tgindex
Fuad kheyredin

Fuad kheyredin

Статистика

የልብ ንግግር… የሀሳብ ዓለም… ለሀሳብ @Fukheyredin

Последний пост
4 мая 2025 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 725
−3 за 2 дн.
Сутки
−2
−0,12%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 950
20 постов
Вовлечённость
344,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ዓመታት እያለፉ ነው። እኛ ደግሞ እንድንኖር በተፈረደብን ህይወትና  እኛን ከሚሸሹ ህልሞቻችን መሀል ነን።  ህያው የምንሆንባቸው ትዝታዎች አሉን… የነበረውን ናፍቆት ፣ ሳቅ ፣ ሀዘን እያስታወስን አንገት እንነቀንቃለን በፈገግታ፣ በአግራሞት።  እና ሁሉንም እናይና  እንዲህ እንደመድማለን…   በተፃፈልን እጣፈንታና ራሃ መሆንን አምርሮ በሚፈልግ ልብ መሃል ነን ሁልጊዜ። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • አንዳንድ ሰው  ከአንደበቱ ማር ይዘንብለታል። ሲያገኝህ ለስለስ ባለ ፈገግታ ይገድልሃል። ሆን ብለህ ብትፈልግ እንኳን ድርቅና አታይበትም።  ተፈጥሮ ሆኖ ይሁን ተለማምዶት እኔንጃ። …   እና እንዲህ አይነት ሰው ሲያገኝህ  ካንተ የሆነ ነገር መጠቀም ፈልጎ እንደሆነ እንዳታስብ። ወይም በጣም ወዶኛል፣ ተመችቼዋለሁ ብለህም እንዳትደመድም። በቃ እርሱ በዚህ መልኩ ማስተናገድ ልምዱ ሊሆን ይችላል። ተፈጥሮውም ሊሆን ይችላል። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • የሰዎችን መጥፎ ጎን ብቻ ለማስታወስ ከተቀመጥክ ለማንም ውዴታ አይኖርህም። ፍፁም ንፁህ ፍጡር ስለማይኖር ቅርብ ሰዎችህን እንኳን ባልተለመደ መልኩ በጥቁር ዓይን መመልከት ትጀምራለህ። ከዚያ ቀንህም አያፈካህም፣ ሌሊትህም አያሳርፍህም። አንዳንዴ መጥፎ ጎናቸው ጋር ስትደርስ አይንህን ስበር፣ አይቶ እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍንም ተለማመድ። አንዳንዴ "መርሳት"ን ተደገፈው። አንተም አጠገብህ ያሉትም ሰላም እንዲሆኑ። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • "ያሳዝናል! ነገሩ የተወሰኑ ቀናት ይሆንና ያልፋል ብዬ አስቤ ነበር። ግን ህይወቴ ሆነ።" ዴስቶቪስኪ አንዳንዴ… ብዙም የማንኖርባቸውና መሻገሪያችን የሚመስሉን ነገሮች ራሳቸው መዳረሻችንም ይሆናሉ። ድንገት የተፈጠሩ ናቸው እንልና ዝንተዓለሙን እነርሱ ውስጥ እንኖራለን። ለተወሰኑ ቀናት አስበን እንጀምራቸውና የህይወታችን ክፍል ሆነው ይቆያሉ። የጓደኝነት ህይወት፣ የስራ ዓይነትና ወይም ለሆነ ችግር መፍትሄ ያደረጋችሁትን አስቡ። ብዙዎች ለሆኑ ቀናት መታለፍ የተጀመሩ ናቸው፣ አሁን ግን ህይወት ሆነዋል። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • ስናድግ ዝምታም አብሮን ያድጋል። ለሰዎች ከምናወራው በበለጠ ወደውስጥ የምናወራው መብዛት ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የምንመላለሰው የውይይት ሀሳቦች መሀል የሚገራርሙ መመሰጦች ውስጥ እንገባለን። የመገለል ፍላጎት ይቆጠጠረናል። ለብቻ የመሆን። ብዙም ቅልቅል አለመውደድ። ጥሩ ስሜት አለው። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • ኑህ ልጁን አልመሰለም። ዩሱፍም እንደ ወንድሞቹ አልነበረም። በአንድ ጎጆ ስር እልፍ መልኮች ይኖራሉ። ዥንጉርጉር ቀለሞች። ሙሉ በሙሉ ዘመደ መጥፎ የሆነ ሰው ቢኖር… ከሰውዬው ምግባር ጋር አይገናኝም። መለኪያ ሆኖም አይቀርብም። ምርጥ አባት ምርጥ ልጅ ላይወልድ ይችላል። ምርጥ ወንድምም ወንድሙን በምርጥነት ላያንፀው ይችላል። ነብይ አደምን በልጆቹ መሀከል ስለነበረው መበዳደል ምን ብለህ ትወቅሰዋለህ? ምንም!! @fuadkheyr @fuadkheyr

