የግጥም ጥግ
Статистикаያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥ ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ። የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት በ @Esamif @amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 34
- 1/48двое суток
- 38
- 1/72трое суток
- 42
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ካልፈለግኸው ልትጥላት ህሊናህን ሰላም ስጣት በመጥበቡ አትደነቅ ለተፈጥሮ የለም ቅጣት መቀየር ነው ቀለበቱን ከዚኛው ጣት ወደዛ ጣት ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
ተከለለ ጀምበራችን ፤ ክፍት አደረ ያ በራችን ቃላቶቼ አቅም አጡ ፤ እቅዶቼ ከ'ጄ ወጡ ት'ከሾቼ ደከሙብሽ ባሳደግሁት ተቀድሜ ያዘመመ ፍቅራችንን ለብቻዬ ተሸክሜ። ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
አፍላነት ሲሰክን ቁዘማ ካበዛ፣ ልብ ቀልብ ከገዛ። በይሉኝታ ሳይሆን በማስተዋል ጠፍር አምሮቱን ካሰረ ፣ ቀልድ አልጥምህ ካለው ነገር ካመረረ ። ድንገት ዝ...ም ካለ 'ባሳብ ተጎትቶ፣ በደረቱ ኪስ ላይ ካዋለ እስኪሪብቶ። ማድመጥ ከጀመረ ሀሳብ አስጨርሶ፣ መልበስ ከጀመረ ሱሪውን ተኩሶ። በቃ እድሜውን ፈጀ፣ ወንድ ልጅ አ..ረ...ጀ !! ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
በከተማው በርዶት ሲዘዋወር የሚያቅፈው ያጣ ህፃን ካደገ በኋላ ከተማውን አንድዶ ይሞቀዋል። በነፃ የተሰጠንን አንንፈግ። ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
አለሽ ድንቅ ውበት፣ ከ'ሾህ ተጋፍቶ የፈነደቀ። አለሽ ፅኑ እምነት፣ ከገፅሽ ማጀት የተጠመቀ። አለሽ ሴትነት። ወኔን ከብልሀት የደባለቀ። ቢጥል ቢያነሳሽ የህይወት ሞገድ፣ ሰውነትሽ ላይ ይበቅላል መውደድ። ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
:ላባ ቀሊል ነሽ ለነፋስ ግርድ ነሽ ለመሬት፣ እድልሽ አናሳ ከ'ሳት ወይ ከፅህፈት። ማንም አይፈልግሽ ከስስ ገላሽ ውጪ ከቀለምሽ ቆንጆው፣ ...ግና ስትርቂ ትርፍ ነሽ ለሁሉም ጉድለት ነሽ ለጎጆው። (መታሰቢያነቱ ፦ ቦታቻውን ለማያውቁ ሰዎች ይሁንልኝ ) ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
