤ አሁን ላይ ሆነን ልናስታውሰው የምንችለው በየደረጃው ለስሜታችን የቀረበ ከነበረና ከብርታቱ ይሆናል። ከፈጠረው የተለየ ትውስታ፥ ነገር ግን ማናችንም በኖራቸው ህይወቶች የምናስታውሳቸው ትዝታዎች አሉን። 📖ነብይና ፈላስፍ ቡርሐን አዲስ
видео или голосовое, без подписи
"አንዳንድ ጊዜ ብዙም ማህበራዊ መስተጋብር የሌላቸው ከሰው መሀል ወጥተው ዳር የሚይዙ ሰዎች ማህበራዊ ኑሮ የሚጠሉ አይደለም ፤ ከዚህ ይልቅ የውሸት ድራማን ፣ ድድብናንና አስመሳይነትን መቋቋም ስለሚከብዳቸው ነው።" #Osho /ኦሾ
видео или голосовое, без подписи
በሴት የመከበብን ሚስጥር የምናውቀው እኔ ፣ ጠቢቡ ሰለሞን እና አባቱ ዳዊት ነን...... ጋሼ እንኳንም ተወለዱ 💜
видео или голосовое, без подписи
ከሁለት አይነት ሰዎች ጋር ለአንድ ደቂቃ እንኳ መቆየት አትችልም። ① የማይረዳህ ② የማያከብርህ (ኒዛር ቀባኒ)
ፈላስፋው ዘርዓ ያዕቆብ ከጠላቱ ሸሽቶ ብቻውን በዋሻ ውስጥ የቆየበትን ጊዜ ሲገልፅው "ብቻዬን ስሆን መንግስተ ሰማያት የገባሁ መሰለኝ" ይላል። The Wisdom Of The Enneagram የሚል አስገራሚ መጽሐፍ ላይ Individualist የሆኑ ሰዎችን ታላቅ የመፍጠር አቅም እንዳላቸው ይገልፃል። መንጋው ስር በልቶ ፣ መንጋው ስር ጠጥቶ በመፃፍ አላምንም። ምናልባት ሥነ ፅሁፍን ከሌላው ልዩ የሚያደርገው ዓለምና መንጋዎቿን ቆርጠህ እንድትጥል በማድረጉ ይመስለኛል። ምክንያቱም ለመፃፍ የምነሳሳው እረጅም ሰዓት ብቻዬን ስሆን ነው። Individualist የሆኑ ሰዎች እራሳቸውን ሰርክ እንደ አዲስ የሚሰሩ (የሚቀይሩ) ፣ እራሳቸውን የሚያሳድጉ ፣ ልምዳቸውን ወደ ተሻለ ነገር የሚለውጡ ናቸው ይላቸዋል። ጋሽ ፀጋዬ " ላንድ አፍታ እንኳን እንገንጠል ከሰው መንጋ እንነጠል " ሲል ጤናማ ስለሆነው የመነጠል ጥበብና ውበት እየነገረህ ነው። ደግሞ ሌላ ልጨምርልህ ... ካህሊል ለሜሪ በፃፈላት ደብዳቤ ላይ "ዓለምን በቅጡ መረዳት የሚፈልግ እሱ ከዓለም በእጅጉ መለየት አለበት" ብሏል። ብቻህን ሆነህ Meditate አድርግ ፣ አዲስ ነገር ተማር (እወቅ) ... ደራሲ ከሆንክ ደግሞ አንብብ ፣ ፃፍ ... እኔም ይህቺን ውብ ኸሚስ ፣ ብቻዬን ከዓለምና ከህዝቦቿ ርቄ የብቻነት ደስታዬን እያጣጣምኩ ይሄን ፃፍኩ። መልካም ኸሚስ! ❤❤
እኔ ጠላሻለሁ… እንደ ጫማ ሽታ ልክ እንደ በሽታ ጌታ በባሪያው ላይ እንደ ሚበረታ፤ እኔ ጠላሻለሁ… እንደ ረጅም መንገድ ላብታም እንደ መስገድ ከጠጡ በኋላ እንደ መንገዳገድ፤ እኔ ጠላሻለሁ… ገንዘብ እንደ ማጣት ዳገት እንደ መውጣት ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት፤ እኔ ጠላሻለሁ… ልክ እንደ መልከስከስ እምነት እንደ ማርከስ ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ፤ እኔ ጠላሻለሁ...(ወዘተ)... አሁን ግን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል ጠላሁሽ ያበዛሁ ወድጄሽ ነው መሰል! (እዮብ ዘ ማርያም)