- Последний пост
- 25 мая
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Make your health! @hakimmelaku
የአሜሪካ የምግብ መመሪያ (Dietary Guidelines for Americans) 2025-2030 አዲሱ የአሜሪካ የምግብ መመሪያ ጃኑዋሪ 7 እለት ይፋ ተደርጓል። ለጤናችን የሚበጀውን እውነተኛ ምግብ እንመገብ በሚል አርስት የወጣው መመሪያ ጤንነት የሚጀምረው ከማእድ ነው ሲል አጽንኦት ሰጥቷል። በበሽታ ተከላካይ፣ ገንቢ እና ሌሎችም ለጤና ተስማሚ ንጥረ ምግቦች የበለጸገ ተፈጥሮአዊ ምግብን አበክሮ መክሯል። አትክልት እና ፍራፍሬ በበቂ እና አዘውትረን እንድንመገብ ሲያበረረታታ ለጤና ጎጂ የሆኑ (በተለይም መጥፎ ኮሌስትሮል የሚጨምሩ ስቦችን እና አልኮልን) ከአመጋገባችን እንድንገድብ አሳስቧል። ስኳር የተጨመረባቸው ምግቦችን እና መጠጦችን እንዲሁም አርቲፊሻል ማጣፈጫ (Artificial sweetener) ከነአካቴው ገዝቷል። ሙሉ መመሪያውን በPDF ተያይዟል። በሚቀጥሉት ፖስቶች ስለዚህ የምግብ መመሪያ ተከታታይ ማብራሪያዎችን እና ከኢትዮጵያ የምግብ መመሪያ ጋር በንጽጽር የምናይ ይሆናል። @hakimmelaku
🎁 የገና ስጦታ ከዶ/ር መላኩ እንኳን አደረሳችሁ። ዶ/ር መላኩ ከ PULSE gifts ጋር በመተባበር የገና ስጦታ አዘጋጅቷል። ሶስት ሰዎችን ሰርፕራይዝ እናደርጋለን። ለመሸለም የዶ/ር መላኩን አካውንት (TikTok or Facebook / Instagram) ✅ Follow @hakimmelaku ✅ Like @hakimmelaku ✅ share @hakimmelaku ✅ እንዲሁም Gena @hakimmelaku ብለው ኮሜንት በማድረግ ቢያንስ 5 ጓደኞችዎትን ታግ በማድረግ ብዙ ላይክ ያገኘ እንሸልማለን። መልካም እድል። ስለጤናዎት እየተማሩ ይሸለሙ። በዓሉ የደስታ፣ የጤና ይሁንልን! https://vm.tiktok.com/ZMD6V8fVo
የአሳች ፈዋሾች ውሸት እንዴት መለየት ይቻላል? በአለም አቀፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ ደረጃ የስኳር ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል። በስኳር ህመም ዙርያ የሚነገሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችና አሳች ፈዋሾችም እንዲሁ እንደወረርሽኝ በስፋት ይታዩ ጀምረዋል። የስኳር በሽታን ለማዳን የሚሰጡ የባህል ህክምና ምርቶች እዚህም እዚያም ይሰማሉ። ይባስ ብሎም ብዙ ታዳሚ ያላቸው ጋዜጦችና ቴሌቪዥን ሚዲያ ተቋማት ሳይንሳዊ ማስረጃ የሌላቸው ጎጂ አፈ ታሪኮች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ማሰራጫና ነጻ ማስተዋወቂያ መድረኮች ሆነዋል። እነዚህ አሳች ፈዋሾች ብዙ ሰሚ ጆሮና ፈውስ ፈላጊ የሚያገኙበት ምስጢር ዘርፈ ብዙ ቢሆንም አንዱ ምክንያት በማህበረሰቡ ዘንድ ስለስኳር ህመም የግንዛቤ እጥረት መኖሩ ነው። ብዙውን ጊዜ በማህበረሰብ አእምሮ ውስጥ የሚታመኑ ተረት ተረቶችና አፈ ታሪኮች ላይ በመመስረት አንዳንዴም ትንሽ እውነት አዘል መረጃ በማሰራጨት ነው ቢዝነስ የሚሰሩት። በእርግጥስ እነዚህ 'አቋራጭ ፈውስ' ይሠራሉን? ለመሆኑ በአሁኑ ጊዜ ለስኳር ህመም ዘላቂ ስርየት የሚሰጥ መድኃኒት በአለም ላይ አለ ወይ? ‘የስኳር ህመምን ይፈውሳሉ’ ውሸቶች እንዴት መለየት ይቻላል? 1️⃣ ሁሉንም አይነት በሽታ ‘’ለመፈወስ፣ ለማከም ወይም ለመከላከል ይረዳል” ተብሎ የሚቀርብ ማንኛውም ለማመን የሚከብድ ወሬ (too good to be true) ውሸት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። አንድ ሰው በአንድ ቅጠል “ፈጣን የህመም ማስታገሻ”፣ “ፈጣን ክብደት መቀነስ” ወይም “የተረጋገጠ የደም ስኳር ማረጋጊያ” እሰጣለሁ ካለ እውነት አይደለም ማለት ነው። እነዚህ የእፈውሳለሁ ማደናገሪያዎች እምብዛም በሳይንሳዊ ማስረጃ አይደገፉምም። 2️⃣ አጠራጣሪ ቃላት መጠቀም ለምሳሌ “ሁሉም ተፈጥሯዊ”፣ “ተአምራዊ ፈውስ”፣ “ፈጣን እና ህመም የሌለበት ፈውስ”፣ ‘ምንም የጎኞሽ ጉዳት የሌለው’ ወዘተ የሚል ሃረጎች ካሉበት ተዓማኒነት ይጎለዋል። 