- Последний пост
- 18:31
- Последнее чтение
- 17:06
- Постов за неделю
- 15
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 457
- 1/48двое суток
- 5 107
- 1/72трое суток
- 5 508
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
🛑 አራተኛ ሳምንታችን (1 ወራችን) ሊፈፀም ነው‼️ 28ኛ ቀን ደረስን። አራተኛው ሳምንት ዛሬ ይፈፀማል። 9ኛ ክፍል በሚቀጥሉት ቀናት ያልቃል። በዓላማ ተነስ። እሁድ የእረፍት ቀን ሳይሆን የሳምንቱ ቁልፍ ቀን ነው። በዚህ ከቀጠልክ አይምሮህ ውስጥ ወዳሰብከው የኢንትራንስ ውጤት እየተጠጋህ ነው፤ ካቆምክ ግን ጸጸት ይጀምራል። ዛሬ ሁላችሁም Math's Unit 7 ፤ ታጠናላችሁ። ከ 2-3 የብሔራዊ ፈተና የሚወጣበት የጂኦሜትሪ ቻፕተር ነው። ከዛ እሱን ስንጨርስ የትላንቱን Bio Unit 5 እና Hist Unit 7 & 8 ፈተና እንፈተናለን። ዛሬ እሁድን ቀለል አርገንላችኋል፤ ከኛ እኩል የሆናችሁ ጨርሳችሁ በደምብ እረፍት አርጉ፤ ወደኋላ የቀራችሁ ይሄን ቀን ተጠቀሙበት! ዳይ ወደ ጥናት! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ብታጠናም ባታጠናም ክረምቱ ያልቃል! ስለዚህ ተጠቀምበት‼️ ክረምቱ እየሮጠ ነው፤ ነሀሴ 9 ደርሰናል፤ አንተም በፕሮግራም እያጠናህ ነው፤ ስለዚህ መጨነቅ የለም! የዚህ ክረምት ቀናት ልፋትህ ብሔራዊ ፈተናን በምርጥ ውጤት ያሳልፉሀል! የዛሬውን ጥናት እና ፈተና ጨረስክ? ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! ሁሉም ተማሪ ማለፍ ይፈልጋል፤ ፍላጎት በቂ አይደለም፤ የሚያልፈው ለአላማው ሲያጠና የሚያድረው ወይም ዕቅዱን ለማሳካት ሳይሰለች ዋጋ የሚከፍለው ነው! ስላንተ ነው የማወራው! እያንዳንዱን ሰከንድ ተጠቀም። የሚባክን ጊዜ የለም! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ቅዳሜን በዲስፕሊን መጠቀም ግዴታ ነው‼️ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ተማሪ በየአመቱ ብሔራዊ ፈተናን ይፈተናል፤ 30ሺው ብቻ ወደ ዩኒቨርስቲ ያልፋል። በውጤት ያ ደስታ በዛሬው ጥረትህ ይወሰናል። ሌሎች ቅዳሜና እሁድን ፈታ ሲሉበት አንተ ደግሞ ጥግ ድረስ ትጠቀምበታለህ። ከዛ ማለፍህ ይረጋገጣል። ዛሬ ናቹራሎች G-9 Bio Unit 5 እና ሶሻሎች G-9 His Unit 7 & 8 እናጠናለን። እነሱን አጥንተን እንደጨረስን ትላንት ያጠናነው ላይ ጥያቄ እንሰራለን። አደራ ቅዳሜህ እንዳይባክን፤ ቀኑን ሙሉ በሙሉ ተጠቀምበት። @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 የአርብ ምሽት የፊልም ግብዣችን "Good Will Hunting" የተሰኘው ምርጥ ፊልም ነው። በህይወታችሁ ከማትረሱት ምርጥ ፊልም ይሄ ይሆናል፤ ብዙ ነገር ትማሩበታላችሁ። በተለይ በራስ መተማመን መገንባት የምትፈልጉ ልጆች እዩት። ✅ ከታች ባለው ሊንክ ቀጥታ ገብታችሁ ፊልሙን ማየት ትችላላችሁ።👇 https://hurawatch.sx/player?id=489&type=movie&title=Good%20Will%20Hunting ✅ ወይም ከታች ያለውን አፕሊኬሽን ስልካችሁ ላይ ጫኑና የፊልሙን ርዕስ Search አርጋችሁ እዩት፤ የእንግሊዝኛ Subtitle አብሮት አለው። ፊልሙን የምታዩበትን አፕሊኬሽን በዚህ ሊንክ Download አርጋችሁ ጫኑት።👇 https://reezn.org/download/
🛑 በዚህ ክረምት ✅ ዕቅድ + ዲስፕሊን = ምርጥ ውጤት‼️ ይሄ ክረምት የሁሉም ተማሪ ህይወት የሚቀየርበት ነው። 9ኛ ክፍል የረሳኸውን፣ ያልገባህን ሁሉ በዚህ ክረምት ገብቶህ መጨረስ አለብህ። ከዛ ወደ 10ኛ ክፍል እንቀጥላለን። መስከረም ላይ ደግሞ 12ንቀን እየተማርን ማታ 11ን እንከልሳለን። ከእናንተ የሚጠበቀው የምንላችሁን በዲስፕሊን ማድረግ ነው። የዛሬው ጥናት እንዴት እየሄደ ነው? የትላንቱን ፈተና ጨረሳችሁ? የዛሬውን Bio እና Geoስ? የጨረሳችሁ ልጆች የሚገርም ፊልም እንጋብዛችኋለን፤ ያልጨረሳችሁ አሁኑኑ በሞራል የዛሬን ጥናት ጨርሱ! ዳይ ወደ ጥናት! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 የቀረህን ጊዜ ተጠቀምበት! አልረፈደም‼️ የዛሬው SAT በጣም ወሳኝ ነው‼️ ነሀሴን 7 ቀን ገፍተናል። ምንም ያልጀመራችሁ ልጆች ገና ነኝ ብላችሁ አትጨነቁ ከእናንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አርጉ፣ ከዛ ፈጣሪ ያግዛችኋል። ብዙ ልጆች የኢንትራንስ ውጤት ሲመጣ የሚቆጫቸው ጊዜዬን ብጠቀም ኖሮ ብለው ነው። እስካሁን ካልጀመርክ ጀምር!አልረፈደም‼️ የዛሬው ፕሮግማችን ናቹራሎች SAT Unit 4 ፤ ሶሻሎች SAT Unit 4 እና Geo Unit 6 ነው። ዛሬ SAT ስለ Passge ነው፤ በብሔራዊ ፈተና SAT ላይ ከ 8 ጥያቄ በላይ ይወጣል (English ላይ ራሱ ከ 10 በላይ የ Passge ጥያቄ አለ)፤ Unit 6 Geo ከ 3-5 ጥያቄ በላይ ይመጣል፤ ስለዚህ ሁለቱም ቻፕተሮች ወሳኝ ናቸው። በፕሮግራም የምታጠኑ ሁሉ በርቱ ይሄን ክረምት በአግባቡ እየተጠቀማችሁ ነው። መልካም ጥናት! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ጥያቄ በደምብ ስራ! ከዛ ከ 500 በላይ ግድ ነው! የትላንቱ Biology እና Eco ወሳኝ ፈተና ተጠናቋል? ውጤትህ ምንም ይሁን፤ ተፈትነህ፤ Correction አይተህ ስህተትህን እወቀው፤ ከዛ ቀጣይ አመት ድጋሚ ከልሰን የብሔራዊ እና የሞዴል ፈተና ስንሰራበት መቼም አትረሳውም፤ ለዋናው ፈተና ገብተህ ምርጥ አርገህ ትሰራዋለህ። የዛሬውን Phy እና His ጥናት ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! የወደፊት ህይወትህ በዚህ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ ነው! ተራ ጥረት ተራ ውጤት ያመጣል። ኢንትራንስ ማለፍ ወይም ከ 500 በላይ ማምጣት ከፈለግክ ይሄንን ክረምት በሞራል ተዘጋጅ‼️ ለጨረሳችሁ መልካም የዕረፍት ለሊት🙏 @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 መዘናጋት የለም! ዲስፕሊን በዚህ ክረምት ግዴታ ነው‼️ ዛሬ የ 9ኛ ክፍል Phys Unit-6 እና His Unit-6 እናጠናለን። ከዛሬው Phy ት/ት ከ 2-4 የብሔራዊ ፈተና ጥያቄዎች ይወጣል፤ ከ Hist ት/ት ደግሞ ከ 2-3 የብሔራዊ ፈተና ጥያቄዎች ይወጣል። አጥንተን ስንጨርስ እረፍት አድርገን ትላንት የተማርነው ላይ ፈተና እንሰራለን። ሞራል ከፍ ዝቅ ይላል፤ ዲሲፕሊን ግን ዘላቂ ነው። አሁን የምትለፋው እያንዳንዱ ልፋት ተጠራቅሞ ቀጣይ አመት ወደ ዩኒቨርሲቲ ያስገባሀል። ውጤትህን የሚወስነው እስከዛሬ በነበረህ ጉብዝና/ስንፍና ሳይሆን፤ በዚህ ክረምት በሚኖርህ ጥረት ነው። ዳይ ወደ ጥናት! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 በፕሮግራም ስታጠና ጊዜህ አይባክንም! ጥሩ እየሄድን ነው በርቱ‼️ ቆራጥ የሆነ ተማሪ በፕሮግራም ያጠናል፣ ዲስፕሊን እና ትከረት አለው!! ስልካችንን ከትምህርት ውጪ ለምንም ነገር አንጠቀምም! ⭐️ "ይሄ ወቅት ለህይወታችን በጣም ወሳኝ ነው!" ይሄንን መቼም እንዳትረሱ። ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለኢንትራንስ ዋጋ ከከፈልክ ዕድሜ ልክህን በራስህ ትኮራለህ! አይቆጭህም! ሁላችሁም የሚገርም ጥረት እያረጋችሁ ነው፤ ጀግኖች በርቱ! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ቤተሰብህን ታኮራለህ በርታ!💪 ለቤተሰብህ መስዋዕትነት የሚመጥን ተማሪ ሁን። እነሱ የደከሙት አንተ ተራ ተማሪ እንድትሆን ሳይሆን የቻልከውን ሁሉ እንድታደርግ ነው። ተራ ተማሪዎች ሲደክማቸው ያቆማሉ፤ ቆራጦች ግን በድካም ውስጥ ያልፋሉ። ዛሬ ናቹራሎች Grade 9 Biology Unit 4 እና ሶሻሎች Grade 9 Economics Unit 5 እና 6 እናጠናለን፤ የዛሬን ጥናት እንደጨረሳችሁ፤ የትላንቱን Eng ፈተና ተፈተኑ። ዛሬ ከፍተኛ ጥረት ካንተ ይፈለጋል፤ ሌሎች ክረምቱን ሲያርፉ፣ ሲዝናኑ አንተ ጥረትህን ጨምር፤ እያንዳንዱን ሰከንድ ተጠቀም። ከዛ መስከረም ላይ በኮንፊደንስ 12ን ትጀምራለህ! በርታ የሚባክን ጊዜ የለም! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ነሀሴን ተጠቀምበት‼️ ክረምቱ ሳያልቅ አጥና‼️ ከመስከረም በኋላ ጊዜ አይኖርህም፤ ቀን 12ን ትማራለህ፤ ማታ 11ን ትከልሳለህ፤ ለ 9እና 10 ጊዜ አይኖርህም፤ ስለዚህ አሁን አብረኸን አጥና። በዚህ ክረምት ካላጠናህ መቼ ታጠናለህ? ኢንትራንስ ማለፍ አለብህ! ቤተሰብ ያንተን ውጤት ይጠብቃል። የዛሬን ጥናት ዛሬውኑ በዲሲፕሊን ጨርስ! ቢደክምህም እንኳ አንብብ። የዛሬውን English ከነጥያቄው አሁኑኑ ጨርስ፤ ከዛ የትላንቱን Math's ፈተና ተፈተን። የዛሬ ዕቅድህን ሳታሳካ አትተኛ። ሰበብ የለም! እንቅልፍና መዝናናት ስትጨርስ ይደርሳል! የወደፊት ህይወትህ የዛሬውን ጥረትህን ይፈልገዋል፤ ዳይ ወደ ጥናት!💪 @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 በሞራል ቀጥል! የዛሬው English ጥናት ወሳኝ ነው‼️ በየአመቱ የ English ብሔራዊ ፈተና ላይ ከ Clause እና Sentence Structure ጋር የተገናኘ ከ 6-8 ጥያቄ አይጠፋም። የዛሬው English ጥናት ለ SAT ፈተና ራሱ ጠቃሚ ነው! ስለዚህ በጥናት ፕሮግራማችን መሰረት ዛሬ መጀመሪያ English እናጠናለን፤ ትንሽ ዕረፍት አርገን ከዛ ከኖቱ ስር ያለውን ጥያቄዎች እንሰራለን፤ በደምብ ዕረፍት አድርገን የትላንቱን Math's Unit 6 ፈተና እንፈተናለን። እቅዱን ተግባራዊ አድርግ። ምንም ሰበብ የለም። ዲሲፕሊንህ ከ 500 በላይ የምታመጣበት ብቸኛው መሳሪያ ነው! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ኢንትራንስ ለማለፍ 3 ነገር በቂህ ነው‼️ ኢንትራንስን ለማለፍ መፍራት፣ መደንገጥ አያስፈልግም፤ 1ኛ ቆራጥ መሆን አለብህ (አልፋለው ብለህ ወስን!) 2ኛ በፕሮግራም አጥና (ጊዜህን አታባክን፣ በየቀኑ በምናወጣልህ ዕቅድ አጥና!) 3ኛ ዲስፕሊን ይኑርህ (ደበረህ ደስ አለህ በየቀኑ ተዘጋጅ)። አለቀ እነዚህን 3 ነገሮች ካደረክ ኮርተህ ታልፋለህ። የዛሬውን ጥናት እና ፈተና ጨረስክ? ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! ሁሉም ተማሪ ማለፍ ይፈልጋል፤ ፍላጎት በቂ አይደለም፤ የሚያልፈው ለአላማው ሲያጠና የሚያድረው ወይም ዕቅዱን ለማሳካት ሳይሰለች ዋጋ የሚከፍለው ነው! ስላንተ ነው የማወራው! ዳይ በርታ! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 4ኛ ሳምንት የጥናት ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ‼️ እንዴት አደርክ የነገው የዩኒቨርስቲ ተማሪ🫡 ? ይሄ ሳምንት በብሔራዊ ፈተና ውጤታማ ለመሆን ወሳኙ ነው! በዛሬ ፕሮግራም Grade 9 MATH'S Unit 6 እናጠናለን። በዚህ ምዕራፍ ጂኦሜትሪን ከዜሮ ትማራላችሁ፤ በብሔራዊ ፈተና ከ 3-4 ጥያቄ ይወጣበታል። እነሱን አጥንተን ስንጨርስ ናቹራሎች የትላንቱን Phy Unit 5፤ ሶሻሎች የትላንቱን Hist Unit 5 ፈተና ትሰራላችሁ። በዚህ ክረምት ዝግጅት ብቻ የብሔራዊ ፈተና ውጤታችሁን ከግማሽ በላይ ማምጣት ትችላላችሁ! በርቱ ፈጣሪ ይርዳችሁ! መልካም የጥናት ሳምንት!