FastMereja.com
Статистика- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 21
- Всего постов
- 70
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 416
- 1/48двое суток
- 4 767
- 1/72трое суток
- 5 141
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
በአማራ ክልል እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ ትምህርት ቤት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል። #FastMereja I እውቀት፣ እምነትና ሙያ በአንድ ጣሪያ ስር፦ በዙይ ሃሙሲት ከተማ እየተገነባ ያለው ግዙፉ የልማት ፕሮጀክት ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከሚሰራቸው የልማት ስራዎች አንዱ የሆነው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ዙይ ሃሙሲት ከተማ የሚገነቡ ትምህርት ቤት (ዓለማዊ እና መንፈሳዊ) እና ክሊኒክ እናስቃኛችሁ። ከገዳሙ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በዙይ ሃሙሲት ከተማ ገዳሙ መንፈሳዊና ዓለማዊ እውቀትን፣ ሙያዊ ክህሎትን እንዲሁም ማህበራዊ አገልግሎትን ያስተሳሰረ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ እንቅስቃሴ እየሰራ ይገኛል። በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት እንቃኘው። 📍ዘመናዊና የአብነት ትምህርት ቤቶች የፕሮጀክቱ ዋነኛ አላማ «በሁለት ቢላዋ የተሳለ» ማለትም በዓለማዊ እውቀቱ የበቃ፣ በመንፈሳዊ ባህሉና ግብረ-ገብነቱ የበለፀገ ትውልድ ማፍራት መሆኑ ተገልጿል። በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትምህርት ጥራት ክፍተት የሚሞላና በአዲስ አበባ ከሚገኙ ዝነኛ ትምህርት ቤቶች የሚያሳዩትን የዲሲፕሊንና የእውቀት ጥራት የሚደግም ይሆናል የተባለለት በአንድ ክፍል ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች ብቻ በመመደብ የመምህርና የተማሪን ጥብቅ ግንኙነት እንደሚያረጋግጥ የተነገረለት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምር ዓለማዊ ትምህርት ቤት እየተገነባ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የኮምፒውተር፣ የኬሚስትሪ ላቦራቶሪዎችና ዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት የተካተቱበት ሲሆን፣ የተማሪዎችን ልዩ ልዩ ተሰጥኦ ለማልማት የሚያስችል የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ ተዘጋጅቶለታል። ሌላኛው እየተገነባ ያለው ጂ+3 የአብነት ትምህርት ቤት ሲሆን ተማሪዎች የአብነት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ጎን ለጎን ዓለማዊ ትምህርትን መማር ግዴታ አድርጎ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል። ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ የሆኑ ጉባኤ ቤቶች፣ የተማሪዎችና የአባቶች ማደሪያ፣ መመገቢያ አዳራሽና የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ተዘጋጅቷል። «የአብንት ተማሪዎች ነፃ ምግብ፣ አልባሳትና ማደሪያ የሚያገኙ ሲሆን፤ በትምህርት ገበታቸው ወቅትም ለግል ፍላጎቶቻቸው ማሟያ የሚሆን የኪስ ገንዘብ የሚያገኙበት የምርትና የልማት ስራዎች ተመቻችተውላቸዋል።» ሌላኛው ለዘላቂ ገቢ፣ የክህሎት ማዳበሪያና የማምረቻ መጋዘኖች ግንባታዎች ሲሆኑ የአብነት ተማሪዎችም ሆኑ ሌሎች ሰልጣኞች ከትምህርት በኋላ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ እራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚያስችሉ ተግባራዊ የሙያ ማሰልጠኛዎችና ማምረቻዎች በሳይቱ እየተገነቡ ይገኛሉ። የምግብ ማቀነባበሪያ፦ የኑግ፣ የሱፍ፣ የአቮካዶ ዘይቶችን ማቀነባበር፤ የጤፍ፣ የበቆሎና የስንዴ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ። የንፅህና ውጤቶች ማምረቻ፦ ደረቅና ፈሳሽ ሳሙናዎችን በማምረት ለጎንደር፣ ባህር ዳርና አካባቢው ከተሞች ማቅረብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። 