3️⃣ ከፊል ሳይንሳዊ የሚመስሉ ትርጉም የማይሰጡ ቃላትን ለምሳሌ ‘detoxification’ ከተጠቀሙም እውነት አይደለም ማለት ነው። 4️⃣ የተቀመመ መድሃኒታቸው “ሚስጥራዊ ንጥረ ነገር” እንዳላቸውና ውህዱ እንዳይሰረቅብኝ በማለት ምን እንደሆነ ግልጽ ያልሆነ ፈውስ ካላቸውም መጠርጠር ይሻላል። 5️⃣ ‘ብቻ’ የሚል ቅጥያ ካለውም ውሸት ነው ማለት ነው። የኔ ቅመም ብቻ፣ የኔ ቅጠል ብቻ ነው ፈዋሽ ካሉ ችግር አለ ማለት ነው። 6️⃣ የሴራ ፅንሰ-ሀሳብ (conspiracy) የሚነዙ ከሆኑም እንዲሁ አሳች ናቸው ማለት ነው። ለምሳሌ መድሃኒት አምራቾችና ሃኪሞች ተመሳጥረው ነው ዋናውን የሚፈውሰውን መድሃኒት የደበቁት፤ ዶክተሮች በገንዘብ ተደልለው ነው የማያድን መድሃኒት ቀን በቀን እንድትወስድ የሚያደርጉህ ወዘተ ሊሆን ይችላል። 7️⃣ የማይረጋገጡ የአድኖኛል ምስክርነቶች (witnesses) በአብዛኛው የተከፈላቸው ወይም በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ የሆኑ ማስታዎቂያ የሚሰሩ ናቸው። አንዲህ አይነት አሳች ፈዋሾችን ለመዋጋት የሚረዳን ትልቁ መሳሪያ እውቀት ነው። የተረጋገጡና ትክክለኛ የጤና መረጃን ተደራሽነት በማስፋት የተሳሳቱ አመለካከቶችን መቅረፍ ይቻላል። የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መልኣኩ ታዬ ብሎግ https://melakutaye.com/fake-traditional-healers/ እንዲያነቡና ለሌሎችም እንዲያጋሩ በትህትና እጋብዛለሁ። @hakimmelaku
በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም እንዲለዩ የተላለፈ ጥሪ - call for community diagnosis and early referral of Familial Hypercholesterolemia በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም (የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮሌሚያ, Familial Hypercholesterolemia, FH) በጣም ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት የሚያመጣና ለልብ ህመም የሚያጋልጥ የተለመደ በዘር የሚወረስ በሽታ ነው። ሮጠው ያልጠገቡ ልጆችን እና ወጣቶችን በልብ ህመም የሚያሰቃይ ህመም ሲሆን በጊዜ ካልታከመ ገዳይ በሽታ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሰዎች አንዱን እንደሚያጠቃ የተረጋገጠ ሲሆን በዘር ከሚወረሱ የሜታቦሊክ ህመሞች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። ይህንን አስከፊ ህመም ለማከም እያንዳንዱ ሰው ማገዝ ይችላል! እንዴት ቢባል የህመሙን ምልክቶች በራስ፣ በቤተሰብ አባላት፣ በጓደኞች ወይም በስራ ቦታ ላይ በመመልከት እና በመለየት ለትክክለኛ ምርመራ እና ህክምና ወደጤና ተቋም እንዲሄዱ በማበረታታት ህይወት አድን ስራ ሊሰሩ ይችላሉ። ማንም ሰው ሊያያቸው የሚችላቸው የህመሙ ምልክቶች እነዚህ ናቸው፡ 1️⃣ በቆዳና ጅማት ላይ የሚወጡ ቢጫማ እብጠቶች (xanthoma) ዋነኛ የህመሙ ምልክቶች ናቸው። እነዚህ እባጮች በቁርጭምጭሚት አካባቢ የተረከዝ ጅማት (ቋንጃ) ላይ፣ በጉልበት፣ በእጆች ወይም ክርን ላይ ሊወጡ ይችላሉ። በአይን ዙሪያም (xanthelasma) ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ እብጠቶች በቀላሉ የሚታዩ ቀለማቸው ቢጫማ ሲሆን ኮሌስትሮል በቆዳና ጅማት ውስጥ ሲከማች የሚመጡ ናቸው። 2️⃣ የአይን መስታውት ዙሪያ ላይ የሚወጣ ቀለበቶች (arcus cornealis) ሌላኛው የኮሌስትሮል ህመም መገለጫ ሊሆን ይችላል። ይህ ነጭ ወይም ግራጫ ቀለም ያለው ክብ መሰል ሲሆን ኮሌስትሮል በአይን መስታወት ዳርቻ ላይ ሲከማች የሚፈጠር ነው። በአብዛኛው በአረጋውያን ላይ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሲሆን ከ45 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ ሲታይ የኮለኢስትሮል ህመም ምልክት ነው። 