  • አላህ አያረፍድም። ዩሱፍ ላይ እንዳላረፈደው። 👆👆 "አዳምጡት"

  • መካሪ ሁሉ ጨዋ አይደለም። በምክሩ ውስጥ አብዝቶ ስለፅድቅና የሚነግርህ ሰው ፃድቅ ነኝ እያለም አይደለም። በተሸወደበትና በወደቀበት ነገር ውስጥ የከፈለውን ዋጋ እየነገረህ ሊሆን ይችላል። ነፍሱን ማሰር በተሳነው ጉዳይ ላይ "ይህ ነው ክፈተቴ አንተ ግን በዚህ በኩል ነፍስህን አሸንፋት" ይሆናል የሀሳቡ ውጥን። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • “ሰዎችን የመንገዱ አጋማሽ ላይ አትተው። መንገዱን በናንተ ምክንያት ብቻ ጀምረውት ሊሆን ይችላል።” የሚል የዐረብኛ ጥቅስ አነበብኩና እውነት ነው አልኩኝ። በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ስንት እህቶች ከአንዳንድ ወንዶች በተሰጣቸው አጉል የይሆናል ተስፋ መሀል መንገድ ላይ ቀርተዋል? የማያውቁትን መንገድ ጀምረው። በስራ ምክንያት እኛ እናውቀዋለን ብለው መሀል መንገድ ላይ በሚጠፉ ሰዎች ስንት ነጋዴዎች ከሰሩ? ስንት ወጣቶች በጓደኞቻቸው ውትወታ ጀምረውት… መመለስም ማለፍም የተሳናቸው የሱስ አዘቅት ውስጥ ገብተዋል። አይደል? እስኪ ሀሳብ ስጡበት። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • በመጨረሻም ዱንያ ከቤተሰብህ የበለጠ ውድ ነገር ልትሰጥህ አትችልም። ዱንያን በሙሉ ብትዞራት ከነርሱ የበለጠ ዋጋ ያለውን ነገር አታገኝም። ደስታን ከነርሱ ጋርና በነርሱ ውስጥ አብዝተህ ታሸተዋለህ፣ ትኖረዋለህ። ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ። @Fuadkheyr @fuadkheyr

  • ከጊዜ ጋር… የእድሜያችንን እኩሌታ ስናልፍ… ወደ አመሻሽ ላይ እንደድሮው ሁሉንም ነገራችንን ለሰው አንናገርም። መጥፎ የሆኑ ስሜቶቻችንን የመደበቅ ትልቅ ችሎታ ከወዴት እንደመጣ ሳናውቀው ይቆጣጠረናል። እንደጉድ እንችላለን። በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ምንም ያልሆንን ፅኑ መስሎ መታየት እንዴት እንደሆነ እንማራለን። አይገርምም? ወላጆቻችን የራሳቸውን ችግር ሲነግሩን እንኳን በአስተውሎት እናደምጣለን። የኛን ጉዳይ ሳንተነፍስላቸው። እንድናለቅስ የሚያስገድዱን ነገሮች ተፈጥረው እንኳን ፈገግታ ለመላበስ እንውተረተራለን። ፈገግታ የሚያሸነፈው የማይደረመስ የእንባ ግድብ ከየት መጣ? አቤት የአመሻሽ ውበት… @fuadkheyr @fuadkheyr