📍የጤና ተቋም ሁለተኛው ፕሮጀክት የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት (መካከለኛ ደረጃ ክሊኒክ) ግንባታ ሲሆን የአካባቢው ህብረተሰብ ወደ ባህር ዳር ወይም ጎንደር ሳይሄድ እዚያው የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ታስቦ መካከለኛ ደረጃ ክሊኒክ እየተገነባ ይገኛል። ክሊኒኩ እንደ ኤክስሬይ፣ ኢሲጂ፣ ኢኢጂ እና አልትራሳውንድ ያሉ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉለት ይሆናል ተብሏል። የፕሮጀክቱ ማኔጀር አቶ ዳኜ የኋሌ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ ታህሳስ 1፣ 2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ፈጣን እድገት በማሳየት ላይ ይገኛል፣የዓለማዊ ትምህርት ቤት ብሎኮች ስራዎች አልቀው ግንባታቸው 85% ደርሷል። 6 ብሎኮችና 24 ክፍሎች ያሉት ሲሆን የማጠናቀቂያ (Finishing) ስራዎች እየተከናወኑ ነው። የአብነት ትምህርት ቤት የጂ+3 ህንፃ የመጨረሻው ፎቅ የኮንክሪት ድልድል ስራ እየተሰራ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የራሱ የውሃ ሪዘርቫየርና የሮቶ ማከማቻዎች የተገነቡ ሲሆን፣ የብረትና የእንጨት ስራዎች በራሱ የውስጥ አቅም እየተከናወኑ ይገኛሉ። የማጠናቀቂያ ጊዜ የቁሳቁስና የመንገድ እንቅፋቶች በተሻለ ሁኔታ ከተቀረፉ ፕሮጀክቱ ግንቦት 2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ሲሆን፣ ረዘመ ከተባለ ደግሞ አጠቃላይ ማጠናቀቂያው እስከ ጥር 2020 ዓ.ም እንደሚሆን ተገልጿል። በቀጣይ ክፍል ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም በዙይ ሃሙሲት ከተማ እየሰራ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የምናስቃኛችሁ ይሆናል። 📌 በገዳሙ የተሰሩ ስራዎችን ለማንበብ ሊንክ https://www.facebook.com/share/p/1LN517GaiB/ 📷 ከበደ መክብብ
በናይጄሪያ ሃይማኖታዊ መቻቻልን ለማጠናከር ያለመ የሰላም ስምምነት ተፈረመ #FastMereja I በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ በተካሄደ የሙስሊም ዓለም ሊግ ጉባኤ ላይ ከ50 በላይ የሙስሊም እና የክርስቲያን ሃይማኖት መሪዎች የጋራ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ። ይህ በሁለቱ እምነቶች መካከል ያለውን እርስ በእርስ ውይይት እና ግንኙነት የሚያጠናክር የጋራ አካል ያቋቋመው ስምምነት፣ በሃገሪቱ ውስጥ በሁለቱም እምነት ተከታዮች ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮችን፣ ሃይማኖታዊ ትዕግስት ማጣትን እና ጽንፈኛ አመለካከቶችን ለመግታት ያለመ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። ከ200 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ናይጄሪያ በሰሜናዊው ክፍል አብዛኛው የሙስሊም፣ በደቡባዊው ክፍል ደግሞ የክርስቲያን ማህበረሰብ የሚኖርባት በመሆኗ ይህ ስምምነት ለሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና አብሮነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
🩸🩸TOMI TOMI TOMI TOMI 🩸🩸 TOMI PHOTO VELO AND MEKEUP 💯 አዲሱን አመት በማስመልከት ልዩ ልዩ packag ይዘንሎት መተናል ከ 11,900ብር studio package ጀምሮ እስከ 68,900ብር studio + musk + transoprt ያጠቃለለ lexury package ያገኛሉ በስራችን ደስተኛ እደምትሆኑ ጥርጥር የለንም👍🙏🙌🏻 አዲስ ባስገባነው እጅግ ውብ እና ዘመናዊ ቬሎዎች 💯🎁TOMI PHOTO VELO AND MEKEUP 💯 የደንበኞቻችንን አንጀት የሚያርስ ሁሉንም በአንድ የያዘ እና ጥራት ያለው የመስክና የስቱዲዩ ፎቶ ፕሮግራም እና ሙሉ አልባሳት በአንድ ጥቅል አዘጋጅተናል፡፡ ይምጡና ይጎብኙን! 🛑Tomi photo and velo 🛑 * የመስክ እና ስቱዲዩ ፎቶ * ሜካፕ፣ ጥፍር፣ ፀጉር * ቬሎ፣ ሱፍ፣ ካባ፣ * ሌሎች አልባሳትን የያዙ ጥቅሎች 🛑 Tomi Tomi Tomi Tomi 🛑 🩸Tomi Luxry package 53,900 ብር • Mesk video • Laminate album 30 X 90 -10(20) page • Board photo 60*90(ባለመስታወት) • Board photo 50*80-1(ባለመስታወት) . Hexagon (ተገጣጣሚ) board _ 8 pis • Sign board 1 • Thank you cared -200 • Save the date 5 photo • Slideshow • All soft copy የሰርግ አልባሳት • 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት) • 2 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) 1 color • ካባ (በመረጡት አይነት) • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) . የ አፍሪካ ልብስ • የሀበሻ ቀሚሽ • የእራት ቀሚስ • ሜካፕ 👰🏻 • ጥፍር • ፀጉር . የ መስክ እና ስቱዲዮ አበባ (1) • የወንዶች የውበት ሳሎን . ትራንስፖት ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ53,900 