3️⃣ ከቤተሰብ አባላት ውስጥ በወጣትነታቸው ከ50 አመት እድሜ በፊት ድንገተኛ የልብ ድካም (heart attack) ወይም ስትሮክ (stroke) ያጋጠመው ካለም እንዲሁ የዚህ የኮሌስትሮል ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል። 4️⃣ ለሌላ አጠቃላይ የጤና ምርመራ ሲሰራ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት ከተገኘም እንዲሁ የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮሌሚያ ሊሆን ይችላል። ይህን ህመም ማወቅና ተጠቂዎችን በቶሎ መለየት ለምን አስፈለገ? በቅድመ ምርመራ፣ ትክክለኛ ህክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ይህ በዘር የሚወረስ የኮሌስትሮል ህመም ያለባቸው ሰዎች ረጅም እና ጤናማ ህይወት ሊመሩ ይችላሉ። እነዚህን ቀላል ምልክቶች በማወቅ በማህበረሰባችን ውስጥ የዚህ ህመም ተጠቂዎችን የልብ ድካም ሳይዛቸው አስቀድሞ መታከምና መከላከል ይቻላል። በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም በመለየት በወጣትነት የሚመጣን የልብ ድካም ለመከላከል የሚደረገውን ሃገራዊ ጥረት እናግዝ። ይህን ማድረግ እንዲያስችለን በሚኖሩበት፣ በሚሰሩበት ከባቢ ውስጥ የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮልሚያ (FH) ምልክቶችን ይወቁ! ለሌሎችም ያሳውቁ። Read the full article at https://melakutaye.com/call-for-community-diagnosis-and-early-referral-of-familial-hypercholesterolemia-fh/ @hakimmelaku
በህጻናት እና ልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ህመም ስለ ኮሌስትሮል ህመም ስናስብ ብዙውን ጊዜ ከአዋቂዎች ጋር ብቻ እናያይዘዋለን። ነገርግን ይህ የጤና ጉዳይ ህጻናትን እና ታዳጊዎችን ሊያጠቃ ይችላል። በዋናነት ልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ህመም አይነቶች በዘር የሚተላለፉ ሲሆኑ በተጨማሪም ከአመጋገብ መዛባትና እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ ጋር በተያያዘም የልጆች ኮሌስትሮል ሊዛባ ይችላል። በልጆችና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች የኮሌስትሮል ህመም በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ ነው። በተለይም ከውፍረት መብዛትና እና ጤናማ ያሆነ የአመጋገብ ልማድ እየተስፋፋ በመምጣቱ ብዙ ልጆች ገና በለጋ እድሜያቸው የኮሌስትሮል ችግር እያጋጠማቸው ነው። የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ እንዳለው ከሆነ ከአምስት ልጆች አንዱ ያልተለመደ የኮሌስትሮል መጠን ስላላቸው በኋለኛው ሕይወታቸው ለልብ ሕመም የመጋለጥ እድላቸው ይጨምራል። በልጅነት ጊዜ የኮሌስትሮል መዛባት በተለምዶ ከብዙ አስርት አመታት በኋላ የሚጀምረው አተሮስክለሮሲስ የተባለው የደም ቧንቧዎች መጥበብ ችግር ቀደም ብሎ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል። በዚህም ምክንያት በአዋቂዎች ላይ የሚታየው ድንገተኛ የልብ ድካምና ስትሮክ በእንቦቃቅላ ልጆች ላይ ሲከሰት ማየት የተለመደ እየሆነ መጥቷል። ይህን መሰል የጤና ችግር በጊዜ ለማከም እና እንደ ወላጅ የልጅዎን ጤንነት ለመጠበቅ መንስኤዎቹን፣ ምልክቶችን እና የመከላከያ እርምጃዎችን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። በልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል መዛባት ችግሮች መንስኤዎች በልጆች ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል መዛባት ችግሮች መንስኤዎችን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። እነዚህም በዘር በሚወረስ የዘረመል ችግር የሚመጣ (Inherited Cholesterol Disorders) እና በሌሎች የጤና ችግሮች ምክንያት የሚመጣ የኮሌስትሮል ችግር (secondary