የሰፈራችን ጫካ ውስጥ ብቻውን ነው እንዴት እዛ ድረስ በራሱ እንደሄደ ገርሞኛል። ድክም ብሎታል እየመሸ ነው ተስፋ ግን አልቆረጠም። ወደ ሰፈር መመለስ አልፈለገም በችግር ውስጥ ሆኖ ማንም እንዲያየው አይፈልግም ። ቁስሉ የተመረዘበት ይመስላል ብዙ ደም ፈሶታል። ቸልተኛ ነገር ነው አይደለም ለሰውነቱ ለህይወቱም ግድ አይሰጠውም። ገና ከቀን ጀምሮ ስልኳ ላይ ይደውላል ይጠራል ግን አይነሳም ዋጋዋ የገባው ይመስለኛል። ለአመታት ጊዜ ሳይሰጣት ኖሮ የአንድ ቀን መስዋዕትነቱ ሊማርካት እንደማይችል ቢገባውም ገና በምናልባት ሊተዋት አልወደደም ። በ 2005 ላይ ነበር እነሱ ሰፈር ተከራይታ የመጣችው ለሱ የተለየ ቀረቤታ ነበራት ።ከዛ ሁሉ የሰፈር ጎረምሳ እሱ ስቧታል ዛሬ ላይ ለምን ብትባል እንጃ ምናልባት እርጋታውና ቁምነገረኛነቱ የምትል ይመስለኛል ብትልም ደሞ አልተሳሳተችም ደሳለኝ የ 14 አመት ወዳጄ ነው በቅርበት አውቀዋለሁ በእድሜ በጣም ታናሼ ነው። እሷም አትነግረው እሱም አያምንላት እንዲሁ በአይን ፍቅር ሲቃጠሉ ቆይተው በተገናኙ በ 2ኛው አመት ወደ ፍቅር ገቡ። በቃ ምን ልበላችሁ መልካም አፍቃሪ አይገልፃትም እሱ ግን ማን ጎሽ እንዳለው አይታወቅም ከቀን ወደ ቀን ኩራቱ እየባሰ ሄደ ያምርበታል'ኮ ግን ምንም ቢሆን ገደብ ያስፈልገዋል ። ግዜ አይሰጣትም ስልክ አይመልስላትም ብቻ ብዙ ብዙ ምናልባት የመጀመሪያው ስላልሆነች ይሆናል ። እሷም ከእለት እለት የሱ ፍላጎት ማጣት እረብሿታል መሰል ሁሉ ነገሯ ልውጥውጥ ብሏል። አንድ ቀን ቢጨንቃት መጥታ አማከረችኝ ተይው ማርቲ እሱ ለሁሉም ሰው እንዲህ ነው ደሞ የክፋት አይደለም ውስጡን ታውቂው የለ የዋህ ቢጤ ነው አልኳት ። እንደ ማፈር ብላ ከሌላ ሴት ይሄድ እንደሆነ ጠየቀችኝ ሳሚ በፈጠረህ አትዋሸኝ አለች ። ምዬ እንደማያደገው ነገርኳት አመነችኝ ቻው ተባብለን ተለያየን ያን ቀን ማታ ሳስብበት አመሸሁ እሱ እንደሆነ ለማንም ግድ የለው ካንዴም ሶስቴ በሷ ጉዳይ ላወራው ሞክሬ በተቀመጥኩበት ነው ጥሎኝ የሄደው ስለዚህ ለምን እሷም ከምትጎዳ እኔም ብቻዬን ከማረጅ አናግሬያት አብረን አንሆንም ብዬ ወሰንሁ። በ ማግስቱም ስፈራ ስቸር ጠየቅኋት እሷም ለበቀል ነው መሰል በደስታ ተቀበለችኝ። እሱም እንደለመደው አንድ ማታ ወደ ጎጆዬ ሳያንኳኳ ዘው ብሎ ገባ መርፌና ክር ሆነን .... አላመነም ሳሳሳሳ ሳሚ አንተ ከሀዲ ቆሻሻ ብሎ ጮኸ የራስህ ጥፋት ነው ምናባህ ጠብቀህ ነበር ብላ ጮኸችበት ። መልስም ሳይሰጥ አይኑ ላይ በገባለት ነገር ወርውሮ ሳተኝ ቡና መፍጫ ነበረ ። ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ምንም ደደብ ብሆን ወንድ ልጅ ነኝ ውሳኔዬ ቢሳሳትም ማንም እንዲረማመድበት አልፈልግም። በውስጥ ልብስ እንዳለሁ ከጓዳ ቢላ አፈፍ አድርጌ ወደሱ ተጠጋሁ እሱም በንዴት ነው መሰል ወደኔ ሲሮጥ ሆዱን ወጋሁት ። እሷ ደንግጣ ፍራሹ ላይ ቆማለች ግን ጨካኝ የሆነች መሰለኝ እንዴት ብትጠላው ነው? በሰላም መለያየት እየተቻለ። ፍቅር ካለመስጠት ውጪ ምን አደረጋት? .... ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