ብር ብቻ 🩸Luxry package 40,000 ብር • Mesk video • Laminate album 30 X 90 -10(20) page • Board photo 60*90(ባለመስታወት) • 6 pc hexagon • Sign board 1 • Thank you cared -200 • Save the date 5 photo • Slideshow • All soft copy የሰርግ አልባሳት • 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት) • 2 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) 1 color • ካባ (በመረጡት አይነት) • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) . የ አፍሪካ ልብስ • የሀበሻ ቀሚሽ • የእራት ቀሚስ • ሜካፕ 👰🏻 • ጥፍር • ፀጉር . የ መስክ እና ስቱዲዮ አበባ (1) • የወንዶች የውበት ሳሎን ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ40,000 ብር ብቻ 🩸Luxry package 33,900 ብር • Mesk video • Laminate album 30 X 90 -12 (24) page • Board photo 50X80-1 • Board photo 40*60-1 • Sign board 1 . 6 pc hexagon • Thank you cared -200 • Save the date 5 photo • Slideshow • All soft copy የሰርግ አልባሳት • 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት) • 2 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) 1 color • ካባ (በመረጡት አይነት) • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) . የ አፍሪካ ልብስ • የሀበሻ ቀሚሽ • የእራት ቀሚስ • ሜካፕ 👰🏻 • ጥፍር • ፀጉር • የወንዶች የውበት ሳሎን ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ33,900 ብር ብቻ 🩸Premium pakage 2 -29,900 ብር • Laminate album 30 X 90 -10 (20) page • Board photo 50X80-1 • Sign board 1 • Thank you cared -200 • Save the date 5 photo • Soft copy 150 • Slideshow የሰርግ አልባሳት • 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)1 color • 1 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) • ካባ (በመረጡት አይነት) • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) . የ አፍሪካ ልብስ • የሀበሻ ልብሽ • የእራት ቀሚስ • ሜካፕ 👰🏻 • ጥፍር • ፀጉር . አበባ የመስክ እና የ ስቱዲዮ (1) • የወንዶች የውበት ሳሎን ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ29.900 ብር ብቻ 🩸Special package (2) -23.000 መስክ ወይም ስቱዲዩ • Laminate album 30 X 90 -10 (20) page • Board photo 50X80-1 • Sign board 1 • Thank you cared -200 • Soft copy 150 • Save the date 5 photo .Make up👰🏻 . ጥፍር . ፀጉር የሰርግ አልባሳት • 2 ቬሎ የመስክ ወይም የ ስቱዲዮ (በመረጡት አይነት)1 color • ካባ (በመረጡት አይነት) • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) • የሀበሻ ልብስ . የ አፍሪካ ልብስ ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ23.000 ብር ብቻ 🩸Mini package 1 (studio or mesk) 18,000 መስክ ፎቶ እና የሰርግ አልባሳት • Sign board 1 • Thank you cared -200 • Soft copy 150 • Save the date 5 photo . Make up👰🏻 . ትፍር . ፀጉር የሰርግ አልባሳት • 2 ቬሎ የመስክ ወይም የ ስቱዲዮ (በመረጡት አይነት)1 color • ካባ (በመረጡት አይነት) • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ18.000 ብር ብቻ 🩸Luxury Mesk Pacage (mesk) 15500 👉የመስክ ፎቶ እና የሰርግ አልባሳት . Mesk Video • Soft copy 150 • Save the date 5 photo . Make up👰🏻 . ጥፍር . ፀጉር • 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)1 color • 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት) • ካባ • የሀበሻ ልብስ •የ አፍሪካ ልብስ ይህን ሁሉ ጨምሮ 🔥በ15500 ብር ብቻ 🩸only studio package 1 -በ11,900 ብር ብቻ) . 2 ቬሎ (በመረጡት አይነት) . 2 ሱፍ ( በመረጡት አይነት) .የ ሀበሻ ልብስ . ካባ . Thank you card . Make up👰🏻 . ጥፍር . ፀጉር ይህን ሁሉ 🔥በ 11,900 ብቻ 👉አድራሻ: ቁ.1 አዲስ አበባ 22 ከ አክሱም ሆቴል ወረድ ብሎ ትጋት ህንፃ 2ተኛ ፎቅ F1-03 ✅አሁኑኑ ደውለው ኦርደር ያርጉ👇 ☎️ 0926455964 (አአ)