dyslipidemia) ናቸው። በሌሎች የጤና ችግሮች ምክንያት የሚመጣ የኮሌስትሮል ችግር (secondary dyslipidemia) ሲባል ከሌሎች ተጓዳኝ ህመሞች ጋር የተያያዘ ሲሆን ነው። ለአብነትም የሆርሞን በተለይም የእንቅርት ሆርሞን ማነስ፣ የኩላሊት ህመም፣ ከፍተኛ ውፍረት፣ ስኳር ህመም፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብና እንቅስቃሴ አለማድረግ ወይም ጎጂ ሶሶች ሊሆኑ ይችላሉ። በዘር በሚወረስ የዘረመል ችግር የሚመጣ የኮሌስትሮል መዛባት (familial hypercholesterolemia) በልጆች ላይ በጣም የተለመደው ከፍተኛ የኮሌስትሮል መንስኤ ነው። በዘር የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ይህም ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ በአደገኛ ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ መጥፎ ኮሌስትሮል መብዛት ያመጣል። በጄኔቲክ ችግር ምክንያት የህመሙ ተጠቂ ልጆች ጎጂ ኮሌስትሮልን በጉበት በኩል ማጽዳትና ማስወገድ ስለማይችሉ ኮሌስትሮል በደም ቧንቧዎች ውስጥ ይከማቻል። ስርጭቱ በአለም ዙሪያ ከ300 ሰዎች ውስጥ 1 ያህሉን ያጠቃል። ወላጆች ልጆቻቸው ላይ ሊያስተውሏቸው የሚገቡ የፋሚሊያል ሃይፐር ኮሌስትሮሌሚያ (familial hypercholesterolemia) ምልክቶች ምንድን ናቸው? የፋሚሊያል ሃይፐር ኮሌስትሮሌሚያ (familial hypercholesterolemia) ለመለየት የኮሌስትሮል ምርመራ መቼ ማድረግ ይመከራል? የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መላኩ ድህረ ገጽ https://melakutaye.com/high-cholesterol-in-children-and-teens/ እንዲያነቡናለሌሎች እንዲያጋሩ በትህትና እጋብዛለሁ። @hakimmelaku
እርጣት (menopause) የሴቶች ሆርሞን ኡደት አንዱ ምዕራፍ ! https://vt.tiktok.com/ZSP7TGqW7/
የሽንት ቀለም የጠጣነው ውሃ በቂ መሆኑን ይጠቁማል? የሽንት ቀለም በቂ ውሃ እየጠጣን መሆን አለመሆኑን የሚያመላክት ጠቃሚ ፍንጭ ነው። ኩላሊት በቂ ውሃ ሲደርሰው የምንሸናው ሽንት ነጣ ያለ ቢጫ ይሆናል። ትክክለኛው ሽንት እንደቀጭል የሎሚ ጭማቂ (lemonade) ፈዘዝ ያለ ቢጫማ ይመስላል። ዉሃ ሲያንሰን ደግሞ ሽንት ወደሻይነት ቀላ ይላል። የመቅላት ደረጃዎችን ከፖስተሩ ላይ ያወዳድሩ! @hakimmelaku
ማረጥ (menopause) ምልክቶች ማረጥ ኖርማል የሴትነት ህይወት ተፈጥሯዊ ምእራፍ እንጅ በሽታ አይደለም። ብዙ ሴቶች ሄድ መጣ የሚሉ ቀለል ያሉ የማረጥ ምልክቶች ብቻ ይታይባቸዋል። ነገር ግን አንዳንድ ሴቶች ምቾት የሚነሱ ምልክቶቹ ሊያስተናግዱ ይችላሉ። በተለይም አንዳንዶቹ በእንቅልፍ፣ ስሜት፣ ማህበራዊ ግንኙነቶች እና በስራ ላይ ተጽእኖ ማሳደር የሚደርሱ ምልክቶች ሊያዩ ይችላሉ። እንዲህ ሲሆኑ ተገቢ የህክምና እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል። የማረጥ ምልክቶች መካከል፤ ✅ሰውነት ሙቀት ሙቀት ማለት 🔥 በተለይም ደረት አካባቢ የሚነሳ የሚዘፍቅ ማተኮስ፣ ሌሊት ላይ ማላብ (hot flushes)፣ ✅የእንቅልፍ ማጣት፣ ✅የስሜት ለውጦች፤ ብስጭት ብስጭት ማለት፣ ጭንቀት፣ የስሜት መዋዥቅ ✅ራስ ህመም፣ አእምሮ ጭጋግ መልበስ፣ የማስታዎስ ችግር፣ ትኩረት ማጣት፣ ✅የልብ ምት መፍጠን፣ ✅የብልት መድረቅ፣ የወሲብ ስሜት ማጣት፣ የሽንት ማጣደፍ፣ ተደጋጋሚ የሽንት ኢንፌክሽን ወዘተ ይገኙበታል። ዝርዝር ጽሁፉን በዚህ ሊንክ ማንበብ ይችላሉ https://melakutaye.com/menopause-symptoms-in-amharic/ @hakimmelaku