🙏 @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ይሄን ክረምት በፕሮግራም የምታጠኑ ተማሪዎች በርቱ👏👏👏 ክረምቱን መዘጋጀት ያልጀመራችሁ አዲስ ተማሪዎች አሁንም አልረፈደም ጀምሩ! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ሶስተኛ ሳምንታችን ሊፈፀም ነው‼️ 21ኛ ቀን ደረስን። ሶስተኛው ሳምንት ዛሬ ይፈፀማል። በዓላማ ተነስ። እሁድ የእረፍት ቀን ሳይሆን የሳምንቱ ቁልፍ ቀን ነው። በዚህ ከቀጠልክ አይምሮህ ውስጥ ወዳሰብከው የኢንትራንስ ውጤት እየተጠጋህ ነው፤ ካቆምክ ግን ጸጸት ይጀምራል። ዛሬ ናቹራሎች Grade 9 Phy Unit 5 ፤ ሶሻሎች History Unit 5 ታጠናላችሁ። ከዛ ሁላችንም የትላንቱን Math's Unit 5፣ Eng Unit ፈተና እንፈተናለን። ሻምፒዮኖች እንዲህ ነው የሚዘጋጁት። ሳምንቱን በድል አብረን እንጨርሳለን! ዳይ ወደ ጥናት! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ብታጠናም ባታጠናም ክረምቱ ያልቃል! ስለዚህ ተጠቀምበት‼️ ክረምቱ እየሮጠ ነው፤ ነሀሴ 2 ደርሰናል፤ አንተም በፕሮግራም እያጠናህ ነው፤ ስለዚህ መጨነቅ የለም! የዚህ ክረምት ቀናት ልፋትህ ብሔራዊ ፈተናን በምርጥ ውጤት ያሳልፉሀል! የዛሬውን ጥናት እና ፈተና ጨረስክ? ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! ሁሉም ተማሪ ማለፍ ይፈልጋል፤ ፍላጎት በቂ አይደለም፤ የሚያልፈው ለአላማው ሲያጠና የሚያድረው ወይም ዕቅዱን ለማሳካት ሳይሰለች ዋጋ የሚከፍለው ነው! ስላንተ ነው የማወራው! እያንዳንዱን ሰከንድ ተጠቀም። የሚባክን ጊዜ የለም! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 ቅዳሜ፡ ለብሔራዊ ፈተና ወሳኝ ቀን! በውጤት ቀን የቤተሰቦችህን ኩራት አስብ። ያ ደስታ በዛሬው ጥረትህ ይወሰናል። ሰበብ የለም። በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ተፎካካሪዎችህ የምትበልጠው ቅዳሜና እሁድን ጥግ ድረስ ስትጠቀም ነው። በሙሉ ትኩረት አጥና። ዛሬ ሁላችንም Math's Unit 5 እንጨርሳለን (በጣም አጭር ነው፤ ብሔራዊ ፈተና 2 ጥያቄ ቢወጣበት ነው) ፤ ከዛ English Unit 3 እናጠናለን፤ ከ 5 በላይ የኢንትራንስ ጥያቄ ይወጣበታል። የእነሱን ጨርሰን ትላንት ያጠናነው ላይ ፈተና እንሰራለን። ቅዳሜ መባከን የለበትም! ዳይ አሁን እንጀምር! @FutureXapp ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 የአርብ ምሽት የፊልም ግብዣችን "The Persuit of Happiness" የተሰኘው ምርጥ ፊልም ነው። ፊልሙን ለማየት ከታች ያለውን አፕሊኬሽን ስልካችሁ ላይ ጫኑና የፊልሙን ርዕስ Search አርጋችሁ እዩት፤ የእንግሊዝኛ Subtitle አብሮት አለው። ፊልሙን የምታዩበትን አፕሊኬሽ በዚህ ሊንክ Download አርጋችሁ ጫኑት።👇👇 https://reezn.org/download/