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
“አላማዬ ሀብታም መሆን እንጂ፣ የሀብታም ሚስት መሆን አይደለም!” አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ #FastMereja I ታዋቂዋ አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ በህይወትና በስራ ስኬቷ ዙሪያ በሰጠችው አዲስ አስተያየት በራሷ ጥረትና ልፋት ከፍተኛ የፋይናንስ ነፃነት ማሳካት ዋና ግቧ እንደሆነ ገለጸች። አርቲስቷ ሌሎች ሰዎችን በመጠጋት ወይም በጋብቻ ጥላ ስር በመሆን ሀብትን ከመሻት ይልቅ በራሷ ሙያዊ ጥረት፣ ትጋትና የስራ ፈጠራ የተሟላ ሀብት ማፍራት እንደምትፈልግ አጽንኦት ሰጥታ ተናግራለች። ይህ የአርቲስት ቬሮኒካ አስተያየት በተለይም በሴቶች ዘንድ የራስን አቅም ማጎልበት፣ በራስ መተማመንን ማዳበር እና በኢኮኖሚ ራስን የመቻልን አስፈላጊነት የሚያጎላ በመሆኑ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመዝናኛው ዘርፍ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
የባር እና የአልኮል መጠጥ ቤቶች በስራ ቀናት ከቀኑ 9 ሰዓት በፊት እንዳይከፈቱ ታገደ #FastMereja | የስራ ባህልን ለማሻሻል፣ የስራ ሰዓት ላይ የሚደረግ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀምን ለመግታት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚል ባሮችና የአልኮል መጠጥ ማከፋፈያዎች በስራ ቀናት ከቀኑ 9:00 ሰዓት በፊት እንዳይከፈቱ የዩጋንዳ መንግስት ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ። የዩጋንዳ የአካባቢ አስተዳደር ሚኒስቴር አዲሱን መመሪያ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ እርምጃው በስራ ሰዓት በሚደረግ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም ምክንያት የሚከሰተውን የስራ ፈትነት፣ የማህበራዊ ህይወት መዛባት እና የወንጀል ድርጊቶች ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ገልጿል። በሚኒስትር ባላም ባሩጋሃራ በተፈረመው ደብዳቤ ለአካባቢ አስተዳደሮች፣ ከንቲባዎች እና ለጸጥታ አካላት መመሪያው በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ ታዟል። በዚህ አዲስ ህግ መሰረት ማንኛውም ባር፣ ባህላዊ የመጠጥ ቦታ ወይም አልኮል የሚሸጥ ድርጅት በሳምንቱ የሥራ ቀናት ከቀኑ 9 ሰዓት በፊት አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ምንም ዓይነት የአልኮል መጠጥ መሸጥ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ሲሆን፣ ይህንን መመሪያ በሚጥሱ ነጋዴዎች እና ድርጅቶች ላይ ከባድ ህጋዊ እርምጃ እና የእስራት ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተገልጿል። የአካባቢ አስተዳደር እና የጸጥታ አካላት መመሪያውን ሳይተገብሩ በሚቀሩ ወይም ህጉን በተደጋጋሚ በሚጥሱ የንግድ ተቋማት ላይ የንግድ ፈቃድ የመሰረዝ እና ድርጅቶቹን እስከመጨረሻው የመዝጋት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። ውሳኔው በሀገሪቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ሰፊ ውይይት ያስነሳ ሲሆን፣ አንዳንዶች እርምጃውን የዜጎችን ስነ-ምግባር እና ምርታማነት ለማሻሻል ጠቃሚ ነው ሲሉ ሲደግፉት፣ ሌሎች ደግሞ በትግበራው ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተደራሽነት እና ቁጥጥር ተጋላጭነቶችን በማንሳት አስተያየት እየሰጡበት ይገኛሉ።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ወንድ ልጅ መገላገሏን አበሰረች #FastMereja I በዓለም አቀፍ ደረጃ በሩጫ ስፖርት በርካታ ድሎችን ያስመዘገበችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የመጀመሪያ ወንድ ልጇን በሰላም መገላገሏን ዛሬ ይፋ አድርጋለች። አትሌቷ በደስታ የተሞላውን የሕይወት ምዕራፍ በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ፣ የልጇን መወለድ በሰላምና በጤና ያበሰረች ሲሆን በእርግዝናዋ ወቅትና በፅናት በታገለችባቸው አታካች የሕይወት መንገዶች ውስጥ ያልተለያት የደጋፊዎቿና የመላው ኢትዮጵያውያን ጸሎትና ድጋፍ ትልቅ ብርሃን እንደሆናት ገልጻለች። ፈጣሪ የእናትነትን አክሊል ስላጎናፀፋት ምስጋናዋን ያቀረበችው አትሌት ጉዳፍ፣ ውድ ደጋፊዎቿ አዲሱን ልጇን በጸሎታቸው እንዲያስቡላትና በቤታቸውም ሰላምና በረከት እንዲበዛ ተመኝታለች። “ዛሬ በአርሴማ ቀን የዓለማት ጌታ በታላቅ ምህረቱና ቸርነቱ ወንድ ልጃችንን በሰላም አቅፌ እንድስም አድርጎኛል።”