ቆሽታችን እንዳያር ምን እናድርግ? የኑሮ ውድነቱ፣ የአናዳጁ መብዛት ሕይወትን ከባድ አድርጎብናል። ቢሆንም ከጤና የሚበልጥ ሃብት የለምና በተቻለን ጭንቀት ለመቀነስ ማሰብ፣ ማቀድና ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ ይገባል። ጭንቀትን መቆጣጠር ያስፈልጋል። እኛ ላልፈጠርነው፣ የማይመለከተን ወይም ከእኛ ቁጥጥር ውጭ ላለ ችግር አብዝቶ መጨነቅ መጠበብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ይልቁንም በእኛ አቅም ማድረግ የምንችለው መፍትሄ ላይ ብቻ ማተኮር ይገባል። ባስ ካለ ከባለሙያ ጋር መመካከር። ማስታዎስ ያለብን ቆሽትን የሚያሳርረው የአእምሮ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ጫናዎች አሉ። ጤናማ አመጋገብ ከሌለን ቆሽትን ያስጨንቃል፤ በሂደት ቆሽትን ይጠብሳል። በተቃራኒው ጤናማ አመጋገብ ስንከተል ቅሽት ያገግማል፣ ይለመልማል። በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግም ቆሽትን ይጎዳል። ስለዚህ እየተንቀሳቀስን ቆሽታችንን እናስደስት። ከመጠን ያለፈ ውፍረት በተለይም ቦርጭ ለቆሽት አደገኛ ነው። ሸንቀጥ ስንል ደግሞ ቆሽታችን ትቦርቃለች፣ ፋታ ታገኛለች። አልኮል እና ሲጋራ ማጨስ ለቆሽት መርዝ ናቸው። አልኮል ስንጠጣ እና ሲጋራ ስናጨስ ቆሽትን ምድጃ ላይ ጥዶ እርርርርር አድርጎ እንደማቃጠል አስቡት። ጣፋጭ ነገሮችንም ማዘውተር እንደዚያው ለቆሽት ጎጂ ነው። አልኮል፣ ሲጋራ፣ ጣፋጭ ምግቦችን ስናቆም ደግሞ ቆሽት እፎይ ትላለች። የዚህን ሙሉ ጽሁፍ በዶ/ር መላኩ ብሎግ ያገኙታል https://melakutaye.com/stress-exhausts-pancreas-when-ethiopians-say-my-pancreas-got-burned-out/ @hakimmelaku
“ቆሽቴ አረረ” ስንል? ኢትዮጵያዊያን ሲናደዱ፣ ሲጨነቁ፣ በንዴት ድብን ሲሉ ‘ቆሽቴ አረረ’ ይላሉ። በእርግጥ ስንበሳጭ ቆሽት ላይ ምን ጉዳት እንደሚፈጠር እና ከስኳር በሽታ ጋር ምን ግንኙነት አለው? ቆሽት በሆድ ውስጥ የሚገኝ ኤንዛይም እና ሆርሞን የሚያመነጭ የሰውነት ክፍላችን ነው። ቆሽት ኢንሱሊን የሚባል ወሳኝ ሆርሞን ያመነጫል። የኢንሱሊን ሆርሞን ዋና ተግባሩ ለሰውነታችን ተቀዳሚ ነዳጅ የሆነውን ግሉኮስ ወደህዋሶቻችን እንዲገቡ በማገዝ ለሃይል ሰጪነት / እንደነዳጅ እንዲቃጠል ያደርጋል። ስኳሩን ከደም ውስጥ አውጥቶ ወደ ሴሎች / ህዋሳት ሰርጎ በመግባት ሰውነት ለሃይል ምንጭነት እንዲጠቀምበት ያደርጋል። የኢንሱሊን ምርት ወይም ተግባር መስተጓጎል በሚፈጠርበት ጊዜ ስኳር ጥቅም ላይ መዋል ስለማይችል ደም ውስጥ እየተከማቸና እየበዛ መሄድ ይጀምራል። ስኳር በደም ውስጥ እየተከማቸ በጊዜ ሂደት ወደ አደገኛ ደረጃ ከፍ በማለት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ይዳርጋል። ይህ የቆሽት ሆርሞን የማምረት ስራ መስተጓጎል ሰዎች ሲናደዱ ‘ቆሽቴ አረረ’ ከሚሉት ጋር የሚቀራረብ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያዊያን “ቆሽቴ አረረ” አገላለጽ ከስኳር ህመም መነሻ ምክንያትን ያንፀባርቃል። የተራዘመ ጭንቀት እና ከፍተኛ ጫና ሲኖርብን ቆሽት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያመጣል። ጭንቀት ብቻዉን በራሱ የስኳር በሽታን ባያመጣም ከልክ ያለፈ ጭንቀት፣ ብስጭት፣ ንዴት ወዘተ ቀስ በቀስ ለቆሽት መጎዳት እንደአንድ ተጨማሪ አጋላጭ ምክንያት ይሆናል። የቆሽት ስራ መስተጓጎል ሂደት ረዥም ዓመታትን የሚፈጅ የሜታቦሊክ ጫና እንጅ በንዴት ብቻ አይደለም። የዚህን ሙሉ ጽሁፍ በዶ/ር መላኩ ብሎግ ያገኙታል https://melakutaye.com/stress-exhausts-pancreas-when-ethiopians-say-my-pancreas-got-burned-out/ @hakimmelaku
እርጣት (menopause) ማረጥ የሴቶች ሆርሞን ኡደት አንዱ ምዕራፍ ነው። በአብዛኛው ከ45 እስከ 51 አመት እድሜ ላይ ይመጣል። የማረጥ ምልክቶች መካከል፤ • ሰውነት ሙቀት ሙቀት ማለት 🔥 በተለይም ደረት አካባቢ የሚነሳ የሚዘፍቅ ማተኮስ፣ • የእንቅልፍ ማጣት፣ • ብስጭት ብስጭት ማለት፣ • ራስ ህመም፣ • የልብ ምት መፍጠን ወዘተ ይገኙበታል። የሆርሞን ህክምና አለው። ተጨማሪ ለማንበብ https://melakutaye.com/menopause/ @hakimmelaku
የማርበርግ ቫይረስ እንዴት ይተላለፋል? https://vt.tiktok.com/ZSfGGCYDV/
ኮሌስትሮልን ማከም ለምን አስፈለገ? ብዙ ሰው ‘እኔ እኮ ጮማ አልበላም፤ ቅባት አላበዛም፤ ብዙ ቦርጫም አይደለሁም’ ስለሆነም ‘የኮሌስትሮል መድሃኒት በጭራሽ አልዎስድም’ የሚሉ አሉ። ‘ምንም የህመም ስሜት አይሰማኝም፤ የኮለስትሮል መድሃኒት አያስፈልገኝም’ ይላሉ። ለመሆኑ ኮሌስትሮልን ማከም ለምን አስፈለገ? በደምዎ ውስጥ ከፍ ያለ ኮሌስትሮል መኖሩ ለልብና የደም ስር ህመም ተጋላጭነት ይጨምራል። በደም ስር ግርድግዳ ላይ እንደማስቲካ እየተጣበቀ የደም ስር እንዲደርቅና እንዲጠብ በማድረግ የደም ፍሰትን ሂደት ያውካል። በሂደት የደም ቧንቧዎች መደፈን ያስከትላል። የዚህ ዓይነቱ የደም ስር ህመም የቤት ስሙ አቴሮስክሌሮሲስስ (atherosclerosis) ይባላል። ይህ የደም ስር መጥበብ ልብ ላይ ሲከሰት የደረት ህመም ያመጣል። በተለይም እንቅስቃሴ በምናደርግበት ጊዜ ልባችን ደም ለጡንቻችን ማዳረስ ስለሚያቅተው ሰቅዞ የሚይዝ የደረት ህመም ያስከትላል። ይህ ህመም ባስ ሲል ወደ ክንድ፣ አንገት፣ ሆድ ወይም ጀርባችን ሊሰራጭ ይችላል። አንዳዴ የጨጓራ ህመም የሚመስል ስሜት ብቻ ሊኖረው ይችላል። የልብ ጡንቻ የደም ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ ሲገደብ ድንገተኛ የብ ድካም (Heart attack) የሚባል ገዳይ የሆነ ከባድ ድንገተኛ አደጋ ይደርሳል። ወደ አንጎላችን የሚሄደው የደም ስር ሲጎዳ ደግሞ ድንገተኛ የንጎል መታዎክ (ስትሮክ) ይባላል። ለአንጎል የሚሄደው የደም አቅርቦት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሲስተጓጎል የሚከሰት ነው። ይህም አንደየ ደረጃው ሙሉ ሰውነትን ፓራላይዝ ከማድረግ እስከሞት ያደርሳል። ወደእግር የሚሄደው የደም ፍሰት ሲቋረጥ (peripheral arterial disease) ደግሞ ጋንግሪን (gangrene) ያመጣል። በደቂቃዎች የተዘጋው ደም በህክምና ወይም ኦፕሬሽን እንዲስተካከል ካልተደረገ እግር ወይም እጅ መቆረጥ ያደርሳል። ከላይ የጠቀስናቸው የደም ስር ህመሞች ሁሉም መንስኤቸውና ህክምናቸው ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን በአንድ ላይ ስር የሰደደ የደም ስር ህመም (atherosclerotic cardiovascular diseases, ASCVD) ተብለው ይጠራሉ። ከኮሌስትሮል በተጨማሪ እድሜዎ እየጨመረ ሲሄድ እና ሌሎች የደም ስር የሚያጠቁ ህመሞች ለምሳሌ የስኳር ህመም፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ውፍረት በተለይም ቦርጭ፣ የደም ግፊት መብዛት ወዘተ ካለ ከላይ ለጠቀስናቸው ከኮሌስትሮል ጋር የተያያዙ በሽታዎች የመጋለጥ እድል በከፍተኛ ሁኔታ ጨምራል። ኮሌስትሮል በመድሃኒትም ሆነ ያለመድሃኒት እንዲቀንስ የሚመከረው ከላይ የተጠቀሱትን የደም ስር ህመሞች ለመቀነስ ነው። ውድ የሆነውን ጤናዎትን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ለማዎቅ ተጨማሪ ተግባራዊ ምክሮችን በድህረ ገጽ www.melakutaye.com እና ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን @hakimmelaku ይከታተሉ! @hakimmelaku
без подписи
“ኮሌስትሮልን ለማስተካከል ብዙ ኮሌስትሮል ብላ” የሚሉ ኤክስፐርት-ነን ባዮች 'ከኮሌስትሮል ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮችን ለማዳን ኮሌስትሮል የበዛው ምግብ ተመገብ' የሚል ሃሰተኛ መረጃ ከሚናገር ሰው አርባ ክንድ እንራቅ! ተጽእኖ ፈጣሪዎች ከልብ ጤና ችግር አያድኑንም! በኋላ ልብ በኮሌስትሮል ሲታመም ኤክስፐርት-ነን ባዮች ከጎናችን አይኖሩም። ከፈጣሪ በታች ጤናን የሚጠብቀው ደህንነቱ አና ዉጤታማነቱ የተረጋገጠ ህክምና ነው! @hakimmelaku
