የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴ/ኢ/ተማሪዎች ህብረት
СтатистикаThis channel can be called "UOG Institute of Technology Student Union Official telegram channel". For messages and comments leave at http://t.me/UoG_IOT_student_union_bot
- Последний пост
- 16 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 30
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 486
- 1/48двое суток
- 556
- 1/72трое суток
- 600
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket ለማግኘት የኢሜይል አድራሻችሁን መጎብኘት አትዘንጉ።
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የ2018ዓም የተማሪዎች ውጤት(grade report )
ይነበብ ይነበብ!!! ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ውድ እህቶቻችን እንዴት ከረማችሁ pathfinder የተባለ ግብረ ስናይ ድርጅት በዩኒቨርስቲያችን 30(ሰላሳ) ሴት ተማሪዎችን ማገዝ ይፈልጋል።በመሆኑ ሙሉ መረጃውን ከተያያዘው ፋይል(file) ላይ ተመልከቱ☝️☝️☝️☝️☝️
без подписи
без подписи
без подписи
የሀዘን መግለጫ ሕይወት በተስፋ፣ በሕልምና በውጥን የተሞላች ብትመስልም፣ አንዳንዴ ሰው በሕይወቱ ፈጽሞ ሊረሳቸው የማይችላቸውን ጥልቅ ሀዘኖች ታመጣለች። ዛሬም እጅግ የማይታመንና ቃላት ሊገልጸው የማይችል መራራ ዜና ሰምተናል። ውድ ወንድማችን ፍስሀ አስማማው፣ በኤሌክትሪካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል በ2018 ዓ.ም ተመርቆ፣ ብሩህ የወደፊት ሕይወትን ለመገንባት በተስፋ የተሞላ ጉዞ ላይ ሳለ፣ በ02/11/2018 ዓ.ም በድንገት ከዚህ ዓለም መለየቱ ቅስማችንን ሰብሯል። አንድ እናትና አባት የልጃቸውን ስኬት ለማየት በጉጉት ይኖራሉ። ጓደኞች ደግሞ አብረው የጀመሩትን ጉዞ አብረው ለመጨረስ ያልማሉ። ነገር ግን የሞት ዜና እነዚህን ሁሉ ሕልሞች በአንድ ቅጽበት አቋርጦ ይሄዳል። ዛሬ የምናለቅሰው ለአንድ ወጣት ብቻ አይደለም፤ ለተቋረጠ ሕልም፣ ላልተኖረ የወደፊት ተስፋ፣ ለቤተሰብ ያልተሟላ ደስታና ለሀገር ሊያበረክተው የነበረው አስተዋጽኦ ጭምርም ነው። አንድ ወጣት ሲሄድ አንድ ሕይወት ብቻ አይጠፋም፤ ከእርሱ ጋር ብዙ ሕልሞች፣ ብዙ ተስፋዎች እና ብዙ የወደፊት ታሪኮችም አብረው ይጠፋሉ። የፍስሀ ፈገግታ፣ ትህትናው፣ ከሰዎች ጋር የነበረው መልካም ግንኙነትና ወደፊት የነበረው ትልቅ ተስፋ ከሚያውቁት ሰዎች ልብ ፈጽሞ አይጠፋም። የሰው ሕይወት አጭር ቢሆንም፣ መልካም ስሙ ግን ለዘላለም ይኖራል። በዚህ ከባድ የሀዘን ወቅት ለውድ ወንድማችን ፍስሀ አስማማው ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለምህንድስና ተማሪዎች ለሚያውቁት ሁሉ ከልብ መጽናናትን እንመኛለን። "ሞት ሰውን ከእኛ ሊለየው ይችላል፤ ነገር ግን በፍቅር የተሞላ ትዝታውን ከልባችን አይጠፋም።" እግዚአብሔር ነፍሱን በገነት ያኑር!! "መልካሞች ቀድመው ይጠራሉ እንዲል መጽሐፍ" ነፍስህ በሰላም ትረፍ፣ ውድ ወንድማችን ፍስሀ አስማማው።" 🕊️😭😭
Dr.ሰላም ዋልክ? ይህ የወጭ መጋራት ፎርም ላይ ተጠቃሚው የገባበት ቀን የሚለው 18/01/2014 ዓ.ም.ነገር ግን የገባንበት ቀን ግንቦት1/9/2014 ነው:: የሚል ጥያቄ ጠይቀን ነበር! መልስ:እሱ ችግር የለውም መግቢያ መስከረም ስለሚታሰብ ነው። ሲስተሙ በዚህ ስላለ። ነገር ግን ወጪ መጋራት የተሰላው ከግንቦት 1 ጀምሮ ነው።
በቅድሚያ ውድ ተመራቂዎች በዚህ ታላቅ የስኬት ቀን እንኳን ደስ አላችሁ! ለዚህ ደረጃ ለመድረስ ያደረጋችሁት ጥረትና ትጋት የሚያስመሰግን ነው። ከዚህ በመቀጠል፣ ነገ ጠዋት በሰዓታችን ተዘጋጅተን ወደ መመረቂያ ቦታችን እንድንሄድ በአክብሮት አሳስባለሁ። ለፕሮግራሙ ስኬታማነት በሰዓት መገኘት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ፣ እባካችሁ ከመዘግየት እንቆጠብ። መልካም የምረቃ ቀን ይሁንላችሁ፤ የወደፊት ሕይወታችሁም በስኬት፣ በጤና እና በበረከት እንዲሞላ መልካም ምኞታችን ነው። 🔑 @fasilstudentunion 🔑 #ለወዳጅዎ_ያጋሩ! ሀሳብዎን በነጻነት ይግለጹ 👉 @dawit121221 👉 @Asre_21
እንዴት አደራችሁ? በባለፈው ስልጠና መጨረሻ ላይ ዛሬ እንደምንገናኝ መስማማታችንን በማስታወስ፣ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ በፕሬዚዳንት ህንፃ 6ኛ ፎቅ እንድትገኙ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።
Dr.ሰላም ነህ? የተመራቂ ተማሪዎች የመጨረሻ ገግቢ መውጫ ቀን ልታሳውቀኝ ትችላለህ ተማሪዎቹ ትኬት ሊቆርጡ ፈልገው በጣም ስለተቸገሩ ነው? የሚል ጥያቄ ጠይቀን የተሰጠን መልስ=ሰኔ 21 ነው!!!
ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች ዛሬ የተጀመረው የስራ-ፈጠራ እና የህይወት ክህሎት ሰልጠና ከሰዓትም ይቀጥላል ስለሆነም ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች ጠዋት ያልተግኛቸሁትንም ጨምሮ ከሰአት 8:00 ሰዓት ላይ በተመደባቸሁብት የመሰልጠኛ ክፍሎች አንድትገኙ:: 🔑 @fasilstudentunion 🔑 #ለወዳጅዎ_ያጋሩ! ሀሳብዎን በነጻነት ይግለጹ 👉 @dawit121221 👉 @Asre_21
በቅድሚያ ለሁላችሁም መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን፣ አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ከግቢ መውጫ ጊዜ ሰኔ 21 መሆኑን እናሳውቃለን። በመሆኑም ትኬታችሁን ከወዲሁ በአግባቡ እንድታመቻቹ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ስልጠናው ከቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ ሁሉም እጩ ተመራማሪዎች መገኘት እንዳለባችሁ እናሳስባለን። ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች በሙሉ ሰርተፍኬት እንደሚሰጥ በአክብሮት እንገልጻለን። 📍 ቦታ: አጼ ፋሲል ግቢ መማሪያ ክፍሎች
ለሬሜዲያል ተማሪዎች ሰኔ 02/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ላይ በነበረው የሒሳብ (Mathematics) ፈተና በሲስተም መቋረጥ ምክንያት ፈተና የተቋረጠባችሁ ተማሪዎች ፈተናው ቅዳሜ ሰኔ 5/2018 ዓ. ም የሚሰጥ ስለሆነ በነበራችሁበት መፈተኛ ክፍል ጠዋት 1:30 ላይ በመፈተኛ ክፍሎች እንድትገኙ እያሳሰብን። በሰዓቱ ባለመገኘት ለሚፈጠረው የሰዓት መሸራረፍ ኃላፊነቱ የተማሪው መሆኑን እናሳውቃለን።
በሲስተም ችግር ምክንያት የ mathematics ፈተና ችግር ለገጠማችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ ቀደም ሲል mathematics ፈተና ድጋሜ እንደሚሰጥ በማስታወቂያ መገለጹ ይታወቃል። ሆኖም የትምህርት ሚኒስቴር የፈተናውን ትክክለኛ ቀን ባለማሳወቁ ምክንያት ፈተናው እስካሁን ድረስ ሳይወሰን ቆይቷል። አሁን ግን ከትምህርት ሚኒስቴር በደረሰን መረጃ መሠረት ፈተናው ቅዳሜ ጠዋት 1፡30 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተወስኗል። ስለሆነም ድጋሜ የምትፈተኑ ተፈታኞች በተጠቀሰው ሰዓት በመገኘት ፈተናቸውን እንዲፈተኑ በአክብሮት እናሳስባለን።
ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ የመውጫ ፈተና መግቢያ ትኬትን (Entrance Ticket) ለማግኘት የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች በመከተል የመግቢያ ትኬታችሁን አውርዳችሁ ፕሪንት በማድረግ በፈተናው ቀን ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን። ➫ https://verify.ethernet.edu.et ላይ ይግቡ ➫ 'Get your entrance ticket here' የሚለውን ይጫኑ ➫ የመለያ ስምዎን (Username) እና የይለፍ ኮድዎን (Password) ያስገቡ ➫ 'Download Entrance Ticket' የሚለውን ይጫኑ
ፆመኛ ላልሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሰላም እንደምን አደራችሁ? ዛሬ ይቀርብ የነበረዉ ዜርፎር (የስጋ) ሜኖ በስጋ አቅራቢዉ ችግር ምክንያት ሰኞ የሚቀርብ መሆኑን እንገልፃለን።ያለዉ የተማሪ ቁጥር ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ ከዚህ በኋላ እሁድና ሰኞ የሚቀርብ መሆኑንም ለመግለፅ እንወዳለን።መልካም ጊዜ !!
ነገ የexit exam orintation ስላለ በሰዓቱ እንድትገኙ።
02/10/2018 ለተፈጥሮ ሳይንስ ሬሜዲያል ተማሪዎች በሙሉ ነገ ሰኔ 03/2018 የኬሚስትሪ ፈተና ጠዋት 5:00 ሰዓት ላይ የሚሰጠው ፈተና ወደ 2:00 ከሰዓት 9:00 ሰዓት የሚሰጠው ወደ 5:00 ሰዓት የተቀየረ መሆኑን እያሳወቅን ተፈታኞች 1:30 ላይና 4:30 በመፈተኛ ክፍሎች እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።