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራ አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ #FastMereja I በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ሲሳተፉ የቆዩ የዲያስፖራ አባላት ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀ ልዩ የጉብኝት መርሃ ግብር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። የዲያስፖራ አባላቱ በጉብኝታቸው ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ሙሉ ስራ በመግባቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ከግብ ለማድረስ ለተደረገው ቁርጠኝነትና አመራር አድናቆታቸውን ለግሰዋል። ባለፈው መስከረም ወር ሙሉ በሙሉ ተመርቆ ስራ የጀመረው ህዳሴ ግድብ የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ 50 በመቶ ያህሉን የሚሸፍን ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መንደሮችን ከብሔራዊ የኃይል መረብ ጋር ማገናኘት ተችሏል። የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት፣ የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎች እና የዲያስፖራ ማህበረሰቦች ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ብቻ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ 3.2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም በጅቡቲ ለሚገኘው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት 400 ሺህ ዶላር በቦንድ እና በስጦታ መልክ ማሰባሰብ ተችሏል። የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራ አባላት በጅቡቲ ለሚገነባው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚሆን ከ1.7 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ በቦታው ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም የዲያስፖራው ድጋፍ ከፋይናንስ ባለፈ ለሀገርና ለወገን ያለውን አለኝታነት ያረጋገጠ መሆኑ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ገልጿል።
“ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለውን ትርክት የፈጠረው ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ነው ሲሉ ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ #FastMereja | በኬኒያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ትናንት ምሽት ከአዲስ ኮምፓስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ፣ በግል ህይወታቸው እና በወታደራዊ አገልግሎታቸው ዙሪያ ለሚነሱ ትችቶች ምላሽ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በዚሁ ቆይታቸው “ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለውና በሰፊው የሚናፈሰው ትርክት ያለምንም ማስረጃ በሟቹ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የተቀናበረ መሆኑን ተናግረዋል። “ጄነራልነት የሰጠኝ ብሄራዊ ቲያትር አይደለም” ያሉት ጄነራል ባጫ፣ ምርኮኛም ሆነ ዳንሰኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ “የማረከኝ አካል ካለም ይውጣና ይናገር” ሲሉ የቀረቡባቸውን ወቀሳዎች አስተባብለዋል። አክለውም ይህ አይነቱ ትችት በግል እሳቸው ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን፣ ከወጡበት የብሄር ማንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ስልታዊ ስም ማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።