የአርቲፊሻል ስኳር ጣፋጭነት እና መራራ የጤና ስጋቶች አርቲፊሻል ስኳር ሲባል እንደ ስኳር ጣፋጭነት ያላቸው የምግብና መጠጥ ማጣፈጫነት ጥቅም ላይ የሚዉሉ የስኳር ምትክ ናቸው። የካሎሪ መጠናቸው ዜሮ አሊያም እዚህ ግባ የማይባል እጅግ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ለስኳር ታካሚዎች ስኳርን የሚተኩ ምርቶች ሆነው ያገለግላሉ። የተለመዱ የአርቲፊሻል ስኳር አይነቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፤ አስፓርቴም፣ አድቫንቴም፣ ኒዮቴም፣ ሳካሪን፣ ሱክራሎዝ፣ ዛይሊቶል፣ ኢሪትሪቶል፣ ሶርቢቶል ወዘተ ናቸው። ጣፋጭነታቸው ከስኳር እኩል ወይም የበለጠ ሊሆን ይችላል። አርቲፊሻል ስኳር ያለተጨማሪ ካሎሪ ጣዕምን ስለሚያጣፍጡ የስኳር ፍጆታን በመቀነስ ውፍረት እና ተያያዥ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ ተብለው ቢታሰቡም በተቃራኒው የጤና እክል አደጋን ሊጨምሩ እንደሚችሉ አዳዲስ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በዚህ ዙሪያ ያለውን ግርታ ለማጥራት የዓለም ጤና ድርጅት እኤአ በ2019 አጥኚ ኮሚቴ አዋቅሮ ሰፊ ምርምር እንዲሰራ አድርጓል። በዋናነት ትኩረት የተሰጣቸው የጤና መለኪያዎች መካከል ክብደት፣ የሰውነት ስብ መጠን፣ የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ የኮሌስትሮል መጠን፣ የልብና ደም ስር ህመሞች፣ የኩላሊት ህመም፣ ካንሰር፣ የምግብ ፍላጎትና ረሃብ ስሜት ወዘተ ናቸው። ይህ የጥናት አማካሪ ቡድን የአርቲፊሻል ስኳር አጠቃቀም በጤና ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያጠኑ 370 ወሳኝ ምርምሮችን ገምግሞ የሚከተለውን ውጤት ይፋ አድርጓል። 1️⃣ ለክብደት መቀነስ ይረዳሉ የሚለው ወሬ የተረጋገጠ እንዳልሆነ ነው በጥናቶች የታየው። በተለምዶ እንደሚታሰበው እነዚህን አርቲፊሻል ስኳር ጣፋጮችን መጠቀም ክብደትን ለመቀነስ ላይረዳ ይችላል። እንዲያዉም የምግብ ፍላጎታችንን ሊጨምሩ ስለሚችሉ ተጨማሪ ምግብ በመመገብ ክብደታችን ሊጨምር ይችላል። 2️⃣ የልብ ህመም እና የደም ቧንቧ ችግሮች ያመጣሉ። በቅርቡ የወጡ ጥናቶች እንዳሳዩት ከፍተኛ መጠን ያለው አርቲፊሻል ስኳር መጠቀም ለልብ ህመም ብሎም የሞት ስጋት ተዛማጅነት አላቸው። 3️⃣ የሆድ ህመም ሊያመጡ ይችላሉ። በአንዳንድ ሰዎች ላይ እንደ ጋዝ ወይም ተቅማጥ ያሉ የጨጓራና አንጀት ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። በተጨማሪም ለምግብ መፈጨት፣ በሽታ መከላከልና አጠቃላይ ጤና ጠቃሚ የሆኑ የአንጀት ባክቴሪያዎችን በመጉዳት ስራቸውን ያስተጓጉላሉ። የጠቃሚ የአንጀት ባክቴሪያዎችን ቁጥር እንዲመናመን በማድረግ በሽታ አምጭ ጎጂ ባክቴሪያዎች እንዲነግሱ ያደርጋሉ የሚሉ በርካታ ማረጋገጫዎች በታዋቂ የህክምና መጽሄቶች ላይ እየታተሙ ነው። ✍️ በእነዚህና ሌሎችም ምክንያቶች በመመርኮዝ የአለም ጤና ድርጅት ምግብና መጠጥ ማጣፈጫ አርቲፊሻል ስኳሮችን መጠቀም አይመክርም። ከዚህ ባሻገር አርቲፊሻል ስኳሮች ለክብደት ህክምና እንደማይረዱ ብሎም የልብ ህመምን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የረጅም ጊዜ የጤና ችግሮችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አፅንዖት ሰጥቷል። የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መላኩ ታዬ ብሎግ https://melakutaye.com/artificial-sweeteners-and-their-health-risk/ ማንበብና ለሌሎችም ማጋራት ይችላሉ። @hakimmelaku
ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ የስኳር ታካሚዎች ከሚያነሷቸው መጠይቆች መካከል ‘ፍራፍሬ መመገብ እችላለሁ ወይ?’ የሚለው የተለመደ ጥያቄ ነው። የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን እንዴት መመገብ እንደሚችሉ በርካታ እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች ስለሚሰሙ ግራ መጋባት ይፈጥራሉ። ይህን ፍራፍሬ ብላ፣ ያንን ፍሬ እንዳትነካ፣ ይህ የተፈቀደ ነው፣ ያኛው ግዝት ነው ወዘተ የሚሉ ውዥንብር የሚፈጥሩ ያልተረጋገጡ የአመጋገብ ምክሮች አሉ። አንዱ ሃኪም አዎ ያለውን ሌላኛው አይ ብሎ ሊያወዛግበን ይችላል። ይህ ጽሁፍ የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን በማእዳቸው እንዴት ማካተት እንደሚችሉ ያስረዳል። እርስዎ እራስዎ የስኳር