: አቅጄ ነበረ በልኬ ሰፍቼ አጣማጅ አቻዬን ከ'ቅዴ ከትቼ በውጣ ውረዴ በጎንበስ ቀናዬ ነገን እያሳየሽ የቆምሽ ከኋላዬ ነብስሽ እና ነብሴ አንዳች ሳይሞክሩ እንደተላመዱ ምነው ቢፋቀሩ ቀናት ሲጋልቡ ፣ አዝማናት ሲረግቡ ጣፋጭ ቃሎቻችን ከጎታ ሳይገቡ ልጆቻችን አድገው በወግ ሳያገቡ ይሄን ሁሉ ሳላይ ፍፃሜ ትንቢቱን ባንኜ ሳልነቃው የህልም ዓለም 'ሌቱን እንዳላጣሽ ፈራሁ ያይኖቼን ማረፊያ ወይ አላሳስርሽ እን ስርቆት ዝርፊያ አልተክልሽም ነገር እንደ ደጅ አበቦች ይዤሽ አልዞር ብትሆኝ እንደ ደሜ ስሮች እና ምን ተሻለ፥ እንደው እንደ ዘበት እንደ አፍ ወለምታ ሳይጨነቁበት እንዳስተጋቡት ቃል እንደ ቀን እፎይታ ምነው ቢታከሙት አንቺጋራ መንተው የልብን ወለምታ እውነትን ተናገርሁ አምነሽ ተቀበይኝ እኔ መሽቶብኛል አንቺም አሳድሪኝ። ✍️ Zemed @ getmtg @getmtg
፡ old man says አንድ ጎልማሳ ሰው እንዲህ ሲል ሰማሁት ፥ ሴቶች ለሚፈልጉት ሰው እንዴት እንደሚያቀሉት ብታይ ኖሮ መልፋትህን ታቆም ነበር። አጸፋ የሌለው ፍቅር በወንፊት ላይ ውሀን ለመቅዳት እንደመሞከር ነው ። ወንፊቱም አይሞላ አንተም ውሀ ይዘህ አትሄድም። እሷም ፍቅርህ ዋጋው አይገባት አንተም የራስህ አታደርጋትም። ወንድ ልጅ ሳለህ ምን ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንዳለብህ እወቅ አለበለዝያ ፍቅርም ያልቃል ፍላጎትም ይነጥፋል የጓጓህለት ሁሉ መልኩን ስታይ እንደማይረባ ትረዳለህ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
፡ በመንደር ሲያልፍ ተጠርዞ አይተነፍስ ጭንቅ አርግዞ እጥፍ ቀንበር በጫንቃው ላይ ችግር አየው በግዞት ላይ የዛሬ ወላጁን የነገ ውላጁን በልተው ያድሩ ዘንዳ የሚጠብቁ እጁን ሀገር የሚያቀናው ባዶ እግሩን ተጉዞ ለጓዶቹ ደስታ እሱ ግን ተክዞ ሰማይ ቢደፋበት መች አላማው ሊነጥፍ ቢቸነክሩትም አይችል ቃሉን ሊቀጥፍ ቢቀጥንም ጠጅ ነው ለሺ ይበቃል አንዱ ወንድ ልጅ ማሰሪያው ወንድ ልጅ ገመዱ ✍️ Zemed @getmtg @getmtg