  • "ዱዓዬ እጣፈንታዬን ለመቀየር በቂ አልነበረም ማለት ነው?" የሚሉ ከርታታ ልቦች አሉ። በህይወት ልዩ መልኮች እንቅፋት የተመቱ ልቦች። በህመም፣ በእዳ፣ በትዳር አለመሳካት፣ በሁኔታዎች መዘበራረቅና ግራመጋባት የሚዋኙ ስሜቶችም እንዲሁ። ምን ያህል ጌትዬን ተለማምጠናል? … ከአለሙ ሁሉ እስኪያስቀድመን፣ ከጠያቂዎች ሁሉ እስኪመርጠን። እርሱ የሚለማመጡትን ይወዳል። የሚወደውን ደግሞ ይመርጣል። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • የተሸፈነ ነገር አይገለጥም። በተለይ አንድ ባርያ በርሱና በጌታው መካከል ስላጠፋው ጥፋት ለሰዎች እንዲታያቸው የምንገልጠው መጋረጃ አይኖርም። ደብቀንለት ለመምከር ካልሆነ በቀር ጌታው ጋር ይጨርስ ዘንድ መተው የደጋጎች መገለጫ ነው። ሁሉም ሰው ከራሱ ጋር እንኳን የሚተፋፈርበት መጥፎ ጎን ይኖረዋል። ለራሳችን እንኳን ደግመን ለመንገር የሚቀፈን ስንት ኃጥያት አለን? በቃ ሰዎች አክብረውን እንኳ ጥሩ ጎናቸውን ካሳዩን ይበቃናል። የጥፋት መዝገባቸውን ሙሉ ለሙሉ ብናውቅ እንኳን ከጌታቸው ዘንድ ያወሩ ዘንድ እድል እንሰጣለን እንጂ ለሰው ምላስ አሳልፈን አንሰጥም። እየተሸፋፈንን የምንመካከርበት ሜዳ ናት… ዱንያ። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • አለመፍረድ። ትንሽ በእድሜ ከፍ ስንል፣ ትንሽ በሚፈትኑ የህይወት ተሞክሮዎች ስናልፍ፣ ትንሽ በኢማን መጨመርና መቀነስ ውስጥ ስንመላለስ… የምንረዳው እውነታ ነው። በቃ… "ምናልባት" ብለን ማሰብ እንድንችል የሚያደርገን የብስለት ደረጃ ነው። በሆነ መልኩ ዱንያ ያንገላታቻቸውን ሰዎች ስታይ … "ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራ ማያውቁ ሞኝ ድሆች" ብለህ ጭራሽ እንዳታስብ። ጭራሽ። ትዳር ዓለም ያልዘለቀላቸውን ሰዎች ስታይ "የባህሪ ደካሞች፣ ጥሬዎች" ብለህ እንዳትፈርድ። እነርሱ ብቻ የሚያውቁት ብዙ ማታውቀው ነገር አለ። "ምናልባት" የሚያስብልህ። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • በጣም መንገብገብ፣ በጣም ክፍት መሆን፣ በጣም ራስን መስጠት ብዙ ጊዜ በጣም ያዋርዳል። ሁለተኛ ሰው ወይም አማራጭ የሚታይበት ሰው ያስደርጋል። ሁሉንም ነገር ሰጥቶ አንድ ነገር እንዲሰጡት የሚለምን አይነት ሰው ያስደርጋል። ሰዎች ያልተዘጋጁበትና ያላሰቡት ዓይነት ቦታ ስትመጣላቸው ይኮራሉ። በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ የሚሉትን ዓይነት እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን… በራሳችን እጅ። አንዳንዴ "አይመቸኝም" ያስፈልጋል። አንዳንዴ "ፈልገው ይደውሉ" ብሎ መተውም ያስፈልጋል። … ሲመስለኝ። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • ግብፃዊው ፀሓፊና ፈላስፋ አኒስ መንሱር “የሰዎችን ውስጣዊ ዓለም እንዴት ነው ማወቅ የምንችለው?" የሚል ጥያቄ ተጠይቆ ነበር። እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ባል ሚስቱ በታመመች ጊዜ ይታወቃል። ሚስት ደግሞ ባሏ በደኸየ ጊዜ ትታወቃለች። በመከራ(ችግር) ወቅት የእውነት ጓደኛ ይበጠራል። ልጆች ወላጆቻቸው ሲሸመግሉ ይታወቃሉ። ወንድምና እህቶች የውርስ ጊዜ ይታወቃሉ። ዘመድአዝማድ በብቸኝነት ውስጥ እንግዳ ሆነህ ሲያገኙህ ታውቃቸዋለህ። የእውነት ፍቅር ደግሞ ጥቅም ሲያበቃ ይታወቃል። አማኝ በፈተና ወቅት ይለያል።” @fuadkheyr @fuadkheyr

  • ውስብስብ ጉዳዮቹን ለአላህ አደራ የሰጠ ሰው አይከስርም፣ አይፀፀትም። @fuadkheyr @fuadkheyr

  • አቡበከር የቢላልን ያህል ድብደባ አላስተናገደም።  ድህነትም እንደአቡዘር አልፈተነችውም። ሰይፎች የኻሊድን ያህል ታዘውት በካሃዲያን አንገት ላይ አላሳረፈም። ግን  ከሁሉም የሚበልጥ ሰሓባ ነበር። ለነብዩ ልቡን ሰጥቷል። እንዳሻዎት ያድርጉኝ ብሏል። የልብ ሰው!! @fuadkheyr @fuadkheyr

  • በዙሪያህ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመረዳት አትሞክር። አንዳንድ ጉዳዮችን አለመረዳት ነው የሚሻለው። አንዳንዴ ነገሩን በመረዳትህ የሚመጣብህ የልቦና ቀውስና አንደበትህ ላይ የሰዎች ስም መመላለስ ብቻ ነው። …  በቃ ምናገባኝ ማለት አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ! @fuadkheyr @fuadkheyr

  • ሰዎችም እድል ናቸው። በሆነ አጋጣሚ የምናገኛቸው ወይንም የምናጣቸው። ሁል ጊዜ በነበረበት የምናገኘው አይኖርም። ምናልባት ዛሬ ለኛ የተገባ ሰው… ነገ ላይሆን ይችላል። @fuadkheyr @fuadkheyr

Fuad kheyredin — tgindex