ታካሚ ከሆኑ ወይም የሚያውቁት ስኳር ያለበት ሰው ካለ ይህ መረጃ መነበብ አለበት። ፍራፍሬዎችን በስኳር ህክምና አመጋገብ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ያስፈልጋል? በስኳር ህመም እና በፍራፍሬ አመጋገብ ላይ በጣም ከተለመዱት ሳይንሳዊ ያልሆኑ መረጃዎች መካከል አንዱ ‘የተወሰኑ ፍራፍሬዎች ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው’ የሚል ይገኝበታል። ይህንን በሳይንሳዊ ጥናቶች ያልተረጋገጠ መረጃ ከእውነታ መለየት ይገባል። እንደ እውነቱ ከሆነ አብዛኛዎቹ ፍራፍሬዎች በስኳር ህመም አመጋገብ እቅድ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ። የስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተገዘተ ምንም አይነት ፍራፍሬ የለም። ዋናው ቁምነገር የፍራፍሬ አጠቃቀም መመጠን እና በቶሎ ስኳር ከፍ የማያደርጉትን አይነቶች መምረጡ ላይ ነው። ፍራፍሬዎች ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት እና ፋይበር ምንጭ ናቸው። በማስተዋል መጥነን ከተጠቀምንባቸው ለስኳር ታካሚዎች ተስማሚ የሆነ ምግብ አንድ አካል ሊሆኑ ይችላሉ። ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ ምን ይመስላል? የስኳር ህመም አለብን ማለት ፍራፍሬዎችን ዞር ብለን ማየት የለብንም ማለት አይደለም። ነገር ግን የደም ስኳር መጠን በጣም ከፍ ሳይል እንዴት ፍራፍሬዎችን በጥበብ መመገብ እንዳለብን ማወቅ ይገባል። ዝቅተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ፍራፍሬዎች መምረጥ አብዛኛዎቹ ፍራፍሬዎች በውስጣቸው ተፈጥሯዊ ስኳር ቢኖራቸውም ከፍተኛ ፋይበር ይዘት ስላላቸው በተመገብን ከመቅጽበት የደም ስኳር መጠን በድንገት እንዳያሻቅብ ያደርጋል (low glycemic index)። መጠናችንን መገደብ ፍራፍሬ ስንመገብ ዋና ቁልፉ ልከኝነት ነው። ምንም እንኳ ፍራፍሬዎች ለጤናችን ጠቃሚ ቢሆኑም ቢሆን አብዝተን ከበላን የስኳር መጠን ከፍ ያደርጋሉ። ስለሆነም ፍራፍሬዎችን በተመጣጣኝ መጠን መጠቀም አስፈላጊ ነው። ሁሌም ቢሆን የምንመገበውን ፍራፍሬ መጠን መመጠን (Portion control) ይገባል። ከጭማቂ ይልቅ ሳይጨመቅ ሙሉ ፍራፍሬዎችን መብላት የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት በጤና እና የደም ስኳር ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ሙሉ ፍሬውን ከመብላት በተቃራኒ ነው። የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት ሙሉ ፍሬውን ከመብላት በበለጠ ፍጥነት በደም ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ማስታወሻ፦ የተለያዩ ፍራፍሬዎች የደም ስኳር መጠን ላይ ያላቸው ተጽእኖ የተለያዬ ስለሆነ የደም ስኳር ልኬትን በቅርበት መከታተል ይመከራል። ከምግብ በኋላ ያለን የደም ግሉኮስ መጠንዎን በመፈተሽ የትኛው ፍራፍሬ እና ምን ያህል መጠን ስኳሬን ከፍ ያደርገዋል የሚለውን መረዳት ይቻላል። ሁልጊዜም የደም ስኳር መጠንን መከታተል እና ከጤና ባለሙያ እና የስነ ምግብ ባለሙያ ጋር በመመካከር ግለሰቡን ያማከለ የምግብ እቅድ ማዘጋጀት ይመከራል። የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መላኩ ታዬ ብሎግ https://melakutaye.com/fruits-in-diabetes-diet/ ማንበብና ለሌሎችም ማጋራት ይችላሉ። @hakimmelaku @HealthifyEthiopia
https://vm.tiktok.com/ZMAXMr2bJ/
የማርበርግ ቫይረስ 👉 እያንዳንዱ ሰው የመከላከያ እርምጃዎችን ከተገበረ፣ 👉 የታመሙት በጊዜ ተለይተው ከታከሙ በቀላሉ ልንቆጣጠረው የምንችል ደካማ ቫይረስ ነው። የዚህን ምክራዊ ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መላኩ ድህረ ገጽ ያንብቡ ለሌሎችም ያጋሩ https://melakutaye.com/marburg-virus-disease-in-africa/ @hakimmelaku