አንቺዬ... እንባሽን አርገሽው መሰናበቻ ቃል ስቃዬ እንደ ትንፋሽ መች ተቆጥሮ ያልቃል መጥተሽ ብታይልኝ ያረጀ ጋዜጣ ያለቀ ሲጋራ ይዤ በመዳፌ ጥርሴ እሰከማይታይ በ ጢም ተከቦ አፌ እብድ ተብዬልሽ ስም ወቶልኝ ባገር ስሜ ከምላሴ ጠፍቶኝ እስክቸገር ኸሊቁ እንደረሳው ይሁን ብሎት ርጉም አንዲህ ነው ብዥ ያልኩት በሰው አይን'ንደ ጉም መጥተሽ ብታይልኝ... ጥራር መስሎልሻል ያረፍሽበት ደረት የምትወጂው ጉንጬስ መቼ ስጋ አለበት ደግሞ... ከፍጥረቱ ሁሉ ውል እንዳለሽ ነገር ግዑዛን መች ቀሩ አንቺን ለመዘከር የተዋወቅንበት ቡና ቤት በረንዳ ብዙ ያለፍንበት የቤታችን ጓዳ አብረን የሔድንበት ጭር ያለ ጎዳና አትሞ አስቀምጦት የግሮችሽን ዳና ባለፍኩበት ቁጥር ይታዘበኝ ይዟል ብቻዬን ሳዘግም መንገዱም ተክዟል እኔ ምልሽ... ሴቶቹ በሙሉ እንዴት ነው ሚያስጠሉት አንቺ እንደነበርሽም አንዲህ ነው ሚመስሉት? የጋበዝኩሽ ዘፈን ፍቅሬ እያልኩኝ ውዴ ዛሬ እንደምሰማው ሙሾ ነበር እንዴ? ያ የምንወደው የ ሻይ ቤቱ ወንበር ያኔም እንደ ዛሬ ይቆረቁር ነበር? አቤት መመሳቀል ወየው ቅርፅ ማጣት አንቺ ሔደሻል ብሎ እግዜር ምድርን ቀጣት። እንዲህ እንዲህ እያልኩ... የፃድቃን ትውውቅ የሌለው ቀጠሮ ካገናኘን ብዬ ጉዳት ቁስሌን ቆጥሮ መንገድ ላይ ነው ምውል ስመላለስበት ብትመጪልኝ ምን አለበት ደሞ መንገዱ ዳር... አንዱ ህፃን ቆሞ ተመዘን ይለኛል የሚመዘን አካል መች ከኔ ይገኛል ጉዴ መች አለቀ የ ህዝቡ ሲገርመኝ የልጁ ሲገርመኝ ሚዛኑ አሸሞረ ኪሎዬን ሊነግረኝ 80 ቆጠረ ምንድነው ሰማንያ ስቴጅ የቀደድነው? ከተሰየመበት ዙፋን ያወረድነው? ብቻዬን ሆኜ ነው 80 የሆነው? ወይስ ናፍቆትሽን አንድ ለይ መዘነው? ግዴለም ተሳስቷል.. ስጋ የተባለ ከአካሌ አስኪጠፋ ተይው ደናውን ልብስ ካልሲዬ'ስኪሰፋ ምንምን ብዬልሽ መች ሰው እመስላለሁ ብቻ በተስፋ አለሁ። ብትመጪ ምናለ... ጥዑም ፍቅራችንን ቆፈን አቆራምዶት መንገደኛ ሲያልፈው ረግጦ ተራምዶት ጨክነሽ ላትተይው ቆርጬ ላልረሳው እስኪ ምናለበት መጥተሽ ብናነሳው።
የጠፉት_በጎች....‼️ ለአንዷ በግ ብሎ፣ ከሰማይ ወረደ፤ አንዷን በግ ሊታደግ፣ እንደበግ ታረደ፤ አንዷን በግ አድኖ፣ ወደ አባቱ ሄደ። የምፅአት ቀን ደርሶ፣ መለከት ሲነፋ፤ ዘጠና ዘጠኙ፣ የገቡበት ጠፋ። . የገቡበት_ጠፍቶ፣ ዘጠና ዘጠኙ፤ ታስሰው ታስሰው፣ ከሲኦል ተገኙ!!! ✍️Zemed @getmtg @getmtg
።።።።። እኔ ምልሽ... ታስታውሺ ይሆን ንገሪኝ እውነቱን የህፃናት መዝሙር ያን እንኳን የጥንቱን በዛ በበጋ(*2) እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ... አሁን አይደል የሚገባኝ.. ኑሮዬ ሳያንሰኝ ስቃዬን ልጨምር ያመት ዕቅዴ ላይ"ፍቅር"የምደምር ለካስ እኔ ነበርኩ ያ ምስኪን ታዳጊ በበጋ በሙቀት እጮኛ ፈላጊ አይሰለቸኝ ቀኑ አያደክመኝ መንገድ ላይዘልቅልኝ ነገር በልጅነት መውደድ ስንከራተት ኖሬ.. ዘመን ጨላለመ ፀሀይዋም ጠለቀች እድሜም አይገፋም ጨረቃ ግማሽ ነች። አሁንስ ትዝ አለሽ... መሸበትና ሰው ቤት ገባ ልጅቷን አያት ተከናንባ🧕 በልብሽ ለማደር ሲመሻሽ ገባሁ ተከልለሽ ባይሽ ልጠልፍሽ አደባሁ ትዝ አለሽ ያ ደፋር... እንደ'ንግድነቱ መከበር ሳያንሰው ያሳዳሪውን ልብ የሚያስኮበልል ሰው ደግሞ... መውደድሽ ሳያንሰኝ ማሰቤ ሳይበቃ የማስኮበልልሽ ለሊት በጨረቃ እኔን የገረመኝ በተከበርሽበት ሀገር እንዳትኖሪ፤ ባደግሽበት ደብር እንዳትቀበሪ፤ አምነሽ መከተልሽ ጨለማ ሳትፈሪ። የ'ድላችን ማነስ የኔ አንቺን ይዞ ዓባይ ድረስ መምጣት፤ ያባትሽ ርግማን የፈጣሪ ቅጣት፤ በበጋ ውሀ ሞልቶ መሻገርያ ማጣት። ለካስ እኔ ነበርኩ ያ ግፈኛ ወጣት ከቤቷ አስወጥቶ ለሒያጅ የሚሰጣት በቆምኩበት የፍቅር ዕንባ እያለቀስኩ ዕጣ'ድሌን እየረገምኩ እየወቀስኩ ቀና ብዬ ሳያት ሙሉ ናት ጨረቃ አንቺን ግማሽ ጎኗን ከ እጆቼ ነጥቃ ምናይነት ገድ ነው? የደረሰሽ ዕጣ የደረሰኝ ዕድል ወንዝ'ንኳ ሲሞላ ፍቅር የሚያጎድል ይኸው... አንቺም የለሽ አትመጪም ተመልሰሽ ወዶ መገፋቱ ቀድሞስ መች አነሰሽ እኔም አለሁ... ሌቱ አልበቃኝ ቀኑ ጉዟችንን ስስል እኔና አንቺን ከመዝሙሩ ሳመሳስል አንዲሁ ነን እኔና አንቺ... መውደድ ውሉን ሳያሳጣን ፍቅራችን ነው የሚያሰቀጣን። በዛ በበጋ በዛ በበጋ......
https://t.me/TEWLD_10/2166
፡ "ማፍቀር ማለት በጨለማ ሰማይ ላይ ከፈሰሱት ኅልቆመሳፍርት ከዋክብት፤ አንዷን መርጦ እንደ ጨረቃ ማግዘፍ ነው፡፡" (ከዕለታት ግማሽ ቀን) Join 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/yebrhanambatheater https://t.me/yebrhanambatheater
እስኪ ልጠይቅህ ከሞትክ በኋላ ኑሮ'ንዴት ይዞሀል ያለህበት ቦታ ምኑ ይገዛሀል ቤትህስ እንዴት ነው በልክ የሰሩልህ ለመድከው ሞቀልህ? ልብስ ሲሆን ጊዜ አፈር ምን ምን ይላል መከዳ ሲያረጉት ድንጋዩስ ይደላል? መቃብር ይሞቃል መኖርያ ሲያረጉት ምስጥ ወዳጅ ይሆናል ቀርበው ቢላመዱት? መልስልኝ እስኪ... የምትፈልገውን ህይወት አሳማሪ ምን ይናፍቅሀል ከኔ ተጨማሪ ከአለም የተለየ አካልህ ምን አጣ ንገረኝ ግዴለም ይዤልህ እንድመጣ። @getmtg @getmtg
፡ "ሕይወት ጠባሳችን ዕድሜ ልክ አብሮን እንዲኖር እንጂ ...ዕድሜ ልክ ስናለቅስበት እንድንኖር አትፈቅድልንም፡፡ ካለቀስንም እየኖርን እንድናለቅስ ነው የምታደርገን፡፡" (ከዕለታት ግማሽ ቀን) @getmtg @getmtg
፡ ስለማላጎድል ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡ አልጋ ስር ሳይቀር ቤቱን ብጥር አድርጌ አፅድቻለሁ፡፡ የቶሸሸውን እቃ ሰብስቤ አጥቤያለሁ፡፡ አልጋዬን በስርዓቱ አነጥፌአለሁ፡፡ ልብስና ጫማዎቼን ለነድያን ለመስጠት እንዲያመች አድርጌ በኩርቱ ፌስታሎች አሰናድቼ በሩ ስር አስቀምጫለሁ፡፡ ሦስት ሳምንት ሙሉ ችላ ብዬ የከረምኩትን ውሃ እያንጠባጠበ የሰነበተ የሽንት ቤቱን የእጅ መታጠቢያ ቧንቧ እንኳን ባለሙያ ጠርቼ አሠርቻለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡ ሕይወቴን ሙሉ እናንተ ቤተሰቦቼ ላይ ሸክም ሆኜ መኖሬ ሳያንስ አሁን ደግሞ የቆሸሸና የተዝረከረከ ነገር ትቼላችሁ መሄድ አልፈለግኩም፡፡ ስንት ዘመን ሙሉ ቆሻሻዬን ስታጸዱ፡ ገመናዬን ስትሸፍኑ የኖራችሁት ይበቃችኋል፡፡ አስክሬኔን መስኮት አጠገብ ያለው ሶፋዬ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡ ብዙ ክኒኖች ወስጄ ለመሞት የመረጥኩት ፡ በጽዳት የቆየሁበትን ቤት ላለማቆሸሽ ነው፡፡በተለይ ግን መከረኛዋ ተመላላሽ ሠራተኛዬ ጌጤ፡ ጠዋት መጥታ በሩን ከፍታ ስትገባ በደም ተዘፍቄ፡ ወይ ተንጠልጥዬ አይታኝ በድንጋጤ ክልትው እንዳትል ነው፡ አምስት አመት ሙሉ አንዴ ሰው፡ አንዴ አፈር እየሆንኩ ያሰቃየኋት ይበቃታል፡፡ ዐውቃለሁ፡ ነገ ጠዋት እኔ ባልኖርም ጀምበር በሰዓቷ ትወጣለች፡፡ ሕይወትም ምንም እንዳልተፈጠረ፡ አንድም ሰው እንዳልጎደለ ዑደቷን ትቀጥላለች፡፡ ለዚህ ነው ልሄድ የወሰንኩት፡ በመሞቴ ምንም ስላማላጎድል፡ የትም ስለማልጎድል፡ ማንንም ስለማላጎድል፡፡ (ዥዋ ዥዌ) @getmtg @getmtg
ትንሽ ዕረፍት ምን ይፈጠር ይሆን ባንኖር ዛሬ'ንኳ ይታይ ይሆን እንዴ ህይወት ስውር መልኳ እስትንፋስ ቢቋረጥ እንጃ ምን ይቀራል እጃችን ሳይነካው... የደፈረሰ አለም መች በኛ ይጠራል? እንጃ.... እንዲህ ምንባክነው ኑረት ሞት እስኪሆን በማን እንቅልፍ ላይ ቅዠት ሆነን ይሆን ምናለ ብንማር ዘመም ሲያደርገን መኖር ወደ ገደል ከሞታችን ጋራ ኑሮን ማደላደል አለም አስር ላትሆን በልታን ላትጠረቃ ምን ይለናል ህይወት እዚጋ ቢያበቃ። @getmtg @getmtg
፡ "የሰላም ትክክለኛ ትርጉም ረብሻ አለመኖር አይደለም፤ መነሻው ፍቅር የሆነ ረብሻ በነፍስ ውስጥ እንደመዓበል መተራመሱ ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰላም ውሃው እንደደረቀ ወንዝ ነው፡፡ በሰላም ውስጥ ወንዝ መፍሰስ አለበት፤ ወንዙን ሊሻገሩ የሚታገሉ ነፍሶች መኖር አለባቸው፤ በውሃው ውስጥ የሚጋጩ የሚሳሳሙ ድንጋዮች መኖር አለባቸው፤ አሳዎች መኖር አለባቸው፡፡" (ከዕለታት ግማሽ ቀን) @getmtv @getmtg