የ«Stream Afri» የላይቭ ስትሪሚንግ መተግበሪያ በይፋ ተዋወቀ! #Fastmereja:-በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ስትሪም አፍሪ የተሰኘ የላይቭ ስትሪሚንግ መተግበሪያ በይፋ መበለጸጉ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል። በዴላዌር ዩናይትድ ስቴትስ የተመዘገቡትና ዋና ሥራቸውን ከአዲስ አበባ የሚያካሂዱት ሁለቱ ተቋማት፣ የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ባሉበት ሆነው የዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነት እና ተቢውን የኢኮኖሚ ተፈጥሮ እንዲያገኙ ዓላማ አድርገው የተቋቋሙ መሆናቸዉ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት “ስትሪምአፍሪ” በስፖርት፣ በቱሪዝም፣ በትምህርት እና በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ የሀገርውስጥ ይዘት ፈጣሪዎችን፣ አርቲስቶችን እና አትሌቶችን ከዓለም ዙሪያ ካለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ዘመናዊ የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) መድረክ ነው። በተለይም በቅርቡ በአደይ አበባ ስታዲየም የሚካሄደው የቦብ ማርሌይ ልጆች ኮንሰርት እና ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በጃማይካ የሚያቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት በዚሁ መተግበሪያ በቀጥታ ለዓለም አቀፍ ተመልካች እንደሚተላለፉ ተገልጿል። በሌላ በኩል “ተስፋ ኤአይ” በሀገር ውስጥ የሚገነባውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ኢንጂነሪንግ ተሰጥኦ ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ለማቅረብ የተቋቋመ ሲሆን፤ የኤአይ አውቶሜሽን፣ ኤጀንቲክ መተግበሪያዎችን እና የርቀት የኢንጂነሪንግ ቡድኖችን ያቀርባል። ተቋሙ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ከሀገር ውስጥ ተሰጥኦዎች ጋር የሚያገናኝ የቀጥታ የትምህርት ቻናል በማንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝም ነዉ የተገለፀዉ። የኩባንያዉ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናትናኤል ከበደ በሰጡት መግለጫ፤ “ነሐሴ 21 ቀን የሥራ ማስጀመሪያ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ይዘት ፈጣሪዎች እና ኢንጂነሮች ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ የሚደርሱበትን ክፍት መንገድ የምንፈጥርበት ታሪካዊ ቀን ነው” ብለዋል። በመጪው ነሐሴ 21 በሚካሄደው የ«ሚክስ ማርሻል አርትስ» (MMA) ውድድር ወቅት በቀጥታ ስርጭት አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው መተግበሪያ የቅድመ አባልነት ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ። አገልግሎቱ በiOS፣ በAndroid እና በድረ-ገጽ (Web) ደረጃ የቀረበ ሲሆን፣ ይዘት ፈጣሪዎች ከወዲሁ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ፕሬዚዳንት ከአመራሮች ጋር የመጀመሪያ የትውውቅና የሥራ አቅጣጫ ውይይት አካሄዱ #FastMereja I በቅርቡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ዶ/ር የቻለ ከበደ ከጽሕፈት ቤታቸው ዳይሬክተሮችና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የመጀመሪያ የትውውቅና የሥራ አቅጣጫ ማሰጫ መርሃ ግብር አካሄዱ። በፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ መድረክ፣ በዋናነት በከፍተኛው አመራርና በመካከለኛ አመራሮች መካከል ግልጽና ውጤታማ የግንኙነት መስመር በመዘርጋት ቅንጅታዊ የአሠራር ባህልን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመግቢያ ውይይት ተደርጓል። ዶክተር የቻለ ከበደ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር የዩኒቨርሲቲውን ሀገራዊና ተቋማዊ ተልዕኮ ለማሳካት የውስጥ አሠራርን ማጠናከርና በቡድን የመሥራት ባህልን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋማዊ ስኬት የሚረጋገጠው እያንዳንዱ አመራርና ባለሙያ የተጣለበትን ኃላፊነት በከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት፣ በቅንጅትና በጋራ ጥረት ሲወጣ መሆኑንም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። በውይይቱ ወቅት የተቋሙን የአፈጻጸም ብቃት ማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ በውጤት ተኮር አሠራር ላይ ትኩረት ማድረግ እና ያሉትን ሀብቶች በቁጠባና በውጤታማነት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችሉ ሀሳቦች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል። በመድረኩ የተሳተፉት አመራሮች በአዲሱ ፕሬዚዳንት የቀረበውን አቅጣጫ በመቀበል የተጀመሩ ሥራዎችን ለማስቀጠልና አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር በሙሉ ትጋት ለመሥራት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል። ፕሬዚዳንቱ በቀጣይም ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ የሥራ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ከተቋሙ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሰሜን ጎንደር በዝናብ እጥረት በተከሰተ ድርቅ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ለአደጋ ተጋለጡ፤ 14 ሺህ የቁም እንስሳት ሞቱ #FastMereja | በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ከሚያዝያ አጋማሽ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ የዝናብ እጥረት ምክንያት ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውንና ከ14 ሺህ በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። እንደ ወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገዛአብ እያሱ ገለጻ ከሆነ፣ በወረዳው ስር በሚገኙ 10 ቀበሌዎች ላይ ምንም ዓይነት ዝናብ ባለመጣሉ ድርቁ በሰውና በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። በተጨማሪም በድርቁ ምክንያት ከ9 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ሳይበቅል ቀርቷል። በአካባቢው ከድርቁ ጋር ተያይዞ አዳዲስ የጤና ችግሮች እየታዩ ሲሆን፣ የበሽታዎቹን ዓይነትና መንስኤ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ግብረ-ኃይል ተዋቅሮ የምርመራ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል። የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ከወረዳው አቅም በላይ በመሆኑ አስቸኳይ የምግብ፣ የውሃ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ ያስፈልጋል። በመሆኑም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፣ የረድኤት ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ የወረዳው አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል። (ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው)
የታዋቂዋ ተዋናይት ቤተልሔም (ቤቲ) የ7 ዓመታት የቤት ውስጥ በደል እና የህይወት ውጣ ውረድ ይፋ አደረገች #FastMereja | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበብ ተመርቃ «ታስጨርሺኛለሽ» በተሰኘው ታዋቂ ፊልም ላይ «ኮኪ» የተባለውን ገጸ-ባህሪ በመወደድ ከፍ ያለ አድናቆት አትርፋ የነበረችው ተዋናይት ቤተልሔም (ቤቲ)፤ በ22 ዓመቷ ወደ ትዳር ከገባች በኋላ ላለፉት ሰባት ዓመታት የከፋ የቤት ውስጥ ጥቃት እና የስነ-ልቦና ጫና ይደርስባት እንደነበር በሸገር ኢንፎ ላይ ቀርባ ይፋ አደረገች። ተዋናይቷ በማህበራዊ ሚዲያ የምታሰራጫቸው ደስተኛ ምስሎች የስነ-ልቦና እና የአካል በደሎችን ለመሸፈን የተጠቀመችባቸው የሐሰት ጭንብል እንደነበሩ የገለጸች ሲሆን፣ በእርግዝናዋ ወቅት ሳይቀር በባለቤቷ ከባድ የአካል ድብደባ ይደርስባት እንደነበር ተናግራለች። በተጨማሪም በባሏ እና በቤተሰቦቹ በኩል «ልጁ የኔ አይደለም» የሚል የተስፋፋ የጥርጣሬ ስድብ እና የስነ-ልቦና ጫና ሲደርስባት መቆየቱን ገልጻለች። ይህ በቤት ውስጥ ይፈጠር የነበረው የማያቋርጥ ሁከትና ግጭት በልጆቿ ላይም ከባድ የስነ-ልቦና ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ በተለይም ኩነቱን ሁልጊዜ የሚያየው የሰባት ዓመት የመጀመሪያ ልጇ ለከባድ የጭንቀት ህመም ተዳርጎ በአሁኑ ወቅት በህክምና እና በመድኃኒት ለመታገዝ መገደዱ ተናግራለች። “ሰው ናፍቆኛል ሰባት ዓመት ሙሉ ተቆልፎብኝ ኖሪያለሁ” የምትለው ተዋናይት ቤቲ አሁን ላይ ከዚህ ስቃይ ለመውጣት መወሰኗን ገልጻ፣ ምንም ዓይነት ንብረት ወይም ገንዘብ እንደማትፈልግና የምትሻው የልጆቿን ሰላም፣ ህጋዊ ከለላ እና የአእምሮ እረፍት ብቻ እንደሆነ አስታውቃለች። ጥቃቱን ተቋቁማ ወደ ብርሃን ለመውጣት ለምታደርገው ጥረትም የህግ ከለላ እና ድጋፍ እንዲደረግላት ጥሪ አቅርባለች።
የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት 1 ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ማስገኘቱ ተገለጸ #FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ማስገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ።